ደመ-መስዋዕትን የለመዱት የሉሲፈር / ሳጥናኤል ኃይሎች ሕዝባችንን ሊያናክሱት ቀናቀና በማለት ላይ ናቸው። የእስኮትላንድን መገንጠል እንደ ትልቅ ውድቀት አድርጋ የወሰደችውና እያነሰች የመጣችው ‘ታላቋ ብሪታኒያ‘ ‘ታዛቢ‘ በሌለበት የተጭበረበረ ሬፈረንድም ግዛቶቿን ለማስከበር በቅታለች። ዱሮም 10-ሺህ ኪሎሜትር ያህል በመጓዝ ለማይረቡት የማልቪናስ/ፎክላንድስ ደሴቶች ስትል ከአርጀንቲና ጋር ጦርነት ከፍታ የነበረችው እንግሊዝ ጎረቤቷ የሆነችውን ስኮትላንድን ትለቅቃለች ተብሎ የማይታሰብ ነበር።
ከሬፈረንደሙ በኋላ፡ እንግሊዛውያኑ ተረጋግተዋል፤ የልብልብ ብሏቸዋል፤ ግን ከዚህ ቀደም ሲከተሉት የነበረውን ድብቅና ግልጽ የትንኮላ መንገድ በአፍሪቃ፡ በተለይም በኢትዮጵያ ላይ ለመዘርጋት ሲቁነጠነጡ ይታያሉ። እነርሱ ሊያጠፉን የጥላቻ መርዛቸውን ሲረጩብን እኛ ግን “ማንቸስተር!” “አርሰናል!” እያልን ተወዳዳሪ በሌለው ፍቅረ–ባዕድ ወገናችንን እናደነዝዛለን፣ ከተሞቻችንን እናውካለን። የእግርኳስ ጠላት መሆኔ አይደለም፤ ግን የእንግሊዝ እግር ኳስ አፍቃሪም ይህን ያህል መስዋዕት ለፕሬምየር ሊግ ስለማይከፍል የኛ እንደዚህ መሆን በይበለጥ ስለሚያሳዝነኝ ነው። “ጠላትህን ውደድ!” የሚለውን ምክር ያላግባብ ነው የምንጠቀመው።
‘7‘ ቁጥር ባለፉት የአገራችን የታሪክ ሂደቶች ውስጥ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች፤ 1967፥ 1970፥ 1977፥ 1987፥ 1997 ብዙ ነገሮች የታዩባቸው ዓመታት ነበሩ። 2007 ዓመተምህረትስ ምን ይዞልን ይመጣ ይሆን? ይህ ዓመት ምርጫ የሚካሄድበት ዓመት ነው። ታዲያ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ‘በእንግሊዝ ቡልዶጎች‘ የሚመራው የሉሲፈራውያኑ ኃይል አገራችንን ከመንከስ ወደኋላ አይልም። ሰሞኑን እንደምንታዘበው ኢትዮጵያውያኑን እንዲሁም ዓለምአቀፋዊውን ማሕበረስብ ከሁኔታዎች ጋር ለማለማመድ (conditioning) ይህ ኃይል በመሞከር ላይ ነው።
ለምሳሌ፦
- በትውልድ አገሩ ላይ ሤራ ለመጠንሰስ ሲንቀሳቀስ የነበረውና ከየመን ወደ ኢትዮጵያ የተጠረፈው ግለሰብ፡ የእንግሊዝ ዜግነትን የያዘ ነው። አሁን ይህ ግለሰብ በኢትዮጵያ “ያላግባብ ታስሯል” የሚል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በመንዛት፡ እንግሊዛውያን ኢትዮጵያን በቁራኛ እንዲመለከቱ ይደረጋል። ምናልባት እራሳቸው ሆን ብለው ልከውት ይሆን? (አፄ ቴዎድሮስን እንደተተናኮሉት)። እዚህ ይመልከቱ።
- የመካከለኛውን ባሕር እያቋረጡ በጣሊያን አድርገው ወደ ፈረንሳይዋ ካሌ በመግባት፡ “ወደ እንግሊዝ መጓዝ ይፈልጋሉ” የሚባሉትንና በብዙህ ሺህ የሚቆጠሩትን የኤርትራ/የኢትዮጵያ/ የሱዳን ዜጎችን “ከረሃብ አምልጠው የመጡ ወራሪዎች ናቸው” እያሉ በሕዝባቸው ዘንድ የማስፈራሪያና ጥላቻ ቅስቀሳ ያካሂዳሉ። አብዛኛው ስደተኛ ከአረብ አገር ነው የሚመጣው፡ ሰለነሱ ግን ብዙም አይተነፍሱም። የእንግሊዛዊውን አንባቢ የጥላቻ ሀተታ እናንብብ። እዚህ ፡ እዚህ ፡ እዚህ ይመልከቱ።
- “የኦሮሞ ብሔረሰብ በኢትዮጵያ ተበድሏል” በሚል ዲያብሎሳዊ ወቀሳ የአገራችንን ሕዝብ እርስበርስ ሊያባሉት አስበዋል። ልክ በቀደም ‘በሩዋንዳ ጀነሳይድ ተጠያቂዎቹ ቱሲዎች (ኢትዮጵያውያን ናቸው) ናቸው‘ በማለት ሌላ እልቂት መፈለጋቸውን እንደጠቆሙት። እዚህ ፡ እዚህ ይመልከቱ።
- “ኢትዮጵያ ከ30 ዓመት በፊት ከተከሰተው ረሃብ በኋላ” በሚል ርዕስ ደግሞ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ሁልጊዜ ከረሃብ ጋር የተያያዘ ይሆን ዘንድ እንደገና ለማስታወስ ይቃጣሉ። አንዳንዶቻችን ይህ ጽሑፍ የአኹኒቷን ኢትዮጵያ መለወጥና መሻሻል ካለፈው ጋር እያወዳደረ የሚያቀርብ ጽሑፍ መስሎ ይነበበን ይሆናል። አንታለል! ይህ ጽሑፍ በቅድሚያ ለእንግሊዛውያኑ ነው የቀረበው፤ እንግሊዛውያኑ ደግሞ በዝርዝር የቀረበውን ጽሑፍ ሙሉ በሙሉ ለማንበብ ሰነፎች ናቸው፤ ርዕሱን ካዩት በቂያቸው ነው፤ በተለይ ‘ኢትዮጵያ = ረሃብ‘ የሚሉት ቃላት። እዚህ፡ እዚህ ይመልከቱ።
አብዛኛው የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ቅጥፈት የተሞላበት እንደሆነ ግን እራሳቸው ይመሰክራሉ፤ እዚህ ይመልከቱ።
ያዘኑትን የምታረጋጋ፣ ጻድቃንን የምትጐበኛቸውና ደስታን የምታበሥረው ቅዱስ ገብር ኤል ሆይ ይህ የ 2007 ዓመት የሰላም፣ የፍቅርና የጤና ዓመት እንዲሆንልን የደስታውን ወይን አጠጣን።