Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2012
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
    31  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for December 12th, 2012

Lalibela Among The World’s 9 best places to spend Christmas

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 12, 2012

CNN has picked nine of the most Christmassy places around the world.

Lalibela, Ethiopia

LalibelaMagicLalibela was conceived as a paradise on earth. And its 11 churches, cut from living volcanic rock, are literally anchored in the earth. In scale, number, and variety of form there’s no architecture or sculpture quite like them anywhere. They’re on the global tourist route now, though barely. To Ethiopian devotees they’ve been spiritual lodestars for eight centuries, and continue to be.

Declared a “new Jerusalem” after the real Jerusalem was captured by Muslim forces in 1187 and Ethiopian Christians could no longer go there, Lalibela remains a very religious place.

Ethiopian Christmas (January 7) mass at Bet Medhane Alem – the largest monolithic church in the world – is an occasion on which hundreds of priests in white turbans, adorned with red sashes and gold scarves chant, sway, and pray, surrounded by trenches flooded with some 50,000 worshipers, for whom this is a sacred place of pilgrimage.

See also: Five real life winter wonderlands

The other 8 destinations are:

  • Lapland, Finland

  • Strasbourg, France

  • Quebec, Canada

  • San Miguel de Allende, Mexico

  • Dyker Heights, Brooklyn, New York

  • Barcelona, Spain

  • Manila, Philippines

  • Queenstown, New Zealand

Source: CNN

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

US Sending 20 More F-16s to Egypt, Despite Turmoil in Cairo

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 12, 2012

Will they use them against the Grand Ethiopian Renaissance Dam on the River Nile?

F16Egypt

Instability in Egypt, where a newly-elected Islamic government teeters over an angry population, isn’t enough to stop the U.S. from sending more than 20 F-16 fighter jets, as part of a $1 billion foreign aid package.

The first four jets are to be delivered to Egypt beginning Jan. 22, a source at the naval air base in Fort Worth, where the planes have been undergoing testing, told FoxNews.com. The North African nation already has a fleet of more than 200 of the planes and the latest shipment merely fulfills an order placed two years ago. But given the uncertainty in Cairo, some critics wonder if it is wise to be sending more top gun planes.

“Should an overreaction [by Egypt] spiral into a broader conflict between Egypt and Israel, such a scenario would put U.S. officials in an embarrassing position of having supplied massive amounts of military hardware … to both belligerents,” said Malou Innocent, a foreign policy analyst at the Cato Institute. “Given Washington’s fiscal woes, American taxpayers should no longer be Egypt’s major arms supplier.”

The U.S. government ordered and paid for the fighter jets for Egypt’s military as part of foreign aid for Egypt back in 2010, when Hosni Mubarak ruled. The fighter jets were supposed to be delivered in 2013, and delivery will go ahead as scheduled even though Hosni Mubarak has been removed from power and replaced by Mohamed Morsi, who led the Muslim Brotherhood before becoming Egypt’s president.

Continue reading…

__

Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

በአታ ለማርያም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 12, 2012

ዛሬ ታህሣሥ የእመቤታችን ቅድስት ማርያም በዓል፤ በአታ ነው። በተጨማሪም የሊቀ መላእክ፡ የ ፋኑኤል ዕለት ታስቦ ይውላል። በፈረንጆቹም ዛሬ ሦስት ጊዜ 12/12/12 የቀን መቁጠሪያቸው ላይ አርፏል። እንኳን አደረሰን!

በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ

ሰይጣን በእባብ አካል ተሰውሮ ሔዋንን፤ በእርሱዋም አዳምን በማሳት በእነርሱ ላይ ሞት እንዲሠለጥንባቸው ስላደረገ “በአንተና በሴቲቱ መካከል፣ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደረጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኮናውን ትነድፋለህ” በማለት የፍቅር አምላክ እግዚአብሔር ፈረደበት፡፡ “በአንተ” የተባለው ሰይጣን ሲሆን፣ “በሴቲቱ” የተባለችው ቅድስት ድንግል ማርያም ናት (ገላ.44)፣ “በዘርህ” ሲል የዲያብሎስ የግብር ልጆችን ሲሆን(ዮሐ.849)፣ “በዘርዋ” የተባለው ክርስቶስ ነው(ገላ.316)፡፡ ትርጉሙ እንዲህ አንደሆነም ወንጌላዊው ዮሐንስ “ዘንዶው በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የጠበቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ”አለን፡፡(ራእ.1217) እባብ የተባለው ሰይጣን ስለመሆኑም “ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ”(ራእ.129) ብሎ ጻፈልን፡፡

አዳም በዚህ ፍርድ ቃል ምክንያት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ምን እንደሆነ ተረዳ፡፡ ስለዚህም እግዚአብሔር አምላክ በሔዋንና በእርሱ ላይ የፈረደው ፍርድ እነርሱን ከማዳን አንጻር የርኅራኄ ፍርድ እንደሆነ፤ እርሱና ሔዋን በክፉ ምርጫቸው ምክንያት ያጎሳቆሉትን ተፈጥሮአቸውን ወደ ቀደሞው ክብሩ ይመልሰው ዘንድ ንጽሕት ዘር ከሆነች ታናሽ ብላቴና እንደሚወለድና በመስቀሉ ሞት በእነርሱ ላይ የተላለፈውን የሞት ፍርድ እንደሚሽረው፣ አዳምና ሔዋን የተመኙትን የአምላክነት ስፍራ በክርስቶስ በኩል እንደሚያገኙት እንዲሁም በእርሱ የማዳን ሥራ የመለኮቱ ተካፋዮች እንዲሆኑ አስተዋለ፡፡ ይህም እውን እንደሚሆንም “አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ” በሚለው አምላካዊ ቃሉ አረጋገጠ፡፡ ስለዚህም ለመሰናከሉ ምክንያት የሆነችው ሴት ለትንሣኤውም ምክንያት እንደሆነች ተረዳ፡፡ በዚህም ምክንያት አስቀድሞ ከሥጋዬ ሥጋ ከአጥንቴ አጥንት የተገኘሽ ክፋዬ ነሽ ሲል “ሴት” ብሎ የሰየማትን ሚስቱን “ሔዋን” ብሎ ስም አወጣላት፡፡ ትርጓሜውም የሕያዋን ሁሉ እናት ማለት ነው፡፡ እንዲያ ባይሆንና አባታችን አዳም ይህንን የእግዚአብሔርን አሳብ ባይረዳ ኖሮ እንዴት በሰው ዘር ላይ ሞት እንዲሠለጥን ምክንያት ለሆነችው ሚስቱ ሔዋን የሚል ስምን ያወጣላት ነበር? ነገር ግን በእርሱዋ ሰብእና ውስጥ እርሱንና ወገኖቹን ከሞት ፍርድ ነጻ የሚያወጣቸውንና ወደ ቀደመው ክብራቸው የሚመልሳቸውን ጌታ በሥጋ የምትወልድ፣ የሕያዋን ሁሉ እናት የሆነች ንጽሕት ዘር እንዳለች ከእግዚአብሔር የፍርድ ቃል አስተዋለ፡፡

አዳም ይህን ሲረዳ ክፋዩ ለሆነች ሚስቱ ያለው ፍቅርና አክብሮት ከፊት ይልቅ ጨመረ፡፡ ከእርሱም በኋላ ለሚነሡ ወገኖቹም ለመዳናቸውና ለመክበራቸው ምክንያት ከሴት ወገን የሆነች ቅድስት ድንግል ማርያም እንደሆነ አስተውለው ወንዶች ለእናቶቻቸውና ለእኅቶቻቸው እንዲሁም ለሴት ልጆቻቸው ተገቢውን አክብሮትና ፍቅር እንዲያሳዩ ለማሳሰብ ሲልም ሚስቱን ሔዋን ብሎ መሰየሙንም መረዳት እንችላለን፡፡ እንዲህም ስለሆነ ነቢዩ ኢያሳይያስ “ዐይኖችን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃቸው ላይ ይሸከሟቸዋል”(ኢሳ.604)ብሎ ትንቢት ተናገረ፡፡ ቅድስት ድንግል ማርያም ራሱዋን የጌታ ቤተክርስቲያን በማድረግ፤ ቤተክርስቲያን በልጁዋ ክቡር ደም ተዋጅታ እንድትመሠረት ምክንያት ሆናለች፡፡ ስለዚህም አባታችን አዳም እንዳደረገው ነቢዩም እንደተናገረው ለእርሱዋ ያለንን ፍቅርና አክብሮት በጾታ ለሚመስሎአት እናቶቻችን፤ እኅቶቻችን፣ እንዲሁም ሴቶች ልጆቻችን በማሳየት እንገልጠዋለን፡፡

ከአዳም በኋላ የተነሡ ቅዱሳን አበው በአዳምና በሔዋን መተላለፍ ምክንያት በእነርሱ ላይ የሠለጠነባቸው ሞት የሚወገድላቸውና ወደ ገነት የሚገቡት እግዚአብሔር አምላክ ከቅድስት ድንግል ማርያም በመወለድ እንደሆነ ከአዳም አባታቸው ተምረው ነበር፡፡ ስለዚህም ከክርስቶስ የማዳን ሥራ ተካፋይ ለመሆን እሾኽና አሜካላ በምታበቅለውና ሰይጣን በሠለጠነባት በዚህ ምድር የመዳን ተስፋቸው የሆነችውን የቅድስት ድንግል ማርያምን መወለድ በተስፋ እየተጠባበቁ ቅዱስ ጳውሎስ “ማቅ፣ ምንጠፍና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፤ ተጨነቁ፣ ተቸገሩ፣ መከራ ተቀበሉ፣ ተራቡ፣ ተጠሙም፣ ዓለም የማይገባቸው እነዚህ ናቸው፤ዱር ለዱርና ፍርኩታ ለፍርኩታም ዞሩ”(ዕብ.1133-38) በጽድቅ ተጉ፡፡ ጌታችንም እንደተስፋ ቃሉ ከንጽሕት ቅድስት እናቱ ተወልዶ በመስቀል ላይ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ በመቅረብ ወደ ገነት አፈለሳቸው፡፡ ስለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዳ ጌታችንን መድኀኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እስክትወልድ ድረስ የተስፋ ቃሉ እንዳልተፈጸመ ለማስዳት ሲል ጨምሮ “እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጣቸውን የተስፋ ቃል አላገኙም፡፡ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ አግዚአብሔር ስለ እኛ የምትበልጠውን አስቀድሞ በይኖአልና፡፡” ማለቱ(ዕብ.1139-40)

አባቶቻችን ከሐዋርያት በትውፊት አግኝተው እንደጻፉልን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልክ እንደ ይስሐቅ፣ ነቢዩ ሳሙኤል እና መጥምቁ ዮሐንስ፣ መካን ከነበሩ ወላጆች የተገኘች ናት፡፡ እናቱዋ ሐና በአባቱዋ በኩል ከአሮን ቤት ስትሆን በእናቷ በኩል ከይሁዳ ወገን ነበረች፡፡ አባቱዋ ኢያቄም ግን ከይሁዳ ወገን ነበር፡፡ እነዚህ ወላጆች በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤ ነገር ግን ልክ እንደ አብርሃምና እንደ ሣራ እስከ እርጅናቸው ድረስ ልጅ አልወለዱም ነበር፡፡ በአይሁድ ዘንድ መካንነት የእርግማን ምልክት ተደርጎ ይወሰድ ስለነበር ኢያቄምና ሐና እግዚአብሔር አምላክ ልጅ በመስጠት ይህን ስድብ ያርቅላቸው ዘንድ በቅድስናና በንጽሕና በመጽናት ምጽዋትንም በማብዛት በጸሎት ይተጉ ነበር፡፡ ጸሎታቸውንና ምጽዋታቸውን እግዚአብሔር ስለተቀበለላቸው አምላክን በሥጋ በመውለድ ለዓለም መድኅን የሆነቸውን ቅድስት ድንግል ማርያምን በእርጅና ዘመናቸው ግንቦት አንድ ቀን ወለዷት፡፡ ማርያም ማለት የእግዚብሔር ስጦታ ማለት ነው፡፡ ሐናም እግዚአብሔር አምላክ ስድቤን ከእኔ አርቆልኛልና ከእግዚአብሔር እንዳገኘዋት ለእግዚአብሔር መልሼ እሰጣታለሁ ብላ የተሳለቸውን ስለት አሰበች፡፡ ሦስት ዓመት ሲሞላትም ስለቷን ትፈጽም ዘንድ ከኢያቄም ጋር ልጇን ቅድስት ድንግል ማርያም ይዛ ወደ ቤተመቅደስ አመራች፡፡ በጊዜው ሊቀ ካህናት የነበረው ካህኑ ዘካርያስም ሕዝቡን ሰብስቦ በታላቅ ደስታ ተቀበላቸው፡፡ ነገር ግን ካህኑን ዘካርያስን የምግብናዋ ነገር አሳስቦት ነበረና ሲጨነቅ ሳለ ነቢዩ ኤልያስን ይመግበው ዘንድ መልአኩን የላከ እግዚአብሔር አምላክ(1ነገሥ.196) እናቱ የምትሆነውን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይመግባት ዘንድ ሊቀ መላእክትን ቅዱስ ፋኑኤልን አዘዘላት፡፡ ካህኑ ዘካርያስም የምግቡዋ ነገር እንደተያዘለት ሲረዳ በቤተ መቅደስ ውስጥ እንድታድግ አደረጋት፡፡ ይህ እለት በሁሉም ኦሬንታልና የሐዋርያት የሥልጣን ተዋረድ(Apostolic succession) በተቀበሉ የሚታወቅና የሚከበር ክብረ በዓል ሲሆን በአታ ለማርያም ወይም የቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተመቅደስ መግባት በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህም “ልጄ ሆይ ስሚ፣ ጆሮሽንም አዘንቢዪ ወገንሽን ያባትሽንም ቤት እርሺ፤ ንጉሥ ውበትሽን ወድዶአልና፤ እርሱ ጌታሽ ነውና፡፡”(መዝ.4410) የሚለው ቃል መፈጸሙን እናስተውላለን፡፡

የጌታን መወለድ በተስፋ ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን አበው ይህች ቀን እጅግ ታላቅ እለት ነበረች፤ ምክንያቱም የመዳናቸው ቀን መቃረቧን የምታበሥር ቀን ነበረችና፡፡ ለእኛም ለክርስቲያኖች ይህች ቀን ታላቅ የሆነ በረከት ያላት ናት፡፡ ሙሴ የመገናኛ ድንኳኗንና በውስጡ ያሉትን ነዋያተ ቅዱሳት የጥጃና የፍየሎች ደምን ከውኃ ጋር በመቀላቅል በቀይ የበግ ጠጉርና በሂሶጵ በመንከር ረጭቶ ቀድሶአት ነበር፡፡(ዘጸ.247-8፤ዕብ.918-22) ንጉሥ ሰሎሞንም እርሱ ያሠራውን ቤተመቅደስ እርሱና ሕዝቡ ባቀረቡት የእንስሳት መሥዋዕት ቀደሷት ነበር፡፡(1ነገሥ.823) እነዚህ ሥርዐታት ግን ክርስቶስ በደሙ ለሚዋጃት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ነበሩ፡፡

በዚህች ቀን ቅድስት እናታችን ራሱዋን የጌታ ቤተ መቅደስ በማድረግ የብሉዩዋ ቤተመቅደስ ክርስቶስ በደሙ በዋጃት ቤተክርስቲያን ልትተካ መቃረቡዋን ለማብሠር ወደ ቤተ መቅደስ ያመራችበት ቀን ነው፡፡ ጌታችንም ከእርሱዋ የነሳውን ሥጋና ነፍስ በተዋሕዶ የራሱ ቤተመቅደስ በማድረግና እኛንም በጥምቀት የአካሉ ሕዋሳት እንድንሆን በማብቃት ሥጋችንን የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ ስለዚህም እኛ ክርስቲያኖች የቅድስት ድንግል ማርያምን ወደ ቤተመቅደስ መግባት ባሰብን ቁጥር እግዚአብሔር ቃል ከእርሱዋ በሥጋ በመወለዱ ያገኘነውን ድኅነትና ብዙ ጸጋዎችን እናስባለን፡፡ አሁን እኛ ክርስቲያኖች በጥምቀት ከእርሱዋ የተወለደውን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለብሰነዋል፤ (ገላ.327) ከእርሱዋ በነሣው ተፈጥሮ በኩል ሞትን በመስቀሉ ገድሎ ሲያስወግደው፣ እኛም በጥምቀት ከእርሱ ሞት ጋር በመተባበራችን ሞትን ድል የምንነሣበትን ኃይልን ታጥቀናል፡፡ በጥምቀት ያገኘነውን ጸጋ ሠርተንበትና አብዝተነው ብንገኝ ከትንሣኤው ተካፋዮች መሆንን እናገኛለን፡፡ ይህ ሁሉ የተፈጸመልን እግዚአብሔር ቃል ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ በመወለዱ ምክንያት ነው፡፡

ቅድስት ድንግል ማርያም ብሉይን ከአዲስ ያገኛኘች መንፈሳዊት ድልድይ ናት፡፡ በብሉይ ያሉት ቅዱሳን በሐዲስ ኪዳን ካለነው ጋር አንድ ማኅበር የፈጠሩትና ከቅዱሳን መላእክትም ጋር እርቅ የወረደው ከእርሱዋ በነሳው ሰውነት በኩል ነው፡፡ ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “እንግዲህስ ወዲህ እናንተ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም”(ኤፌ.219) ብሎ አስተማረ፡፡ ራሷን የጌታ ቤተ መቅደስ በማድረግ እኛንም በልጁዋ በኩል የመንፈሱ ቤተ መቅደስ እንድንሆን ምክንያት ሆናልናለችና የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተመቅደስ መግባት ለእኛ ክርስቲያኖች ልዩ ትርጉም አለው፤ ስለዚህም ይህቺን እለት በታላቅ ድምቀት እናከብራታለን፡፡

እግዚአብሔር አምላክ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም

ረድኤትና በረከት ያሳትፈን

ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: