የአድዋ ድል ከእግዚአብሔር የተገኘ ድል ነው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 1, 2014
ከ 118 ዓመታት በፊት ዓድዋ ላይ በኢጣሊያ ላይ አንፀባራቂ ድል የተቀዳጀው የኢትዮጵያ ሠራዊት ጠቅላይ አዛዥ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ለፈረንሣዊው ሙሴ ሞንዶን ከጻፉለት የምሥራች ደብዳቤ እንዲህ ብለው ነበር፦
‹‹የምሥራች በእግዚአብሔር ቸርነት የየካቲት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት ኢጣልያንን ድል አድርጌ መታሁት፡፡ በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ፡፡ አምላከ ኃያላን ረድቶኝ ፈጀሁት፡፡ ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ››
የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ባሕር ተሻግሮ ድንበር አቋርጦ የመጣውን ወራሪው የኢጣሊያ ሠራዊት ድላቸውን አስመልክቶም በወሩ (መጋቢት 23 ቀን 1888 ዓ.ም.) ዳግማዊ ምኒልክ ለሙሴ ሽፋኔም እንዲህ ብለው የዓድዋውን ውሎ ገለጹለት፦
‹‹በጥጋባቸው ዓድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ፡፡ እኔ ግን በድንቁርናቸው ብዛት የእነዚያን ሁሉ ክርስቲያን ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አደረግኳቸው ብዬ ደስ አይለኝም››
አድዋ ላይ በተካሄደው ጦርነት የተገኘው ድል የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው በባርነትና በቅኝ ግዛት የሚማቅቁ አፍሪካውያንና የመላው ጥቁር ሕዝብ እንዲሁም የሕዝበ ክርስቲያን/የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ድል ነው።
የዛሬውንና በመላው ዓለም አንፀባራቂ የሆነውን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስከበረውን የዓድዋ ድል በዚህ ዕለት መሆኑ አጋጣሚ አይደለም።
ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያን በአካል ተገኝተው የጎበኙ አያሌ የውጭ ሀገራት ዜጎች ስለ ሀገራችንና ስለ ሕዝቦቿ በጋራ የሚመሰክሩት አንድ እውነት አለ፤ ይኸውም፡–
‹‹ኢትዮጵያውያን ለሃይማኖታቸውና ለነጻነታቸው ቀናዒዎች ናቸው፡፡›› የሚል ነው፡፡ በአንድ ወቅት ታዋቂው የፈረንሳይ ጋዜጠኛ ዳንኤል ሮፕስ እ.ኤ.አ 1963 ዓ.ም ‹‹አክሌዥያ›› በሚባል ጋዜጣ፤ ‹‹የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ታውቃላችሁን?›› በሚል ርዕስ ባሰፈረው ሐተታ እንዲህ ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል፡–
‹‹ወራሪዎች ምድርዋን በግፍ የያዙባት መሆኑን ታሪክ ያወሳል፤ ነገር ግን ሃይማኖት የእንቅስቃሴዋ መሣሪያ ሆኖ በመገኘቱ ነጻነቷን መልሳ አግኝታለች፡፡ በማዕከላዊው ክፍለ ዘመን ‹‹የካህን የዮሐንስ ግዛት›› በአረመኔው ዓለም ተከቦ የክርስቲያን ምሽግ ሆነዋል እየተባለ ስለ ኢትዮጵያ ይነገር የነበረው
ሁሉ ፍጹም ልበ ወለድ ታሪክ አይደለም፡፡ ከሁለት ሺ ሜትር በላይ ከፍታ ያለውን ደጋማና ለምለም መሬት ቁልቁል የሚያዩት ቀይ፣ ጥቁርና ሰርጥነት ያላቸው የእሳተ ገሞራ ውጤት ባሕርይ ያላቸው ጠረጴዛ መሰል ተራራዎች የጊዜን ውሽንፍር እንዳሳለፉትና የባሕር ዓሣም ሳይበገርና ሳይላላ ማዕበሉን እንደሚያሳልፍ ክርስቲያኒቷ ኢትዮጵያም በታሪክ ውስጥ ጠንካራ ስፍራዋን ይዛ ቆይታለች››
ይህ ጋዜጠኛ እንዳለው ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለትና ሦስት ሺህ ዓመታት በርካታ ፈተናዎች አጋጥመዋታል፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ከተቃጣው አያሌ የውጭ ወራሪዎች ጥቃት አብዛኛው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተሰነዘረ ነበር፡፡ የዚህም ዋነኛው ምክንያት ደግሞ በኢትዮጵያ የረጅም የስልጣኔና የነጻነት ታሪክ ውስጥ የሕዝቡን ብሔራዊ ንቃተ ኅሊና በመቅረጽ ጠቃሚ ሚና የነበራትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በመምታት ሹማምንቱና ሕዝቡ የኢጣሊያንን የበላይ ገዥነት እንዲቀበሉ ለማስገደድ ነበር፡፡
ዛሬም በዩክሬይን እየታየ ያለው ከባድ ውጥረት ነፃነታዊ፣ ዲሞክሪያሳዊ ወይም ግዛታዊ ፍላጎቶችን ይፈልጉ ዘንድ የተከሰተ ሁኔታ አይደለም። ይህ ውጥረት፡ ቀደም ሲል በቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ (ሰርቢያ)፣ በአርመኒያ፣ በጆርጂያ፣ በግሪክ፣ በቆጵሮስ፣ በግብጽ እና በሶሪያ መጀመሩን እናስታውሳለን። እነዚህ ሁሉ አገሮች፣ ሩስያን እና ዪክሬንን ጨምሮ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች አገሮች ናቸው። በተለይ ኢትዮጵያን፣ ግብጽን፣ሶርያን፣ ሩስያን እና ሰርቢያን የሚያስተሳስራቸው ሰምአቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ የእነዚህ አገሮች ዐቃቤ መልአክ ነው።
ይህ በሩሲያ እና በዮክሬን መካከል የሚታየው ፍጥጫ በዚህ በቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት በዓለማችን ታሪካ ቁልፍ የሆነ ሚና የሚጫወት ይሆናል። ቀደም ሲል በሉሲፈራውያኑ የ ዔሣው እና የ እስማኤል ዘሮች ተጠንስሶ የነበረው ሤራ ለመላው ዓለም ነዋሪ የሚጋለጥበት ወቅት ይሆናል። በአንግሎ–አሜሪካውያን መሪነት የሚመታው ይህ የጦርነት ከበሮ በምስራቅ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ከተሰማ በኋላ የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን በር ማንኳኳት ይጀምራል።
ከአድዋ ድል በኋላ፡ መጋቢት 23 1988 ዓ.ም አፄ ምኒልክ ለሩሲያው/ ለሞስኮብ ንጉሥ / ት‘ዛር ኒቆላዎስ 2ኛ (እ.አ.አ 1868 – 1918) በጻፉት ደብዳቤያቸው፡–
‹‹እንደ አውሮፓ ነገሥታት ሥራት ሁሉ ጠብ መፈለጋቸውን ሳያስታውቀኝ፣ እንደ ወምበዴ ሥራት ሌሊት ሲገሰግስ አድሮ ሲነጋ ግምባር ካደረው ዘበኛ ጋር ጦርነት ጀመረ፤ ጥንት ከአሕዛብና ከአረመኔ አገራችን ጠብቋት የሚኖር አምላክ ከእኛ ባይለይ በእግዚአብሔር ኃይል ድል አደረግሁት››
በማለት ድሉ የእግዚአብሔር መሆኑን አስረግጠው ተናግረው ነበር፡፡
ት‘ዛር ኒቆላዎስ 2ኛ ለኢትዮጵያና ለዐቃቤ መልአኳ፡ ለሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያላቸውን አድናቆትና ክብር ለመግለጽ ግዙፍ የሆነውን ደወል ለአዲስ አበባ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በስጦታ መልክ አስረክበዋል።
ንጉሥ ኒቆላዎስ 2ኛ የመጨረሻው የሩስያ ትዛር ነበሩ። ነጉሡ የታላቋ ብሪታኒያና የጀርመን ነገሥታት በጠነሱስት የጥቅምቱ የሩስያ አብዮት ከወንበራቸው እንዲለቁ ተደርገው፡ በቅጥረኛው፡ ቭላዲሚር ኢሊይች ሌኒን ቦልሸቪክ ሰይጣኖች ከነቤተሰቦቻቸው ተረሽነዋል። የአፄ ኃይለሥላሴ እና የትዛር ኒኮላዎስ፡ የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ታሪካዊ እጣ በጣም ተመሳሳይነት አለው።
የሩሲያው ኮሙኒዝማዊ ሤራ ከጅምሩ ያተኮረው በሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና በተከታዩቿ ላይ ነበር። በ “ነጭ” ሕዝቦች መካከል ባለ “ነፍሶች“(Soul) ሆነው የቀሩት ሩስያውያን ናቸው (በተለይ በሴቶቻቸው ላይ የሚንጸባረቀው ቁንጅና ነፍሳቸው እንደ ዔሳው እና እስማኤል ልጆች ገና ስላልተነጠቀ ነው)
ኢትዮጵያን በመክዳት ለአረቦች እና ሶማሊያውያን መቀለጃ እንድንሆን ያደረገንን አመጸኛ ትውልድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እያገዘ ከፍተኛ ሚና ለመጫወት የበቃው የፕሪዚደንት ጂሚ ካርተር መስተዳደር ነበር። ይህን መስተዳደር ከጀርባ ሆነው ሲመሩት የነበሩት፡ በአሁኑ ወቅትም የባራካ ኦባማን መስተዳደር የሚመሩት እርጉሙ የካርተር ብሔራዊ–ጸጥታ አማካሪ፡ ዜቤግኔው ብረዥንስኪ ናቸው። እኚህ ሰው፡ ልክ እንደ ሄንሪ ኪሲንጀር በአፍሪቃውያን፣ በሩሲያውያን እና በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ ጥላቻ አላቸው። ብረዥንስኪ እ.አ.አ በ2007 ዓ.ም የሚከተለውን ተናግረው ነበር፦
“After the collapse of the USSR, the main enemy of the USA will be the Russian Orthodox Church.”
ብረዥንስኪ ፓላንዳዊ ዝርያ ያላቸው ግለሰብ ናቸው። አፄ ኃይለሥላሴ ከስልጣን በተወገዱበት ወቅት ሪፖርት ለመስራት ወደ አዲስ አበባ ተልከው የነበሩት ሪቻርድ ካፑቺንስኪ የተባሉት ታዋቂ ፖላንዳዊ ጋዜጠኛ ነበሩ። ፖላን ያካቶሊኮች አገር ነች። “ጥቁሯ ማዶና/ማርያም” በጣም ከሚከበሩባት አገሮች መካከል አንዷ ፓላንድ ናት። ኦቶማን ቱርኮች አውሮፓን ለመውረር በኦስትሪያዋ ቪየና በር ላይ ሲደረሱ በፖላንድ ጦር ሠራዊት እና ጄነራሏ ነበር ሊገረሰሱ የበቁት። የኢትዮጵያውያን ደም በየመንገዱ በሚፈሱባቸው ዓመታት የሮማው ጳጳስ (ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛው) ከፖላንድ መመረጣቸው አጋጣሚ አልነበረም። በ 110 አገራት ጉብኝት አድርገው የነበሩት እኚህ ጳጳስ ግብጽ እና ሱዳን ደርሰው ወደ ኢትዮጵያ ያልመጡበትም ሌላ ምክኒያት አለው። ለማንኛውም፡ አሁን፡ የአውሮፓው ሕብረት አባል አገር፡ ፖላንድ፡ ልክ የቱርክ ዓይነት ሉሲፈራዊ ሚና በመጫወት ላይ ነች። ጸረ–ክርስቶሷ ቱርክ እስላማውያን ተዋጊዎችን ወደ ሶሪያ በመላክ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች እንደምታስጨፈጭፍ፡ ፓላንድም ፋሽስት የሆኑ ከዳተኛ ዪክሬናውያንን እየረዳች ኦርቶዶክሳውያን በመተናኮል ላይ ናት።
ምዕራባውያኑ በሶቺ የተካሄዱትን የክረምት ኦለምፒክ ጨዋታዎች መሣሪያዎቻቸው በሆኑት የቼችንያ እና ደግስታን ሽብር ፈጣሪዎች በኩል ማሰናከል ስላልቻሉ፤ አሁን በከዳተኛ ዮክሬኒያውያን፣ ሰዶማውያን እና ክራይሚያ–ግማሽ–ደሴት በሚገኙት ቱርክ ታታሮች አማካኝነት ሁከት በመፍጠር ላይ ይገኛሉ። በነገራችን ላይ በዚህ ሳምንት የተዋቀረው የዪክሬን ሽግግር መንግሥት ፕሬዚደንት “የባፕቲስት ቸርች” ተከታይ ነው።
የአድዋ ድል የተገኘው የጊዮርጊስ እለት የካቲት 23 1888 ዓ.ም ነበር፤ አፄ ምኒልክም ጦርነቱ እስከሚጀመርበት የመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ በአድዋ ማይጓጓ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሆነው አምላከ ጊዮርጊስ ከእሳቸውና ከሠራዊታቸው ጋር እንዲሆን በጸሎት እየተማጸኑ እንደነበር በወቅቱ የነበሩ ሰዎች መስክረዋል፡፡ የአፄ ምኒልክ ጸሐፊ የሆኑት ጸሐፌ ትእዛዝ አለቃ ገብረ ሥላሴ ስለ አድዋ ድል በጻፉትና እማኝነታቸውን በሰጡበት የመጽሐፉ ክፍል ድሉ ከእግዚአብሔር የተገኘ እንደሆነ ከመግለፃቸውም በላይ የክርስቲያኖች ደም በከንቱ ስለ መፍሰሱ የተሰማቸውን ሐዘኔታም በመጋቢት 23 1888 ዓ.ም ለፈረንሳዊው ሙሴ ሸፍኔ በላኩለት ደብዳቤያቸው ገልጸዋል፡፡
“ከአላጌ ጦርነት በኋላ፣ ጣሊያኖችን ጦርነት ይቅር፣ የክርስቲያንም ደም በከንቱ አይፍሰስ፣ እርቅ ይሻላል ብላቸው እምቢ ብለው መጥተው በጥጋባቸው አድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ፡፡ እኔ ግን በድንቁርናቸው ብዛት የነዚያን ሁሉ ክርስቲያን ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አደረኳቸው ብዬ ደስ አይለኝም፡፡ ነገር ግን በግፍ የመጡ ሰዎች ናቸውና እግዚአብሔር ግፉን አነጣጠረን“
የምኒልክ ፈረስ በክንፎቹ ሔደ
(ተክለ ጻድቅ መኩሪያ፤ አፄ ምኒሊክ እና የኢትዮጵያ አንድነት፣ 1983 ዓ.ም.)
ምኒልክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ
ግብሩ እንቁላል ነበር ይኸን ጊዜ አበሻ፡፡
በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ
ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡
ምኒልክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ
ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡
መድፋን መትረየሱን ባድዋ መሬት ዘርቶ
እንክርዳዱን ነቅሎ ስንዴውን ለይቶ
የዘራውን እህል አጭዶና ወቅቶ
ላንቶኔሊ አሳየው ፍሬውን አምርቶ፡፡
እንዳቀና ብሎ ለምኖ መሬት
ንግድ ሊያሰፋበት ሊዘራ አትክልት
እየመጣ ሊሰጥ ግብሩን ለመንግሥት
ለጓዙ ማረፊያ አገር ቢሰጡት
ተጠማኝ ሰንብቶ ሆኖ ባለርስት
ወሰን እየገፋ ጥቂት በጥቂት
እውነት እርስት ሆነው ተቀበረበት፡፡
ባሕር ዘሎ መምጣት ለማንም አትበጅ
እንደ ተልባ ስፍር ትከዳለች እንጂ
አትረጋምና ያለተወላጅ፡፡
የዳኛው አሽከሮች እየተባባሉ
ብልት መቆራረጥ አንድነትያውቃሉ
ዓድዋ ከከተማው ሥጋ ቆርጠው ጣሉ፡፡
የእስክንድር ፈረስ መቼ ተወለደ
ደንገላሳ ሲዘል እየተንጓደደ
የሮማውን ኩራት በእግታ አሰገደ፡፡
አገርህን ምኒልክ እንዳሁን ፈትሻት
እጁን ቀምሼ አላውቅም እያለ ሲያማህ
ቀመሰና እጅህን መጥቶ ጠላትህ
ሮም ላይ ተሰማ ለጋስ መሆንህ፡፡
አባተ በመድፋ አምሳውን ሲገድል
ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል
የጐጃሙ ንጉሥ ግፋ በለው ሲል
እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሃን
ዳዊቷን ዘርግታ ስምዓኒ ስትል
ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል
ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ በርሜል፡፡
እንደ በላዔ ሰብአ እንደመቤታችን
ሲቻለው ይምራል የኛማ ጌታችን
የልዳው ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቶቻችንን በአድዋ ጦርነት ሃይማኖት እንዳይበረዝ ሀገር
እንዳይወረር ርስታችን ለባዕዳን እንዳይሆን በተጋደሉበት ዘመን ተራዳኢነቱን ገልፆአል፡፡ የመናገሻ ገነተ ፅጌ ጊዮርጊስ ታቦት ይዘው ጠላትን ድል አድርገዋል በወቅቱ አቡነ ማቴዎስ የእመቤታችን ታቦትና የቅዱስ ጊዮርጊስም ታቦታት ይዘው ዘመቱ የአክሱም ካህናትም የእመቤታችን ሥዕልና ሰንደቅ አላማ ይዘው ተሠለፉ የፅዮን እምቢልተኞችም በእቴጌ ጣይቱ ፊት ይነፋ ነበር፡፡ ከለሊቱ 11፡00 ሠዓት ጦርነቱ ሲጀመር እቴጌ ጣይቱ በማጅራታቸው ድንጋይ ተሸክመው በጉልበታቸው ተንበርክከው በጋለ ፀሎት ወደ እግዚአብሔር ይፀልዩ ነበር፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስም ስራሰላቸው ለሀገሩ ለሃይማኖቱ የተሠለፈውን አላሳፈረውም የሰለጠነውን የወራሪ ጦር በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳዒነት አባቶቻችን ድል ነሱ፡፡
የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት የእመቤታችን አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
Leave a Reply