Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2013
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ምዕራባውያን ስለ ግብጽ ለምን ዝም አሉ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 30, 2013

አራትነት

ግብጽ ኢትዮጵያ ብትሆንና ኢትዮጵያም ግብጽ ብትሆን፤ ወይም ግብጻውያን በኢትዮጵያ ምድር፡ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በአሁኗ የግብጽ ግዛቶች ውስጥ ቢኖሩ ኖሮ ምን ዓይነት ሁኔታ ሊፈጠር ይችል ነበር?

ኢትዮጵያውያን የሚባሉ ሕዝቦች በዚህች ምድር ላይ አይኖሩም ነበር!

ግብጻውያን በአረብ ሙስሊሞች ቁጥጥር ሥር ከገቡበት ከ7ኛው ምዕተዓመት አንስቶ አሁኗ የኢትዮጵያ ግዛት ሠፍረው ቢሆን ኖሮ አባይን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ውሃውን እየበከሉ በካይሮና እስክንድርያ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም በመኻል የሚገኙትን ኑብያውያንንና ኮፕቶችን መርዘው በመጨረስ መላው ምስራቅና ሰሜን አፍሪቃን ይቆጣጠሩ ነበር። ምክኒያታቸው? በጥንታዊቷ ክርስትና ላይ ያላቸው ጥላቻ!

በኢትዮጵያና በግብጽ የረጅም ዘመን ታሪካዊ ግንኙነት የአባይ ወንዝ ባለቤት የሆኑት ኢትዮጵያውያን በግብጻውያን የፖለቲካ፣ ምጣኔዊ ኃብት፣ የሃይማኖት፣ ወይም ማሕበረሰባዊ ኑሮ ላይ ምንም ዓይነት ሚና ተጫወተው አያውቁም። በተቃራኒው፡ በተንኮል ጥበብ የተካኑት ግብጻውያን ግን ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያውያንን ሲተናኮሉ፣ ሲፈታተኑ ብሎም ለዓያሌ ጥፋቶችና ሞቶች ሲያበቋቸው ቆይተዋል። ምናልባት፡ ወይ ምንም ነገር የሌለው ተንኮል ብቻ ነው የሚያስበው፡ ወይም ደግሞ ቅልቅሉ የአርብፈርዖኖች ደም በርግጥ በመመረዙ ምክኒያት ሊሆን ይችላል፡ ከጥንት ጀምሮ እስካሁኑ የኛ ትውልድ ድረስ ያለውን ታሪካችንን መለስ እያልን ስንመረመር በተደጋጋሚ በአገራችን ተፈጥረው የቆዩት አለመረጋጋቶች፣ ጦርነቶችና ረሃብ ነክ ስቃዮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከግብጽ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን እንገነዘባለን።

ይህን ሁሉ የተፈጥሮ ኃብትና ሰብአዊ ጸጋ ያላት ኢትዮጵያ በዝቅተኛ የሰብዓዊ እድገት ደረጃ ላይ በሚገኙት የአርብ ሕዝቦች እስከ አሁን እንዴት እየተታለልች ልትቆይ ቻለች? የሚለውን ጥያቄ ሁላችንም አጥብቀን ልንጠይቅ ይገባናል። እስኪ ልብ ብለን እንመልከት፤ መሬቶቻችንን እንኩ! ወንዙን እንኩ! በጎቹን እንኩ! ፍራፍሬውን እንኩ! ጥራጥሬውን እንኩ! ቡናውን እንኩ! እህቶቻችንን እንኩ! ልጆቻችንን እንኩ! እግር ኳስ ጨዋታውም የሚያሳየው ይኽንኑ ነው፡ ባልጎደለ ችሎታ፤ ኳሱን እንኩ! የሞኝነታችንን ምክኒያት በቶሎ አብረን ልንፈልግ ይገባናል።

በዓይናቸው የሚታያቸውን ነገር ብቻ በመጨበጥ ለቆዳ ቀለማቸውና ለስጋቸው ብቻ የሚኖሩት አውሮፓውያንና አሜሪካውያን ምንም ነገር የሌላትን ግብጽን መርጠው በመደገፍ ሞኞቹን ኢትዮጵያውያንን አሁንም ግራ በማጋብትና በማተራመስ ላይ እንደሚገኙ የአሁኑ የኢትዮጵያ ትውልድ ከእንቅልፉ ነቃ ነቃ በማለት ለግንዛቤ እየበቃ መሆኑ የሚያበረታታ ነው። እስካሁን ድረስ እንደ እባብ ብልህ ለመሆን አሻፈረኝ ሲሉ የቆዩት ኢትዮጵያውያን ከፈጣሪ እግዚአብሔር አምላክ በቀር ሌላ ማንም የላቸውም። በዚህች ምድር ላይ፡ ምናልባት ከእስራኤል በቀር፡ እንደ ኢትዮጵያ ብዛት ባላቸው ጠላት አገሮች የተከበበች አንዲትም አገር የለችም። ለኢትዮጵያ ወዳጅ የሆነች አገር፡ ወይም በክፉ ጊዜ ከርሷ ጋር አብሯት ሊሰለፉ የሚችሉ ሌሎች ሕዝቦች በጭራሽ የሉም። ግብጽ ግን፡ እራሷ የራሷ ጠላት ካልሆነች በቀር ማን ሌላ ጠላት አላት?… ያው እያየነው አይደል!

ግብጽን በመምራትላይ የሚገኙት ቅዥታሙ ፕሬዚደንት ሙርሲ ሰሞኑን በፈላጭ ቆራጭነት የሚፈጽሟቸውን ዓይነት ድርጊቶች የኢትዮጵያ ወይም የሌላው አፍሪቃ መስተዳደር ቢፈጽም ኖሮ፤ ከአውሮፓ፣ ከአሜሪካ እንዲሁም የሰብአዊ መብትታጋዮች ነን ከሚሉት ድርጅቶች በኩል ሊመጣ የሚችለው ተጽእኖና ጣልቃ ገብነት ምን ሊመስል እንደሚችል መገመት አይከብደንም። ሰሞኑን ግብጽ ውስጥ 60 የሚሆኑ ግብጻውያን በሙርሲ አርበኞች ተገድለዋል፣ ፕሬዚደንቱም እንደ አምባገነን መሪ በተለያዩ ከተሞች የሰዓት ዕላፊ አዋጅ በማውጣትና ለሠራዊታቸውም የተኩስ መክፈት ትእዛዝ በማስተላለፍ የአምባገነናዊ ባሕርይ ያላቸው መሪ መሆናቸውን በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ታዲያ ይህ በእንዲህ እያለ፡ ለአፍሪቃው ህብረት ስብሰባ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ አሻፈረኝ ያሉት ፕሬዚደንት ሙርሲ በዛሬው ዕለት ወደ ጀርመን አገር ይጓዛሉ፡ በጀርመን የሚገኙትም የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች እንዲሁም ኮፕት ክርስቲያኖች የተቃውሞ ሰልፍ በበርሊን ለማድረግ ተዘጋጅተዋል።

እንግሊዝ: ኮንጎ በሚካሄደው የነፃነት ትግል ሳቢያ ኢትዮጵያውያኖቹን የቱሲ ጎሣ አርበኞች በመቃወም አንድ ቀን ባለሞላ ጊዜ ውስጥ በሩዋንዳ ላይ የገንዘብ እርዳታ ማዕቀብ ለማድረግ በቅታለች። የሕዝቡን ጩኽት መስማት የተሳናቸው የግብጹ ፕሬዚደንት ሙርሲ ግን የሙስሊም ወንድማማቾቹ አሜሪካዊ፡ የ ማልኩም ኤክስ ልጅ እንደሆኑ ከሚነገርላቸው ከፕሬዚደንት ኦባማ የማበረታቻ የስልክ ጥሪ ይደረግላቸዋል፣ በውጭ ጉዳይ ምኒስትሯ፡ በክሊንተን የጋዛ ሰላም ፈጣሪ ተብለው ሊሞገሱም በቅተዋል፡ በአውሮፓው ህብረት፣ በሳውዲና ኳታር እንዲሁም በዓለም ዓቀፍ ገንዘብ ሰጭ ድርጅቶችም የብዙ ቢሊየን ዶላር ስጦታ እየተበረከተላቸው ነው፡ የአውሮፓው ህብረትም እስከ 5ቢሊየን ዮሮ ለሙርሲ ግብጽ ለመስጠት በመነጋገር ላይ ነው፡ ፕሬዚደንት ሙርሲ ጀርመን የሚጎበኙት ንዘብ ለመለመን መሆኑ ግልጽ ነው።

የማይክሮሶፍቱ ቢል ጌትስም ለግብጽ ኢኮኖሚ ድጎማ በማድረግ ለማዳበሪያ ምርት እስክ አንድ ቢሊየን ዶላር ከኪሳቸው በማውጣት ለግብጽ የሕዝብ ቁጥር ማደግ አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ፡ እዚህ ይመልከቱ፤ በኢትዮጵያ ግን በተቃራኒው ሴቶቻችን እንዳይወልዱ ክትባቶችንና የወሊድ መከላከያዎችን በትጋት ማሠራጨቱን መርጠዋል። እዚህ ይመልከቱ

ዓለም ግራ ተጋብታልች፡ በቅርቡም ሁሉም የሚገባቸውን ያገኛሉ!

በተጨማሪ ይህን ይመልከቱ፡ የ አውሮፓ–አሜሪካና የ ዐረቦች ጥፋታዊ ኅብረት

_

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: