Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • August 2012
  M T W T F S S
   12345
  6789101112
  13141516171819
  20212223242526
  2728293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

የ ማርያም ጠላቶች ዓይን ያወጣ ተንኮል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 3, 2012

ጀግናዋ እህታችን ቲኪ ገላና የኦሎምፒኩን ማራቶን በአስደናቂ ሁኔታ አሸናፊ ከሆነች በኋላ፤ የኢትዮጵያ አትሌቶች ድል ያልተዋጠላቸው አውሮፓውያን ኢትዮጵያን ማጥላላቱን ቀጠሉበት። አንድ ሪፖርት ስታቀርብ የነበረች የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ በሜዳሊያ አሰጣጥ ስነሥረዓት ወቀት፡ ድል ያደረገ ሰው እንደዚህ ኮራፋ ፊት አይኖረውም!” በማለት የቲኪን ድል ለማጣጣል ሞክራለች። ሌሎቹ ደግሞ፡ በድሃዋ ኢትዮጵያ አሁን ምግብ መግዢያ ገንዘብ ታገኛለችወይም እነዚህ አፍሪቃውያን የሆነ የዶፒንግ ቅመማቅመም ካልወሰዱ እንዴት እንዴት ሊሮጡ ቻሉ? ቲኪ ወድቃ እንኳን እኛ አውሮፓውያኑ ልናሸነፋት አልበቃንምይላሉ። በትርኪሚርኪ የስፖርት ዓይነት (የ ዋና ስፖርት ብቻ ብዛቱ ጉድ ነው፤ የደረት፣ የቢራቢሮ፣ የእንቁራሪት፣ የጀርባእንግዲህ ሩጫም፤ ወደኋላ እና ጎንበስ ብሎ በእጅና እገር መሮጥ እንደመጨር ማለት ነው) ብዙ ሚዳሊያ የሰበሰቡት ፈረንጆች፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለ6 ሚሊየን ሕዝብ አንድ የመዋኛ ቦታ ብቻ ስላለ፤ የዋና እስፖርት ላይ ለመሳተፍ አልቻሉም፤ ባጠቃላይ ድሃ ሰለሆኑ በብዙ የስፖርት ውድድሮች መሳተፍ አይችሉም፤ እኛ እንሻላለን፤ እኛ እንበልጣለን፣ እኛ ምርጦች ነንበማለት ሌላውን እያንቋሸሹ፡ እራሳቸውን ያታልላሉ። በ ኦሎምፒኩ የመጨረሻው ቀን፤ ልክ የወንዶች ማራቶን ውድድር እንደተጀመረ፤ የምስራቅ ዓፍሪቃን ድርቅና ረሃብ አስመልክቶ ኃይሌ ገ/ሥላሴና ሞፋራ የተሳተፉበት አንድ ስብሰባ ከእንግሊዙ ጠ/ሚኒስትር ጋር እየተደረገ እንደሆነ ቢቢሲ ቀኑን ሙሉ ሲለፍፍ ዋለ። ይህም ያለምክኒያት አይደለም። አሸናፊዎች ቢሆኑ ጥሩ ምንም መጥፎነት የለውም፤ ግን ታዲያ ስላሸነፉ ከመደሰት አልፈው፤ ለምንድን ነው ወደበላይነት፤ ሌላውን ዝቅ ወደማድረግና ማንቋሸሽነት የሚዘልቁት? እኛ ባገኘናት ድል ከመደሰት በቀር ሌላውን አናንቋሽሽም፡ ዝቅ አናደርግም፤ እንዲያውም ይባስ ብለው ባገኘናት ድል እንዳንደሰት ርካሽ የሆነ ሳይኮሎጂ በመጠቀም ሊያሽሟጥጡብን የሚሞክሩም እብዶች አሉ። እነርሱ ግን ባገኙት ድል በቂ ደስታ ስለማያገኙ ሌላውን ዝቅ በማድረግና በማንቋሸሽ ደስታን ለመግዛት ይሞክራሉ።

ይህ ሁኔታ ሊገርመን ብሎም ለመቀበል እስከሚያዳግተን አይይ! ሊያስብለን ይችላል፡ ነገር ግን ዓለማችንን በማበጣበጥ ላይ ያሉትና ለአጋንንት መንፈስ የተገዙት ፈረንጅ ዘረኞችና እስላም የበላይ ነው! ባዮች ጂሃዲስቶች እራሳቸውን ከፍ በማድረግና ሌላውን በማንቋሸሽ የሚጠቀሙባቸው የስነልቦናዊ ስልቶች አንድ ዓይነት ናቸው፤ ሁለቱን ቡድኖች የሚያገናኟቸው ብዙ ነገሮ አሉ፤ ለምሳሌ፤ ሁሌ እራሳቸውን ከፍ ከፍ ማድረግ፣ ጥፋታቸውን ለመቀበል ዝግጁ አለመሆናቸው፣ አትንገሩን! ባይነት፣ በራሳቸው አለመተማመን፣ የራሳቸውን ድክመት በሌላው ላይ መለጠፍ፣ ሃቅን ሸፋፍኖ በማለፍ በሌላው ላይ በደል መፈጸም፣ ሃቁን ለማውጣት የሚሞክረውን መኮነን ብሎም ማጥቃት፣ ወዘተደካሞች፡ ደካሞች! ይህችን ድርሰት ያንቡ.

ጥቁር አሜሪካዋ የጂምናስቲክ ጀግና ጋቢ ዳግላስ በከፍተኛ ችሎታ ሁለት የኦሎምፒክ ወርቆች ለአገሯ ካስገኘች ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ፤ ውድድሩን ሲያስተላልፍ የነበረው የአሜሪካ የቴሌቪዥን ጣቢያ (NBC) ዝንጆሮውን ጂምናስቲክ ሲሠራ የሚያሳይ የማስታወቂያ ፊልም ወዲያው አቀረበ። ይህን መሰሉን ድርጊትበቀላሉ ማየት አያስፈልግም፤ የስድብ መልዕክት ከማስተላለፉ ሌላ በፈረንጆች የስፖርት ዓለም ውስጥ ገብታ ለማሸነፍ የበቃችው ጥቁሯ አትሌት ተፈጥሮዋ እንደ ዝንጆሮ ከዛፍ ወደዛፍ መዝለል ነው፡ ስለዚህ ድሏ የኛን የበላይነት ዝቅ አያደርገውምየሚል ሥውራዊ መልዕክት ህሊናቸው ለታጠበባቸው የቴሌቪዥን ተመልካቾች ማስተላለፋቸው ነበር። በዚህ አላባቃም፡ ህሊናቸውን ለነጭ ርዕዮተዓለም የሰጡ ጥቁሮች ራሳቸው፡ የራሳቸውን ድንቅ ልጅ፡ ፀጉሯ አስቀያሚ ነውእያሉ ሲያንቋሽሿት ሰንብተው ነበር። ጋቢ በኋላ ላይ በተደረጉት የተናጠል ውድድሮች እንደገና ለማሸነፍ አለመቻሏ፡ እንዲያውም መጨረሻ መውጣቷ የዚህ ቆሻሻ የቅናት ዘመቻ ጉዳተኛ ለመሆን መብቃቷን ነው የሚያሳየው፤ እጅግ በጣም ያሳዝናል!

ባጠቃላይ ለነጮች ብቻ ተመድበዋል በሚባሉት የስፖርት ዓይነቶች፤ እንደነ ታታይገር ውስድ (ጎልፍ) የዊልያምስ እህትማማቾች (ቴኒስ) ፤ ሉዊስ ሃሚልተን (ሞተር ስፖርት) እንዲሁም በ ዋና እና በበረዶ የስፖርት ዓይነቶች ሁሉ ጥቁር ስፖርተኞች ብቅብቅ ማለታቸው አንዳንድ ፈረንጆችን በጣም እያስኮረፈ ነው። በአትሌቲክሱ ዓለምማ ባብዛኛው ጥቁሩ ለዘመናት የበላይነቱን ስላረጋገጠ አውሮፓዊው ተስፋ እየቆረጠ መጥቷል፤ አሁን ለንደን ላይ ነው እንጂ ተመልካቹ ስቴዲየሙን ሞልቶ የሚታየው በሌላ ጊዜማ ወደ ቢራ ቤት ለ ዳርትስፖርት የሚጎርፈው ተመልካች ከአትሌቲክሱ ይበዛል።

