አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የሆነው የቀስተ ደመና ምልክት በአባታችን በኖኅ አማካይነት ከእግዚአብሔር የተቀበልነው የዘለዓለም ሰንደቅ ዓላማችን ነው።
እየተካሄድብን ያለው ጦርነት በአንድ በኩል መንፈሳዊ በሌላ በኩል ደግሞ ሥጋዊ ባሕርይ ያለው ነው። በባዕዳን ጠላቶቹና በወገን ባላጋሮቹ አማካይነት በረቀቀና በጠለቀ መልክ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ከሰንደቅ ዓላማችን እስከ ቋንቋችን ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያዊ መግለጫዎች በሆነው ማንነታችን ላይ ነው።
ከ500 ዓመታት በፊት ከፍልስጤሟ ጋዛ በመጣው የቱርኮች ቅጥረኛ በአህመድ ግራኝ ሠይፍና በአረማውያን ተከታዮቹ ጦር ሕዝባችን አለቀ፡ በሥጋም ደከመ። ይህ መራራ ጽዋ አልበቃ ብሎ አገሪቱና ሕዝቧ በዚያ አስከፊ መቅሰፍት መዳከማቸውን ተመልክተው፡ ከውጭ በኩል ባዕዳኑ አጋጣሚውን በመጠቀም በአንድ በኩል የዘመኑ ኃያል የነበረው ኦቶማን ቱርክ በኢትዮጵያ ላይ ሥጋዊ ጦርነትን አወጀ፣ በሌላው በኩል ደግሞ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የሃይማኖት መረቧን በኢትዮጵያ ለመዘርጋት ቆርጣ ተነሥታ ሠራዊቷን አሠማርታ ነበር።
እነዚያ የኢትዮጵያ የዘር ጠላቶች እንደዛሬው ሁሉ በዚያን ሰዓትም በተባበረና በተቀነባበረ፡ በተቀናጀ መልክ እርሷንና ትውልዷን ጨርሰው ከምድር ገጽ ለመደምሰስ ብዙ ሞከሩ፡ ግን የእግዚአብሔር ኃይል ይበልጣልና፡ እነዚያን ረቂቅና ግዙፋን ጥንብ–አንሺ ወራሪዎች አገር ወዳዱ የኢትዮጵያ ትውልድ “አገሬን ለዲያብሎስ አልሰጥም!” በሚል የተዋኅዶ ክርስትና ወኔአቸው አምላክ የሰጣቸውን ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለቡ ሁሉንም አንድ ባንድ ለበለቡ።
በደቡብ አፍሪቃው የአፍሪቃ ዋንጫ ለ30 ዓመታት ያህል ከውድድሩ ርቃ የነበረችው ኢትዮጵያ በምድቧ ዛምቢያን (አረንጓዴ) ናይጀሪያን (አረንጓዴ) ቡርኪና ፋሶን (አረንጓዴ፣ ቀይ፣ ቢጫ) ገጠመች። በመጀመሪያው የዛምብያ ጨዋታ፡ ጎበዙ ተጫዋች ሳላዲን አንዴም ሁለቴም ያለቀላቸውን ግቦች ሳተ፡ ብዙም አልቆየ በረኛው አብዲ በመጥፎ ባሕርይው ከሜዳ እንዲወጣ ተደረገ፡ ዛምብያም ወዲያው ግብ አስቆጠረች። በኋላም ቢጫ ለብሶ የነበረው የኢትዮጵያ ቡድን ካፕቴንና ቁልፍ ተጨዋች አዳነ ለኢትዮጵያ ቡድን ጎል አስቆጥሮ አቻ ተወጣ።
የቀጠለው ‘ጨዋታ‘ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ነበር። አረንጓዴ ለብሶ ወደ ሜዳ የገባው የኢትዮጵያ ቡድን ዋና ተጨዋችና የቡድን መሪ አዳነ ባልታወቀ አደጋ ቆስሎ ከአፍሪካ ዋንጫ ተሰናበተ፤ በዚህም የኢትዮጵያ ቡድን ዕድል ቶሎ ተቀጨ።
የቀጠለው ጨዋታ ከአረንጓዴዎቹ ከናይጄርያ ጋር ነበር። በዚህም ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡድን የአጨዋወት ችሎታ ከናይጀርያዎቹ አያንስም ነበር፡ ነገር ግን መሆን የለበትምና ኢትዮጵያውያኖቹ እራሳቸው እራሳቸውን በመቅጣት ለናይጀርያ ቡድን ሁለት የቅጣት ምቶችን በአረንጓዴ ሰፌድ ከአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ማልያቸው ጋር አስረክበው ከውድድሩ ተሰናበቱ።
አሁን የመጀመሪያውንና የሚቀጥለውን ዙሮች አልፈው የሄዱት ቡድኖች፡ ማለትም፤ ቡርኪና ፋሶ (አረንጓዴ፣ ቀይ ቢጫ) ከጋና (ቀይ፣ ቢጫ አረንጓዴ) ናይጀርያ (አረንጓዴ፣ነጭ፣አረንጓዴ) ከማሊ (በአግድም፡ አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ) ጋር ተጋጠሙ፡ በመጨረሻም ቡርኪና ፋሶ (አረንጓዴ፣ቀይ፣ቢጫ) ከ ናይጀሪያ (አረንጓዴ፣ ነጭ አረንጓዴ) ተጋጥመው፡ አረንጓዴዋ ናይጀርያ የውድድሩ አሸናፊ ለመሆን በቃች።
እስፖርት፣ ጨዋታዎች ወይም ሙዚቃን የመሳሰሉት ነገሮች ጨዋታዎች ወይም ድምጾች ብቻ አይደሉም። ከነዚህ ነገሮች ጀርባ የሕዝቦች ማንነት፣ የሕዝቦች ስነልቦናዊ ወይም ስሜታዊ ባሕርይ ይንጸባረቅበታል። ለምሳሌ ጣልያንና ጀርመንን የመሳሰሉት አውሮፓውያን ተከላካይነታቸው በጣም የጠበቀና እልህም የተጨመረበት ስለሆነ የሚሰለፉትን የእግርኳስ ሜዳ ልክ እንደ ጦር ሜዳ አድርገው ነው የሚያዩት፤ ስለዚህ ሲከላከሉ፡ አገራቸውንና ሕዝባቸውን በአገር ወዳድነት እንደተከላከሉ አድርገው ስለሚወስዱት ኳስ ሳይሰጡ እስከ ተቀናቃኙ ጎል ድረስ በመሄድ ጎሎችን ያስቆጥራሉ። በዚህም ባሕርያቸው ሁለቱ አገሮች እያንዳንዳቸው አራት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮን ለመሆን በቅተዋል። በዓለም ታዋቂ የሆኑት ኅይለኛ በረኞችም ከነዚህ ሁለት አገሮች ነው የሚወጡት። በዚህም የሕዝቦቻቸውን ጦረኛ ባሕርይ በእግርኳስ ሜዳ ላይ ሳይቀር ያንጸባርቃሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ፡ ከሙስሊም አገሮች የሚመጡትን የሰሜን አፍሪቃ፣ ቱርክና ኢራን የመሳሰሉትን ቡድኖች ስንመለከት፡ ተጫዋቾቹ ልክ እንደ አበደ ውሻ ሙሉውን ሜዳ ወዲያ ወዲህ እያሉ በመሮጥ፡ በጥበብ ለመጫወት ሳይሆን፡ የተቀናቃኙን ቡድን ጨዋታ ለማበላሸት ይሞክራሉ። የሌላውን ማንነት መረበሽ ወይም ማጨናገፍ የእነዚህ ሕዝቦች ባሕርይ ነው። በእግር ኳስ ብቻ አይደለም፣ በሩጫው ዓለምም ከእነዚህ ሕዝቦች ጀርባ ምን እንዳለ ለመረዳት በለንደኑ ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች 1500ሜትር ሩጫ ላይ ኢትዮጵያዊቷን፡ አበባ አረጋዊን፡ ልክ የኢትዮጵያ የእግርኳስ ቡድንን እንዳደነዘዙት፡ አሯሯጧን በማሰናከል እርግጠኛ የነበረውን የወርቅ ሜዳሊያ ነጠቋት። እንደገና ለማየት ቪዲዮውን በቅርቡ አቀርባለሁ።
1ኛና 2ኛ የወጡት ማንም የማያውቃቸው ሁለቱ ቱርኮች እርዳታውን ያገኙት ማንነቷን በመካድ የአረብ ባንዲራ ለማውለብለብ በበቃቸውና እራሷን “ዩሱፍ ጀማል” እያለች በምትጠራው ሯጭ ነበር። የሚያሳዝን ነው!
ወደ አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ ሰንድቅ ዓላማችን ስንመለስ፣ በሰንድቅ ዓላማችን ላይ ያረፈው ባለ ሰማያዊ ቀለምና 5-ማዕዘን የኮከብ ቅርጽ ያለው አርማ ባንዲራችን ላይ ባይቀመጥ ጥሩ ነበር። ምናልባትም ቀደም ሲል ዓለምን የሚገዟት የሉሲፈር አርበኞች፡ ልክ የተበከለ ስንዴውን፣ ክትባቱን፣ የወሊድ መከላከያውን፣ የሳልሳ ዳንሱንና ሰዶማዊ ባሕሉንም አንድባንድ እንድንቀበል እንደሚያስገድዱን ሁሉ፡ ሰንድቅ ዓላማችን ላይም ኮከቡን እንድናሳርፈው በጊዜው አስገድደውን ሊሆን ይችላል፡ ነገር ግን፡ መንግሥት በተቀየረ ቁጥር አብሮ የመቀየር እጣ ወጥቶለት ነው እንጂ አርማው ሰንድቅ ዓላማችን ላይ መቀመጥ የለበትም፤ ጊዜውን ጠብቆ እንደሚነሳም የሚያጠራጥር አይደለም።
በቅኝ ግዛት ሥር የነበሩት ብዙ አፍሪቃውያን አገሮች የኢትዮጵያን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት በመውሰድ ባንዲራዎቻቸው ላይ በማሳረፋቸው ባንዲራችን ለአፍሪቃውያኑ ኩራት እንደሆነ ብዙ ጊዜ ይነገራል።፡ የባንዲራችንን ሦስት ቀለማት ሌሎች አፍሪቃውያን ወንድሞቻችንም በሰንደቅ ዓላማዎቻቸው ላይ በማሳረፋቸው ለአፍሪቃውያንም የተስፋ ምልክት ሆኗል የሚል እምነት አለን፤ በእውነት እንነጋገር ካልን ግን መጀመሪያ አፍሪቃ ማን ናት? አፍሪቃውያንስ እንማን ናቸው? የሚሉትን ጥያቄዎች አጥብቀን መጠየቅ ይኖርብናል። ለረጅም ጊዜ ‘ፓን–አፍሪቃዊ‘ የሆኑ ህልሞችና አመለካከቶች ካሏቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበርኩ። ይህ ፓን–አፍሪቃዊ ህልም በርግጥ አፍሪቃውያንን በአንድ የአፍሪቃዊ መንፈስ የሚያስተሳስር ቢሆን ኖሮ በጣም በጎ የሆነ ተግባር ለመሆን ይበቃ ነበር። ነገር ግን ይህ ሕልም ነው! ዕውን ሊሆንም የሚበቃ ነገር አይመስልም። የአፍሪቃውያንን ሕዝቦች አንድ ላይ ሊያስተባበር የሚችል አንድ–ወጥ ርዕዮተ ዓለም፣ ፖለቲካ ወይም ኅይማኖት አለመኖሩ አንዱ ትልቁ ምክኒያት ነው። አፍሪቃ፡ ከሌሎች ክፍለ ዓለሞች ጋር ሲወዳደር በጀነቲክስ አወጣጥ እንዲሁም በቋንቋና በሃይማኖት እጅግ በጣም የተለያዩ ሕዝቦች የሚኖሩበት አህጉር ነች። ስለሆነም፡ የቆዳ ቀለም ላይ ትኩረት በማድረግና ፓን–አፍሪቃዊ የሆነ ርዕዮተ–ዓለም በመከተል ብቻ ሁሉንም አንድ ለማድረግ መሞከር የሞኞች ህልም ነው። ይህ የፓን–አፍሪቃዊ እንቅስቃሴ እንዲያውም አፍሪቃን እንደ አንድ አገር አድርጎ የሚቆጥረውን የአፍሪቃውያኑን ጠላት ነው ሊጠቅም የሚችለው፤ በቀላሉ ለመቆጣጠርና ለመዋጋት እንዲችል ያመቸዋልና።
አፍሪቃውያኑ፡ ጠንካራና መሠረታዊ አፍሪቃዊ በሆነው የኢትዮጵያኛ ሥርዓት ውስጥ ገብተው ነፃ ለመወጣትና ከፍተኛው እምነታዊ የተራራ ጫፍ ላይ እንዳይደርሱ ለባርነትና ቅኝ አገዛዝ ቀንበር ያበቋቸው ሦስት በጣም ኅይለኛና አሉታዊ የሆኑ ነገሮች አሉ፤ እነዚህም፡
- የቩዱ ጥንቆላ እምነት
- የእስልምና እምነት
- አውሮፓዊ የሆኑ የክርስትና እምነቶች (ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንቲዝም)
ናቸው።
እነዚህ ሦስት የእምነት ጎዳናዎች የኢትዮጵያኛው እምነት የሚከተለውን መንገድ በጣም ይቃረናሉ። አንዱ መንገድ ብቻ ነው ትክክለኛውን አቅጣጫ የሚከተለው፡ ወይ የነርሱ፣ ወይ የኢትዮጵያኛው። ስለዚህ እነዚህ ሁለት የተለያዩ ሥርዓቶችን ያቀፈ አንድ ወጥ የፓን–አፍሪቃ እንቅስቃሴ ፈጽሞ ሊኖር አይችልም።
ሰንድቅ ዓላማንም በሚመለከት፤ የኢትዮጵያ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት በጋና፣ ማሊ፣ ሴኔጋልና ሌሎች አፍሪቃውያን ባንዲራዎች ላይ ማረፉቸው ሕዝቦቻቸውን ወደ ኢትዮጵያኛው ሥርዓት ጎትቶ ሊያመጣቸው አይችልም። ለምሳሌ የአውሮፓውያኑ ክርስትና በተስፋፋባት ጋና የቩዱው የጥንቆላ እምነት ‘ክርስትናውን‘ ሳይቀር በጥልቅ በክሎት ይታያል። በተጨማሪ፡ ጋናም ሆነች ሌሎች ባለ አረንጓዴ፣ ቢጫ ቀይ አገሮች የነዚህን ቀለማት አቀማመጥ እንደ ኢትዮጵያ አረንጓዴው ከላይ፣ ቢጫው ከመኻል፣ ቀዩ ከታች አድርገው አይደለም የሚያቀርቡት። እንዲያውም ጋና ጭራሹን በመገለባበጥ ቀዩን ከላይ አረንጓዴውን ከታች በማድረግ ነው ሰንድቅ ዓላማውን የምታውለበለብው።
በዚህች ዓለማችን የምንጠቀምባቸው ቀለማት፣ አርማዎች እና ምልክቶች ብዙ ነገሮችን ሊነግሩን ይችላሉ። በተለይ የሰንደቅ ዓላማ ቀለማት ልዩ ትርጉም ስለሚኖራቸው በቀላሉ መታየት የለባቸውም። ስለዚህ የሰንደቅ ዓላማ ቀለማት አቀማመጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። ሉሲፈር ሰይጣን ሁልጊዜ መኮረጅ/መቅዳት/መገልበጥ ይወዳልና፣ እግዚአብሔር አምላክ ለኢትዮጵያ ልጆች በአባታቸው በኖህ አማካኝነት ከቀስተ ደመና ወስዶ የሰጣቸውን ቀለማት፡ በመኮረጅ እሱም ለደቂቃውያን ልጆቹ ሰጥቷል፤ ሰዶማውያን እና የቩዱ ጠንቋዮች እነዚህን ቀለማት መጠቀማቸውን እንደምሳሌ ይወሰዳል። ሰዶማውያንም ልክ እንደ ጋና አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀዮቹን ቀለማት ገለባብጠው ነው የሚያውለበልቡት።
6ኛው የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ፡ አቡነ ማቴዎስ በተመረጡበት ቀን የሮማ ካቶሊክ ጳጳስ ዙፋናቸውን ማስረከባቸው የአጋጣሚ ነገር አይመስለኝም። የሮማዋ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብዙ ድንቅ የሆኑ ነገሮችን የሠራች፡ ልትመሰገን የሚገባት ቤተክርስቲያን ብትሆንም፡ ባሁኑ ጊዜ በሰይጣን ቁጥጥር ውስጥ የገባች ትመስላለች። ለሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውድቀት አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ያሉት ሰዶማውያን እና የቩዱ ጠንቋዮች ናቸው። እንደሚታወቀው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቄሶች ሚስት እንዲያገቡ አይፈቀድላቸውም (ሶለባት)። ይህን ሁኔታ የታዘቡት የማርቲን ሉተር ልጆች ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከ 40 – 50 ዓመታት በፊት በብዛት ሠርገው በመግባት ቀስበቀስ ቤተክርስቲያኗን ሊቆጣጠሩ በቅተዋል። አሁን የሚታየው የሕፃናት–ደፈራ ቅሌት ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው። ቤነዲክት 16ኛ ወንበራቸውን ማስረከባቸውም የሰዶማውያን ተጽዕኖ እጅግ ከፍ እያሉ መምጣቱን ነው የሚነግረን። ምስኪኑ አዛውንት ጳጳስ ሊደርስባቸው የቻለውን የሽብር ሁኔታ እንዲሁ በቀላሉ መገመት አይቻልም። በዚህች ዓለማችን ዓይን ያወጣና እጅግ በጣም አደገኛ የሆነ ሽብር ነክ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ያሉት ሁለት ኃይሎች አክራሪ ሰዶማውያን እና እስላሞች ናቸው። እነዚህ ኃይሎች ከላይ ከመደክቧቸው ሦስት የእምነት ክፍሎች ጋር በተገኘው አጋጣሚ ሁላ እይተመሣጠሩ ሉሲፈር የነፍስ–አዳኙን ያገለግላሉ።
በካቶሊኮች ዘንድ ቅዱስ “ማለኪ” ተብለው በ12ኛው ምዕት ዓመት ላይ በአየርላንድ የሚታወቁት ካቶሊካዊ ቄስ ተንብየውታል የተባለውን የ “ቅዱስ ማለኪ ትንቢት” እ.አ.አ በ1595 ዓ.ም የካቶሊክ መነኮሳት አሳትመወት ነበር። በዚህም ትንቢታቸው ማለኪ ስለመጨረሻዎቹ 10 የሮማ ካቶሊክ ጳጳሳት ተናግረዋል ይባላል። አሁን ወንበራቸውን ያስረከቡት በነዲክት አስራ ስድስት፡ 111ኛው ጳጳስ ሲሆኑ በትንቢቱ 9ኛው መሆናቸው ነው። ስለዚህ 10ኛውና ቆየት ብሎ የተጨመረው 112ኛው የሮማ ጳጳስ የመጨረሻው ይሆናሉ፡ ስማቸውም “ጴጥሮስ ሮማኑስ” ይሆናል ብለው ማለኪ መናገራቸው ተገልጿል።
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከኢትዮጵያ ጋር ባላት የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግኑኝነት፡ ከፍተኛ የቫቲካን ባለሥልጣናት ለመሆን የበቁ ኢትዮጵያውያን የሉም። ልክ በዓለማዊውም ዓለም እነ አሜሪካና እንግሊዝ ጋር ግኑኝነት በመመሥረት ቀዳሚ ከሆኑት አገሮች መካከል ኢትዮጵያ ትገኝበታለች፡ ኢትዮጵያውያንም በነዚህ አገሮች መኖር ከጀመሩ ከብዙ የዓለም አገራት ቀድመው ነበር። ነገር ግን በሕብረተሰቡ የፖለቲካ፣ የምጣኔ ሃብት፣ በባህላዊ ወይም ሃይማኖታዊ ሕይወት ውስጥ ኢትዮጵያውያን እስካሁን ምንም ዓይነት ሚና ለመጫወት አልበቁም፡ ብንል አልተጋነነም። የፖለቲካ መሪዎች ለመሆን የበቁ ወይም በብዙኃን ዜና ማሠራጫዎች ውስጥ ገብተው ታዋቂነትን ያተረፉ ኢትዮጵያውያን የሉም። ይህም፡ ብቃት፡ ወይም ችሎታ ሳይኖራቸው ቀርቶ ሳይሆን፡ ኢትዮጵያውያን የሉሲፈር ኃይሎች በሚመሩት ዓለም ውስጥ ገብተው እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር ስላልፈቀደ ነው። ሌላ ምክኒያት ሊኖር አይችልም። ምናልባት ማንነታቸውን የካዱት ወይም ቆዳቸውን የቀየሩት ኢ–ኢትዮጵያውያን ታዋቂ የአሜሪካ ሴነተር ወይም ዝነኛ የቢቢሲ ጋዜጠኛ የመሆን እድል ይኖራቸው ይሆናል።
በሌላ በኩል ግን፡ ልክ ፕሬዚደንት ኦባማ (በርግጥ ኬኒያዊ አባት ከነበራቸው) ባጭር ጊዜ ውስጥ፡ ባቋርጭ የመጀመሪያው አፍሪቃ–አሜሪካዊ ፕሬዚደንት ለመሆን እንደበቁት ላለፉት ዓመታት በቫቲካን ከምዕራብ አፍሪቃ የፈለቁ የ“ካቶሊክ” አገልጋዮች ቁልፍ የሆኑ ሥልጣኖችን መያዝ ጀምረዋል፡ ለዚህም አሁን የምናውቃቸውን ናይጀሪያዊውና ጋናዊው ካርዲናሎችን እንደ ምሳሌ አድርገን መውሰድ እንችላለን። እነዚህ ግለሰቦች ካቶሊክኛ የመንፈሣዊ ትምህርት እውቀትና ብቃት እንደሚኖራቸው የሚያጠራጥር ነገር አይደለም። ነገር ግን ወደ ቫቲካን ያመጣቸው መንፈስ የአውሬው መንፈስ ሊሆን እንደሚችል ከተለያዩ ሁኔታዎች መገንዘብ እንችላለን። ምዕራብ አፍሪቃውያኑ የቤኒን፣ ናይጄሪያና ጋና ተወላጆች ከፍተኛ የቩዱ ጥንቆላ ተጽዕኖ ባለው መናፍስታዊ ኑሮ እንደሚመሩ የአደባባይ ምስጢር ነው። ከኢትዮጵያ ውጭ ያለችው የካቶሊክ ቤተክርስቲያንም እምነቷን በምእራቡ አፍሪቃ፣ በሃይቲ እና ብራዚል ከሚገኘው ቩዱኛ የጥንቆላ ባህል ጋር በማዋሀዷ እራሷን ለሉሲፈር አሳልፋ ልትሰጥ በቅታለች።
አክራ ጋና እስካሁን በአፍሪቃ ደረጃ “ሰላማዊ ለመሆንና መንግሥቷም ጽኑ አቋም ሊኖረው የቻለው ያለ ምክኒያት አይደለም። መቼም በዚህ ዓለም ታዋቂነትንና አድናቆትን ያተረፉ ነገሮች በእግዚአብሔር ቤት ከንቱዎች ናቸውና፡ እንደ እነ ማህተመ ጋንዲና ንክሩማኽ የመሳሰሉትን መሪዎች ባድናቆት ልንቀበላቸው የቻልንባቸውን ምክኒያቶች መመርመር ግድ ነው። ስለ ማንዴላ ብዙ ማለት አልችልም፡ ምናልባት በሮብን ደሴት ቆይታቸው ከአፓርታይዱ ሥርዓት በኋላ የነጩ ነዋሪ ደህንነት በሰላም ይጠበቅ ዘንድ አዘጋጅተዋቸው ይሆናል፡ ሆኖም ይህ ነው ለማለት በጣም ይከብዳል። ጋንዲ ግን፡ በደቡብ አፍሪቃ ቆይታቸው እሥር ቤት ውስጥ ከጥቁሮች ጋር ባንድ ላይ መሆን አልፈልግም የሚል የዘረኝነት አቋም እንደነበራቸው የተረጋገጠ ነገር ነው፤ አንዳንዴም ሰዶማዊ ሳይሆኑ አይቀሩም የሚባል ነገር አለ። ለማንኛውም፤ እሳቸውም ሕንዳውያን በእንግሊዞች ላይ እንዳያምጹ “ሰላማዊ አብዮቱን” በመከተል ማቀዝቀዣ መሪ ለመሆን የበቁ ናቸው።
የመጀመሪያው የጋና ፕሪዚደንት፡ ክዋሜ ንክሩማኽም ቀድመው ዝናን ሊያተርፉ የበቁት፡ ኢትዮጵያውያን፡ በተለይ አፄ ኅይለሥላሴ የመሪነቱን ቦታ በመያዝ አፍሪቃውያኑን እንዳያነሳሱ በአውሮፓውያኑ ዘንድ ፍራቻ ስለነበር ነበር። አዲሱ የአፍሪቃ ህብረት ሕንፃ ፊት ለፊት የንክሩማኽ ሃውልት እንዲቆም የተደረገውም ምናልባት በዚሁ ምክኒያት ሳይሆን አይቀርም። ንክሩማኽ እንደሌሎቹ የምዕራብ አፍሪቃ መሪዎች ሁሉ ሕይወታቸው በቩዱ ጠንቋዮች አማካይነት ይመራ ነበር። ይህን ጋናውያኑ እራሳቸው እዚህ ላይ ይመሰክራሉ። የቩዱ ፓስተሮች በፕሮቴስታንቱ ካቶሊኩና እስላሙ ዋሻ ውስጥ ሰርገው በመግባት ብሎም ከነፃ–ግንበኞች (ፍሪሜሰኖች፟) ጋር ግንባር በመፍጠር በሉሲፈር የሚመራውን ዓለም በመመገብ ላይ ይገኛሉ።
ከጠቅላይ ምኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ባንድ ወቅት “የተገደሉት“የጋናው ፕሬዚደንት አታ–ሚልስ የሚያውቁት ምስጢር ሊኖር ይችላል። የሰይጣኑ “ባፈሜት“ (ማሆሜት) አምላኪዎች እንደነበሩ የሚታወቁትና በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሠርገው በመግባት አምልኮተ ጣዖትንና ሰዶማዊነት ሲያስፋፉ የነበሩት “ናይትስ ኦፍ ቴምፕላርስ” ኢትዮጵያ ድረስ ሄደው የሙሴን ጽላት የመስረቅ ዕቅድ እንደነበራቸው የሚታወቅ ነው። ባፈሜት በ ፍየል መልክ ተመስሎ የተሳለ በአለ–ክንፍ ጣዖት ነው። ምስጢረኛው ባቄላ፤ ቡናችንን ያገኘችው ፍየል በክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ዘንድ ለሥጋ ምግብ አትቀርብም። የሚገርመው፡ አረብኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ‘ባ‘ፈሜት ላይ ያለውን የ “ባ/በ ፊደል በሚገባ ማለት/መናገር አይችሉም። የባፈሜት ጣዖት አምላኪዎቹ ናይትስ ኦፍ ቴምፕላርስ ድብቅ የእስላም አርበኞች እንደነበሩም ይወራል፡ እዚህች ላይ እንመልከት። ናይት ኦፍ ቴምፕላርስ እና እነዚህ ቡድኖች ምናልባት በኢትዮጵያውያን ጠቋሚነት በፈረንሳዩ ንጉሥ፡ ፊሊፖስ በ14ኛው ምዕተ–ዓመት ለመጨፍጨፍ በቅተዋልም ይባላል። አውሮፓውያን በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው ደስ የማይል ሬከርድ የዚህ ቁጭት ይሆን?
ቴምፕላሮች ከተወገዱ በኋላ ነፃ ግንበኞች/ፍሪሚሰኖች በተለይ በስኮትላንድ ውስጥ እነሱን ተክተው በተመሳሳይ መልክ ቫፈሜትን ማምለኩን ቀጥለዋል። አብዛኛው በዓለማችን አሉ የሚባሉት ድብቅ ማኅበረሰቦች የነዚሁ የፍሪሜሰኖች ልጆች ናቸው። ብዛት ያላቸው የአገራቱ መሪዎች፣ የገንዘብ ድርጅት ባለቤቶችና ሃብታም የሆኑ ግለሰቦች ሁሉ ፍሪሜሰናዊ ግኑኝነቶች አሏቸው። ለምሳሌ የፕሬዚደንት ቡሽ ቤተሰቦች እንዲሁም አዲሱ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ መሠረቱ በአሜሪካዋ የ ‘የል‘ ዩኒቨርሲቲ ለሆነው፡ የ ‘ራስ ቅልና አጥንቶች‘ (ስካል ኤንድ ቦንስ) አባልነት የተመዘገቡ ፍሪሜሰኖች ናቸው። ይህ ድርጅት ቀደም ሲል “የሞት ወንድማማችነት” ወይም ‘ብራዘርሁድ ኦፍ ዴዝ‘ የሚል ስያሜ ነበረው። በኋላ የመጡት ሙስሊም ወንድማማቾች ከዚሁ ጋር የሚያያዝ መሆኑ አሜሪካ በአሁኑ ሰዓት በግብጽ የምታደርገው እርዳታ ይነግረናል። ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ…
ጋናም ከመጀመሪያ ፕሬዚደንቷ ከ ክዋሜ ንክሩማኽ እስከ ኮፊ አናን ድረስ በቩዱ በኩል ፍሪሜሰኖችን ለማገልገል የተመረጠች አገር ናት። ጋና፡ ሰላም ያገኘችውና ዜጎቿም በያገሩ በብዛት ተሰደው በሰላም እንዲኖሩ መቻላቸው፡ እንዲሁም የነዳጅ ዘይት እንድታወጣ የተፈቀደላት በዚሁ ምክኒያት ነው። ነፍስ ከተሸጠ ዓለማዊውን ነገር ማግኘት ይቻላል! ፕሬዚደንት ኦባማ በአፍሪቃ ጉብኝታቸው አስቀድመው ወደ ግብጽ እና ጋና መሄዳቸው፡ የእስልምናና የቩዱ መንፈስ አብሮ እየሠራ መሆኑን ሊነግረን ይችላል። የረጅም ጊዜ የጋና ፕሬዚደንት የነበሩት ‘ጄሪ ሮውሊንግስ‘ ስኮታላንዳዊ ዝርያ ነበራቸው፡ በዚህም የፍሪሜሴኖች አባል በቀላሉ ለመሆን ችለዋል። ታቦተ–ጽዮንን ለመስረቅ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ የነበረውን ስኮትላንዳዊ ፍሪሜሰን፡ ጀምስ ብሩስን እግረ መንገዴን ልጠቁም።
ራሳቸውን ለሉሲፈራውያኑ የቩዱ–ፍሪሜሰን ቡድን ከሸጡት ጋናውያን መካከል አፈ–ጮሌው ወስላታ፡ ‘ኮፊ አናን‘ ይገኙበታል፤ እዚህ እንመልከት። ኮፊ አናን ለሚሊየን ‘ኢትዮጵያውያን‘ ቱሲ ነገዶች በሩዋንዳ መጨፍጨፍ ዋናው ተጠያቂ ናቸው። የሩዋንዳ እልቂት የፍሪሜሰኖች መሣሪያ በሆነው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አነሳሽነት በአፍሪቃ ለሚካሄደው የሕዝብ ቁጥር ቅነሳ አጀንዳ የተፈጸመ እልቂት ነው። ኮፊ አናን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንዲሁም ፕሬዚደንት ክሊንተን ለዚህ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ተጠያቂዎች ናቸው። ኮፊ አናን የቩዱ እና ፍሪሜሰኖችን ሰይጣናዊ አምልኮት ከተቀበሉት ብዙ ታዋቂ ግለሰቦች መካከል አንዱ ናቸው። ከ 2007ቱ የኬኒያ ምርጫ በኋላ በተፈጠረው ብጥብጥ ወደ ኬኒያ፡ እንዲሁም ባለፈው ዓመት ላይ ወደ ሶርያ በመሄድ ተቀናቃኞችን እንዲያደራድሩ የተደረገው በፍሪሜሰኖች አነሳሽነት ነበር።
ባጠቃላይ፡ ደቡብ ዓፍሪቃ፣ ጋና፣ ግብጽ፣ ናይጀርያና ኬንያ በአፍሪቃ የፍሪሜሰኖች ማዕከል ናቸው። ከዓመት በፊት የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) ሊቢያን ለማጥቃት ሲወስን የአፍሪቃው ህብረት ተቃውሞውን ሲገልጥ፡ በተባበሩት መንግሥት የጸጥታው ምክር ቤት በጊዜው ተወክለው የነበሩት ደቡብ አፍሪቃና ናይጀርያ ግን አፍሪቃውያኑን በመክዳት ለኔቶ ድጋፋቸውን መስጠታቸው አንዱ ምሳሌ ነው። በተለይ ደቡብ አፍሪቃ በአፍሪቃ ለሚካሄዱት ለውጦች ሁሉ አርአያ እንድትሆን በፍሪሜሰኖቹ ተዘጋጅታለች። የሰዶማውያንን ጋብቻ አስቀድማ የተቀበለች፣ ፅንስን ማስወረድ ይፋ ያደረገች፣ የወሊድ መከላከያዎችን ቀድማ ያሰራጨች፣ የተኩስ መሣሪያዎችን ለነዋሪዎች የፈቀደች አገር ደቡብ አፍሪቃ ነች።
ወደ ጋና ስንመለስ፡ በመጪው ማክሰኞ በቫቲካን በሚካሄደው የሮማ ካቶሊክ ጳጳስ ምርጫ እጩ ከሆኑት ግለሰቦች መካከል ጋናዊው ካርዲናል ጴጥሮስ/ፒተር ቱርክማን አንዱ ናቸው። ከላይ የጠቀስኩትና የመጨረሻዎቹ 10 ጳጳሶችን የተመለክተው የ “ቅዱስ ማለኪ ትንቢት“፡ 112ኛውና የመጨረሻው ጳጳስ፡ “ጴጥሮስ ሮማኑስ” የሚል መጠሪያ እንደሚኖራቸው ተገልጧል። የሚገርመው፡ እኝህ ጋናዊ ካርዲናል በጋናዋ የትውልድ መንደራቸው በፋንቲ ቋንቋ ከዱሮ ጀምሮ “ጴጥሮስ ሮማኑስ” ተብለው እንደሚጠሩ ይነገራል። የመጨረሻ ስማቸው “ቱርክሰን” የ “ቱርክ ልጅ” የሚል ትርጓሜ መያዙ፣ በእስላም አጎታቸው ተንከባካቢነት ማደጋቸው፣ ባለፈው ዓመት ባዘጋጁት ጥናታዊ ፊልም ላይ እስልምናን የሚነቅፍ ንግግር ማድረጋቸው፤ ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ “ሰዶማዊነት የነጮች በሽታ ነው” ብለው መናገራቸው፡ ሰውየውን ከብዙ ነገሮች ጋር እንዲተሳሰሩ፡ በጣም ተርጣሪ የሆነ ሚና ተጫዋች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። ካርዲናል ቱርክሰን ለጵጵስና ይመረጣሉ የሚል እምነት የለኝም። ምናልባት ሊመረጥ የሚችለው ጣሊያናዊ ወይም አርጀንቲናዊ (እነሱም ጣልያኖች ናቸው) ወይም ሰሜን አሜሪካዊ ካርዲናል ነው። ነገር ግን ካርዲናል ቱርክሰን የሚመረጡ ከሆነ፡ እሳቸው አሁን እንደሚሉት ሳይሆን፡ ልልና ተሐድሷዊ የሆነ ፖሊስ በመከተል፡ ሰዶማውያኑንም እስላሙንም በይበልጥ ያስጠጋሉ፤ በዚህም የካቶሊክን ቤተክርስቲያን ወደ ታላቅ ውድቀት ይዘዋት ሊሄዱ ይችላሉ የሚል ግምት አለኝ። ፕሬዚደንት ኦባማ ለፕሬዚደንትነት ከመመመረጣቸው በፊት እና ከተመረጡ በኋል የሚከተሉትን በጣም የተለያየ መንገድ እንደ ምሳሌ መውሰድ ይቻላል። እሳቸውም ቀደም ሲል ሰዶማውያንን፣ ጽንፈኛ እስላሞችን በጥብቅ እንደሚቃወሙ ይለፍፉ ነበር፡ አሁን ግን ሁሉንም አቅፈው በመያዝ አሜሪካን ለጥፋት እያበቋት ነው። ፕሬዚደንት ኦባማ የየትኛው ምስጢራዊ ድርጅት አባል እንደሆኑ አይታወቅ ይሆናል፡ ነገር ግን እሳቸውም ቢሆኑ ላይ ከተጠቀሱት አብረው እንደሚሰሩና የእግዚአብሔርን መንግሥት ሳይሆን የሉሲፈርን መንግሥት እንደሚያገለግሉ አካሄዳቸው ያሳየናል። ስለዚህ የጥቁር ዝርያ ስለሆኑ ለአፍሪቃና አፍሪቃውያን ቁም ነገር ያደርጋሉ ብሎ ማመን ሞኝነት ነው። እነዚህ ቡድኖች ለዓላማቸው ሲሉ እንኳን እኛን የራሳቸውንም ሕዝብ ለአደጋ ከማብቃት ወደ ኋላ አይሉም። በ2012 ዓ.ም አፍሪቃ 4 መሪዎቿን ምስጢራዊ በሆነ መልክ አጥታለች። በአገራቱ ሁከትና አለመረጋጋት ለመፍጠር መሪዎችን እንደሚገድሉ/እንደሚያስገድሉ ያደባባይ ምስጢር ነው፤ ታዲያ አቡነ ጳውሎስን እና ጠቅላይ ምኒስትር መለስን (ነፋሳቸውን ይማርላቸው) እነዚህ ኃይሎች አስገድለዋቸው ይሆን? ይህን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይጠረጠራል፡ ደፍሮም ጨረር ነው ይላል! ግን፡ የፕሬዚደንት ኦባማ፣ የፕሬዚደንት ሙርሲና የሼክ አላሙዲ የወንድማማችነት ቡድን፡ ግብጽ፡ ሳውዲ ዓረቢያ እና ካታር ስለዚህ ጉዳይ ምን የሚያውቀው ነገር ይኖር ይሆን? ምስጢሩን የጢስ እሳት ቀስተ ደመና አንድ ቀን ያበራልናል።
“እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና። ስለዚህ። አንተ የምትተኛ ንቃ ከሙታንም ተነሣ ክርስቶስም ያበራልሃል ይላል። እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ።
ስለዚህ የጌታ ፈቃድ ምን እንደ ሆነ አስተውሉ እንጂ ሞኞች አትሁኑ።” [ኤፌሶን 5፥ 12: 17]