ከአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የተሰረቀው ታቦት ከጅቡቲ በተዓምራት ተመለሰ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 27, 2014
የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱአት፤ እኛንና ሕዝባችንን እንዳትገድል በስፍራዋ ትቀመጥ፡፡[1ኛ ሳሙ. 5፤ 12]
በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በደብረ ብርሃን ከተማ ልዩ ስሙ ጎሸ ባዶ ከሚባለው አካባቢ ከጥንታዊቷ አፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የተሰረቀው የመድኀኔዓለም ታቦት ከጅቡቲ በተዓምራት ተመለሰ፡፡
ከአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የተሰረቀው የመድኀኔዓለም ታቦት ጅቡቲ ውስጥ ለ17 ዓመታት በአንድ ግለሰብ ቤት ተደብቆ ከቆየበት ተዓምራቱን በመግለጡ በተደናገጠው ቤተሰብ ጠቋሚነት፤ ጅቡቲ ለሚገኘው ለምሥራቀ ጸሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በማስረከብ ሚያዚያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል፡፡
“በ1938 ዓ.ም. የተቀረጸውና በአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የነበረው የመድኀኔዓለም ታቦት ሐምሌ 28 ቀን 1989 ዓ.ም. የቤተ ክርስቲያኑን በርና መስኮት ተሰብሮ መሰረቁን ለወረዳው ቤተ ክህነትና ለፖሊስ በወቅቱ አሳውቀን ነበር፡፡ ለማፈላለግ ያደረግነው ጥረት ሁሉ መና ሆኖብን ቆይቷል፡፡ እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ ወደ ቤቱ ይመለስ ዘንድ ፈቀደ፡፡” ይላሉ የገዳሙ አስተዳዳሪ ቄስ ኃይለ ጊዮርጊስ መኮንን፡፡
ጅቡቲ እንዴት እንደተወሰደ እስካሁን በግልጽ የታወቀ ነገር እንደሌለ የሚገልጹት የጅቡቲ ምሥራቀ ጸሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ዮናስ መልከ ጼዲቅ “ታቦቱ በግለሰቡ ቤት ታላቅ ተዓምራትን ነው ያደረገው፡፡ በቤቱ ውስጥ ደብቆ ያስቀመጠው ግለስብ ሚስት ስታብድ ልጁ ሞቶበታል፡፡ በዚህ የተደናገጠው ሌላው የሰውየው ልጅ በቤታቸው ውስጥ ታቦት እንዳለና ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲወሰድ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ጉዳዩን በመከታተል ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲና ከሌሎችም ጋር መረጃ በመለዋወጥ ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ችለናል” ብለዋል፡፡
__
Like this:
Like Loading...
Related
This entry was posted on April 27, 2014 at 20:56 and is filed under Ethiopia, Faith, Infos.
Tagged: ቅዱስ ገብርኤል, ተዓምራት, አፄ ዋሻ ማርያም ገዳም, የመድኀኔዓለም ታቦት, ጂቡቲ. You can follow any responses to this entry through the RSS 2.0 feed.
You can leave a response, or trackback from your own site.
Leave a Reply