Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2013
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for February 10th, 2013

መታየት ያለበት ቪዲዮ፡ የኢትዮጵያ ጠላቶች እንቅስቃሴ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 10, 2013

ይህን ፊልም ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ማየት ይገባዋል። እዚህ ፊልም ላይ የቀረቡት የስነልቦናዊ እንዲሁም የአእምሮ ሥነዕውቀት ምርምራዊ ገለጣዎች በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን የሚመለከቱ ናቸው። ላለፉት አስር ዓመት ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ ይህን በተመለከቱ ጥቆማዎችንና ማስጠንቀቂያዎችን በተደጋጋሚ ለማቅረብ ሞክሪያለሁ፤ አሁንም የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ መጠቆሙን አላቋርጥም።

በተለይ ይህን በተመለከተ በተለያዩ የኢንዱስሪ አገሮች በቅርብ ሆኜ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ለመታዘብ ስለበቃሁ የዚህን ሳይንሳዊ ተልዕኮ አስከፊነት/አደገኛነት አሁንም በድጋሚ ልጠቁም እሻለሁ። ይህም ፊልም አንድ ትልቅ ማስረጃ።

ሰለዚህ ጉዳይ የተሻለ እውቀት ያላቸውና በተለያዩ የዓለማችን ምርጥ ዮኒቨርሲቲዎች በሙያው የሠለጠኑ ኢትዮጵያውያን አሉ፡ ስለድርጊቱም ብዙ የሚያውቁት ነገር አለ፤ ነገር ግን ለሕዝባቸው ይህን እውቀት እንዳያካፍሉ ብሎም የዋሁን ኢትዮጵያዊ እንዳያስጠነቅቁ ተደርገዋል፣ በረቀቀ ሰንሰለት ሊታሠሩ በቅተዋል፤ በሕይወት ካሉ፡ ምናልባት በቅርቡ ምን ነክቶን ነው? ለምን ይህን ሳናደርግ ቀረን?” የሚሉ ጥያቄዎች መጠየቃቸው አይቀሬ ነው። ከጠላት ጋር በማበርም ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን ለዲያብሎስ ላብራቶሪ አሳልፈው በመስጠት ለጊዚያዊ ጥቅም የሚሯሯጡት ደግሞ የሚጠብቃቸው መለኮታዊ ፍርድ ምን ሊሆን እንደሚችል መገመት አያዳግትም፤ አምላክ ይማራቸው።

የፊልሙ አርእስት እንደሚናገረው የሥነ እውቀት ሊቆች የአምላክን መኖርና አለመኖር ለማረጋገጥ የተለያዩ የአእምሮ መመርመሪያ መሣሪያዎችን የተጠቀሙት በአንዳንድ የራሳቸው አገር ግለሰቦች ላይ ቢሆንም፡ ዋናው ትኩረታቸው ግን በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች እና በ ቲቤት መነኮሳውያን ላይ ነው። ይህ ያለምክኒያት አይደለም።

ቲቤታውያንና ኢትዮጵያውያንን የሚያገናኟቸው ብዙ ነገሮች አሉ። በከፍተኛ ተራሮች ላይ ከሚኖሩት ጥቂት ሕዝቦች መካከል ቲቤታውያንን ኢትዮጵያውያን ይገኙበታል። ከፍተኛ የመልከዓ ምድር አቀማመጥ ያሏቸው ቦታዎች ላይ የሚገኘው የኦክስጅን መጠን በጣም ዝቅተኛ ነው፤ ታዲያ የኦክስጅን መጠን በማነሱ በተፈጥሮ ጤናማዎች፣ ብዙ ርቀት ተጉዘው መሄድና ብዙ ዘመናት ዘልቀው ለመኖር የሚችሉ ሕዝቦች ለመሆን በቅተዋል። ተራሮች ላይ የሚወለዱ ሕዝቦች በአካል ከሳ ያሉ፤ በህሊና/በመንፈሥ የመጠቁ ሕዝቦች ናቸው። ልብ ብለን ታዝበን ከሆነ መንፈሣዊ የነበሩት ሐዋርያት፣ ነብያትና ቅዱሳን ከኢትዮጵያውያን ጋር በአካልም የተሣሰሩ ስለነበሩ ልክ እንደ ኢትዮጵያውያን ከሳ ያሉ፣ ምጥጥያለ የፊት ገጽታ የነበራቸው ነበሩ። ከሳ ያሉ ሰዎች ያለብዙ ምግብ የመኖርና ብዙ የመጾም ብሎም ብዙ ችግሮችና መከራዎችን የማሳለፍ ብቃት አላቸው። ስጋችን ከሳ ባለ ቁጥር በአካላችን ዙሪያ/ላይ የሚገኘውንና በዓይን ብቻ ለማየት የማይቻለው መንፈሳችን(Aura)ተለቅ እያለና እየተቀደሰ ይመጣል። በርግጥ ይህን መንፈስ ለማየት የሚችሉ ግለሰቦች አሉ፤ ነገር ግን ባሁኑ ጊዜ መነጽር የሚያዘወትሩት የሳይንስ ሊቆች ይህን መንፈስ እንዲሁም ምናልባት መንፍሱን ይወልዳል ብለው የሚገምቱትንና አንጎላችን ውስጥ የሚገኘውን ጵኒያል‘ (ጵኒኤል ?)የሚባለውን አምላካዊእጢ (Pineal gland) በዘመናዊ መሣሪያዎችን ዓማካይነት ለማየት/ለመነካካት እየቃጣቸው ነው።

ይህ በ ቅንጭላታችን ውስጥ የሚገኘውና “pineal gland” ተባሎ የሚታወቀ እጢ የበቆሎ ፍሬ ዓይነት ቅርጽና መጠን ያለው ሲሆን እዚህ ስዕል ላይ እንደሚታየው አቀማመጡም አንጎላችን መካከል ውስጥ ነው። የህክምና ባለሙያዎች እንደሚነግሩን፡ በእርግዝና ወቅት እናቶች ማህፀን ውስጥ ከሁሉም የአካላችን እጢዎች አስቀድሞ በሦስተኛው ሳምንት በደንብ ቅርጽ ይዞና ተለይቶ የሚታየው እጢ ይህ እጢ ብቻ ነው።

በምዕራቡ ዓለም፡ ይህ እጢ ለአካላችን አስፈላጊ እንዳልሆነ፡ እንዲያውም እያደር ከሚመጣ ለውጥ (ኢቮሊሽን) ያገኘነው እጢ እንደሆነ እስከ ቅርብ ጊዜ ይታመንበት ነበር።

ነገር ግን፡ ይህ እጢ ሜላኒንወይም ሜላቶኒንየተባለውን የኬሚካል ቅመም/ሆርሞን የሚያመነጭ በጣም ጠቃሚ እጢ እንደሆነ አሁን ተረጋግጧል።

ሜላኒን ጠቆር ባለ የሰው ቆዳ ላይ የሚነጸባረቅ የማቅለሚያ ቅመምም ነው። ሜላኒን ብዙ ጥቅም ያላቸው ሕይወት ሰጭ ሚናዎችን የሚጫወት ሆርሞን እንደሆነ ይነገርለታል። በተለይ ከመጠን ከፍ ያለ የጨረር ብርሃን በሚታዩባቸውና እንደ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተራራዎች ላይ በሚኖሩ ሕዝቦች ላይ ከፍተኛና ጤናማ የሆነ የሚላኒን መጠን ይገኛል። ቆዳቸው ነጣ ባሉ ሰዎች ላይ ዝቅተኛ የሚላኒን ክምች ይገኛል። ማለትም ከጸሐይ በተራቀ ቁጥር የፒንየል እጢውን ቀስቅሶ ለማሠራት አስቸጋሪ ነው፡ ስለዚህ ይህ እጢ በቂ ብርሃን ከማጣት የተነሳ ይሞታል ማለት ነው። ይህ እጢ ከሞተ ደግሞ ግለሰቦች ወይም ሕዝቦች ብዙ ሰብዓዊ ነገሮቻቸውን ሊያጢ ይበቃሉ፡ ነፍሳቸው ይዳከማል ማለት ነው።

በፈረንጆች ላይ የሚታየው አንዱ ትልቁ ችገር ይህ ነው ሊሆን የሚችለው። በፈረንጅ ሕዝቦች መካከል ሚላኒንን ሊያፈልቅ የሚችለው የፒኒያል እጢ ያለው የሕዝብ ቁጥር ምናልባት 10% ብቻ እንደሆነ ይነገራል። እግዚአብሔር አምላክን መካድ ወይም እምነት አልባነት ወይም በክርስቲያናዊ ሕይወት ላይ የሚታየው ዓይን ያወጣ ጦርነታዊ ዘመቻ ፈረንጅ በሆኑ ሕዝቦች ላይ በብዛት እየታየ መምጣቱም ይህን ነው የሚጠቁምው።

ከጸሐይ መራቅ ባመጣው ችግር ምክኒያት ተፈጥሮአቸው ደክሞም ወደ አምላክ ለመቅረብ የሚታገሉት ጥቂቶቹ ፈረንጆች የእግዚአብሔርን ጸጋ ለማግኘት ይችላሉ፡ እንዲያውም ምናልባት ጠቆር ካለው ሕዝብ በተሻለ ሁኔታ፡ ምክኒያቱም እግዚአብሔር ጉድለታቸውን ያያልና፡ ያዝናልና፡ ይሰጣልና፡ በመንፈስ ደካሞች ብጹዓን ናቸውና።

ነገር ግን ሃቅን ለረጅም ጊዜ አፍኖ መያዝ አይቻልምና፡ የዚህን እጢ ልዩ ሆርሞን ጥቅም ቀስበቀስ እየተረዳ የመጣው አብዛኛው ፈረንጅ ይህን እንደ ትልቅ ጉድለት አድርጎ በውስጡ በመቀበሉና ከባዱን የመንፈሳዊ ሥራ ለመሥራት ባለመውደዱ፡ አምላክ አለመኖሩን መምረጥ፡ ለአምላክ የቀረቡትንና የእርሱን ፈጣሪነት የተቀበሉትን ጠቆር ያሉትን ሕዝቦች በተለያዩ መንገዶች በማሳሳት፣ በማታለል ብሎም በቀጥታ በመዋጋት ወደ ጦርነት መንገድ መሄዱን መርጧል። በፈረንጅ የቅኝ አገዛዝና የባርነት ቀንበር ሥር የወደቁት ጥቁር አፍሪቃውያንም የዚህ የሜላኒን ጦርነት ተቀዳሚ ዒላማዎች ለመሆን በቅተዋል። ለዚህም ነው የመጀመሪያ የቅኝ አገዛዝ ተልዕኮ ኃይማኖትነክ ባሕርይ ይዞ የመጣው። ለዚህም ነው በጥንታውያን ደቡባዊ አፍሪቃ (የ ኮይሳን ፣ ሳን ሕዝቦች) እና ምሥራቃዊ አፍሪቃ (ቱሲ፣ ሌምባ) አፍሪቃውያን ሕዝቦች ላይ ቀደም ሲል ከፍተኛ የጭፈጨፋ በደል ሲፈጽሙ የነበሩት ባንቱ አፍሪቃውያን የሚከተሉት የቩዱ አምልኮት፡ እንደ ሮማ ካቶሊክ፣ እስልምና፣ ፕሮቴስታንታዊነት ከመሳሰሉት ባዕዳዊ እምነቶች ጋር በመተሳሰር/በመዋሐድ የአፍሪቃውያኑን ነፍስ ሊያደክም የበቃው። ልብ ብለን ከታዘብን ከምዕራባውያን ሥልጣኔ ሽፋን ሥር የጣዖትና የእስላም መንፈስ ጎልቶ ይታያል። የባርነት አስከፊ መቅሰፍት የባሪያ ገዢና ባሪያ ሕዝቦችን ታሪክ ጋር በማያላቅቅ መልክ ማስተሳሰሩ ሌላ ተጨማሪ ማስረጃ ነው። ይህም መንፈስ ከአውሮፓና አሜሪካ ውጭ በመላው አፍሪቃ፡ በእስያ እንዲሁም በአንዳንድ የኢትዮጵያ ደቡባዊ አካባቢዎች በተለይወይጦበሚባሉ ህዝቦች ዘንድ ይስተዋላል። ሥር የሰደደ አጕል እምነት ማሸነፍ አዳጋች ነው!

*ወይጦዎች በአባይ ወንዝ ውሃ ላይ ስለሚፈጽሙት የአምልኮት ባህል ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።

ይህ ጵኒኤልየሚባለው እጢ ምናልባት ነፍሳችንየሚቀመጥበት የአንጎላችን ክፍል ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። በዚህ እጢ አማካይነት ከዝቅተኛ የአካል ተፈጥሮ ወደ ከፍተኛው ተፈጥሮ መጓዝ እንችላለን የሚሉም አይጠፉም፡ ሦስተኛው ዓይናችን ነው በሚገባ ልንጠቀምበት፡ በየጊዜውም ልንንከባከበውና ልንቀሰቅሰው ይገባናል። እውርመሆን የተቀሩት ሁለት አይኖችን ብርሃን ማጣት ሳይሆን የዚህ ሦስተኛ አይን መታወር ነው። ደንቆሮመሆን የሁለቱ ጆሮዎች ድምጽ ማጣት ሳይሆን የዚህ ሦስተኛ አይን(ጆሮ) መደንቆር እንጂ።

በትክክለኛ ጸሎት እና በእምነት ይህን እጢ ዘወትር የምናንቀሳቅስ ከሆነ ከፈጣሪአችን ጋር ለመገናኘት እድል ይኖረናል፡ የእግዚአብሔርንም ፊት ለማየት እንችላለን ተብሎ ይታሰባል። እጃችንን ሦስት ጊዜ ለጸሎት ስናማትብ ከግንባራችን መኸል መጀመራችን ወይም እዚያው የግንባራችን ቦታ ላይ የኢትዮጵያ ሴቶች በመስቀል ቅርጽ መነቀሳቸው ምንን ይነግረን ይሆን?

ጵኒኤልየሚለውን ቃል የግእዝ መጽሐፍ ራእየ እግዚአብሔር ይለዋል። “ጵኒኤልማለት የአምላክ ፊትማለት ሊሆን ይችላል። ታዲያ ጲኒኤል እጢየአምላክን ገጽታ የሚያሳይ እጢ ሊሆን ይችላልን?

ኦሪት ዘፍጥረት ላይ፡ የይስሐቅ ልጅ፡ ያዕቆብ፡ ከእግዚአብሔር እና ከሰዎች ጋር ታግሎ ከዘለቀ በኋላና ስሙም ወደ እስራኤልበሚለወጥበት ጊዜ ይህን ተናግሮ ነበር፡

ያዕቆብም። እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል ብሎ ጠራው። ጵኒኤልንም ሲያልፍ ፀሐይ ወጣችበት፥ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር።” (ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 32 .30:32)

ሰለጠንኩ የሚለው ዓለም በዋነኝነት ለስጋውና ለሆዱ የሚኖር ስለሆነ አንድን ነገር ለመቀበል ማየትንና መዳሰስን አማራጭ የሌለው ተቀዳሚ ተግባር አድርጎ ይወስደዋል። ሃቁ ግን በአካባቢያችን/በዓለማችን ዙሪያ ከሚገኙት ነገሮች መካከል 97% የሚሆነው በዓይኖቻችን ማየት ወይም በእጆቻችን መዳሰስ አይቻለንም። ይህም ማለት አብዛኛው በአካባቢያችን ብሎም ራቅ ብሎ የሚገኘውን ነገር ልንደርስበት የምንችለው ልዩ በሆነ መንፈሣዊ በሆነ መንገድ፡ በጸሎት ብቻ እንጂ ሦስት ወርድና ስፋት ያለውን ብቻ በሚያየው ዓይናችን ቀድመን በማየት ወይም በእጆቻችን የሠራናቸውን የተራቀቁመሣሪያዎች በመጠቀም አይደለም። ወደ ጠፈር ስለተጓዝን የበላይነቱን ልንይዝ አንችልም። ሆኖም፡ ሙከራዊ የልምምድ ጥበቡን የተካኑት የዓለማችን ሊቃውንት ከፍተኛ የሰው ልጅ እውቀትና ልምድ ካለው ከአጋራቸው ከዲያብሎስ ጋር በመሆን ምስጢራዊ የሆኑትን የዓምላክን ሥራዎች ከመርመር ወደኋላ አላሉም። ለዚህ ነው ውስጣዊውን የሰውን ልጅ ማንነት ሊገልጹ የሚችሉትን እጢዎች፣ መቅኒዎች፣ ደሞች እንዲሁም መሠረታዊ የአካላት ቅመማቅመሞች (DNA)በጣም ጠልቀው ለማጥናት የተነሳሱት።

ፊልሙ ላይ የሚታየው መሣሪያ ጊዜው ያለፈበት ነው፤ በአሁኑ ጊዜ ቴክኖሎጂው እጅግ በጣም የተራቀቀ ስለሆነ በተለይ የአእምሮ ሳይንስን በተመለከተ የተሠሩት መሣሪያዎች አንድን ነገር/ሰው ሩቅ ሆኖ መቆጣጠር የሚያስችሉ፣ በቀላሉ የሚንቀሳቀሱና በጣም ሥውሮች ናቸው። መሣሪያዎቹም የሚያገለግሉት 1ሚሊየን የማይሞሉትን ምስጢራዊ የፈረንጅ ቁንጮዎች ነው። ለምሳሌ በየከተሞቻችን ተዘርግተው የሚታዩትን የኪስ ስልክ (ሞባይል) ወይም የረቂቅ ሞገድ ሰሃን(ማይክሮዌቭ)አንቴናዎችን በመጠቀም ከጠፈር ሉሌዎች(ሳተላይቶች)የሚላከቱን ዲያብሎሳዊ የጥቃት ጨረሮች ለማፈንጠቅ ይችላሉ።

በአፍሪቃ፡ በተለይ በኢትዮጵያ ላይ ያነጣጠሩ የጠፈር ሉሌዎች ብዙ ናቸው፡ እንደ አይ ኤስ ኤስ‘/ISS የመሳሰሉትም ዓለም አቀፋዊ የጠፈር መርከቦች ዓይኖቻቸውን በኢትዮጵያ ላይ ነው በይበልጥ ያነጣጠሩት። ይህችን አጭር ቪዲዮ እንመልከት።

አገራችን ውስጥ ለኛ የተደበቁ ለዲያብሎስ ጠላታችን ግን የተገለጡ ብዙ ምስጢራዊ ነገሮች አሉ። በተለይ ከተዋሕዶ ዕምነታችን ጋር የተያያዘው መንፈሳዊ ኑሯችን፡ እኛ በውስጡ ስላለን ይህን ያህል ከፍተኛ ትኩረት ላናደርግለት እንችላለን፡ ነገር ግን፡ ውጭ ያሉት፣ በተለይ መንፈሳዊ ኃብት የጎደላቸው፣ በተለይ እኛን በጠላትነት የሚቀርቡን ይህን ምስጢር ገልጦ ለማየት ያላቸው ጉጉት እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው። በፈርንጁ መካከል እላይ የጠቀስኳቸው 10% የሚሆኑት ነዋሪዎች በእግዚአብሔር አማኞች ሊሆኑ ይችላሉ፡ ከመካከላቸውም በጣም ጥሩዎችና መላዕክት የመሳሰሉ ይገኙበታል። ነገር እነዚህ ጥሩ ፈረንጆች ከእኛ ከኢትዮጵያውያን ጋር በእግዚአብሔር በኩል፡ በመለኮታዊው መሥመር ካልሆነ በቀጥታ ምንም ዓይነት የዓካል ግኑኝነት አይኖራቸውም። ከኛ ጋር ግኑኝነት ያላቸው ወይም እኛን የሚቀርቡን ለኛ በጎ የማይመኙልን ወይም እኛን ከላብራቶሪ ዓይጠ መጎጥ ለይተው ማየት የማይፈልጉት የሉሲፈር ልጆች ናቸው። ሥራው እጅግ በጣም አስቀያሚ ከሆነ ጨካኝ ኃይል ጋር ነው ተፋጥጥን ያለነው። ይህን ሃቅ እየከነከነንም ቢሆን ምራቃችንን እየዋጥን በግድ መቀበል ይኖርብናል።

90% በመቶ የሚሆኑት ተመራማሪዎች ወይም ሊቃውንት ወደ ሥነ እውቀቱ ዓለም ለመግባት ሲወስኑ አምላክን በመካድ፤ ማለትም እግዚአብሔርን አናውቅም፣ አለመኖሩንም እናውቃለን በማለት ነው። ይህም ማለት የሳይንሱን ዓለም ብቻ ሳይሆን ዓለማችንን ባጠቃላይ የሚቆጣጠሩት ኢአማንያን የአምላክን መኖር ሳይሆን የአምላክን አለመኖር ነው ለማረጋገጥ የሚታገሉት። ይህም ማለት፡ አምላካዊ የሆኑ ግኝቶች ላይ በደረሱ ቁጥር እነዚህን ግኝቶች ወይ ይደብቋቸዋል ወይም ያጠፏቸዋል። ስለዚህ፡ ከመጀመሪያው አንስቶ ተልዕኳቸው የእግዚአብሔርን ክብር ለመቀነስ ብሉም አምላክን ለመዋጋት ነው። ከአምላክ ጋር ጦርነት የሚገጥም ደግሞ ሰይጣን ነው። ስለዚህ ለእነዚህ ቅዱስ መንፈስ ለራቃቸውና ጋኔን ለተዋሐዳቸው የሉሲፈር አርበኞች እግዚአብሔር ምስጢሩን ፈጽሞ ሊያካፍላቸው አይችልም። ሃይማኖታዊ ወይም መንፈሳዊ የሆኑትን ትክክለኛ እውቀቶችም ለማይታወቀው፣ ለተናቀውና ድሃ ለሆነው ኢትዮጵያዊ እንጂ በንዋይ ለበለጸጉት ሕዝቦች ሊሰጥ አይችልም።

የሁለት ሺህ ዓመቱን የተራቀቀ መንፈሳዊ ጥበብ የተካነችው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ያልደረሰችበትን ጉዳይ በጥቂት መቶ ዓመታት ውስጥ እውቀቱን አግኝተናል ብለው በከንቱ የሚመኩት አምላክከጂ ፈረንጆች መለኮታዊ ምስጢሩ ላይ በጭራሽ ሊደርሱበት እንደማይችሉ ከዕለት ወደ ዕለት የምንታዘበው ነው።

ሰይጣን ብዙዎቻን እንደምናስበውና ብዙ የተሳሉ ስዕሎችም እንደሚያሳዩን አስቀያሚና አፀያፊ የሆነ ፍጡር አይደልም። እንዲያውም የሚያምርና ማራኪ እንጂ። ይህ ፊልም፡ ምንም እንኳን የታሪክ ጣቢያው እንደ ተለመደው ነገሮችን ነካ ነካ እያደረገ በሳይንስና በእምነት መካከል ስላለው ግኑኝነት ለማቅረብ ቢሞክርም፡ የሚያስተላልፋቸውን ድብቅ መልዕክቶች ግን ከፍተኛ ሙያዊ ብቃት ባለው መልክ ነው እያስተላለፈ ያለው።

በፊልሙ ላይ በተደጋጋሚ የሚታዩትና በሃገረ ኢትዮጵያም ተደጋጋሚ ቆይታዎችን ለማድረግ የበቁት ክርስቲያንየሥነ እውቀት ተመራማሪው፡ አቶ ሮበርት(ቦብ)ኮርኑክ ድብቅ የሆኑ ታሪኮችን ተከታትለው ለመመርመር በየመንደሩ በትጋት ደፋ ቀና ማለታቸው አድናቆትን ሊያተርፍላቸው ይገባል። ነገር ግን እንደ እኔ ከሆነ አቶ ኮርኑክን ማመን የለብንም፣ በሚያቀርቡልንም መረጃ መንፈሳዊ ኩራት ሊሰማን አይገባም፣ እሳቸውን ለመሳሰሉትም ሰዎች የሚመለከታቸው ገዳማትና ዓብያተ ክርስቲያናትም በሮቻቸውን ዝም ብለው ሊከፍቱላቸው አይገባም። ከዚህ በፊት አቅርቤው በነበረው በዚህ ምስል ላይ ከሚታዩት አራት የኢትዮጵያ ዋና ዋና ጠላቶች መካከል ልክ አቶ ኮርኑክን የመሰለው ሰው ይገኝበታል። ይህ ሰው የሚወክለው ሰዶማውያንን ነው፤ በተለይ በአፍንጫ አማካይነት የሚታየው ገጽታም አደገኛ በሆኑት ሰዶማውያን ላይ ይንጸባረቃል። አቶ ኮርኑክ የሙሴን ጽላት ፍለጋ በሚል ሳውዲ ዓረቢያ ላይ ትኩረት ማድረጋቸውና እዚያም ብዙ ጊዜ ማሳለፋቸው የሚታወስ ነው። ይህን በተመለከተ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል።

ፊልሙ ላይ እንደምናየው፤ አቶ ኮርኑክ በአንድ በኩል የታቦተ ጽዮንን(ጽላተ ሙሴ)መኖር በመቀበል እንዲሁም በኢትዮጵያ መሆኗን በማመን፤ ጽላቷ በዓለም ተወዳዳሪ የሌለው ኅይል ሊኖራት ይችላል ብለው በስሜት ይገልጻሉ። በሌላ በኩል ግን የሚከተለው የቪዲዮው ቁራሽ ላይ ጽላቷ እራሷ ሳትሆን ኅይል ያላት ኃይለኛ የሆነው የኢትዮጵያውያን አእምሮ ነው፡ ምክኒያቱም ኢትዮጵያውያን ከልጅነታቸው ጀምረው ስለ ጽላቷ ኅይለኛነት አሳማኝ በሆነ መልክ ተሰብከዋልናይሉናል።

ይህ አባባላቸው የሳቸውንም የሌሎቹንም የሳይንስ ሊቆች ተልዕኮ ነው የሚያንጸባርቀው። አምላክን ለመዋጋት አእምሮን መዋጋት አለብን። አእምሮን ለመዋጋት፣ በመጀመሪያ አስፈላጊውን መረጃ ከሰበሰብን በኋላ አካላዊ (ጄነቲካል) ጥቃቶችን መፈጸም አለብን። አዎ! የሉሲፈር አርበኞች የተለያየ መንገድ እየፈለጉ ጥንታውያን ኢትዮጵያውያንን መዋጋቱን ቀጥለውበታል፤ አገር ቤት ያለውን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር እጅግ በጣም ከባድ ስለሆነ፡ ጭካኔ የተሞላባቸውን ዲያብሎሳዊ ሙከራዎች ውጭ በሚገኘው ኢትዮጵያዊ ላይ ነው የሚያካሂዱት። ይህ በጣም ሊያስደንግጠን ይችላል፡ አዎ! ጉዳዩ በጣም ከባድ ነው፡ አሳዛኝም ነው፡ ግን ልንክደው የማንችለው ሃቅ ነው። ዶክትሮችን አለማዘውተር፣ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ነቅቶ በመኖር ነገሩን ፓራኖይድ ነው!” በሚል ተልካሻ የግድየለሾች ሃተታ ማለፉ ሞኝነት ነው።

ኢትዮጵያውያን በባዮሎጂው/በሕክምናው ሆነ በመንፈሳዊው ዓለም በጣም ጥንታዊ የሆነ ክብረ ወሰን ያላቸው ሕዝቦች ናቸው። ይህን የመሰለ ጸጋ ያገኘ ሕዝብ ደግሞ ለምርምራዊው የሳይንሱ ዓለም እጅግ በጣም ማራኪ ነው። በነጠላ በግልም ሆነ በስብስብ በኢትዮጵያውያኖች ላይ የሚከራ ጥቃቶች እየተካሄዱ ነው። ሆስፒታሎች፡ ለምሳሌ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል፡ ፒንኤል እጢዎችንበተመለከት የላብራቶሪ ምርመራ መረጃዎችን አሜሪካና አውሮፓ ለሚገኙ ዮኒቨርሲቲዎች ማስተላልፈፉን አስታውሳለሁ። መረጃውን በቅርብ አቀርባለሁ። ውጭ በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የጸሎት ሥነስርዓት ወቅት በምዕመናኑ ላይ ጨረር የሚያፈነጥቁ ቪዲዮ ካሜራዎችን እየተጠቀሙ ጉዳት እያደረሱ ነው፡ ፊልም የሚያነሳ ሁሉ ለቴሌቪዥን የሚሆን ምስል አይቀርጽም፤ አብዛኞቹ ምስሎች ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ነው የሚቀርቡት። በተለይ መንፈሳዊ የሆኑ አባቶች አውሮፓና አሜሪካ በምንም ዓይነት ለረጅም ጊዜ መቀመጥ አይገባቸውም። እግዚአብሔር ይጠብቃቸው እንጂ በእነዚህ አባቶች ላይ ሊፈጸሙባቸው ስለሚችሉት ሳይንሳዊ ሙከራዎች ባሰብኩ ቁጥር አዙሮ የሚጥለኝ ይመስለኛል። ይህች ዓለም ገነት አደለችም፡ በተለይ ባሁኑ ጊዜ የመንፈሳዊው ጦርነት እየተጧጧፈ የመጣበት ጊዜ ነው፡ ለዲያብሎስ ጥቃት ተቀዳሚ ዒላማ የሚሆኑት እንደ እኛ ጥንታዊ ክርስትናን የሚከተሉት ክርስቲያኖች ናቸው፡ አባቶች ናቸው። ስለዚህ፡ ከሉሲፈር ልጆች ወጥመድ ለመውጣት በተለይ አባቶች ቶሎ ወደ አገራቸው በመግባት ለኢትዮጵያውያኑ አንድነት እግዚአብሔር የሰጣቸውን ጸጋ በጾም በጸሎት ሊጠቀሙበት ይገባል። መንፈስ ቅዱስ እየራቃቸው በመጡት የእስያ፣ አሜሪካና አውሮፓ አገራት በመቀመጥ በአገራቸው ጥናታዊት ቤተክርስቲያን ላይ፣ በአገራቸውና በሕዛባቸው ላይ እያመጹ ከጠላቶቻቸው ጋር የሚያሳዝንና የሚገርም ህብረት መፍጠር እግዚአብሔርን ነው የሚያስቆጣው። ስለዚህ እናት ቤተክርስቲያናቸውን አገራቸውንና ሕዝባቸውን ማገልገል ባይፈልጉም፣ እራሳቸውን ከአውሬው ዋሻ ለማዳን ቢሞክሩ ዲያብሎስን ይጎዳሉና ቶሎ ሊያስቡበት ይሞክሩ።

ለማንኛውም ይህን ባለ 12ክፍል ቪዲዮ በጥሞና እንከታተል

ቸሩ እግዚአብሔር መተሳሰቡንና ፍቅሩን ያውርድልን ፡ ከጠላት ሤራም ይጠብቀን

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: