Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • June 2013
  M T W T F S S
   12
  3456789
  10111213141516
  17181920212223
  24252627282930
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

ቅዱስ ጸበላችን የጽላተ ጽዮን ተዓምር ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 19, 2013

ሣንሱር ያልተደረገ ጽሑፍ ነው ስህተት ካለ ክቡራን ወንድሞችና እህቶች እድታርሙኝ በትህትና እጠይቃለሁ…

Tsebelሉሲፈር ሰይጣን/የንጋት ልጅ/የአጥቢያ ኮከብ/ብርሃን መልአክ፡ ዓለማችንን ሙሉ በሙሉ በእጁ አስገብቶ የእግዚአብሔርን ልጆች ለማጥፋት ብሎም የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስን ሁለተኛ መምጣት በመጠባበቅ የተቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ይገኛል። ጌታችን በብርሃን መልክ ሆኖ ወደ ምድራችን እንደሚመለስ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። ታዲያ ሉሲፈርና ልጆቹ በእጆቻቸው በሚሠሯቸው ነገሮች ይተማመናሉና ተራቅቀዋልየሚሏቸውን ሌዘር ጨረር አፈንጣቂ መሣሪዎች አምርተው ክርስቶስን በሌዘር ለመዋጋት በመዘጋጀት ላይ ይገኛሉ።

ጽላተ ሙሴ/ታቦተ ጽዮን በኢትዮጵያ መሆኗን እኛ ኢትዮጵያውያን ባናውጅም እንኳ፡ የሉሲፈር ልጆች ይህን ሃቅ በራሳቸው የተገነዙበት ከሺህ ዓመታት በፊት ነው። ይህ ቅዱስ ጽላት ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ አሁን እንደ ቀላል አድረገን የምናያቸውን ተዓምራት ከመፈጸሙ በፊት፡ እስራኤላውያንን ከግብጻውያን ባርነት ነፃ አውጥቶ ቀይ ባሕርን የከፈለላቸው፤ እየሱስ ክርስቶስና ቅድስት እመቤታችን በግዮን/ዓባይ ወንዝ በኩል አድርገው ወድ ቅድስት ኢትዮጵያ እንዲመጡ፣ እንዲሁም ጌታችን በውሃ ላይ ይራመድ ዘንድ የተጠቀመበት እጅግ በጣም ኃይለኛ ጽላት ነው የሚል እምነት አለኝ።

ነብዩ ሙሴ እሥራኤላውያንን ነፃ እንዲወጡ ከመርዳቱ በፊት ለ40 ዓመታት ያህል የኢትዮጵያ ንጉሥ የነበረ ነበር። በኢትዮጵያ ቆይታው ጽላቱ ከተዋሃዳቸው ኢትዮጵያውያን ዘንድ አስፈላጊውን ትምሕርት፡ በቂ የሆነውን ኃይል ካገኘ በኋላ ነበር ወደ ፈርዖን ግዛት ተመልሶ በእርግጠኛ መንፈስ የእግዚአብሔርን ልጆች ነፃ ለመውጣት የበቃው።

በዘመናችንም ቢሆን የጽላቱን ኃይለኛነት ለማሳወቅ ምሳሌዎችን መዘርዘር አስፈላጊ አይደለም፡ ዓይን፣ ጆሮና ልብ ያለው ሁሉንም መገንዘብ ይችላል። ቅዱስ ጽላቱ ለሰው ልጅ ሁሉ የተላከ ነው፡ ለእግዚአብሔር ወዳጆች ጋሻና ጦራቸው ነው። ቅዱስ ጽላቱ በቅድስት ኢትዮጵያ እንደመገኘቱ የኢትዮጵያንና የአምላኳን ወዳጆች ይባርካል፣ ጠላቶቻቸውን ደግሞ ይቀስፋል። በተለይ በኢትዮጵያ አገራችን የሚገኙትና መልካቸውን ያልቀየሩት/የማይቀይሩት ኢትዮጵያውን የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆኑ ከጽላቱ ጋር ተዋሕደዋል፤ የጽላቱ ኃይል እነርሱ ላይ/ውስጥ አድሮባቸዋል።

እነርሱ ከጽላቱ ጋር ሆነው የተፈጥሮ ኃይልን ማዘዝ ይችላሉ። ባገኙት ኃይልም በሰማይ ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሳተላይቶች፣ አንጋፋዎቹን በኑክሌር ኃይል የሚሰሩ መብራት ኃይል ማመንጫዎችን እንዲሁም የኮምፒውተር ኔትወርኮችን በመዝጋት አሁን ያለው ስልጣኔ ላይ ከፍተኛ አደጋ የማድረስ ችሎታው አላቸው። የሉሲፈር ኃይሎች ይህን ስለሚያውቁ፡ ኢትዮጵያን በጠፈር መርከቡ፣ በሳተላይቱ በተቻላቸው ዘዴ ሁሉ ሌት ተቀን አተኩረው ይመለከታሉ/ይቆጣጠራሉ።

በቅድስት አገራችን የሚገኙ ቅዱሳን ቦታዎች፤ ዓብያተ ክርስቲያናት፣ ገዳማት በጽላቱ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ቅዱሳን ቦታዎች ናቸው። ጽላቱ ወንዞቻችንን፣ ሃይቆቻችንና ዛፎቻችንን ይቆጣጠራል፣ ዓባይን ይቆጣጠራል፣ ጣና ሃይቅን ይቆጣጠራል፣ በቅርቡም ቀይ ባሕርን ከሉሲፈር ተከታዮች እጅ ነፃ አውጥቶ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ይበቃል። አገራችን የሚገኙ የጸበል ቦታዎች ተዓምር አምጪና ፈዋሽ የሆኑት፡ ጽላቱ፡ ቅዱስ መንፈስን እንዲያርፍባቸው ስለሚረዳ ነው። ስለዚህ ከጽላቱ ጋር የተዋሐዱት ቅዱሳን ኢትዮጵያውያን በቅዱስ መንፈስ እየተመሩ አዳዲስ ጸበላትን ሲያገኙና ዓብያተ ክርስቲያናትንም ባጠገባቸው ሲያሠሩ የጽላቱን፤ የመንፈስ ቅዱስን በረከት ለማግኘት ተዓምራትን ለማየት እድሉን ለማግኘት እንችላለን ማለት ነው። የዚህ ጠላቶች ግን ወዮላቸው!

የሉሲፈር ልጆች ይህን ምስጢር ደርሰውበታል፣ ወደ ቅድስት ኢትዮጵያም ጠጋ፣ ወደ ቅዱሳን ቦታዎቻችንም ቀረብ እያሉ ሊፈታተኑን፣ ሊረብሹን እና ሊዋጉን ይሻሉ። ባንድ በኩል ፀረክርስቶስ የሆኑ ሃይማኖቶችና ሰዶማውያን የጣዖት አምልኮቶች በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥታቱና ሳይንስ ዓምላኪ ቡድኖች፡ ሁሉም በአንድ መንፈስ ጽላቱን በመቆጣጠር ጌታችን እየሱስ ክርስቶስ ሲመለስ እንይዘዋለን ብለው በማሰብ ከፍተኛ የሆነ ዝግጅት በማድረግ ላይ ናቸው።

ለዚህም ዓላማቸው በኢትዮጵያ አካባቢ የሚገኙትን ምድሮች አንድ በአንድ በመቆጣጠር ጥንታዊ ክርስቲያን የሆኑ ሕዝቦችን በሊባኖስ፣ በኢራቅ፣ በሶርያ እና በግብጽ በማጥፋት ላይ ይገኛሉ። ኦርቶዶክስ የሆኑትን ሰርቢያን በቦምብ ደበደብው የአገሪቷን ክፍል ለእስማኤላውያን አሳልፈው ሰጡ፣ ጆርጂያን ሩስያንና አርመንያን የግብረሰዶማውያንን መርዝ በመርጨት እየተተናኮሏቸው ነው፣ የግሪክና ቆጵሮስንም ምጣኔ ኃብት አራቁተው ሕዝቦቹን ለማበርከክ እየሞከሩ ነው። በነገራችን ላይ ቆጵሮስ ባንክ ውስጥ በብዛት የሚገኘው ገንዘብ የኃብታም ሩስያውያን እና የግብጽ ኮፕቶች ገንዘብ ነው።

በመዝሙረ ዳዊት፣ በሶፎኒያስ እና በአሞጽ መጽሐፍት የተገለጸችው ኢትዮጵያ ከእስራኤል የበለጠ ኃይልና ክብር እንዳላት የሉሲፈር ኃይሎች ሳይቀሩ ያውቃል/ያምናሉ። ሉሲፈርያውያኑ ነጻግንበኞች(ፍሪሜሶኖች)፡ ቴምፕላሮችንና ጀስዊቶችን ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ጽላቱን እና ቅዱሳን የሆኑ የኢትዮጵያ/የእግዚአብሔር ንብረቶች ወደ አገሮቻቸው ለመውሰድ ሞክረዋል። ስኮትላንዳዊው ነጻ ግንበኛ ሌባ፡ ጀምስ ብሩስ እንደምሳሌ ይጠቀሳል።

ArkC14ኛው ክፍለዘመን የንበሩትና ናይት ኦፍ ቴምፕለርስ“(የቤተመቅደሱ ባለሟሎች)በመባል የሚታወቁት የነጻግንበኞች ቅድመአያቶች፤ በንጉሥ ላሊበላ ወንድም በንጉሥ ሃርቤይ ለአውሮፓውያን በተፃፈ ደብዳቤ እንዲሁም በአፄ አምደጽዮን ወደ ፈረንሳይ በተላኩ መልዕክተኞች ናይት ኦፍ ቴምፕላርስ በመላው አውሮፓ እንዲጨፈጨፉ ኢትዮጵያውያን አድርገዋል ብለው ፍሪሜሶኖች ያምናሉ። ስለዚህም ኢትዮጵያን ከድህነት እንዳትላቀቅና ሁልጊዜ ከጦርነት አዙሪት ውስጥ እንዳትወጣ በማድረግ ሃገራችንን እየተበቀሏት ይገኛሉ። ዓባይንም በተመለከተ፡ ግብጽንና ሳዑዲ ዓረቢያ እስከ አፍንጫቸው በማስታጠቅ እንዲጠግቡና እንዲኮሩብን ያደረጉት እነርሱው ናቸው። ግብጽ ቅዥታማ የማስፈራርያ ፕሮፓጋንዳዎችን እንድትነዛ የተገፋፋቸው በፍሪሜሶናዊው የ የራስ ቅል እና አጥንቶች/ ስካል ኤንድ ቦንስ)አባል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ነው። ጆን ኬሪ ለግብጽ ሁለት ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ስጦታ ለቁንዶ በርበሬና ጨው ጺማሙ ለፕሬዚደንት ሙርሲ ካበረከቱ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ወርደው በኢትዮጵያውያን ላይ አላገጡ። ሃርድ ቶክየተባለውን የቢቢሲ ፕሮግራም ያየ ይህን በግልጽ የሚታዘበው ነው። 50 ዓመት የምስረታ በዓሏን በምታከብረው አፍሪቃ የተገኙት ጆን ኬሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአፍሪቃውያን ጋር ስለ አፍሪቃ ወይም ስለ ኢትዮጵያ ሁኔታ ሳይሆን ስለ አፍጋኒስታን፣ ፓኪስታንና ሶርያ ነበር ሆን ብለው የተነጋገሩ። የወደቀችውም ኢትዮጵያዊት(ሱዳን የወደቅችው ኢትዮጵያ ናት)የቢቢሲዋ ዘይነብ በዳዊም እየተቁነጠነጠች በአፍሪቃውያኑ ተማሪዎች ላይ በመሰላቸትና በንቀት መልክ እጆቿን ትጠነቋቁልባቸው ነበር። ምን ነካት?

ለመሆኑ አፍሪቃዊ የሚባሉት ፕሬዚደንት ኦባማ የአፍሪቃውያኑን 50ዓመት በዓል ለማክበር ለምን ወደ አዲስ አበባ አልሄዱም? በመጭዎቹ ቀናት ወደ ኢትዮጵያ ሳይሆን ወደ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪቃና ታንዛንያ ያመራሉ።

ሥልጣን ላይ ያሉ የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች እና የሮማው ጳጳስ ኢትዮጵያን አንዴም ጎብኝተዋት አያውቁም፡ ይህም ያለምክኒያት አይደለም። ምክኒያቱ፡ አንዴም፡ ቴምፕላሮችን፣ በኋላም ፍሪሜሶኖችን በተደጋጋሚ ያሳፈረች አገር ስልሆነች፣ በተለይ ደግሞ ታቦተ ጽዮን በቅድስት ኢትዮጵያ ስለምትገኝ ነው። አንድ አሜሪካዊ የፖለቲካ ሰው የፕሬዚደንትነቱን ሥልጣን ለመረከብ ሲዘጋጅ አስቀድሞ ምስጢራዊ የሆነውን የፍሪሜሶኖች/ነፃ ግንበኞች አጀንዳ ለማራመድ ብቃትነት እና ታማኝነት ሊኖረው ይገባል። እንደ አብርሃም ሊንከን እና ጆን ኤፍ ኬነዲ የመሳሰሉት ፕሬዚደንቶች በመኻል አሻፈረኝ ስላሉ ከፕሬዝደንትነቱ በግድያ ተወግደዋል።

አቶ ኦባማ ለፕሬዚደንትነት ከመብቃታቸው በፊት የኢሊኖይ ግዛት ሴነተር ነበሩ። ሴነተር ከመሆናቸው በፊት በፍሪሜሶኖች ምን ዓይነት ሥልጠና እንዳደርጉ አላውቅም፤ ነገር ግን እ..አ በ2005 .ም ላይ ቺካጎ ከተማ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ተገናኝተው ነበር። ይህም ዝም ብሎ አልነበረም።(በቅርቡም ከኢትዮጵያዊእሥራኤላዊቷ የቁንጅና ውድድር አሸናፊ ጋር መገናኘታቸው ይታወሳል።)ባራክ ኦባማ በ2006 .ም ወደ ምስራቅ ዓፍሪቃ አምርተው በኢትዮጵያ፣ ኬኒያ እና ሶማሊያ ጠረፍ በሚገኘው ባለሦስትዮሽ ቦታ ላይ በመገኘት የሉሲፈርን በረከት ተቀበሉ። እዚህ ተመልከቱ። ይህን ቦታ(‘ቱርካናሃይቅ ብለውታል)ምድራዊ ማዕከሉ በዓረቢያና በቱርክ ሲሆን ፓዙዙበሚል ስም የተጠራው ጋኔን የሚገኘው ግን እዚህ ቱርካና ሃይቅ አካባቢ ነው። ይህ ጋኔን The Exorcist 2በሚለው ተንቀሳቃሽ ሰዕል ላይ የተጠቀሰ ነው።

ሴነተር ኦባማ: ጁላይ 24, 2008 ወደ ጀርመኗ በርሊን ጎራ ብለው ከ200ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የከተማዋ ድል ቅስትእና የ ብራንደንበር በርአጠገብ ሆነው ንግግር አሰሙ። ለፕሬዚደንትነት በእጩ ተዋዳዳሪነት በመቅረብመለኮታዊውንቅባት የተቀቡትና ከጨለማ ኃይሎች አስፈላጊውን ማበረታቻ ቅመም የተቀበሉት ከዚህ በኋላ ነበር። ከዚህ ቀን በኋላ ሴኔተር ኦባማ ሁሉንም የምርጫ ፕራይመሪዎች አሸነፉ።

ለምን ጀርመን? ለምን በርሊን? ጀርመን፡ ምክኒያቱም ደቡብ ጀርመን፣ ባቫርያ ግዛት ዓለምን የሚመሩት የፍሪሜሰኖች/ኢሉሚናቲ እናት አገር ስለሆነች። በርሊን ደግሞ የሉሲፈር ዓምልኮቶች መገለጫ ከሆኑትና ምናልባትም በዓለማችን ዓይነተኛ ሚና ከሚጫወቱት ጣዖታዊ መገለጫዎች የሚገኙባት ከተማ ነች። ከነዚህም ቁልፍ ቦታዎች መካከል በግሪኩ አክሮፖሊስ” “ፕሮፒሌዓበሚል በሚታወቀው ጥንታዊ ኃውልት ቅርጽ የተሠራው የ ብራንደንበርግ በር እንዲሁም ጴርጋሞንየሚል መጠሪያ የያዘው ሙዚዬም ይገኙበታል።

ጴርጋሞን በጥንቷ ግሪክ በአሁኗ ቱርክ የምትገኝ ከተማ ናት። በጥንታውያኑ ግሪኮች አፈ ታሪክ ዜውስ/ጁፒተር/ድያ በመባል የሚታወቀው የአማልክቶቻቸው አምላክ ተቀማጭነቱ በፔርጋሞን ነበር። እዚያም የዜውስ/ጁፒተር ሃውልት ቆሞ እንደነበረና ነዋሪዎቹም ጣዖታዊ መስዋዕቶችን ለአማልክቶቻቸው ያቀርቡ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (የሐዋርያት ሥራ 14)ቅዱስ ጳውሎስ እና ባርናባስ እዚህ ቦታ ላይ እንደነበሩና ይህን ጣዖታዊ ተግባር አጥብቀው እንደተቃወሙ ያስረዳናል። ጳውሎስን ሄርሜን አሉት፡ ባርነባስን ድያ/ጁፒተር አሉት። ይህ፡ ሰይጣን የበርነባስ ወንጌልበማለት ሙስሊሞችን እንዴት እንዳታለላቸው አያሳየንምን? ብርሃንን ጨለማ፡ ጨለማን ብርሃን!

..አ በ1880ቹ ዓመታት ላይ፡ ማለትም፡ በእንግሊዝና በቱርክ የምትደገፋዋ ቱርክ በኢትዮጵያ ከተሸነፈች በኋላ፡ ጀርመናውያን የአርኬዎሎጂ አጥኝዎች ወደ እስላሟ ኦቶማን ቱርክ በመጓዝ የዚህ የዜውስ/ድያ/ጂፒተር መናገሻና መቀመጫ በሆነችው እና ቅዱስ ዮሐንስ ሰይጣን በሚኖርበት“(ረዕይ. 2:12-17)ብሎ በጠቆመን በ ጴርጋሞን ከተማ በመገኘት ከኦቶማን ቱርክ መሪዎች የዜውስን/ድያን/ጁፒተርን ኃውልት ገዝተው ወደ በርሊን ከተማ አመጡት። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ይህ ኃውልት በበርሊን ከተማ ጴርጋሞን ሙዚዬምውስጥ ይገኛል።

የሰይጣኑ የዜውስ/ጁፒተር ኃውልት ወደ በርሊን በመጣ በዓመት ውስጥ፡ አውሮፓውያን መንግሥታት አፍሪካን ለመቀራመት እዚህችው በርሊን ከተማ ላይ በ1884.ም ላይ አንድ ዲያብሎሳዊ ውል አጸኑ። ጣልያን ኢትዮጵያን:ሌሎቹም የተቀሩትን አፍሪቃ ሃገራት እንዲወሩ ዕቅዱን አወጡ።

አረመኔው ሂትለር ጨካኝ ለሆነው ተግባሩ ቡራኬውን ያገኘው ከእዚህ ቦታ ላይ ነበር። በበርሊን ከተማ እስከ መቶ ሺህ የሚሆኑ ቱርኮች ይኖራሉ።

ሴነተር ኦባማ ለፕሬዚደንትነቱ ከበቁ በኋላ በይፋ ከጎበኟት የመጀመሪያዎቹ አገሮች መካከል ቱርክ፡ ሳዑዲ አረቢያን ግብጽ ይገኙበታል። ፕሬዚደንት ኦባማ ከፍተኛ የፖለቲካ ቀውጥ ውስጥ በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ወደ በርሊን መመለሳቸው የአጋጣሚ አይደለም። በነገው ዕለት በበርሊን ቆይታቸው የሰይጣኑን የጁፒተርን ኃውልት ይሳለማሉ። አዲስ ድል ይሰጣቸው ይሆን?

የአሜሪካ ፕሬዚደንቶች ኢትዮጵያን የማይጎበኟት ጽላተ ጽዮን የተቀቡትን የጁፒተርን ቅባት እንዳያደርቅባቸው ይሆን?

ባራክ (Yes We Scan!)ኦባማ ባርቅባላቅባማአህሊባማ

ባላቅ = ባራክ?

[ራዕይ 2:14-17]

ዳሩ ግን ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉና እንዲሴስኑ በእስራኤል ልጆች ፊት ማሰናከያን ሊያኖርባቸው ባላቅን ያስተማረ የበልዓምን ትምህርት የሚጠብቁ በዚያ ከአንተ ጋር ስላሉ፥ የምነቅፍብህ ጥቂት ነገር አለኝ። እንዲሁ የኒቆላውያንን ትምህርት እንደ እነዚህ የሚጠብቁ ሰዎች ከአንተ ጋር ደግሞ አሉ። እንግዲህ ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፥ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።

መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፥ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፥ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል

_

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: