“ምስጢራውያኑ” ወደ ኢትዮጵያ ለምን ይጎርፋሉ?
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 22, 2014
ዛሬ: እ.አ.አ. ማርች 22 ነው። ሦስተኛው ወር፡ 22ኛው ቀን መሆኑ ነው፤ ይህም = 322።
እነዚህ ቁጥሮች በምስጢራውያኑ የሉሲፈራውያን ማህበረሰብ ፡ ማለትም በ “ቅል እና አጥንቶች” (Skull & Bones) ዘንድ ከፍተኛ ትርጉም አላቸው። አደገኛው የቀድሞው የ ዩኤስ ፕሬዚደንት ጆርጅ ቡሽ እና ወስላታው: ድንች–ፊት የውጭ ጉዳይ ምኒስትር፡ ጆን ኬሪ: የዚህ ርኩስ ቡድን አባላት ናቸው።
ሙሉ ጨረቃ በምትታይበትና የፋርስ ዛራቱስትራውያን አዲስ ዓመታቸውን በሚያከብሩባቸው በእነዚህ ቀናት ክራይሚያ ከሩስያ ጋር እንደገና ተቀላቀለች፣ ጆርጅ ቡሽ ደግሞ ኢትዮጵያን ጎበኙ። ባዕዳውያን ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙባቸው ሁለት ምክኒያቶች አሉ፤ አንደኛውና ዋናው ምክኒያት ሕዝባችንን፡ አገራችንን ለመተናኮል (95%ው) ሲሆን ሌላው ደግሞ ሕዝባችንን ይቅርታ ለመጠየቅ ብሎም ራሳቸውን ለንስሐ ለማዘጋጀት ነው። ታዲያ ጆርጅ ቡሽ በዚህ “322” ሰሞን ወደ ኢትዮጵያ ያስወሰዳቸው ምክኒያት የትኛው ይሆን?
Leave a Reply