Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • August 2012
  M T W T F S S
   12345
  6789101112
  13141516171819
  20212223242526
  2728293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

ሞኝነት እስከ መቼ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 23, 2012

    PS: Republished Post from July

መቅበጥበጥ ላይ የምትገኘዋ ቱርክ ከመቶ ዓመታት በኋላ እንደገና ወደ አፍሪቃው ቀንድ፡ ወደ ኢትዮጵያችን ጠጋ ጠጋ በማለት ላይ ትገኛለች። በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት (ራስ ተፈሪ/አፄ ኃይለሥላሴ አልጋወራሽ ነበሩ)በሐረር ከተማ እ...1910-1912 .ም ድረስ የኦቶማን ንጉሥ ነገሥት ግዛት በሐረር ከተማ አንድ ቆንሲል ከፍቶ ነበር። የዚህን ቆንሲል ህንፃ ያሁኗ ቱርክ ለማደስ ዝግጁ እንደሆነች ሰሞኑን አስታወቃለች። ከዚህ በተጨማሪ የእስላሞችን ነበይ የሙሀመድን ባላጋሮች በኢትዮጵያ ተቀብሎ ያስተናገዳቸውና በስህተትአልነጃሺየሚሉትን ክርስቲያን የኢትዮጵያ ንጉሥ ፡ አርማሕን ፡ እንዲሁም የሙሀመድን ባላጋሮች የሚያስታውሱ ሃውልቶች በትግራይ ውስጥ ለማቆም ከጥቂት ቀናት በፊት ከስምምነት ደርሳለች። ሕዝበ ዲያስፐራ ይህን ዜና በቸልተኝነት ማለፉ አሳሳቢ ነው!

የኢትዮጵያ ነገሥታት ከመጽሐፍ ቅዱስ የተማሩትን ክርስቲያናዊ ሥነምግባር በመከተል፤ ጻድቁ አብርሃምም እንግዳን የመቀበል ልማዱ እግዚአብሔርን ለመቀበል አብቅቶት ስለነበር፤ ኢትዮጵያውያን ለሚመጣው እንግዳው ሁሉ(ለጠላቶቻቸውም ጭምር)ተመሳሳይ አቀባበል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ሕዝባችን በእንግዳ ተቀባይነቱ ምናልባት የዓለም ቻምፒዮን ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ይህ በጐ ተግባር ብዙውን ጊዜ ከጥቅሙ ጉዳቱንና መዘዙን ነው ይዞብን የመጣው። ይህን እንግዳ ተቀባይነታችንን እንደሞኝነት አድርገው የቆጠሩት፤ ግብጾች፣ አረቦችና ቱርኮች አገራችንን በየጊዜው እየተተናኮሉ ለውድቀት እንድትጋለጥ አድርገዋታል። የማሽኮርመም ጥበቡን የተካነችው ቱርክ ታሪካዊ ጠላታችን ነች፤ እስከ መጥፊያዋ ጊዜም(ተቃርቧል)ወደድንም ጠላንም አደገኛ ጠላታችን ሆና ነው የምትቀርበን። በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፡ ግራኝ አህመድ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ የአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ ተስፋፍቶ የነበረው በቱርኮች ደጋፊነት ነበር። በ19ኛውም መቶ ክፍለዘመንም ቱርኮች ግብጾችንና የሱዳን መሀዲስቶችን በመደገፍ አያሌ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናትን አቃጠሉ፣ ሕዝቡን አረዱ፣ ቅርሶችን አወደሙ፣ ከዚህም አልፈው ለዐፄ ዮሐንስ ኅልፈት ምክንያት ሆኑ።

ታዲያ ይህን ሁሉ በደልና ጥፋት በሕዝባችን ላይ ደግመው ደጋግመው ሲያደርሱ የነበሩት ቱርኮች በንግሥት ዘውዲቱ ጊዜ እንዴት ቆንሲል በሐረር ከተማ ሊከፍቱ ቻሉ? በጊዜው ቱርክ በ አናቶሊያ ግዛቷ የሚኖሩትን አርመናውያን፣ ግሪኮችና አሹር ክርስቲያኖችን ለመጨፍጨፍ የተዘጋጀችበት ጊዜ ነበር። ባሁኑ ጊዜም በክርስቲያኖችና በኩርዶች ላይ ግልጽ የሆነ በደል በመፈጸም ላይ ናት። አሁን ቱርክ የምትባለዋ አገር የአርመኖችና የግሪኮች ምድር ናት ወደፊትም ትሆናለች። ቱርኮች ከመካከለኛው እስያ በወራሪነት እስከ ቁንጥንጥንያ ከመግባታቸው በፊት ቦታው የክርስትና ማዕከል ነበር። ታዲያ ባሁን ጊዜ የዚህን የክርስቲያናዊ ሥልጣኔ የሚያንጸባርቁትንና የ2ሺህ ዓመታት ያህል ታሪክ ያላቸውን ዓብያተ ክርስቲያናት፣ ገዳማትንና የትምሕርት ማዕከላት ለማደስ በቱርክ የቀሩት ጥቂት አርመኖችና ግሪኮች ፈጽሞ አይፈቀድላቸውም። አዲስ ቤተክርስቲያን መስራት ጭራሽ የማይታሰብ ጉዳይ ነው።

በአገራቸው ይህን ዓይነት ግልጽ ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚፈጽሙት ቱርኮች እንዴት ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የእስልምና ቅርሶችን እንዲያድሱ ፀረክርስቲያን የጥላቻ ትምህርት ቤቶችና ተቋማትን ለመሥራት ተፈቀደላቸው? ማን ነው ይህን ዕድል የሰጣቸው? ይህን የጥፋት በረከት ለቱርኮች የሰጠ በኢትዮጵያና በሕዝቧ ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸመ መሆኑን በኋላም እንደሚያስጠይቀውና እንደሚያስቀጣው አይገነዘብምን?

በጐረቤት አገር፤ በሶማሊያምየተራበውን የሶማሊያ ወንድማዊ ሕዝብ እንረዳለንበማለት ብዛት ያላቸው ቱርካዊ እርዳታ ሰጪዎች ወደ ሶማሊያ በመጉረፍ ላይ ይገኛሉ። ሁልጊዜ የመጀመሪያው መግቢያቸው በሶማሊያ በኩል ነው። አሁን የግራኝ መሀመድ መንፈስ እንደገና እየጠራቸው ይሆን? ከሃያ የጥፋትና የእልቂት ዓመታት በኋላ የሉሲፈር ዋና መሃንዲስ የሆነችውም እንግሊዝ ለሶማሊያ አሳቢ በመምሰል ስብሰባዎችን በመጥራት ላይ ናት። ለካውካስ ሕዝቦች በመቆርቆር በአፍጋኒስታንና ኢራቅ ከፍተኛ የገንዘብና የዲፕሎማሲ መስዋዕት የሚያደርጉትና የሚደሙት አውሮፓውያንና አሜሪካውያንም የሶማሊያ ነገርከእንቅልፋቸው የቀሰቀሳቸው ይመስላል አንድ ነገር ማድረግ አለብንበማለት ላይ ናቸው። ለመሆኑ ሶማሊያ ውስጥ ምን ተገኝቶ ይሆን? ወይስ ሌላ ያሰቡት ነገር አለ?

የሰሜኑ አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን(ኔቶ)አባል የሆነችው ቱርክ በዚህ በፍጻሜው ዘመን የጎግ ማጎግን ሚና ለመጫወት የተዘጋጀች አገር የሆነች ትመስላለች። ቱርክ፡ ልክ እንደ አረቦቹ አገራት፡ ዓለማችንን ወደ አንድ መንደር ለማምጣት ቆርጠው በተነሱት የምዕራባውያን ኃይሎች እየተረዳች ነው። ወደ ምዕራባውያኑ ዓለም ላለፉት 60 ዓመታት በብዛት ተሰደው የሚኖሩት ቱርኮች ለአገራቸው እድገትዓይነተኛ አስተዋጽኦ በማድረጋቸውም ገና ድህነት ላይ የምትገኘው ቱርክ፡ አለሁ አለሁ፤ ጠገብ ጠገብ በማለት ላይ ትገኛለች። ቱርክ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች ፈጽሞ ወዳጅ ልትሆን አትችልም። ቱርክ ለኢትዮጵያ ዲያብሎሳዊ ተልዕኮ እንዳላት ሁኔታዎቹ ሁሉ በግልጽ ያሳዩናል። አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያን ማንነት ለማጥፋት ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ዙሪያ የክፋት ድሯን በዝግታ በመጠንጠን ላይ ትገኛለች። የመጥፊያ ጊዜዋ የተቃረበው ቱርክ በየቦታው ብቅ ጥልቅ በማለት የሌላትን ጉልበት ለማሳያት ትሞክራለች፤ ባንድ በኩል እስራኤልን ትተናኮላለች፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከሱኒ እስልምናው ዓለም ጋር በማበር ፀረሺዓ የሆነ ትግል በኢራን፣ የመንና ሶርያ ላይ ታካሂዳለች። በቅርቡም ከ አዘርበጃን ጎን በመቆም በአርመኒያ ላይ ልትዘምት በመዘጋጀት ላይ ነች። በዓለም የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያን ሕዝቦች እንደሆኑ ለሚታወቁት አርመንያኖች እና ኢትዮጵያውያኖች ቱርኮች ታሪካዊ ጠላቶቻቸው ናቸው። አሁን ቱርክ ተብላ የምትታወቀው ግዛት የአርመንያኖች አገራቸው ነበረች። አርምንያኖች አሁን ልክ እንደ ኢትዮጵያ የባሕር መውጫ እንኳን የላቸውም። በነገራችን ላይ፣ 22ቱ የአረብ አገሮች፣ እንድያውም ከአፍጋኒስታን በስተቀር ሁሉም እስላም ነን የሚሉትና 54 የሚጠጉት አገሮች የባሕር አዋሳኝ ግዛት አላቸው። እንደ ኢትዮጵያና አርመኒያ የመሰሉት ሞኝ የክርስቲያን አገሮች ግን ያላቸውን ለጠላት እያስረከቡ በስቃይ ይኖራሉ። አይበቃንም? መቃድሹን እንኩ፣ በርበራን እንኩ፣ ጅቡቲን እንኩ፣ አሰብና ምጽዋን እንኩ፡ ውሰዱ እያለች ግዛቷን ለባዕድ ሸርሸረን በመስጠት በየጊዜው ተታለልን፡ አሁን ሁሉ ግልጽ ሆኖ በሚታይበት ዘመን ተመሳሳይ ስህተት (ኃጢአት)ስንሠራ ወደ እንስሳነት እንደተለወጥን ሆኖ አይሰማንምን?

ባሁኑ ጊዜ ባካባቢያችን እየተካሄደ ያለውን ሁኔታ በሚገባ አጠንቅቀን ልናገናዝብ ይገባናል። የኤርትራ ሁኔታ ቸል መባል የለበትም። በኢትዮጵያ ስም አንድ ሆነው በተፈጠሩ ሕዝቦች መካከል ልዩነት እንዲኖር ሰውሰራሽ የሆነው የጥላቻ መንፈስ የተገኘው ከዲያብሎስ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። ስለዚህ አጋንንታዊው የጎሰኝነት መንፈስ የፈጠረውንና ከያቅጣጫው የሚነዛውን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ መግታት ይኖርብናል። ከኤርትራ ጋር እንደገና አንድነት ፈጥሮ መኖሩ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዓላማ መሆን አለበት፣ እናንት እና እኛመባባሉ ጠላታችን ዲያብሎስን ብቻ ነው የሚጠቅመው። ሱዳን ለሁለት ተከፍላለች፣ ከደቡብ ሱዳን ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ሊኖረን ይገባል፡ እንዲያውም ሁለቱ ሕዝቦች ወደ ኮንፌደረሽን ደረጃ ለማምራት ቢበቁ የጠላቶቻቸው ዓላማ ሁሉ ከንቱ ይሆናል፣ ደቡብ ሱዳናውያንም ከዕልቂት ሰይፍ ይተርፋሉ። ቀይ ባሕርንም ተሻግሮ፤ የመን ውጥንቅጧ ይወጣል፤ እንደገና ለሁለት የመከፋፈል እጣ ይደርሳታል። የዲያብሎስ መዲናዋ ሳዑዲ ዓረቢያም ያልተጠበቀ የውጥንቅጥ ማዕበል ይዟት እንደሚሄድ እርግጠኛ ነኝ።

ከጥቂት ወራት በፊት አንድ የወታደሮች አሰልጣኝ አሜሪካዊ ፡ ሳዑዲ ዓረቢያን የተመለከተና አወዛጋቢ ሆኖ የተገኘ ትምህርታዊ መግለጫ ወታደራዊ በሆኑት የአሜሪካ ተቋማት ለማቅረብ በቅቶ ነበር። በዚህም መግለጫው ላይ፤ አሜሪካ ጦርነት ማካሄድ ያለባት ከ አክራሪ ጂሃዲስቶች ጋር ብቻ ሳይሆን ከእስልምና ጋርም መሆኑን ይጠቁማሉ። እንደሰውየው ከሆነ አሜሪካ መካና መዲናን ሙሉ በሙሉ ማውደም ይኖርባታል፤ ሳውዲ አረቢያም ለረሃብና ዕልቂት መጋለጥ አለባት፡ እንደሁኔታውም፡ በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን መቅጣት አማራጭ የሌለው እርምጃ ነው። ባጠቃላይ በጃፓኖቹ ሂሮሺማና ነጋሳኪ የተደረገው ዓይነት የአቶም ቦምብ ጥቃት በመካና መዲና መውረድ ይኖርበታል ያላሉ። ይህም በርግጥ በጣም ሊቀፈንና ሊረብሽን ይችል ይሆናል፡ እኔንም ረብሾኝ ነበር። ሙሉውን መልዕክት ለመመልከት እዚህች ይጫኑ

ነገር ግን ታሪክ እንደሚያስተምረን ይህ ላይ የቀረበው የጥቃት ፕላን ፈጠነም ዘገየም አንድ ቀን እንደሚፈጸም አንጠራጠር። የኒው ዮርኩ የመስከረም 11 ሽብርተኞች ሳውዲዎችና ግብጾች ነበሩ፡ ታዲያ ተመሳሳይ ጥቃት በአሜሪካ ምድር በድጋሚ የሚፈጸም ከሆነ አሜሪካ ሳውዲ ዓረቢያን ከምድረበዳው ሥር ለመቅበር እንደምትነሳ አንጠራጠር። እነዚህ አትኩሮት ፈላጊ የሆኑት የእስላም አገሮች እና አክራሪ እስላሞች አገራቸው ባልሆኑት አገሮች ሳይቀር ጠግበው በመፈንጠዝ ያዙን ልቀቁን በማለት ላይ ይገኛሉ፣ ባሁን ጊዜ ያላመሱትና ያልበጠበጡት የዓለም ክፍል የለም። መንግሥታቱና የዜና ማሰራጫዎቹ ለዘብ ያሉ ቢመስሉንም፡ ከአፍሪቃ እስከ እስያ፡ ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ ያሉ ሕዝቦች ትዕግስታቸው እያለቀና በመቆጣት ላይ ይገኛሉ። ከሰዶማውያን ቀጥሎ በዓለም ላይ የጥላቻ መርዛቸውን በመርጨት ላይ የሚገኙት የአክራሪ እስልምናው ተከታዮች ናቸው። እነዚህ እኛ ብቻ እንናገርባይ ኃይሎች አሁን ግድ ነው መታየት፣ መታወቅ ይኖርባቸዋልና ለዓለም ማህበረሰብ በፈቃዳቸው እራሳቸውን እያጋለጡ ነው፤ ከሁሉም የተለየ ልብስ በመልበስ፣ የተለየ መማሪያ ቦታ በመክፈት፣ የተለየ የጸሎትና የመመገቢያ ቦታ እንዲሰጣቸው በመጠየቀ እራሳቸውን ከሌላው በማግለል ላይ ይገኛሉ። ይህ አልበቃቸውም፣ የሌላውን መብት ሁሉ በመጋፋት፤ አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን በመሳደብ በማንቋሸሽ ላይ ናቸው። ኮፕት ክሪስትያኖችን ለመጨፍጨፍ እጆቹን በማሻሸት ላይ ያለው አዲሱ የግብጽ እስላማዊ መንግሥትም የእስልምና ጠበቃ በመሆን በኢትዮጵያ ላይ ተንኮሉን በፍጥነት ጀምሮታል። ሊንኩ ክርስቲያንና ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በካይሮ ሰልፍ ወጡ በኢትዮጵያ የሙስሊሞችን ጭቆና አወገዙ ይላል። ይህ በእንግሊዝኛው ‘projection’ የሚሉት ነገር ነው። ይታየን አዲስ አበባ ክርስቲያኑና ሙስሊሙ በአንድነት ወጥቶ በኮፕቶች ላይ የሚካሄደውን በደልና ግድያ ሲቃወም። ጨምላቆች! እባቡ መሪያቸው፡ ሙርሲ አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት ጥቁሩን ድንጋይ ለመሳለም፡ ዘይቱንም ለመቅመስ መጀመሪያ ወደ ሳውዲ ዓረቢያ ጎራ ማለት ግድ ነበረበት። (ፕሬዚደንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ባይመጡም ተመሳሳይ የሆነ ጉዞ መጀመሪያ በግብጽ ከዚያም በሳውዲ አረቢያ አድርገው ነበር።)

ባንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ሙስሊሞች ከአገሬው ተወላጅና ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር መጋጨቱን አዘውትረዋል። ሕንፃዎችን ያበላሻሉ፣ ፈረንጅ ያልሆኑትን ክርስቲያኖች በግልጽ ይሳደባሉ፣ ዓብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በሚገኘው የጠበል ውሃ ላይ ይተፋሉ፣ ይሸናሉ፤ ልጃገረዶችን በየመንገዱ እያስገደዱ ይደፍራሉ፤ በትውልድ አገሮቻቸው ደግሞ ክርስቲያኖችን፣ ሂንዱዎችን፣ ቡድሃውያንን ይገድላሉ የአምልኮ ቦታዎቻቸውንና ቤቶቻቸውን ያቃጥላሉ። ታዲያ ይህ ሁሉ እንደው ዝም እንደተባለ የሚቀጥል ይመስለናልን? በፍጹም፤ ለእነዚህ መዳንእምቢላሉ ሰዎች መጥፊያቸው እየተዘጋጀላቸው ነው። የሚጠፉትም ለአጭር ጊዜ ከነርሱ ጋር በመተባበር ሲረዷቸው በነበሩት ፀረክርስቶሳውያን የምዕራብ ኃይሎች አማካኝነት ነው። ሳውዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያ ታይቶ ከነበረው የረሃብ ቸነፈር የከፋ ስቃይ የምታይበት ጊዜ ሩቅ አይደልም፡ ያው ረሃቡም የመን ገብቶ ዳርዳር እያለ ነው፤ ፈጣሪ ይርዳቸው፡ ግን እንደ ኢትዮጵያ ረሃቡን ድል አድርገው ለማገገም የሚችሉ ሕዝቦች አይደሉም።

እየተራበች እየተጠማች ስደተኛውን ሁሉ እንደ ወንድሞቿና እህቶቿ፤ እንደ እናቶቿና እንደ አባቶቿ አድርጋ የምታስተናግደው ኢትዮጵያስ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር የመዘርጋት እድል ተሰጥቷታል፤ በትዕቢት የተወጠረችው፡ በነዳጅ ዘይት ገንዘብ የምትዋኘውና በኢትዮጵያውያን ላይ አስከፊ በደል የምትፈጽመው ሳውዲ ግን እጣዋ ሲዖል ካልሆነ ሌላ ሊሆን አይችልም።

የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት። ኢትዮጵያ የተባለች አንደኛ እናትህ ናት፣ ሁለተኛ ዘውድህ ናት፣ ሦስተኛ ሚስትህ ናት፣ አራተኛ ልጅህ ናት፣ አምስተኛ መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባድነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሣ።(አፄ ዮሐንስ ፬ኛ)

_______________________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: