Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • January 2013
  M T W T F S S
   123456
  78910111213
  14151617181920
  21222324252627
  28293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

ቅኝ አገዛዝ 2.0

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 13, 2013

Gebezenetበአውሮፓው ህብረት የአፍሪቃ ሞግዚት የሆነችው ፈረንሳይ፡ በመጀመሪያ ወደ አይቮሪኮስት ሰርጋ በመግባት የክርስቲያኑ ፕሬዚደንት ባግቦ መንግሥት ተገልብጦ በእስላሙ የዋታራ መንግሥት እንዲተካ አደረገች፤ ከዚያ ወደ ሊቢያ ከፍ ብላ ኮሎኔል ቀጣፊን ደብድባ ከገደለች በኋላ የእስላሞች መንግስት በትሪፖሊና ቤንጋዚ በጥቂት ሣምንታት ልዩነት እንዲቋቋም አስተዋጽኦ አበረከተች። ከዚያም ከአልጀሪያ ጋር በመተባበር፡ የአልጀሪያ፣ ሊቢያና ማሊ ትዋሬጎችን አሰባስባ ለረጅም ጊዜ ያዘጋጃቸውን አክራሪ እስላሞች ወደ ማሊ እንዲገቡ በማድረግ መሣሪያ እስከ አፍንጫቸው እያስታጠቀች ላከቻቸው። አክራሪ እስላሞቹ ልክ እንደ ባርነቱ ዘመን ለአፍሪቃውያኑ የአረብን የበላይነት ለማሳየት የማሊን ቀበለኛ አፍሪቃዊ የእስላም ሥልጣኔ የሚያንጸባርቁትን የሥነ ሕንፃ መታሰቢያዎቻቸውን አንድ ባንድ አፈራረሱ፡ የነበሩትንም ጥቂት ክርስቲያኖች ጨረሷቸው።  ፈረንሳይና ተባባሪዎቿ አረቦች በመቶ ዓመት ሊደረግ የማይቻለውን ጥፋት በአንድ ዓመት ውስጥ ለማድረስ ከተቻላቸው በኋላ፤ አሁን ፈረንሳይ እሳት አጥፊና የማሊ አዳኝ መስላ ወደ በረሃው ሠራዊቷን ላከች። ፕሮግራም የተደረጉት አፍሪቃውያንም ፈረንሳይ ከአክራሪ እስላሞች እንዳዳነቻቸው አድርገው በመውሰድ ‘ሲሳም ተከፈት!’ እያሉ በጭብጨባ ወደቦቻቸውን ለአውሮፓውያን መንግሥታት ክፍት ማድረግ ይጀምራሉ። ሌሎች አውሮፓውያን እንዲሁም አሜሪካ የኮምፒውተር ጨዋታዎቻቸውን ለመቀጠል አብረው ወደ ማሊ ይገባሉ፡ የዜና ማሰራጫዎቻቸውም የማታላል ቅመማቸውን እንደ ተለመደው ይነሰንሳሉ።

ከሁሉ የሚገርመው ግን፡ ወደ ሶማሊያ ሠራዊቶቻቸውን እንዲልኩ የኢትዮጵያን ተደጋጋሚ ጥሪ ለመቀበል ለዓመታት አሻፈረኝ ሲሉ የነበሩት ከንቱ ምዕራብ አፍሪቃውያን የፈረንሳይንና የአውሮፓውን ሕብረት ጥሪ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በመቀበል ሠራዊቶቻቸውን ወደ ማሊ ለመላክ ዝግጁ ማድረጋቸው ነው።

ይህ የአውሮፓውያን ጣልቃ ገብነት የሚያሳየን “ቅኝ አገዛዝ 2.0” መጀመሩን ነው፡ በባህሉና ስነልቦናው መስክ አፍሪቃውያኑን ለዘመናት ካሹ በኋላ እንደገና አፍሪቃን ለመጫረት በመዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ነው። ይህንም ተልዕኳቸውን ስኬታማ ለማድረግ እንደ ቀድሞው ብዙም መልፋት አይኖርባቸውም፡ በ እስልምና እና አክራሪ እስላሞች ዘንድ አንድ ጥሩ መሣሪያ አግኝተዋል፡ አሁን የፈልጉትን አፍሪቃዊት አገር ጽንፈኞቹን በመጠቀም ውስጣዊ ሁከት፣ የሕብረተሰብ መናጋት ወይም የእርስ በርስ መተላለቅን በቀላሉ መፍጠር ይችላሉ። ከዚያም የውጥንቅጥ ሊቆቹ ሰላማዊ አፍሪቃውያንን እናድናለን በማለት ሰተት ብለው በመግባት፤ የሚሰረቀውን እያታለሉ ይሰርቃሉ።

ይህን መሰሉን ስልት በአገራችን በኢትዮጵያም ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ዒላማዋቸውም ወደዚያ እንደሆነ እየተመለከትን ነው። በአፍሪቃው ቀንድ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ ናቸው። ቀደም ሲል ከኤርትራ ጋር የድንበር ግጭት እንዲፈጠር ተደርጎ በተባበሩ መንግሥታት ሥም ቁልፍ የሆኑ ቦታዎችን በመውሰድ በኢትዮጵያና/ኢትዮጵያ (‘ኤርትራ‘ አልልም) ግዛቶች ውስጥ የሉሲፈር ኃይሎች ሠፈሩ። ምን ሠርተው እንደሆነ እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው። ምንም እንኳን ኢ-ዓማንያን ቢሆኑም፡ “ኢትዮጵያ የዳዊትና የሰለሞን ዝርያዎች የሚኖሩባት ምድር ነች፡ እርሷን እንዳትደፍሩ!” የሚለውን ታሪካዊ የማስጠንቀቂያ ትዕዛዝ በፍራቻ በመጠበቅ፣ የሰለሞን ዝርያ ሳይሆኑ አይቀሩም፣ ሕያው የሙሴን ጽላት በውስጣቸው ሳይሸከሙ አይቀሩም ብለው የሚገምቷቸውን ቤተ-እስራኤላውያን አንድ ባንድ ከኢትዮጵያ በማስወጣት ኢትዮጵያን ለመድፈር በመዘጋጀት ላይ ይገኛሉ፤ ለዚህም አሁንም፡ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ኢትዮጵያዊነታቸውን በመካድ የወደቁትን ወገኖች እንዲሁም ጭንፈኛ አክራሪ እስላሞቹን እየተጠቀሙ ነው። መጨረሻ ጦርነቱና መተላለቁ በሁለቱ ከዳተኞች ጸረ-ክርስቶስ ኃይሎች መካከል እንደሚሆን እናያለን።

ሁሉ ነገር አለን፣ ሁሉንም እናውቃለን፣ ከጥቁር ሕዝቦች እንሻላለን የበላዮች ነን በማለት ራሳቸውን እንደ አምላክ እየቆጠሩ ያለአግባብ የሚክቡት እነዚህ ኃይሎች ቤታቸው ሞልቶ፡ ሆዳቸው ጠግቦ የሌላውን ነጥቆ ለመውሰድ ወደ ሩቅ አገራት እየሄዱ የስርቆት ልምዳቸውን ቀጥለውበታል። እንደ ኢትዮጵያ ያሉት አገሮች ግን የራሳቸውን አፈር አልምተው እንዳይመገቡ፣ እግዚአብሔር ያፈለቀላቸውን ውሃ ጠጥተው እንዳይኖሩ ይከለክላሉ።

የሆነ ሆኖ፡ ባፈለጋቸው መንገድ መልካቸውን እንደ እስስት እየቀያየሩ ቢመጡም ኢትዮጵያን ለማንበርከክ አይቻላቸውም፡ ዕቅዳቸውም ግቡን አይመታም ፣ የኢትዮጵያ አምላክ ይህችን ምስኪን አገር፡ ይህን እንደ በግ ሞኝ የሆነ ሕዝብ ይጠብቃልና። አምላካችን ጽላቱን በተናቁት በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ውስጥ ስለቀበረው፤ አውቀዋል፣ መጥቀዋል፣ ተራቀዋል የሚባሉት ግብዝ ሊቃውንቶቻቸው እንኳ ፈልፍለው ሊያገኙት አይቻላቸውም። እንዲያውም፣ በታሪክ፡ ከጥንት ጊዜ አንስቶ ከኢትዮጵያ (በአባይ በኩል?) እየተነሱ መላው አውሮፓን ሲያጥለቀልቁ የነበሩትን እንደ ወረርሽኝ የመሳሰሉትን የበሽታ መቅሰፍቶች እንደገና ይልክባቸዋል። አንማርም፣ ንስሐ አንገባም፡ አሻፈረን ከራስ በላይ ነፋስ በማለት ያለ ቅጥ የጠገቡትን የእግዚአብሔር ጠላቶች ሲቀጣ በኛ ትውልድ ለማየት እንደሚያበቃን አንጠራጠር፤ ጊዜው ሩቅ አይደለም።

በውኑ በኃጢአተኛ ቤት የኃጢአት መዝገብ፥ የተጸየፈም ውሽተኛ መስፈሪያ ገና አለ ይሆን? በአባይ ሚዛንና በከረጢት ባለ በተንኰል መመዘኛ ንጹሕ እሆናለሁን? ባለ ጠጎችዋን ግፍ ሞልቶባቸዋል፤ በእርስዋም የሚኖሩ በሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ ተንኰለኛ ነው። ስለዚህ እኔ ደግሞ በክፉ ቍስል መታሁህ፤ ስለ ኃጢአትህም አፈርስሁህ። ትበላለህ፥ ነገር ግን አትጠግብም፥ ችጋርህም በመካከልህ ይሆናል፤ ትወስዳለህ፥ ነገር ግን አታድንም፤ የምታድነውንም ለሰይፍ እሰጣለሁ። [ሚካ ምዕራፍ 6፥11-14]

_

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: