Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2013
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የ አቡነ ማትያስ ግብጽ ጉብኝት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 13, 2013

AbuneMathiasCon

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ርዕሰ ለቃነ ጳጳሳት፡ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በፊታችን ሰኞ፡ ሰኔ በግብጽ አቅደውት የነበረውን የአራት ቀናት ጉብኝት መሠረዛቸውን በመስማቴ እፎይ! ብያለሁ። እግዚአብሔር እንደሚጠብቃቸው ብተማመንም፡ የአባይ ወንዝ ማዕበል በተነሳበት በዚህ ቀውጢ ወቅት ወደ ጅቦች ዋሻለመሄድ እንዴት ፈቃደኛ ሆኑ? አማካሪዎች ምነው ዝም አሉ? የሚል ስጋት ነበረኝና። የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ወደ ግብጽ ባይሄዱ ጥሩ ነው፡ ፕሬዚደንት ሙርሲም ከሁለት ሣምንታት በፊት አዲስ አበባን ሲጎበኙ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በቦሌ አቀባበል ስላላደረጉላቸው ተገቢና በጣም ጥሩ ነገር ነው ብያለሁ።

ይህ የበላይነት ስሜት ሳይሆን፡ በእውነት ለመናገር፡ ግብጾች በጣም የሚናቁ ከኢትዮጵያውያንም ልዩ አትኩሮት የማይገባቸው ሰዎች ናቸው። ፈጠነም ዘገየም፡ ሞኝነታችንን ትተን እነዚህን ሕዝቦች ወደታች የምንመለከትበት፡ እስካሁንም ዝም ብለን በመታለላችን የምናፍርበት ዘመን እንደሚመጣ እርግጠኛ ነኝ። ኢትዮጵያ፡ በደቡብ ግብጽ የሚገኙትን የቀድሞ ግዛቶቿን ከማስመለስ፡ ኢትዮጵያውነታቸውን እንዲክዱና እንዲወድቁ የተደረጉትን ኑብያውያን እንዲፈወሱ ከማድረግ በቀር ከግብጽ የምትፈልገው አንድም ነገር የለም። ስለዚህ፡ የበላይነቱን የያዙት፡ ቅዱሳኑ ተራሮች ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሕሊናው ውስጥ በማስቀመጥ፤ ለዘንዶው መስገዱን በፍጥነት ማቆም ይኖርበታል።

አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌሟ የኢትዮጵያ ገዳም ለረጅም ጊዜ ቤተክርስቲያናችንን ያገለገሉ አባት ስለሆኑ የግብጻውያኑን ሁኔታ በደንብ ያውቁታል የሚል እምነት አለኝ።

ባለፈው የካቲት ፳፩ አቡነ ማትያስ መንበረ ጵጵስናውን ሲረከቡና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፮ኛ ፓትርያርክ ሆነው ሲሾሙ የግብጹ ኮፕት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ጳጳስ አቡነ ቴዎድሮስ በቦታው አልተገኙም ነበር። ግን፡ አቡነ ቴዎድሮስ ባለፈው ወር ላይ በ ቫቲካን እና በአውስትርያ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። እህታማ የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርኳን ስትመርጥ እሳቸው አዲስ አበባ ባለመገኘታቸው ሲያሳዝነን፡ የመጀመሪያ ጉብኝታቸውን በአውሮፓ፡ ያውም በቫቲካን ማድረጋቸው ግን ግራ የሚያጋባ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ወደፊት፡ አባይን አስመልክቶ ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ከሆነ ማን አስገድዷቸው ሊሆን እንደሚችል ከ1300 ዓመታት ግብጻዊ ልምድ በኋላ መገመት የሚያዳግተን አይመስለኝም። አቡነ ማቲያስና አቡነ ቴዎድሮስ በ ተክለ ሐይማኖት ቀን ነበር ለፓትርያርክነት የበቁት።

abuna_paulos_morsiከሁለት ሳምንታት በፊት በካይሮ የኢትዮጵያን ባንዲራ እንዲያቃጥሉ እንዲሁም ኢምባሲውን ለማጥቃት ብሎም ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ለማደን ሲንቀሳቀሱ የነበሩት አንዳንዶቹ ድርጅቶች የኮፕቶችን ስም የያዙ ነበሩ። በአገራቸው እንደ ሁለተኛ ዜጎች የሚታዩት ኮፕቶች የሚያሰቃዩቸውን የሙስሊም ወንድማማቾችን ፍላጎት ለማሟላት ሲሉ ጸረኢትዮጵያ የሆኑ ተቃውሞዎችን እንዴት ከሁሉ ቀድመው ሊያሰሙ በቁ? አዎ! ኮፕት ክርስቲያኖች ግብጽ አገራቸውን ይወዳሉ፡ እንደ ኢትዮጵያ፡ ጠላት፡ ለሚሉት የውጩ ወገንም ተቃውሟቸውን በካይሮ መንግዶች ላይ ያሰማሉ። በኢትዮጵያ ያሉ ሙስሊሞች ደግሞ የኢትዮጵያን ደህንነት ለማናጋት እንደ ግብጽና ሳዑዲ ከመሳሰሉ ጠላቶች ጋር በማበር የአዲስ አበባ መንገዶችን ያቆሽሻሉ። የግብጽ ክርስቲያኖች እና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በጥቂቱ ለማነጻጸር ይህችን ደብዳቤ እንይ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ሊወሱ የሚገቧቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ፦ የግብጽ ኦርቶዶክሳዊት ቤተከርስቲያን ፓትርያርክ፡ አቡነ ቴዎድሮስ 118ኛው የግብጽ ፓትርያርክ በመሆን ባለፈው ጥቅምት ፳፭ በዓለ ሲመታቸው ሲከናወን የግብጹ ፕሬዚደንት መሐመድ ሙርሲ በዚህ ታላቅ ስነሥርዓት ላይ ለመገኘት አሻፈረኝ ብለው ነበር። በሌላ በኩል ግን እባቡ የግብጽ ፕሬዚደንት ሙርሲ፡ ከ ዓመት በፊት፡ በሐምሌ ፱ ፪ሺ፬ ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ ተጉዘው ከቀድሞው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተከርስቲያን ፓትርያርክ፡ ከብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጋር ተገናኝተው እንደነበር የሚታወስ ነው። የአገራቸውን ፓትርያርክ እንኳን ደስ ያለዎት!’ ለማለትና ለማነጋገር አሻፈረኝ ያሉት ፕሬዚደንት ሙርሲ የኢትዮጵያን ፓትርያርክ ለመጎብኘት በቁ! ፎቶዎቹ ላይ እንደምናየው። አቡነ ጳውሎስ ፕሬዚደንት ሙርሲን ከጨበጡ ከ1ወር በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩን።

አንድ የግብጽ ፕሬዚደንት ወደ ኢትዮጵያ የተጓዘው ከ 17 ዓመታት በኋላ መሆኑ ነው። አቡነ ጳውሎስ መታመም የጀመሩት ፕሬዚደንት ሙርሲ ጋር ከተገናኙ፡ (June 16) (መስቀል ኢየሱስ July 17 ነው) 17 ቀናት በኋላ ሲሆን፡ ማረፋቸው የታወቀው ደግሞ በ17ኛው ቀን፡ ልክ በ July 16 ነው (መስቀል ኢየሱስ)። የቀድሞው የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጳጳስ፡ አቡነ ሸኑዳ lllኛውም ያረፉት እ..March 17, 2012 .ም ነበር። (በ ቅዱስ ማትያስ ዓመታዊ በዓል)

AbunePaulosMursiባለፈው ዓመት፡ ፕሬዚደንት ሙርሲ፡ ለአፍሪቃ መሪዎች ስብስባ ወደ አዲስ አበባ ከማምራታቸው በፊት በፕሬዚደንትነት ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኟት ሳዑዲ ዓረቢያን ነበር። ወደ አዲስ አበባ ከማምራታቸው ከሦስት ቀናት በፊት በሳውዲ ቆይታቸው ከሳውዲ የልዑላን ቤተሰቦች ጋር ተገናኝተው፡ ከጥቁሩ ድንጋይም አስፈላጊ ነው የሚሉትን ጂሃዳዊ ቅመም ተቅብለው ነበር። የሳዑዲ ዜጋ የሆኑት ሸህ ሙሐመድ አላሙዲ በወቅቱ ሳዑዲ እንደነበሩ ይነገራል፡ ታዲያ አቡነ ጳውሎስ እና ጠቅላይ ምኒስትር መለስ ዜናዊ ባረፉባቸው ቀናት ከኢትዮጵያ ራዳር ተሠውረው የነበሩት ሸህ አላሙዲ በሙርሲ የሳዑዲ ቆይታ ከግብጹ ፕሬዚደንት ጋር ተገናኝተው ይሆን?

ፕሬዚደንት ሙርሲ ወደ አዲስ አበባ እንደሚያመሩ ሲገለጥ፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሙስሊሞች መሪያችን መጣ!” በሚል መንፈስ ጩኽታቸውን ለማሰማት በየጎዳናው ሲወጡ ታዩ። ይህን ድርጊት ተመሳሳይ በሆነ መልክ በመድገም ከዓመት በኋላ ባለፈው ግንቦት ፪፭ በሙስሊሞች የተመራ የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ ታየ። የሙስሊም ወንድማማቾች መሪያቸውን፡ የሙርሲን መምጣት በናፍቆት ሲጠባበቁ የነበሩትና በኢትዮጵያ የግብጽ ተጠባባቂ ሠራዊት አባላት የሆኑት እነዚህ ቅጥረኞች አሁንም አጋጣሚውን ተጠቅመው ህውከትና አለመረጋጋትን ለመፍጠር ሞከሩ፤ እግረ መንገዳቸውንም የግብጽ፣ የሳዑዲና ካታር አርበኞች እነማን እንደሆኑ እራሳቸውን በግልጽ አሳወቁ።

ፕሬዚደንት ሙሐመድ ሙርሲ፣ ፕሬዚደንት ባራክ ሁሴን ኦባማ እና ሸህ ሙሐመድ አላሙዲ፡ ስለ አቡነ ጳውሎስ እና ስለ ጠቅላይ ምኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ምን የሚያውቁት ነገር አለ?

__

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: