Happy Epiphany — እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን!
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 18, 2013
ሌላ ጊዜ የምመለስበት፡ ወቅታዊና አንገብጋቢ አጭር የጥምቀት መልዕክት፡
-
አገር ቤት ያላችሁ ታታሪ መንፈሳውያን መሪዎች፣ አባቶች፤ ባካችሁ ቅድስት አገራችንን ለቃችሁ (ለስብሰባም ቢሆን)፡ በተለይ ወደ ሰሜን አሜሪካ መሄዱን አቁሙ
-
ውጭ ያላችሁ ታታሪ ኢትዮጵያውያን መንፈሳዊ መሪዎችና አባቶች ባላችሁበት ቦታ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ የማትሠሩ ወይም የተዋሕዶ ክርስትናንን ለአገሬው የማታስተዋውቁና ተመሳሳይ ኃላፊነት የሌላችሁ ከሆነ፡ ባካችሁ ወደ አገራችሁ ቶሎ ተመልሳችሁ ነፍሳችሁን ከአውሬው ወጥመድ አድኑ
በ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ
የጥምቀት ዓይነት ልዩ ልዩ ነው፤ አማናዊ ጥምቀት ግን፡
-
በውሀ
-
በመንፈስ ቅዱስ
-
በሥቃይ
መጠመቅ ነው። (ሉቃ. 3፥16፣ 12፥50)
የዮሐንስ ጥምቀት ወደፊት የሚመጣውን ያመለክት ነበር (ማቴ. 3፥11-12)
—የክርስቲያን ጥምቀት የተፈጸመውን የክርስቶስን የአዳኝነት ሥራ ያሳስባል (ሮሜ. 6፥3-4)
—የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በበዓለ 50 ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተደረገ (የሐዋ. 1፥5፣ 2፥1-4)
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ምእመናን ሁሉ አንድ አካል እንዲሆኑ በመንፈስ ይጠመቃሉ። (1ቆሮ. 12፥13) “እለ ጥሙቃን በመንፈስ ቅዱስ” (ቀሌምንጦስ)
ክርስቶስ ሲጠመቅ መንፈስ ቅዱስ መውረዱ ለእኛ ጥምቀት ምስጢር ማስረጃ ነው። (ሉቃ. 3፥21-22፣ የሐዋ. 2፥38፣ ቲቶ. 3፥5)
የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የውሀን ጥምቀት ሊከተል ይችላል። (ዮሐ. 8፥4-17፣ 10፥44-48)
ጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ ያደርገናልና በዚህ መሠረት ከኅጢአት እንደ ተለየን ቈጥረን በአዲስ ሕይወት እንኖራለን (ሮሜ. 6፥1-11) የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 245 ተመልከት።
ጌታ እየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበት ዋና ምክንያት፦
-
በጥምቀቱ ጥምቀተ ክርስትናን ሊመሠርትልን
-
ውሀውን ሊባርክልንና ሊቀድስልን
-
ከእግዚአብሔር የመወለድን ጸጋ ሊያድለን
-
ስርየተ ኅጢአትን ሊሰጠን
-
ጽድቀ ተስብኦንና ትንቢተ ነቢያትን ሊፈጽም
Leave a Reply