Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2014
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    262728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ርጉም አረቦች እህታችንን ሊሰቅሏት ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 15, 2014

ማን ነው፡ ! የአባይን ቧንቧ እንዘጋለን! ብሎ በመዛት እህታችንን ከስቅላት ሊያተርፋት የሚችል?

EthioMadonnaአፋችን ተለጉሟል፣ እጆቻችን ተሣስረዋል። በእህቶቻችን፣ በወንድሞቻችን፣ በልጆቻችን ላይ ርኩስ አረቦች የሚፈጽሙትን በደል ማቆም፣ መቋቋም አቃተን። ከሱዳን እስከ ሳዑዲ የስለት ሲሳይ፣ የጅራፍ ተቀባይ ሲሆኑ እንደ ቆሻሻ ተቆጥረው ከፎቅ ሲወረወሩ ፣ መሆን ያለበት ነገር እንደሆነ አድርገን በመቁጠር ዝም ብለን ኑሮአችንን እንገፋለን። ለምንድን ነው የምዕራብ መገናኛ ብዙኃን ሁሉንም ነገር እሲያራግቡልን ድረስ የምንጠብቀው?

እህታችን እናቷ ተዋሕዶ ክርስቲያን አባቷ እስላም ናቸው። እህታችን ከእናቷ ጋር በክርስትና እምነት ያለ እስላም አባቷ አድጋ ከክርስቲያን ሰው አረገዘች። ከእስልምና አንፃር ወንጀሏ ምንድን ነው? ከክርስቲያን ማርገዟ፡ ክርስትናን መቀበሏ። በእስልምና ወንዶቻቸው የክርስቲያን ሴቶች እንዲያገቡ ሲፈቀድ፡ ሴቶቹ ግን ክርስቲያን ወንድ እንዲያገቡ አይፈቀድም፡ ያው የሞት ፍርድ ያስከትላል። ይህም ዲያብሎሳዊውን ተንኮል በግልጽ የሚያሳይ ነው። እግዚኦ! እንበል።

ዓረቦች ጠላቶቻቸው እንደሆንን አድረገው ማሰብ ከጀመሩ ሺህ ዓመታት አስቆጥረናል፤ ታዲያ እነርሱን ላለማስከፋት እያልን የወገኖቻችንን ውድ ደምና ነፍስ እንዲሁም ቅዱስ ውኃችንን፡ ውድ እንጀራችንን በመስዋዕት መልክ ለነርሱ ማቅረቡን ቀጥለናል፤ ለምን፡ መከፋት ቀርቶ እየፈረጡ ተነው አይጠፉም! መቼ ነው፡ አታስፈልጉንም፣ አትምጡብን፣ አንመጣባችሁም ማለት የሚቃጣን? መጪው ትውልድ እንደሚረግመንና እረፍት እንደሚነሳን እንዴት አይታወቀነም?

አረመኔው የሱዳን ፕሬዚደንት፡ ኦማር አልበሽር፡ በቀድሞዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፓትርያርክ ሞት እጃቸውን ካስገቡት ግለሰቦች መካከል አንዱ ናቸው። እኝህ አጭበርባሪ ሰው ላለፉት 6 ወራት ብቻ አዲስ አበባን ለ አምስት ጊዜ ያህል ተመላልሰው ጎብኝተዋል፤ እግረመንገዳቸውንም አንበጣን፣ ጨለማን እና ሞትን በሳዑዲና በግብጽ አምላክ ስም ይዘው መጥተዋል። በአዲስ አበባ የአንበጣ መንጋ? መቼ ነው በአዲስ ታይቶ የሚታወቀው? የአረብ አውሮፕላኖች ለአንበጣዎች መናኽሪያ ከሆነችው ከአረቢያ በረሃ ያመጡት ሊሆን አይችልምን?

አባይን አስመልክቶ ከግብጽ ጋር የወታደራዊ ልምምዶችን እያካሄዱ የሕዳሴ ግድቡን እደግፋለሁ!” ማለታቸው እኛን ሊያሳምነን ይገባልን? እንደው ማነው አሁን እኚህን አታላይ የግብጽ ቱጃር የሚያምነው? የላይቤሪያዋ ፕሬዚዳንትን የመሳሰሉት የአፍሪቃ መሪዎች በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የቀበር ስነሥርዓት ወቅት ወደ አዲስ አበባ ያልመጡት የሱዳኑ ፕሬዚደንት እዚያ በመገኘታቸው ምክኒያት ነበር። ለምንድን ነው ኢትዮጵያውያን ከነዚህ የአረብ ቡችሎች ጋር ይህን ያህል መቀራረቡን የሚሹት? ቀደም ሲል፡ ንጉሥ ኃይለሥላሴም፣ እስራኤልን ተወት በማድረግ ወደ አረቦቹ ጠጋ ጠጋ ማለት ሲጀምሩ ነው በኋላ ላይ መቃብራቸውን ለመቆፈር የበቁት። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ከአረቡ ሆነ ከ ቱርኩ፣ ከኢራኑ ሆነ ከግብጹ ጋር፡ በአገር እና በግል ደረጃ የጠበቀ ግኑኝነት ማድረግ የለባቸውም። እነዚህ አገሮች/ሕዝቦች በዘመን ፍጻሜ ከፍተኛ ጸረክርስቶሳዊ የሚጫወቱ መሆናቸውን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይነግረናል። ታዲያ ለምንድን እራሳችንን የምናታልለው?እናስታውስ፣ ኢትዮጵያ ከነዚህ ሕዝቦች በራቀችበት ዘመን ነበር በሁሉም ረገድ ጤናማ፣ የሠለጠነ እና የበለጸገ ማሕበረሰባዊ ኑሮ የነበራት።

በአዱሱ መስከረም 1 ዓመታችን ሽብር ፈጣሪዎች ኒውዮርክን በማጥቃት ዓለምን ለወጡ። በዛሬው ዕለት ደግሞ በኒዮርክ ለ3ሺሆቹ ሟቾች አንድ መታሰቢያ በኒዮርክ ከተማ ቆመ፡ የእህታችን የሞት ፍርድም እንዲሁ ለብዙዎችን ዓለምን ይለውጥልናል።

በአዱሱ መስከረም 1 ዓመታችን ሽብር ፈጣሪዎች ኒውዮርክን በማጥቃት ዓለምን ለወጡ። በዛሬው ዕለት ደግሞ በኒዮርክ ለ3ሺሆቹ ሟቾች አንድ መታሰቢያ በኒዮርክ ከተማ ቆመ፡ የእህታችን የሞት ፍርድም እንዲሁ ለብዙዎችን ዓለምን ይለውጥልናል።

አይይኢትዮጵያ አገሬ፡ እምዬ ጽዮን አልቅሺ

እህታችንን ይሰቅሏቸዋል፣ ግን አይሞቱም፡ ክርስቶስን አልካዱምና። ነፍሳቸው በሺህ እጥፍ ይጠነክራል፣ ከመላዕክትም ጋር አብሮ ይጓዛል፤ በበዳዮቿም ላይ ኃይለኛ ፍርድንም ይፈርዳል፡ ይበቀላል፤ ወዮላቸው የዲያብሎስ ደቀመዛሙርት፡ ወዮላቸው!

የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የሚጠብቁት ኢየሱስንም በማመን የሚጸኑት ቅዱሳን ትዕግሥታቸው በዚህ ነው። 

ከሰማይም። ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው። መንፈስ። አዎን፥ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል ይላል ብለህ ጻፍ የሚል ድምፅ ሰማሁ።[ራዕይ ፲፬᎓፲፪፲፫]

__

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: