Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • May 2014
  M T W T F S S
   1234
  567891011
  12131415161718
  19202122232425
  262728293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Archive for May 11th, 2014

የነፈስ አዳኞቹ ዘመቻ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 11, 2014

ማስጠንቀቂያ፡ ደካማ ልብ ላላቸው የሚሆን ጽሑፍ አይደለም!

ከሁለት ዓመታት በፊት በአዲስ አበባ የረር ሥላሴ፡ እንዲሁም እንጦጦ ቅዱስ ራጉኤል ዓብያተ ክርስቲያናት አካባቢ በጣም አስገራሚ፥ አሳዛኝና አስደንጋጭ የሆኑ ሁለት ሁኔታዎች ለመታዘብ በቅቼ ነበር።

RagKidsከ እንጦጦ ኪዳነምህረት ወደ ራጉኤል የሚወስደውን አስፋልት መንገድ በእግሬ መውጣት እንደጀመርኩ፤ መኻል መንገድ ላይ ሁለት ሴት ህፃናት (ፎቶዎቹ ላይ ያሉት) ከየት እንደመጡ አላውቅም፣ ወደ እኔ ጠጋ ብለው ጋሼ ወዴት ነው የምትሄደው?” ካሉኝ በኋላ ወደ ራጒኤል እንደምሄድ ነግሪያቸው አብረውኝ ለመሄድ ወሰኑ። ራሷን በለበሰችው የዝናብ ኮት የሸፈነችው ልጅ እጄን ጨበጥ አድርጋ እያወዛወዘችው አብራኝ መራመድ ጀመረች። ከዚያም የተለያዩ ጥያቄዎችን እየጠያየቁኝ ለአምስት ደቂቃ ያህል ከሄድን በኋላ ከመንገዱ በታች ወርደው እንደሚሄዱ አስታወቁኝ፣ እኔም በሉ እሽ፣ ግን እስቲ ፎቶ ላንሳችሁ ብዬ ሁለት ሦስት ጊዜ ቀጭቀጭ አደረግኳቸው። ልጆቹ ምን እንደሚመስሉ ወይም ምን እንደለበሱ በደንብ ለመታዘብ የበቃሁት ፎቶዎቹን ወደ ኮምፒውተሬ ለመገልበጥ ከበቃሁ በኋላ ነበር።

የተሸፈነችው ሕፃን የሉሲፈራውያኑን ራስ ቅል እና አጥንቶች” (Skull & Bones) ምልክት ደረቷ ላይ ለጥፋለች፡ እንደሚታየውም፡ የሙታውያን ገጽታ በምሲኪኗ ህፃን ዓይኖች ላይ ይንጸባረቃል።

ቅዱስ ራጉኤል ሁከትን ከሚፈጥረው ርጉም ጠላታችንና ሰይጣናዊ ከሚሆነው መልአከ ሞት በጸሎቱ ይጠብቃት!

AddisYererSkull2በሌላ ቀን፡ የረር ሥላሴ መንገዱን ወረድ ብዬ መሄድ እንደጀመርኩ ቤተክርስቲያኗ አጠገብ ብዙ ሰዎች ተሰብስበው ከሩቁ አየሁ፤ እግረ መንገዴንም አንድ ህፃን አግኝቼ ሰዎቹ ለምን እንደተሰበሰቡ ጠይቅኩት፣ እሱም አንድ ሰው እራሱን ስለሰቀለ ነውአለኝ። ቦታው እንደደረስኩም በርግጥ 20 ዓመት እድሜ የሚሆነው አንድ ወጣት ልክ ቤተክርስቲያኗ አጥር ሥር በሚገኘው ትልቅ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ አየሁት። በጣም አዘንኩ፣ ተረበሽኩ፣ በቦታው የነበሩትን ፖሊሶች ለማነጋገር ሞከርኩ፣ ፈቃደኞች ግን አልነበሩም፤ ይገባኛል፣ በወቅቱ ሁላችንም ተረብሸን ነበር።

እንዳልተነገራቸው ሹክ አለኝ።

በአካባቢው ይህን የመሰለ አሳዛኝ ሞት ሲከሰት ለ4ኛ ጊዜ መሆኑን ከገለጸለኝ ከአንድ ደቂቃ በኋላ ይህ ፎቶው ላይ የሚታየው ወጣት ከጫካው ውስጥ አንገቱን አቀርቅሮ ወደኛ ጠጋ በማለት መጣ። እኔም፡ ደህንነቱን ከጠይቅኩት በኋላ፡ ከየት መጣህ? የለበስከውን ሹራብህንስ ከየት አገኘኽሁ?” በማለት ጠይቅኩት። ልጁ ግን፡ አሁንም አንገቱን በማቀርቀር፡ እ፣ እ፣ እ ይለን ነበር። ይኽ የለበሰው ልብስ የሙታን ምልክት ያለበት ልብስ ነው፡ ቶሎ አውልቆ እንዲያቃጥል ምከሩትአልኳቸው ለጓደኞቹ። እነርሱም፡ አይ፡ ልጁ ጴንጤ ነው!|” አሉኝ።

ሥሉስ ቅዱስ ሆይ የዲያብሎስን እሾህ ከሥጋና ከነፍሳችን ላይ ነቅላችሁ ጣሉልን!

የሞት አምባሳደሮች?

በዩክሬይን በመካሄድ ላይ ያለው የፖለቲካ ድራማ ከበስተጀርባው ሥርሰደድ ኃይማኖታዊ ታሪክ አለው። ዩክሬይን የሚባል አገር ከ1918 .ም በፊት በዓለም ካርታ ላይ አልነበረችም። ይህች ኪቭ ሩስበመባል የሩሲያ ኦርቶዶክስ ክርስትና የተመሠረተባት ቦታ፡ ከ አንደኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በጀርመናውያኑ ነገሥታት ተንኮል ከሩሲያ ተቆርሳ ነበር በዪክሬይንነት ተሰይማ ልትመሠረት የበቃችው። ልክ ለሰርቢያ ኦርቶዶክስ ክርስትና ምንጭ የሆነችውን ኮሶቮበአልባናውያን በማስወረር በ50 ጊዜ ውስጥ ከሰርቢያ እንደገነጠሉት፣ ዪክሬይንንም፡ ቀደም ሲል፡ በመልክዓምድር፣ አሁን ደግሞ በመንፈስ ለመገንጠል እየሞከሩ ነው። ሤራው የተጠነሰሰው፣ በርጉሙ የጥላቻ ፋብሪካ፡ በ ዚበግኔው ብሬዥንስኪ ዓማካይነት ነው። እኚህ የፖላንድ ዝርያ ያላቸው አሜሪካዊ፣ የእነ ፕሬዚደንት ካርተር እና ኦባማ የቅርብ አማካሪዎች ሲሆኑ፣ ካቶሊካዊ አመጣጥ አላቸው። ምዕራቡ የዩክሬይን ክፍል ለተወሰኑ ጊዚያት በፖላንድሊቶቭስክ መስተዳደር ሥር ለተወሰነ ጊዜ ቆይቶ ነበር። የዚህ ቦታ ነዋሪዎች ልክ እንደ ፖላንድ እና የባልቲክ አገሮች፡ በሩሲያ እና በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ዲያብሎሳዊ ኃይል የተሞላበት ጥላቻ ያሳያሉ።

በዩክሬይን የተጀመረው ዘመቻ፣ ካቶሊካውያን እና አጋሮቻቸው በኦርቶዶክሳውያን ላይ የቀጠሉት ዘመቻ ነው። አሁን ኪቭ ከተማ ላይ የተቀመጠው መንግሥት ከዓመታት በፊት ለዚህ ወቅት በተዘጋጁ የምዕራብ ቅጥረኞች የሚመራ ነው። ፕሬዚደንቱ የ ባፕቲስት ፓስተር፣ ጠቅላይ ሚንስትሩ ደግሞ የአደገኞቹ የሳይንቶሎጂ አምልኮት አባል ናቸው። አጭበርባሪዎቹ ሴነተር ማክቃዔል፣ የሲአይኤ ሃላፊ፣ እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኬሪ ወደ ዩክሬይን አንቴናቸውን መዘርጋት ከጀመሩ ቆይተዋል። እነዚህ የሉሲፈር / ሳጥናኤል አገልጋዮች ከሰርቢያ፣ ጆርጂያና ዪክሬይን በኋላ፣ ወደ ተቀሩት ኦርቶዶክስ ክርስቲያን ሕዝቦች፤ ወደ አርመኒያ፣ ግብጽ እና ኢትዮጵያ ለመዝመት በመጣደፍ ላይ ይገኛሉ።

ባለፈው ጥቅምት መጨረሻ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ወደ ሳዑዲ አረቢያ በመሄድ ሳዑዲዎች በኢትዮጵያውያን ላይ አደኑን እንዲጀምሩ ሁለትመቶ ሺህ የሚጠጉትም ወገኖቻችን እንዲጠረፉ ፊርማቸውን በሪያድ አስቀመጡ። ባለፈው ሣምንትም፡ ለግብጽ መንግሥት 10 አፓቺ ሄሊኮፕተሮችን ለማበርከት ቃል ከገቡ በኋላ፡ ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው ቅጥረኛ የሆኑት የኢትዮጵያ ጠላቶች ሁከት እንዲፈጥሩ መስኮቱን ከፈቱላቸው። ዕለቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት መሆኑ፣ ቀደም ሲል በዚሁ ዕለት ሰዶማውያንን የሚቃወም ታላቅ ሰልፍ እንዳይካሄድ መደረጉ ያለምክኒያት አልነበረም። አቶ ጆን ኬሪ፡ ልክ እንደ ጆርጅ ቡሽ ቤተሰቦች፡ የሉሲፈራውያኑ የራስ ቅል እና አጥንቶችቡድን አባል ናቸው።

ከሳምንታት በፊት ጆርጅ ቡሽ ፡ አሁን ደግሞ ጆን ኬሪ ተከታትለው ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው ደስ አላለኝም፡ እንደ ጥሩ ዜናም መወሰድ ያለበት አይመስለኝም። እነዚህ ግለሰቦች፣ ቁልፍ የፖለቲካ ሚና የሚጫወቱ ግለሰቦች ከመሆናቸው ጀርባ ሌላ አጸያፊ የሆነ ማንነት ያላቸው አደገኛ ሰዎች ናቸው። ሰማያዊ ከረባት አስረው ፈገግ ስላሉልን የሚወዱን ወይም የማይጎዱን ግለሰቦች እንዳይመስሉን፣ ከካሜራ ውጭ ብዙ ቀፋፊና ዘግናኝ የሆኑ ነገሮች ላይ የሚሠማሩ ናቸው።

ያው ሰሞኑን በአሜሪካዋ ኦክላሆማ ከተማ ከመጽሐፍ ቅዱስ አሠርቱ ቃላት ጎን ፔንታግራም የተነደፈበትና የፍየል ጭንቅላት ያለው አንድ ኃውልት ለሰይጣን እንዲቆም ተደርጓል። ፕሬዚደንት ኦባማ ተማሯባት በምትባለዋ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስን የሚረግሙ ሰይጣናዊ የ ጸሎትሥነስርዓት ይካሄዳል። በትናንትናው ዕለት ደግሞ አመታዊውን የዩሮቪዥን ዘፈን ውድድር ፊቷ በጺም የተሞላችው አውስትሪያዊት አሸናፊ እንድትሆን ተደርጋለች። በጣም የሚያስደነግጥ ነው፡ አቀራረቧና መመሳሰሏ ሆን ተብሎ በምስሎች የምናውቃቸውን የኢየሱስ ክርስቶስ አቀራረቦች እንዲገጥሙ ተደርገዋል።

DSB2ባለፈው ሳምንት የአዲስ አበባ ቆይታቸው፡ ጆን ኬሪ፡ አፍሪቃውያን ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት የተፃፉትን መፃሕፍትእየተርጎሙ ኑሯቸውን በዚህ ዘመን መግፋት አይኖርባቸውምሲሉ፡ በተዘዋዋሪ የኢትዮጵያን ክርስትና ማንቋሸሻቸው ነው። በጣም ያሳዝናል! በይበልጥ የሚያሳዝነው ግን ወገናችን እነዚህ ሰዎች የሚረጩትን መርዝ ሳይመረምር በመቀበል የእነርሱ አምላኪ ለመሆን መብቃቱ ነው። ሰልጥነዋልእየተባለ ስልጣኒያቸው ያፈራውን ቆሻሻ በማግበስበስ የራስን ስልጣኔ ማንቋሸሽ ብሎም ማጥፋት በጣም ያሳዝናል፡ ይረብሻል። ዱሮ ሴቶች አጫጭር ቀሚስ እየለበሱ እንዲወጡ ይደረግ ነበር፡ አሁን ደግሞ ወንዶቹ ሱሪያቸው እስከሚወልቅና የኋላቸው እስኪታይ ድረስ ዝቅ አድርገው እንዲለብሱ እየተደረገ ነው። ይህ ሁሉ ጣጣ ከሰዶማውያን አጀንዳ ጋር የተያያዘ ነው።

ፎቶዎቹ ላይ የሚታዩትን የሙታን ምልክቶች የሚለብሱ ወገኖቻችን በጣም እየበዙ፡ ማንም በየመንገዱ የሚያየው ነው። ይህ እንዲያው ዝምብሎ ቀላል የሆነ ነገር ሊመስለን ይችላል፡ ግን አይደለም። እነዚህ ልብሶች እንዳይልበሱ፣ ምልክቶቹ ያሉባቸው ልብሶች ሁሉ እንዲቃጠሉ መደረግ አለበት።

እግዚአብሔር ከነፍስ አዳኞች ይጠብቀን

እንደ ሰይፍ ምላሳቸውን አሰሉ፤ መራራ ነገርን ለማድረግ፥ ንጹሕንም በስውር ለመንደፍ ቀስትን ገተሩ፤ ድንገት ይነድፉታል አይፈሩምም። ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ፤ ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ፤ ማንስ ያየናል? ይላሉ[መዝሙር 643:5]

__

 

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: