በያየህይራድ ወንጌሌ
አንድ ሰው ከራሱ ጋር ወይም ለራሱ የሚገባው ቃል፥ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ወገኖች ወይም ሰዎች ወደውና ተስማምተው የሚገቡት ቃል ውል፥ እግዚአብሔር በፈቃዱ ለሰው ልጆች (ለፍጥረታቱ) የሚሰጠው ቃል ነገሩ የሚጸናበት (የነገሩ ማጽኛ) ቃል ኪዳን ይባላል። የምንመለከተው ቃል ኪዳንም በጽሑፍና ፊርማ ሳይሆን እንደ ብሉያት መጻሕፍት ብቸኛ ተቀባዮችና ቀደምት ሐዲሳውያን እንደ እስራኤልና ኢትዮጵያ ባሕል በቃል ኪዳን በልብ መዝገብ ስለሚጸና ነው።
እግዚአብሔር አምላክ ከፍጥረት መጀመሪያ ጀምሮ በመረጣቸው አባቶች በኩል በተለያዩ ጊዜያት ከፈቃዱ የሆኑ የፀጋ ቃል ኪዳኖች ለሰው ልጆች ሰጥቷል። ሰዎች ቃል ኪዳኑን ሲቀበሉም እግዚአብሔር ለሰጠው የተስፋ ቃል የሚታይ ምልክትን ያሳያል፤ የቃል ኪዳኑም መፈጸም የመጽናቱና የመጠበቁም ማረጋገጫ ነው።
ከእግዚአብሔር አምላክ በተለያዩ ጊዚአት በተመረጡ ሰዎች በኩል ለሰው ልጆች የተሰጡ ዋናዎቹ ቃል ኪዳኖች ምልክቶቻቸውን የመፈጸሙ ማረጋገጫዎች፦
ቃል ኪዳን የተሰጠው |
ቃል ኪዳን ተቀባዮች |
ቃል ኪዳኑን የመቀበሉ ምልክት |
የተሰጠው ተስፋ |
ቃል ኪዳኑን የመፈጸሙ የመጽናቱና የመጠበቁ ማረጋገጫ |
መጽሐፍ ቅዱስ |
አዳም |
አዳምና ሒዋን |
የሕይወት ዛፍ መልካምና ክፉን የሚያስታውቅ ዛፍ |
በሕይወት መኖር |
የሕይወት ዛፍ |
ዘፍ 2፥8-17 ሆሴዕ 6-7 |
ኖኅ |
ዘሩ የምድር ሕዝብ ሁሉ እንስሳትና አራዊትም ሁሉ |
|
በምድር ላይ መኖር |
ቀስተ ደመና |
ዘፍ 9፥1-17 |
መልከ ጼዴቅ |
የምድር ሕዝብ |
ሕብስትና ወይን |
የድኅነት ካህን መሥዋዕት |
የክርስቶስ ክህነት መገለጥ (ህብስትና ወይን / ስጋውና ደሙ |
ዘፍ 14፥18-20 መዝ 109፥3 ዕብ 5፥5-7፥10-11፤6፥19-20፤7፥1-28
|
አብርሃም
ሙሴ
ሕገ ኦሪት |
በአብርሃም አባትነት ለዘሩ የምድር ሕዝብ ሁሉ። ሕዝበ እስራኤል (ሕዝበ ኢትዮጵያ) በምድር ሕዝብ ሁሉ |
ግዝረት (የሥጋ ሸለፈት መቆረጥ) |
የተስፋይቱ ምድር ከነዓን (ኢየሩሳሌም) ለአሕዝብ ሁሉ በረከት ሕይወት በተስፋይቱ ምድር፥ በአገራቸው በእስራኤል። በሰዎች ልብ ማደር |
ጥምቀት፣ የልብ ሰለፈት መገረዝ |
ዘፍ 17፥1-21 ሮሜ 4፥11፤9 ዘጸ 19፥5-9፤ 24፥7-8 ዘጸ 25፥1-22፤40፥20። 2ቆሮ3፥3 |
ዳዊት |
ዘሩ |
የፍርዱ ዙፋን ንግሥና |
ዘላለማዊ መንግሥት (ንግሥና) |
የጌታ ከዳዊት ዘር መወለድ፤ የዓለም ንጉሥ መወለድ፤ ዘላለማዊ ንጉሥ |
2ሳሙ 7-8፥17 ኢሳ9፥7 ኤር 23፥5-7፤33፥14-17 ሕዝ34፥33፤ 37፥24 ማቴ1፥1፤9፥2፤12-23፤ 1ዜና 28፥5 መዝ44፥6-7 ዕብ 1፥8 ማቴ 19፥28፤ ራዕ3፥21 |
በጌታ በኢትየሱስ ክርስቶስ |
በክርስቶስ በትክክልና በእውነት ለሚያምን ሁሉ |
ትክክለኛ ጥምቀት (ክርስትና) የእግዚአብሔር የጸጋ ልጅነትን ማግኘት |
ድኅነት፡ ዘላለማዊ ሕይወት |
ቅዱስ ቁርባን |
ኤር 31፥31-34 ዕብ 8፥8-12 ማቴ 26፥26-28 1ኛቆሮ 11፥23-27 ዮሐ 6፥53-58 |
__