የፈረንጁን ዓለም በይበልጥ እልህ እያስያዘ የሚያናድዳቸው የስፖርት ዓይነት የረጅም ርቀት ሩጫ ነው። የረጅም ርቀት ሩጫ የግለሰቦችን ብሎም የሕዝቦችን ኢቮሊሽናዊ የበላይነትና ጥንካሬ ያሳያል ብለው ያምኑ ስለነበር ከጥቂት ዓመታት በፊት ጥቁር ለረጅም ርቀት ሩጫ ብቃት የለውም፡ እኛ ምርጦቹ ነጮች ነን የበላይነቱን የያዝነውየሚል ደረቅ ፍልስፍና ነበራቸው። በጊዜው የቼክ፣ የፊንላንድ፣ የእንግሊዝ ወይም የጣሊያን የረጅም ርቀት ሯጮች አሸናፊዎች ስለነበሩ። አሁን ግን ኢትዮጵያውያንና ኪኒያውያን የበላይነቱን ስለያዙ ፍልስፍናቸው ሁሉ ውድቅ ሆነ፣ ይህም አናደዳቸው። ጥቁር ሕዝቦች የበላይነቱን ስለያዙ እኛ እንበልጣለንእያሉ ሌላውን ሲያንቋሽሹ ተሰምቶም ታይቶም አይታወቅም። በ1968 የሚክሲኮው ኦሎምፒክስ ወቅት “Black power” ብለው እጆቻቸውን አንስተው የነበሩት ጥቁር አሜሪካውያን ሁኔታው የጊዜውን የአፓርታይድ ሥርዓት ጭቆና ያንጸባርቅ ስለነበር ነበር ለዚያ ያበቃቸው።

2012 .ም ግን ግሪኳ አትሌት ጣሊያኑ እግር ኳስ ተጨዋች ሲሠነዝሩት የነበረው ዘረኝነት የተሞላበት ስድብ ከበታቸኝነት ስሜት የመነጨ ነው። የፈረንጅ ሥልጣኔ ባጠቃላይ ከዚህ የበታቸኝነት ስሜት ፈልቆ የወጣ ሥልጣኔ ነው። ብዙ የሚደነቅ ነገር እንዳላቸው ሁሉ ለክፋት፣ ለሸርና ለጥፋት የሚያነሳሳ መንፈስም እንዳላቸው የሚታወቅ ነው። ስለዚህ ድሆቹንስፖርተኞቻችንን ከመተናኮል ወደኋላ አይሉም። ከሦስት በላይ የኢትዮጵያ አትሌቶች የጡንቻ ችግር ውስጥ መግባታቸው፤ ወንዶቹ ሯጮቻችን መደካከም፣ የኬኒያውያን ሯጮች ይህን ያህል መድከም ሊያሳስበንና እንድንጠራጠር ሊያደርገን ይገባል። የጡንቻ ህመም በምስራቅ አፍሪቃውያን ዘንድ ያልተለመደ ነው። የሶማሊያው ተወላጅ ሞ. ፋራም ኢትዮጵያውያኖችን ያዋርድ ዘንድ ተዘጋጅቶ የቀረበ የእንግሊዝ ዞምቢ ነው። እንግሊዝ ኢትዮጵያን በሁሉም መስክ ለመተናኮል ሶማሊያውያንና መሰሎቻቸውን ነው ሲጠቀሙ የቆዩት፣ አሁንም አዲስ ነገር አይኖርም። ታዝበን ከሆነ፤ ሞ. ፋራ ድሉን ከተቀዳጀ በኋላ ቀድሞ በመሄድ አቅፎት የነበረው ለ አዘርበጃን የሮጠውን ከዳተኛ ኢትዮጵያዊ ነበር፣ ኢትዮጵያውያኖቹን ግን ሰላምታ እንኳን ሊሰጥ አለመፈለጉ በግልጽ ይታይ ነበር።

በተረፈ፣ ውዲቷ አገራቸውን በመክዳት በተለይ አረብ ለሆኑ አገሮች የሚሮጡ ኢትዮጵያውያንእየበዙ መምጣታቸው በጣም አሳሳቢ ነው። እናት አባቶቻቸው የሰጧቸውን ስም በመቀየር ብሎም ኃይማኖታቸውን በመካድ ለኢትዮጵያ ጠላቶች የተሰለፉት ስፖርተኞች የሚጠብቃቸው ፍርድ ቀላል እንደማይሆን ማወቅ አለባቸው።

ገንዘቡ የሚመች ፍራሽ ሊገዛላቸው ይችል ይሆናል፤ ጥሩውን እንቅልፍ/ዕረፍት ግን አያገኙትም!

___________________________________

One Response to “የ ማርያም ጠላቶች ዓይን ያወጣ ተንኮል”

 1. Nesanet said

  I like all your analysis, but the statement you wrote on the last line is not true. No one wants to leave their own country/mother land, rather there is a problem. Do you know that how Ethiopian Athletics federation is corrupted.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: