ጾመ ነነዌ 2005 በ ዓባይ ዙሪያ ያሳያቸው ምልክቶች
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 2, 2013
- እሑድ የካቲት 17፦ ከኢትዮጵያ ምድር፡ ነዳጅ ዘይትና ጋዝ ለመጀመሪያ ጊዜ የማውጣት ተስፋ እንዳለ ተወደሰ
- ሰኞ የካቲት 18፦ የዓለም አቀፍ ቢሲኪሌት ስፖርት ህብረት፡ 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያውያን ዓመት ነውን? በሚል ጥያቄ ይጀምርና፡ ኢትዮጵያውያን በቢሲኪሌት ስፖርት በጣም ሊበለጽግ የሚችል ችሎታ እንዳላቸው ያስታውቃል
- ማክሰኞ የካቲት 19፦ በግብጿ አስዋን የሞቃት–ነፋስ ፊኛ መጓጓዣ ፈንድቶ የ19 ቱሪስቶች ህይወት አለፈ (ከሁለት ዓመታት በፊት በዚሁ የጾም ጊዜ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ አውሮፕላን በሽብር ፈጣሪዎች ቦምብ ቤይሩት ሌባኖን ባሕር ጠረፍ ላይ መውደቁንና የንጹሐን ወገኖቻችን ሕይወት ማለፉን እናስታውሳለን)
- ማክሰኞ የካቲት 19፦ በገብርኤል ዕለት፡ የሳውዲ ባለሥልጣን፡ “ኢትዮጵያውያን አረቦችን ይጠላሉ፡ የአባይን ቧንቧ በመዝጋትም ሱዳኖችን እና ግብጾችን በውሃ ጥማት የመቅጣት ምኞት አላቸው” ብለው እንዲናገሩ ገብርኤል አፋቸውን ከፈተለን፤ በማግስቱም እኝሁ ሰው የኢትዮጵያውያንን አፍ በፔትሮ-ዶላር ለመዝጋት ወደ አዲስ አበባ አመሩ
- ማክሰኞ የካቲት 19፡– ብዛት ባላቸው የቱርክና አረብ ከባብ ምግቤቶች የፈረስ ብቻ ሳይሆን አሳማም የተደባለቀበት የስጋ ሳንድዊች መገኘቱ ተገለጠ
- ረቡዕ የካቲት 20፡– የተባበሩት መንግሥታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከኢትዮጵያ ገበሬዎች ላይ 28 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በቆሎ መግዛቱ ታወቀ
- ሓሙስ የካቲት 21፡– በማርያም ዕለት፡ አቡነ ማቲያስ 6ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ጳጳስ ሆነው ተመረጡ። በዚሁ ዕለት ቤነዲክት 16ኛው ከጵጵስናቸው ተሰናበቱ
- ሓሙስ የካቲት 21፡– በሊቢያዋ ቤንጋዚ፡ ሊቢያውያን ሙስሊሞች በግብጽ/ኮፕቶች ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት በማድረስ በውስጧ የነበሩትን 100 ክርስቲያኖችን አሠሯቸው። ከዚያም ጸጉሮቻቸውን ሸልተው ከላጩባቸው በኋላ እጆቻቸው ቆዳ ላይ የተነቀሱትን መስቀል አሲድ/ኮምጣጤ እየረጩ በመፋቅ አጠፉባቸው። ይህን ጭካኔ የተሞላበት ዜና ሳነብ አቡነ ማቲያስ ቀኝ እጃቸው ላይ የተነቀሱት መስቀል ታየኝ
- ኃሙስ የካቲት 21፡– ኢትዮጲያዊት–አይሁዷ፡ የ2013ቱን የእስራኤል የቁንጅና ውድድር አሸነፈች
- ዓርብ የካቲት 22፡– አቡነ ማቲያስ በአቡንነት ለብዙ ዓመታት በኖሩባት በቅዱሷ ኢየሩሳሌም፡ ኢትዮጵያውያን ሴትና ወንድ ሯጮች የከተማዋን የማራቶን ሩጫ ውድድር በሬኮርድ አሸነፉ
- ዓርብ የካቲት 22፡– የአውሮፓ ከብቶች የሚመገቡት 45ሺህ ሜትሪክ ቶን የሚሆን በመርዝ የተበከለ በቆሎ ከሰርቢያ ወደ ጀርመን መግባቱ ተጠቆመ። ወተቱንም ሊበክል ይችላል። ታዲያ የኢትዮጵያ በቆሎ ይህን ይተካ ዘንድ ታስቦ ይሆን?
- ዓርብ የካቲት 22፡– ብዛት ያላቸው ግብጻውያን ሙስሊሞች በአስዋን ከተማ ቤተክርስቲያን ላይ ጥቃት ፈጸሙ፤ ክርስቲያኖችና ፖሊሶች ቆሰሉ
አንመኝላቸውም! ግን መሆን ያለበት ይሆናል፤ በሰሜን አፍሪቃና በሳዑዲ አረቦች፡ እንዲሁም በተባባሪዎቻቸው ላይ ከፍተኛ መቅሰፍት እየመጣባቸው ነው! የመቅሰፍቱ ምንጭም ልክ ከሙሴ ጊዜ ጀምሮ እንደነበረው ሁሉ የኢትዮጵያ ተራሮች ነው የሚሆነው።
“ስለ ግብጽ የተነገረ ሸክም። እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና እይበረረ ወደ ግብጽ ይመጣል፤ የግብጽም ጣዖታት በፊቱ ይርዳሉ፥ የግብጽም ልብ በውስጥዋ ይቀልጣል።
ግብጻውያንን በግብጻውያን ላይ አስነሣለሁ፤ ወንድምም ወንድሙን፥ ሰውም ባልንጀራውን፥ ከተማም ከተማን፥ መንግሥትም መንግሥትን ይወጋል።
የግብጽም መንፈስ በውስጥዋ ባዶ ይሆናል፥ ምክራቸውንም አጠፋለሁ፤ እነርሱም ጣዖቶቻቸውን በድግምት የሚጠነቍሉትንም መናፍስት ጠሪዎቻቸውንም ጠንቋዮቻቸውንም ይጠይቃሉ።
ግብጻውያንንም በጨካኝ ጌታ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ውኆችም ከባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙም ያንሳል ደረቅም ይሆናል።
ወንዞቹም ይገማሉ፥ የግብጽም መስኖች ያንሳሉ ይደርቃሉም፤ ደንገልና ቄጤማ ይጠወልጋሉ።
በዓባይ ወንዝ ዳር ያለው መስክ በዓባይም ወንዝ አጠገብ የተዘራ እርሻ ሁሉ ይደርቃል፥ ይበተንማል፥ አይገኝምም።
ዓሣ አጥማጆቹ ያዝናሉ፥ በዓባይም ወንዝ መቃጥን የሚጥሉት ሁሉ ያለቅሳሉ፥ በውኆችም ላይ መረብ የሚዘረጉት ይዝላሉ።“ [ትንቢተ ኢሳያስ 19፥1-8]
Leave a Reply