ኪዳነ ምሕረት
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 23, 2013
በንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ
እግዚአብሔር ወልድ፡ “ኢየሱስ ክርስቶስ” ተብሎ ከቅድስት ድንግል ማርያም በመወለዱ የተገኘው ዘለዓለማዊ የምሕረት ቃል ኪዳን “ኪዳነ ምሕረት” ይባላል። የዓመቱም በዓል በዛሬው የካቲት ፲፮ ቀን ይውላል።
የመጀመሪያዎቹ አዳምና ሔዋን የፈጣሪያቸውን ፈቃድ መተላለፋቸው በየራሳቸውና በልጆቻቸው ላይ የዲያብሎስን ገዢነት የኃጢኣጥትን ቀንበርና የሞትን ፍዳ አመጣባቸው። በየዘመናቱ ለደጋጎች ልጆቻቸው የተሰጡት አምላካውያት ቃል ኪዳናትና የ፭ሺ፭፻ ዓመታት ንስሓቸው ግን እግዚአብሔር ወልድን ከሰማየ ሰማያት ልዕልናው ወደምድር አውርዶ ሰው ለመኾን አበቃው፡ መለኮታዊውም ፈቃድ በመጨረሻዎቹ ኣዳምና ሔዋን፡ በኢየሱስ ክርስቶስና በድንግል ማርያም ስለተፈጸመ፡ ይህ ፍቅርና ርኅራኄ የሰው ልጆች የእግዚአብሔር ልጆች የሚኾኑበትን የመጨረሻውን ክብር አቀዳጃቸው፤ የኃጢኣት ሥርየትንና የትንሣኤ ሕይወትን አስገኘላቸው። ይህ፡ የልጅነት ጸጋ ይህ የሥርየት ነጻነት ይህ የትንሣኤ ክብር ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖር ዘንድ በመለኮታዊ የምሕረት ቃል ኪዳን ለአንዴና ለመቼውም ጊዜ ታተመ!
ማኅተሙም፡ እግዚአብሔር ወልድ ከድንግል ማርያም፡ ከሥጋዋ ሥጋን፡ ከነፍሷም ነፍስን ነሥቶ የተዋሓደውና በመስቀል ላይ የሠዋው ዛሬም እኛ እውነተኞች ኢትዮጵያውያን በንስሓ ነጽተን ከቅዳሴ ጸሎት በኋላ የምንቀበለው ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው። በእርሱ በልጇ
በኪዳነ ምሕረት ክብረ በዓል መናፍቁ ተጋለጥ
በኪዳነ ምሕረት ቃል ኪዳን የተያዘውን መናፍቅ ስናይ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ የሆነ ሰው ሁሉ በዘመናችን በተለቀቀው አደገኛ ተኩላ እንዳይበላ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው እንገነዘባለን።
የመምጣትህና የዓለሙ መጨረሻ መቼ ይሆናል? በማለት ሐዋርያት ክርስቶስን በጠየቁት ጊዜ ክርስቶስ የመለሰላቸው መልስ፦ “ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ ብዙዎችንም ያስታሉ” የሚል ነበር ማቴ. 24 ቁ. 3፥8 ይህ አምላካዊ ቃል ይፈፀም ዘንድ አስመሳዩ ተኩላ በጎቻችንን ሊነጥቅ ሲያደባ ነሐሴ 15 ለ 16 አጥቢያ ከሌሊቱ 5 ሰዓት ላይ በሐመረ ኖህ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ቅጥር ግቢ ውስጥ ተይዟል።
ይኽ ተኩላ በአዲስ አበባ ውስጥ ያደገ ሲሆን ከሰባዊነት ወደ ተኩላነት ከተለወጠበት ጊዜ ጀምሮ በአዲስ አበባና አካባቢዋ በደብረ ዘይት፣ በናዝሬት፣ በቁልቢና፣ በደብረ ሊባኖስ በመሳሰሉት እየተገኘ ዓላማውን ለማሳካት ሲሯሯጥ መቆየቱን በተያዘበት ዕለት ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ሰጥቷል።
ይኽ ተኩላ ርካሽ ዓላማውን ለማሳካት አመች ነው ተብሎ እሱን ከመሳሰሉት እበላ ባዮች የተሰጠው መመሪያ ምንና ምን እንደሆነ ሳይረዳ የሚሰብከው ልብስ የቤተ ክርስቲያናችንን የካህናት ልብስ በቀሚሱ ላይ ካባ በመደረብ በአንገቱ ላይ መስቀል ማንጠልጠል በተጨማሪ ዳዊትና የመሳሰሉት መጻሕፍትን ከነማሕደራቸው በግራና በቀኝ ጎኑ ማንጠልጠል ሆኖ ቁጥጥሩ በላላበት ቦታ ዓላማውን ማራመድ እንደነበር በወቅቱ ሳይሸሽግ ተናግሮአል።
ወዲያውኑ ይኽ አስመሳይ ተኩላ በተለያዩ የሕዝብ ብዛት በሚታይበት በሸንኮራው ጠበል ተገኝቶ ዓላማውን ሲያመቻች እንደነበረ የተደረሰበት መሆኑ ተገልጿል።
josephbiddulph said
Thanks for the lovely picture of the Crowning of Our Blessed Lady in Heaven. We have been praying for Our Lady’s intercession in our vigil outside an abortion clinic in Cardiff. The weather here is bitingly cold.
addisethiopia said
Thank you, Sir! Please do continue praying for the protection of the unborn, for life. Thanks!