ፈረንጅ በኢትዮጵያውያን ላይ ያወጣቸው 10 ቀልዶች…
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 31, 2014
አብረን እንስቅ ይሆን? እንናደድ ይሆን? ሳቅንም ተናደድንም በሕዝቦች ላይ የሚሰሙ ቀልዶች፡ በተለይ ኢትዮጵያውያንን የሚመለከቱት የፈረንጅ ቀልዶች ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በሞራል ለማውደቅ ብሎም እነርሱን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ፡ የቀልዱ ባለቤቶቹም ምን ያህል ስሜት–አልባ እና ኢ–ሰብአዊ መሆናቸውን ያሳያሉ።
ወደ ቀልዶቻቸው፦
- ለምንድን ነው ኢትዮጵያውያን መፋቂያ አፋቸው ላይ የሚሰኩት?
- ነፋስ እንዳይወስዳቸው
- ወደ ኢትዮጵያ መድኃኒት መላክ ከንቱ ነው፤ ለምን?
- ምክኒያቱ፡ የመድኃኒቱ ማሸጊያ ላይ፡ “ከምግብ በኋላ ይውሰዱ” ስለሚል
- ኢትዮጵያውያን ከስንት ኪሎ ክብደት ጀምሮ ሲኒማ ቤት መግባት ይፈቀድላቸዋል?
- ከ 5 ኪሎ በላይ፤ ያለዚያ ወንበሩ ወደላይ ይታጠፋል
- ኢትዮጵያ ያሉ ሊፍቶች ምን ዓይነት ምልክት ይለጥፋሉ?
- ከፍተኛ ክብደት 200 ኪሎ ወይም 500 ሰዎች
- ኢትዮጵያውያን ታዛ/ጥላ ሲፈልጉ ምን ያደርጋሉ?
- የልብስ መስቀያ ሽቦ ይዘረጋሉ
- የኢትዮጵያዊው ጉሮሮ ምነው አበጠ?
- የበቆሎ ፍሬ ስለዋጠ
- የኢትዮጵያ ሆስፒታል በሮች ላይ ምን ተለጥፏል?
- “የድንገተኛ አደጋ በሽተኞች፡ ባካችሁ በበሩ ሥር ሾልካችሁ ግቡ!”
- በዓለም በጣም አደገኛ የሆነው የመኪና እሽቅድምድም የትኛው ነው?
- ሥጋ ጭኖ ኢትዮጵያን ማቋረጥ
- ጂፕስ እግሩ ላይ የተለጠፈበት ኢትዮጵያዊ ምንድን ነው?
- የጎልፍ ኳስ መምቻ
- አንድን ኢትዮጵያዊ ኃብታም እንዴት ለይቶ ማወቅ ይቻላል?
- ወገቡ ዙሪያ ባሠረው የሮሌክስ ሰዓት
Leave a Reply