Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • August 2012
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for August, 2012

ሞኝነት እስከ መቼ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 23, 2012

    PS: Republished Post from July

መቅበጥበጥ ላይ የምትገኘዋ ቱርክ ከመቶ ዓመታት በኋላ እንደገና ወደ አፍሪቃው ቀንድ፡ ወደ ኢትዮጵያችን ጠጋ ጠጋ በማለት ላይ ትገኛለች። በንግሥት ዘውዲቱ ዘመነ መንግሥት (ራስ ተፈሪ/አፄ ኃይለሥላሴ አልጋወራሽ ነበሩ)በሐረር ከተማ እ...1910-1912 .ም ድረስ የኦቶማን ንጉሥ ነገሥት ግዛት በሐረር ከተማ አንድ ቆንሲል ከፍቶ ነበር። የዚህን ቆንሲል ህንፃ ያሁኗ ቱርክ ለማደስ ዝግጁ እንደሆነች ሰሞኑን አስታወቃለች። ከዚህ በተጨማሪ የእስላሞችን ነበይ የሙሀመድን ባላጋሮች በኢትዮጵያ ተቀብሎ ያስተናገዳቸውና በስህተትአልነጃሺየሚሉትን ክርስቲያን የኢትዮጵያ ንጉሥ ፡ አርማሕን ፡ እንዲሁም የሙሀመድን ባላጋሮች የሚያስታውሱ ሃውልቶች በትግራይ ውስጥ ለማቆም ከጥቂት ቀናት በፊት ከስምምነት ደርሳለች። ሕዝበ ዲያስፐራ ይህን ዜና በቸልተኝነት ማለፉ አሳሳቢ ነው!

የኢትዮጵያ ነገሥታት ከመጽሐፍ ቅዱስ የተማሩትን ክርስቲያናዊ ሥነምግባር በመከተል፤ ጻድቁ አብርሃምም እንግዳን የመቀበል ልማዱ እግዚአብሔርን ለመቀበል አብቅቶት ስለነበር፤ ኢትዮጵያውያን ለሚመጣው እንግዳው ሁሉ(ለጠላቶቻቸውም ጭምር)ተመሳሳይ አቀባበል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ሕዝባችን በእንግዳ ተቀባይነቱ ምናልባት የዓለም ቻምፒዮን ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ይህ በጐ ተግባር ብዙውን ጊዜ ከጥቅሙ ጉዳቱንና መዘዙን ነው ይዞብን የመጣው። ይህን እንግዳ ተቀባይነታችንን እንደሞኝነት አድርገው የቆጠሩት፤ ግብጾች፣ አረቦችና ቱርኮች አገራችንን በየጊዜው እየተተናኮሉ ለውድቀት እንድትጋለጥ አድርገዋታል። የማሽኮርመም ጥበቡን የተካነችው ቱርክ ታሪካዊ ጠላታችን ነች፤ እስከ መጥፊያዋ ጊዜም(ተቃርቧል)ወደድንም ጠላንም አደገኛ ጠላታችን ሆና ነው የምትቀርበን። በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን፡ ግራኝ አህመድ ኢትዮጵያን በወረረ ጊዜ የአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ ተስፋፍቶ የነበረው በቱርኮች ደጋፊነት ነበር። በ19ኛውም መቶ ክፍለዘመንም ቱርኮች ግብጾችንና የሱዳን መሀዲስቶችን በመደገፍ አያሌ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናትን አቃጠሉ፣ ሕዝቡን አረዱ፣ ቅርሶችን አወደሙ፣ ከዚህም አልፈው ለዐፄ ዮሐንስ ኅልፈት ምክንያት ሆኑ።

ታዲያ ይህን ሁሉ በደልና ጥፋት በሕዝባችን ላይ ደግመው ደጋግመው ሲያደርሱ የነበሩት ቱርኮች በንግሥት ዘውዲቱ ጊዜ እንዴት ቆንሲል በሐረር ከተማ ሊከፍቱ ቻሉ? በጊዜው ቱርክ በ አናቶሊያ ግዛቷ የሚኖሩትን አርመናውያን፣ ግሪኮችና አሹር ክርስቲያኖችን ለመጨፍጨፍ የተዘጋጀችበት ጊዜ ነበር። ባሁኑ ጊዜም በክርስቲያኖችና በኩርዶች ላይ ግልጽ የሆነ በደል በመፈጸም ላይ ናት። አሁን ቱርክ የምትባለዋ አገር የአርመኖችና የግሪኮች ምድር ናት ወደፊትም ትሆናለች። ቱርኮች ከመካከለኛው እስያ በወራሪነት እስከ ቁንጥንጥንያ ከመግባታቸው በፊት ቦታው የክርስትና ማዕከል ነበር። ታዲያ ባሁን ጊዜ የዚህን የክርስቲያናዊ ሥልጣኔ የሚያንጸባርቁትንና የ2ሺህ ዓመታት ያህል ታሪክ ያላቸውን ዓብያተ ክርስቲያናት፣ ገዳማትንና የትምሕርት ማዕከላት ለማደስ በቱርክ የቀሩት ጥቂት አርመኖችና ግሪኮች ፈጽሞ አይፈቀድላቸውም። አዲስ ቤተክርስቲያን መስራት ጭራሽ የማይታሰብ ጉዳይ ነው።

በአገራቸው ይህን ዓይነት ግልጽ ኢሰብዓዊ ድርጊት የሚፈጽሙት ቱርኮች እንዴት ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የእስልምና ቅርሶችን እንዲያድሱ ፀረክርስቲያን የጥላቻ ትምህርት ቤቶችና ተቋማትን ለመሥራት ተፈቀደላቸው? ማን ነው ይህን ዕድል የሰጣቸው? ይህን የጥፋት በረከት ለቱርኮች የሰጠ በኢትዮጵያና በሕዝቧ ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸመ መሆኑን በኋላም እንደሚያስጠይቀውና እንደሚያስቀጣው አይገነዘብምን?

በጐረቤት አገር፤ በሶማሊያምየተራበውን የሶማሊያ ወንድማዊ ሕዝብ እንረዳለንበማለት ብዛት ያላቸው ቱርካዊ እርዳታ ሰጪዎች ወደ ሶማሊያ በመጉረፍ ላይ ይገኛሉ። ሁልጊዜ የመጀመሪያው መግቢያቸው በሶማሊያ በኩል ነው። አሁን የግራኝ መሀመድ መንፈስ እንደገና እየጠራቸው ይሆን? ከሃያ የጥፋትና የእልቂት ዓመታት በኋላ የሉሲፈር ዋና መሃንዲስ የሆነችውም እንግሊዝ ለሶማሊያ አሳቢ በመምሰል ስብሰባዎችን በመጥራት ላይ ናት። ለካውካስ ሕዝቦች በመቆርቆር በአፍጋኒስታንና ኢራቅ ከፍተኛ የገንዘብና የዲፕሎማሲ መስዋዕት የሚያደርጉትና የሚደሙት አውሮፓውያንና አሜሪካውያንም የሶማሊያ ነገርከእንቅልፋቸው የቀሰቀሳቸው ይመስላል አንድ ነገር ማድረግ አለብንበማለት ላይ ናቸው። ለመሆኑ ሶማሊያ ውስጥ ምን ተገኝቶ ይሆን? ወይስ ሌላ ያሰቡት ነገር አለ?

የሰሜኑ አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን(ኔቶ)አባል የሆነችው ቱርክ በዚህ በፍጻሜው ዘመን የጎግ ማጎግን ሚና ለመጫወት የተዘጋጀች አገር የሆነች ትመስላለች። ቱርክ፡ ልክ እንደ አረቦቹ አገራት፡ ዓለማችንን ወደ አንድ መንደር ለማምጣት ቆርጠው በተነሱት የምዕራባውያን ኃይሎች እየተረዳች ነው። ወደ ምዕራባውያኑ ዓለም ላለፉት 60 ዓመታት በብዛት ተሰደው የሚኖሩት ቱርኮች ለአገራቸው እድገትዓይነተኛ አስተዋጽኦ በማድረጋቸውም ገና ድህነት ላይ የምትገኘው ቱርክ፡ አለሁ አለሁ፤ ጠገብ ጠገብ በማለት ላይ ትገኛለች። ቱርክ እንደ ኢትዮጵያ ላሉ አገሮች ፈጽሞ ወዳጅ ልትሆን አትችልም። ቱርክ ለኢትዮጵያ ዲያብሎሳዊ ተልዕኮ እንዳላት ሁኔታዎቹ ሁሉ በግልጽ ያሳዩናል። አሁንም ቢሆን የኢትዮጵያን ማንነት ለማጥፋት ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ዙሪያ የክፋት ድሯን በዝግታ በመጠንጠን ላይ ትገኛለች። የመጥፊያ ጊዜዋ የተቃረበው ቱርክ በየቦታው ብቅ ጥልቅ በማለት የሌላትን ጉልበት ለማሳያት ትሞክራለች፤ ባንድ በኩል እስራኤልን ትተናኮላለች፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከሱኒ እስልምናው ዓለም ጋር በማበር ፀረሺዓ የሆነ ትግል በኢራን፣ የመንና ሶርያ ላይ ታካሂዳለች። በቅርቡም ከ አዘርበጃን ጎን በመቆም በአርመኒያ ላይ ልትዘምት በመዘጋጀት ላይ ነች። በዓለም የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያን ሕዝቦች እንደሆኑ ለሚታወቁት አርመንያኖች እና ኢትዮጵያውያኖች ቱርኮች ታሪካዊ ጠላቶቻቸው ናቸው። አሁን ቱርክ ተብላ የምትታወቀው ግዛት የአርመንያኖች አገራቸው ነበረች። አርምንያኖች አሁን ልክ እንደ ኢትዮጵያ የባሕር መውጫ እንኳን የላቸውም። በነገራችን ላይ፣ 22ቱ የአረብ አገሮች፣ እንድያውም ከአፍጋኒስታን በስተቀር ሁሉም እስላም ነን የሚሉትና 54 የሚጠጉት አገሮች የባሕር አዋሳኝ ግዛት አላቸው። እንደ ኢትዮጵያና አርመኒያ የመሰሉት ሞኝ የክርስቲያን አገሮች ግን ያላቸውን ለጠላት እያስረከቡ በስቃይ ይኖራሉ። አይበቃንም? መቃድሹን እንኩ፣ በርበራን እንኩ፣ ጅቡቲን እንኩ፣ አሰብና ምጽዋን እንኩ፡ ውሰዱ እያለች ግዛቷን ለባዕድ ሸርሸረን በመስጠት በየጊዜው ተታለልን፡ አሁን ሁሉ ግልጽ ሆኖ በሚታይበት ዘመን ተመሳሳይ ስህተት (ኃጢአት)ስንሠራ ወደ እንስሳነት እንደተለወጥን ሆኖ አይሰማንምን?

ባሁኑ ጊዜ ባካባቢያችን እየተካሄደ ያለውን ሁኔታ በሚገባ አጠንቅቀን ልናገናዝብ ይገባናል። የኤርትራ ሁኔታ ቸል መባል የለበትም። በኢትዮጵያ ስም አንድ ሆነው በተፈጠሩ ሕዝቦች መካከል ልዩነት እንዲኖር ሰውሰራሽ የሆነው የጥላቻ መንፈስ የተገኘው ከዲያብሎስ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል። ስለዚህ አጋንንታዊው የጎሰኝነት መንፈስ የፈጠረውንና ከያቅጣጫው የሚነዛውን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ መግታት ይኖርብናል። ከኤርትራ ጋር እንደገና አንድነት ፈጥሮ መኖሩ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዓላማ መሆን አለበት፣ እናንት እና እኛመባባሉ ጠላታችን ዲያብሎስን ብቻ ነው የሚጠቅመው። ሱዳን ለሁለት ተከፍላለች፣ ከደቡብ ሱዳን ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ሊኖረን ይገባል፡ እንዲያውም ሁለቱ ሕዝቦች ወደ ኮንፌደረሽን ደረጃ ለማምራት ቢበቁ የጠላቶቻቸው ዓላማ ሁሉ ከንቱ ይሆናል፣ ደቡብ ሱዳናውያንም ከዕልቂት ሰይፍ ይተርፋሉ። ቀይ ባሕርንም ተሻግሮ፤ የመን ውጥንቅጧ ይወጣል፤ እንደገና ለሁለት የመከፋፈል እጣ ይደርሳታል። የዲያብሎስ መዲናዋ ሳዑዲ ዓረቢያም ያልተጠበቀ የውጥንቅጥ ማዕበል ይዟት እንደሚሄድ እርግጠኛ ነኝ።

ከጥቂት ወራት በፊት አንድ የወታደሮች አሰልጣኝ አሜሪካዊ ፡ ሳዑዲ ዓረቢያን የተመለከተና አወዛጋቢ ሆኖ የተገኘ ትምህርታዊ መግለጫ ወታደራዊ በሆኑት የአሜሪካ ተቋማት ለማቅረብ በቅቶ ነበር። በዚህም መግለጫው ላይ፤ አሜሪካ ጦርነት ማካሄድ ያለባት ከ አክራሪ ጂሃዲስቶች ጋር ብቻ ሳይሆን ከእስልምና ጋርም መሆኑን ይጠቁማሉ። እንደሰውየው ከሆነ አሜሪካ መካና መዲናን ሙሉ በሙሉ ማውደም ይኖርባታል፤ ሳውዲ አረቢያም ለረሃብና ዕልቂት መጋለጥ አለባት፡ እንደሁኔታውም፡ በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ሙስሊሞችን መቅጣት አማራጭ የሌለው እርምጃ ነው። ባጠቃላይ በጃፓኖቹ ሂሮሺማና ነጋሳኪ የተደረገው ዓይነት የአቶም ቦምብ ጥቃት በመካና መዲና መውረድ ይኖርበታል ያላሉ። ይህም በርግጥ በጣም ሊቀፈንና ሊረብሽን ይችል ይሆናል፡ እኔንም ረብሾኝ ነበር። ሙሉውን መልዕክት ለመመልከት እዚህች ይጫኑ

ነገር ግን ታሪክ እንደሚያስተምረን ይህ ላይ የቀረበው የጥቃት ፕላን ፈጠነም ዘገየም አንድ ቀን እንደሚፈጸም አንጠራጠር። የኒው ዮርኩ የመስከረም 11 ሽብርተኞች ሳውዲዎችና ግብጾች ነበሩ፡ ታዲያ ተመሳሳይ ጥቃት በአሜሪካ ምድር በድጋሚ የሚፈጸም ከሆነ አሜሪካ ሳውዲ ዓረቢያን ከምድረበዳው ሥር ለመቅበር እንደምትነሳ አንጠራጠር። እነዚህ አትኩሮት ፈላጊ የሆኑት የእስላም አገሮች እና አክራሪ እስላሞች አገራቸው ባልሆኑት አገሮች ሳይቀር ጠግበው በመፈንጠዝ ያዙን ልቀቁን በማለት ላይ ይገኛሉ፣ ባሁን ጊዜ ያላመሱትና ያልበጠበጡት የዓለም ክፍል የለም። መንግሥታቱና የዜና ማሰራጫዎቹ ለዘብ ያሉ ቢመስሉንም፡ ከአፍሪቃ እስከ እስያ፡ ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ ያሉ ሕዝቦች ትዕግስታቸው እያለቀና በመቆጣት ላይ ይገኛሉ። ከሰዶማውያን ቀጥሎ በዓለም ላይ የጥላቻ መርዛቸውን በመርጨት ላይ የሚገኙት የአክራሪ እስልምናው ተከታዮች ናቸው። እነዚህ እኛ ብቻ እንናገርባይ ኃይሎች አሁን ግድ ነው መታየት፣ መታወቅ ይኖርባቸዋልና ለዓለም ማህበረሰብ በፈቃዳቸው እራሳቸውን እያጋለጡ ነው፤ ከሁሉም የተለየ ልብስ በመልበስ፣ የተለየ መማሪያ ቦታ በመክፈት፣ የተለየ የጸሎትና የመመገቢያ ቦታ እንዲሰጣቸው በመጠየቀ እራሳቸውን ከሌላው በማግለል ላይ ይገኛሉ። ይህ አልበቃቸውም፣ የሌላውን መብት ሁሉ በመጋፋት፤ አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን በመሳደብ በማንቋሸሽ ላይ ናቸው። ኮፕት ክሪስትያኖችን ለመጨፍጨፍ እጆቹን በማሻሸት ላይ ያለው አዲሱ የግብጽ እስላማዊ መንግሥትም የእስልምና ጠበቃ በመሆን በኢትዮጵያ ላይ ተንኮሉን በፍጥነት ጀምሮታል። ሊንኩ ክርስቲያንና ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በካይሮ ሰልፍ ወጡ በኢትዮጵያ የሙስሊሞችን ጭቆና አወገዙ ይላል። ይህ በእንግሊዝኛው ‘projection’ የሚሉት ነገር ነው። ይታየን አዲስ አበባ ክርስቲያኑና ሙስሊሙ በአንድነት ወጥቶ በኮፕቶች ላይ የሚካሄደውን በደልና ግድያ ሲቃወም። ጨምላቆች! እባቡ መሪያቸው፡ ሙርሲ አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት ጥቁሩን ድንጋይ ለመሳለም፡ ዘይቱንም ለመቅመስ መጀመሪያ ወደ ሳውዲ ዓረቢያ ጎራ ማለት ግድ ነበረበት። (ፕሬዚደንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ባይመጡም ተመሳሳይ የሆነ ጉዞ መጀመሪያ በግብጽ ከዚያም በሳውዲ አረቢያ አድርገው ነበር።)

ባንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ሙስሊሞች ከአገሬው ተወላጅና ከጸጥታ አስከባሪዎች ጋር መጋጨቱን አዘውትረዋል። ሕንፃዎችን ያበላሻሉ፣ ፈረንጅ ያልሆኑትን ክርስቲያኖች በግልጽ ይሳደባሉ፣ ዓብያተ ክርስቲያናት ውስጥ በሚገኘው የጠበል ውሃ ላይ ይተፋሉ፣ ይሸናሉ፤ ልጃገረዶችን በየመንገዱ እያስገደዱ ይደፍራሉ፤ በትውልድ አገሮቻቸው ደግሞ ክርስቲያኖችን፣ ሂንዱዎችን፣ ቡድሃውያንን ይገድላሉ የአምልኮ ቦታዎቻቸውንና ቤቶቻቸውን ያቃጥላሉ። ታዲያ ይህ ሁሉ እንደው ዝም እንደተባለ የሚቀጥል ይመስለናልን? በፍጹም፤ ለእነዚህ መዳንእምቢላሉ ሰዎች መጥፊያቸው እየተዘጋጀላቸው ነው። የሚጠፉትም ለአጭር ጊዜ ከነርሱ ጋር በመተባበር ሲረዷቸው በነበሩት ፀረክርስቶሳውያን የምዕራብ ኃይሎች አማካኝነት ነው። ሳውዲ ዓረቢያ በኢትዮጵያ ታይቶ ከነበረው የረሃብ ቸነፈር የከፋ ስቃይ የምታይበት ጊዜ ሩቅ አይደልም፡ ያው ረሃቡም የመን ገብቶ ዳርዳር እያለ ነው፤ ፈጣሪ ይርዳቸው፡ ግን እንደ ኢትዮጵያ ረሃቡን ድል አድርገው ለማገገም የሚችሉ ሕዝቦች አይደሉም።

እየተራበች እየተጠማች ስደተኛውን ሁሉ እንደ ወንድሞቿና እህቶቿ፤ እንደ እናቶቿና እንደ አባቶቿ አድርጋ የምታስተናግደው ኢትዮጵያስ እጆቿን ወደ እግዚአብሔር የመዘርጋት እድል ተሰጥቷታል፤ በትዕቢት የተወጠረችው፡ በነዳጅ ዘይት ገንዘብ የምትዋኘውና በኢትዮጵያውያን ላይ አስከፊ በደል የምትፈጽመው ሳውዲ ግን እጣዋ ሲዖል ካልሆነ ሌላ ሊሆን አይችልም።

የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት። ኢትዮጵያ የተባለች አንደኛ እናትህ ናት፣ ሁለተኛ ዘውድህ ናት፣ ሦስተኛ ሚስትህ ናት፣ አራተኛ ልጅህ ናት፣ አምስተኛ መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፣ የዘውድ ክብር፣ የሚስት ደግነት፣ የልጅ ደስታ፣ የመቃብር ከባድነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሣ።(አፄ ዮሐንስ ፬ኛ)

_______________________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያ ተከብባለች – አዎን ከሁሉም አቅጣጫ!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 23, 2012

P.S: Republished Post from June 2012

ያዝነው ዓመት መጀመሪያ ላይ ሳዑዲ አረቢያ በአገሯ የሚመረቱትን እህል እና አታክልት ወደ ውጭ እንዳይላኩ ከለከለች። በተለይ በሳዑዲ የሚመረት ድንች ወደ ውጭ እንዳይላክ ተከልክሏል። የተሰጠውም ምክኒያት ሳውዲ የውሃ ኃብት ይዞታዋን መንከባከብ ይገባታል የሚል ነው።

በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግሥታት የቀድሞው የምጣኔ ኃብት አማካሪ የነበሩትና ስዊዝራንዳዊ የማሕበረሰብ አጥኚ፡ አቶ Jean Ziegler ከአንድ የስፓኝ ራዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሳዑዲ አረቢያ ወደ ስዊዘርላንድ በኤክስፖርት መልክ አሁን የምትልካቸው ድንቾች ኢትዮጵያ ውስጥ የተመረቱ ናቸው ብለው ነበር። ከኢትዮጵያ በሳውዲ በኩል ወደ አውሮፓ ማለት ነው። የሳዑዲ ባለስልጣናትና ንጉሣን ቤተሰቦች ለህክምና ወደ ስዊዘርላንድ ይላካሉ፤ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ደግሞ በሳዑዲ አረቢያ ሆስፒታሎች የኢትዮጵያን ፍራፍሬዎች ጭማቂ ፉት እያሉ ይታከማሉ። አማካሪዎቹ እነማን ቢሆኑ ነው? የትኛውስ ጋኔን እየጠራቸው ይሆን? ከዚህ በፊት አንድ የማውቃቸው ሰውየ አዲስ አበባ መንገድ ላይ አገኘኋቸውና፤ እባክህ ልጄ ከውጭ አገር መድኃኒቱን ላክልኝአሉኝ። ደስ ይለኛል ግን መድኃኒቱ ባይፈውሰዎት እኔን እንዳይረግሙኝ፡ እዚህ እናንተ ጋር እኮ ሁሉም ነገር አለ፤ መድኃኒቱንም ቅዱሳን ተራራዎቻችን፤ አብያተክርስቲያኖቻችንና ገዳሞቻችን አጠገብ ያገኙታል፤ እስኪ ከጠበሏ ፉት ይበሉአልኳቸው። ወደጠበል እንደሄዱና ደህንነታቸውም እንደተመለሰላቸው ስሰማ በጣም ደስ አለኝ፤ እንኳን መድኃኒቱን አልላኩላቸው አልኩ። ለህክምና እያሉ ውጭ የወጡና ከፈውሱ ይልቅ በሽታ፡ ስቃይ ገዝተው የተመለሱና እድሜያቸውም ያጠረባቸው ብዙ ሰዎች አውቃለሁና። በርግጥ ዘመናዊ ህክምና አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ አለ።

የነዳጅ ዘይት ለመጀመሪያ ጊዜ ከምድር በብዛት ከመውጣቱ በፊት፡ በድህነትና በኋላቀርነት ለዘመናት በበረሃ ተከብበው ይኖሩ የነበሩት አረቦች ዱሮ በገንዘብና ምግብ እጥረት የተጋለጡ ነበሩ። ከሁሉ ይበልጥ እጥረታቸው በተለይ የውሃ ጥማት ነበር። እነዚህ የበረሃ ሕዝቦች ሌት ተቀን ስለ ውሃ ነበር ሲያስቡ የሚውሉት፤ በመጀመሪያ አረቢያን ለቀው እስከ ደቡብ አውሮፓ ድረስ ለብዙ የወረራ ጦርነቶች ያደፋፈራቸው የእስልምና እምነታቸው ብቻ ሳይሆን ውሃ ለማግኘት፣ የለማ ቦታ ለማየት ከፍተኛ ፍላጎትና ናፍቆት ሰለነበራቸው ነበር። ባጠቃላይ እንደ አረብ ውሃ የሚናፍቀው ሕዝብ በዓለም ላይ የለም።

ታዲያ ይህን የውሃ ጥማታቸውን እንዴት ማርካት ይችላሉ?

የነዳጅ ዘይት ተቆፍሮ ከመውጣቱ በፊት፡ የባትሪና ኤሌክትሪክ ጥበብ በቅድሚያ ተደርሶበት ነበር። በዘመናችን በቴክኖሎጂው ቀድመው ያደጉት አገሮችና ሕዝቦች ሞተሮቻቸውን፤ መኪናዎቻቸውን ገና ከመቶ ዓመታት በፊት፡ በባትሪና በኤሌክትሪክ ሃይል የማንቀሳቀስ ችሎታው ነበራቸው። የመጀመሪያዎቹ የኤሊክትሪክ መኪና በብዛት መሠራት በጀመሩበት ወቅት አንዳንድ በነዳጅ ዘይት የሚሠሩ መኪናዎችም እንደ አማራጭ ተደርገው ይመረቱ ነበር፤ ነገር ግን የሚገማ ጭሳቸው ተዋድጅነት ስላላገኘ፡ የኤሊክትሪክ (እለቄጥሩ) መኪናዎቹ (ሠረገላዎች) ይመረጡ ፤ በሰፊውም ተቀባይነት አግኝተው ነበር።

ይህ ዓይነቱ ሁኔታ ያላስደሰተው የሉሲፈር ቡድን ግን ዓለምን በዘይት ለማስከር፤ የእግዚአብሔርን ልጆች ጤንነት ለመጉዳት እንዲሁም ተፈጥሮን ለማበላሸትና ውሃ የተጠሙትን አረብ ልጆቹን ማገልገል ስለፈለገ በነዳጅ ዘይት የሚንቀሳቀሱትን መኪናዎችና ሞተሮች እውቀቱን ባካፈላቸው አውሮፓውያን በኩል እየተመረቱ እንዲወጡ አዘዘ። ስለመጀመሪያዎቹ ኤሊክትሪክ ሠረገላዎች እዚህች ላይ ይመልከቱ

ይህን የተገነዘቡት አረቦችም እየቆዩ ነቁ ተበረታቱ (አዎፓውያን አበረታቷቸው) ፤ ውሃ የሚያገኙበትንም ጎዳና መጥረግ ጀመሩ። ቆየት ብለውም እኛ ቆሻሻውን ጥቁር ውሃ፡ ዘይትን፡ ስለምናወጣ መጀመሪያ እረፍት የሌላቸውን ምዕራባውያንን በነዳጅ እናስክር፡ ከዚያ ዶላራቸውን እየተቀበልን በ ጎተራ እያስቀመጥን እንመዝብራቸው፡ ዘይቱ ይጣፍጣቸዋል፡ ያስከራቸውማል፡ በስካራቸው ላይም እንዳሉ፡ በጠበል ውሃ ኃብት የተካነችውን ኢትዮጵያን ለረሃብና ድህነት እንዲያጋልጡልን እንቆስቁሳቸው፡ ከዚያ ኢትዮጵያውያኑ ደክመው፣ ድኽይተው በረሃብ አለንጋ ሲገረፉ፡ እኛን ለመለመን ይገደዳሉ፣ ዶላር ናፈቀን ብለው እሱን ማምለክ ይጀምራሉ፣ ከዚያ ያዘጋጀናቸውን ልጆቻችንን ለስለስ፡ ሸልሸል ብለው ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ካደረግን በኋላ የተቀደሱትን የኢትዮጵያ የጠበል ውሃዎች መጥጠን እንጨርስባቸዋለን፤ ዱሮም ነብያችን ውሃው ሲጠማው የኢትዮጵያ አየር ሸቶት ነበር ሰላዮቹንም ወደኢትዮጵያ ተልከው እንዲሄዱ አድርጎ ነበር።ይላሉ።

የኢትዮጵያ ጠላቶች አገሪቷን ለመቆጣጠር ዳርዳር እያሉ ነው፡ የወረራውም ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ አገራችን ከባሕር እንድትነጠል ተደርጋለች፤ በኤርትራ የሚገኙት ልጆቿም እንዲያምጹ፡ ጥላቻ እንዲገዙ ተደርገዋል፤ በዚህም ምክኒያት አደገኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ምድር ሰላም ጠባቂ መስሎ ሰተት ብሎ በመግባት ሥራውን እየሰራ ነው፤ ባካባቢዋ የሚገኙትም አገሮች አንድ ባንድ በጠላቶቻችን እጅ ሥር በመግባት ላይ ናቸው፤ በአየር ላይም መንኮራኩሮቻቸው በተራቀቁ ሌንሶች ታጥቀዋል ወደ አገራችንም ላይ ካነጣጠሩ ውለው አድረዋል።

በተለይ አፍጋኒስታን ልክ የኢትዮጵያ ዓይነት ተራራማ የመልክዓምድራዊ ባሕርይ ስላላት ለወታደራዊ ልምምድ አመች ነች፤ የኔቶ ወታደሮችም ለኢትዮጵያ ወረራ የሚረዳቸውን ብዙ ልምድ በአፍጋኒስታን በመቅመስ ላይ ናቸው። የአረብ ጸደይ የሚል እንቅስቃሴ እንዲደረግ በመገፋፋት ደግሞ ውጭ የሚገኙ የሰሜን አፍሪቃና የመካከለኛው ምስራቅ ተወላጆች በምን ዓይነት መልክ መንግሥታቱን መገለባበጥ እንደሚችሉ አስፈላጊውን ልምድ በመቅሰም ላይ ናቸው፤ ውጭ የሚገኙ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ለዚህ ዓይነቱ ሉሲፈራዊ ዘመቻ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ በመዘጋጀት ላይ ይገኛሉ። እሽ፡ አሁን ሰሜን አፍሪቃ በነርሱ እጅ ገብታለች፣ ጅቡቲና ኬኒያ ሁልጊዜ የነርሱ ናቸው፤ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ሶማሊያና የመንም በቅርቡ ሙሉበሙሉ በነርሱ እጅ ይወድቃሉ፤ የዓለም ትኩረት በአፍጋኒስታን፣ ኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ፍልስጤምና ግብጽ ላይ ነው፤ ነገር ግን ትልቁ የሉሲፈር ዓይን ግን በኢትዮጵያ ላይ ነው ያረፈው።

ይህች ብዙ ምስጢር የተደበቃበት አገራችን ምን ያህል ድብቅ ኃብት እንደያዘች ለኛ ለሞኞቹ ነው እንጂ እስካሁን ያልተገለጥልን፣ ሉሲፈርማ ገና ድሮ ከአዳምና ሔዋን ጊዜ አንስቶ ነው ይህን ምስጢር ያውቅ የነበረው። አሁን የቴክኖሎጂ ነገር እጅግ እየተራቀቀ በመጣበት ዘመናችን የሉሲፈር ምርጥ ልጆች የምስጢሩ ተካፋዮች ለመሆን በቅተዋል ፤ በዓይኖቻችን ሊታዩ የማይቻሉትን አንዳንድ ረቂቅ ነገሮችንም ለማየት እየተቻላቸው ነው፤ ታይተው የማይታወቁ፡ እኛ መናፍስት የምንላቸውን ነገሮች ለመከታተል ችሎታውን እያገኙ ነው። ከዚህ ቀደም ይህን ጽሑፍ አቅርቤ ነበር፤ ይህ ቦታ የኢትዮጵያ ምስጢራት ከተደበቁባቸው ቦታዎች አይርቅም፤ እነዚህ ቦታዎች የኢትዮጵያን ብርቅ ገዳማት የሚያጠቃልል ነው። የሉሲፈር ሠራዊት ይህን ቦታ ቃኝቶ ደርሶበታል፣ የነካተሪናን አውሎ ነፋስ የሚቀሰቅሰው የእግዚአብሔር አምላክ እስትንፋሽ፣ ኃያሎቹ ቅዱሳናት ከሚገኙባቸው የኢትዮጵያ ተራራዎችና ገዳማት እንደሚፈልቅ ተገንዝበወታል።

የሉሲፈር ወገኖች ባወጡት ፕላናቸው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በረሃብና በሽታዎች እንዲደክምና እንዲዋረድ ይደረጋል፡ በኋላም ማንነቱን ለማወቅ ስለሚሳነው ፣ አገሩን እየለቀቀ መሰደድ ይጀምራል፣ በመጨረሻም አገሩን፣ ወገኑን፣ እራሱንም አሳልፎ እስከመሸጥ ይደርሳልየሚል ሃሳብ አላቸው። ይህንንም ዕቅዳቸውን አሁን በሥራ ላይ ለማዋል በመታገል ላይ ይገኛሉ። ግማሹ የሕዝባችን ክፍል አውቆም ሆነ ሳያውቅ ለአገሪቷ ጠላቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይሠራል፤ እነርሱንም በማገልገል ላይ ይገኛል፣ ገንዘብና ቁሳቁስ እንዲያፈቅር ተደርጓል፣ ሰይጣን ለ6ሺህ ዓመታት ያህል የተዋጋለትን ክቡር ነፍሡን ለሰይጣን አርበኞች አሳልፎ በመስጠት አንድ ቀን የማይቆየውን ጊዜአዊ እርካታ በመሸመት ላይ ይገኛል።

ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?” – ማር. 8 36 –

 በመጨረሻ ብዙ ተዓምር እንደምናይ፡ የኢትዮጵያ ጠላቶችም አንድ በአንድ እንደሚቀነጠሱ፡ ዓለምም ለመገረም እንደሚበቃ አንጠራጠር። አንመለስም፤ ንስሐ አንገባም ብለው የከበቡን ኃይሎች ውጊያውን የተያያዙት እጅግ በጣም ግዙፍ ከሆነውና ከማይሸነፈው ኃይል ጋር ነው።

_____________________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ወርቃማ መሠረቷ በተቀደሱት ተራሮች ላይ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 11, 2012

እንኳን ደስ ያለን እህት መሠረት ደፋር!

ድንቅ አሯሯጥ፣ ማርያማዊ የምስጋና አሰጣጥ ወቅት 

ስሜታዊ የሽልማት ስነሥርዓት

እንዳንቺ ለ5ሺ የለፋ ማን አለ!

በእመቤታችን የፍልሰታ ጾም ጸሎቷ ድሉን ሰጠሽ ፤ እንዳንች ላሰባት እጹብ ድንቅ ድል፤ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ብርታትን እንደምትሰጥ ለዓለም አስመሰከርሽ። የጥሩነሽም የመዳብ መዳይ ጥሩ ነው፤ በወርቅ ላይ መዳብ ወርቅ ነው።

እህታችንን አበባን ዲይብሎስ አታለላት፤ ከዳተኛዋን ጀማል ልኮ ፍዝዝ እንድትል አደረጋት ፣ በማርያም ስለቀናም ቱርኮቹን እንድትረዳ ጀማልን ፊቷ ላይ ቸክሎ ውዥንብር ፈጠረባት፤ ከ500 ሜትር በኋላ እባባዊ ተንኮሉ ግልጥ ብሎ ይታይ ነበር፤ የራሷን ፍጥነት ተከትላ መሮጥ ነበረባት። ግን ምንም አይደለም፡ ሌላ ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ትሞክራለች፡ ሌሎቻችሁ እንዳትታለሉ ሁልጊዜ ነቃ በሉ፡ ነገሮች ባጭር ጊዜ ውስጥ ሊለዋወጡ እንደሚችሉ ከዛሬው ጉድ ተማሩ፡ የእባብን መንሸላሸል እያያችሁ ሁልጊዜ ከበስተኋላችሁ እንዲቀር አድርጉ፡ ነገሩ ሩጫ ብቻ፡ ስፖርት ብቻ እንዳልሆነ ተገንዘቡ።

___________________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

The Ethiopians Tick The Clock Kenyans Count The Seconds

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 5, 2012

Well done, Tiki!

  • They Drop the bottle
  • You pick the bottle
  •  You win the Gold

What a powerful performance, what a demonstration of perseverance – even after 42Km and 2 ½ challenging running you still seem to have enough energy to celebrate big time with the crowd – that’s what I call the spirit of Abebe Bikila – the Ethiopian spirit.

The Gold is yours, the Olympic Record is yours (2:23:07) and the joy is ours.

The last women’s Olympic record is 2:23.14 set by Naoko Takahashi of Japan at the 2000 Games in Sydney.

 

 

 

 

 

 

 

 

 

_________________________________

 

 

Thank You, Tiki Gelana!!!

_________________________________

 

 

 

 

 

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

There Is Only One Tirunesh – Tirunesh Dibaba

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 4, 2012

What a stunning victory!

What a devastating performance!

What a lively atmosphere inside the stadium!

Congratulation, Tirunesh!

 

See Tirunesh Photo Album

________________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , | 1 Comment »

የ ማርያም ጠላቶች ዓይን ያወጣ ተንኮል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 3, 2012

ጀግናዋ እህታችን ቲኪ ገላና የኦሎምፒኩን ማራቶን በአስደናቂ ሁኔታ አሸናፊ ከሆነች በኋላ፤ የኢትዮጵያ አትሌቶች ድል ያልተዋጠላቸው አውሮፓውያን ኢትዮጵያን ማጥላላቱን ቀጠሉበት። አንድ ሪፖርት ስታቀርብ የነበረች የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ በሜዳሊያ አሰጣጥ ስነሥረዓት ወቀት፡ ድል ያደረገ ሰው እንደዚህ ኮራፋ ፊት አይኖረውም!” በማለት የቲኪን ድል ለማጣጣል ሞክራለች። ሌሎቹ ደግሞ፡ በድሃዋ ኢትዮጵያ አሁን ምግብ መግዢያ ገንዘብ ታገኛለችወይም እነዚህ አፍሪቃውያን የሆነ የዶፒንግ ቅመማቅመም ካልወሰዱ እንዴት እንዴት ሊሮጡ ቻሉ? ቲኪ ወድቃ እንኳን እኛ አውሮፓውያኑ ልናሸነፋት አልበቃንምይላሉ። በትርኪሚርኪ የስፖርት ዓይነት (የ ዋና ስፖርት ብቻ ብዛቱ ጉድ ነው፤ የደረት፣ የቢራቢሮ፣ የእንቁራሪት፣ የጀርባእንግዲህ ሩጫም፤ ወደኋላ እና ጎንበስ ብሎ በእጅና እገር መሮጥ እንደመጨር ማለት ነው) ብዙ ሚዳሊያ የሰበሰቡት ፈረንጆች፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ለ6 ሚሊየን ሕዝብ አንድ የመዋኛ ቦታ ብቻ ስላለ፤ የዋና እስፖርት ላይ ለመሳተፍ አልቻሉም፤ ባጠቃላይ ድሃ ሰለሆኑ በብዙ የስፖርት ውድድሮች መሳተፍ አይችሉም፤ እኛ እንሻላለን፤ እኛ እንበልጣለን፣ እኛ ምርጦች ነንበማለት ሌላውን እያንቋሸሹ፡ እራሳቸውን ያታልላሉ። በ ኦሎምፒኩ የመጨረሻው ቀን፤ ልክ የወንዶች ማራቶን ውድድር እንደተጀመረ፤ የምስራቅ ዓፍሪቃን ድርቅና ረሃብ አስመልክቶ ኃይሌ ገ/ሥላሴና ሞፋራ የተሳተፉበት አንድ ስብሰባ ከእንግሊዙ ጠ/ሚኒስትር ጋር እየተደረገ እንደሆነ ቢቢሲ ቀኑን ሙሉ ሲለፍፍ ዋለ። ይህም ያለምክኒያት አይደለም። አሸናፊዎች ቢሆኑ ጥሩ ምንም መጥፎነት የለውም፤ ግን ታዲያ ስላሸነፉ ከመደሰት አልፈው፤ ለምንድን ነው ወደበላይነት፤ ሌላውን ዝቅ ወደማድረግና ማንቋሸሽነት የሚዘልቁት? እኛ ባገኘናት ድል ከመደሰት በቀር ሌላውን አናንቋሽሽም፡ ዝቅ አናደርግም፤ እንዲያውም ይባስ ብለው ባገኘናት ድል እንዳንደሰት ርካሽ የሆነ ሳይኮሎጂ በመጠቀም ሊያሽሟጥጡብን የሚሞክሩም እብዶች አሉ። እነርሱ ግን ባገኙት ድል በቂ ደስታ ስለማያገኙ ሌላውን ዝቅ በማድረግና በማንቋሸሽ ደስታን ለመግዛት ይሞክራሉ።

ይህ ሁኔታ ሊገርመን ብሎም ለመቀበል እስከሚያዳግተን አይይ! ሊያስብለን ይችላል፡ ነገር ግን ዓለማችንን በማበጣበጥ ላይ ያሉትና ለአጋንንት መንፈስ የተገዙት ፈረንጅ ዘረኞችና እስላም የበላይ ነው! ባዮች ጂሃዲስቶች እራሳቸውን ከፍ በማድረግና ሌላውን በማንቋሸሽ የሚጠቀሙባቸው የስነልቦናዊ ስልቶች አንድ ዓይነት ናቸው፤ ሁለቱን ቡድኖች የሚያገናኟቸው ብዙ ነገሮ አሉ፤ ለምሳሌ፤ ሁሌ እራሳቸውን ከፍ ከፍ ማድረግ፣ ጥፋታቸውን ለመቀበል ዝግጁ አለመሆናቸው፣ አትንገሩን! ባይነት፣ በራሳቸው አለመተማመን፣ የራሳቸውን ድክመት በሌላው ላይ መለጠፍ፣ ሃቅን ሸፋፍኖ በማለፍ በሌላው ላይ በደል መፈጸም፣ ሃቁን ለማውጣት የሚሞክረውን መኮነን ብሎም ማጥቃት፣ ወዘተደካሞች፡ ደካሞች! ይህችን ድርሰት ያንቡ.

ጥቁር አሜሪካዋ የጂምናስቲክ ጀግና ጋቢ ዳግላስ በከፍተኛ ችሎታ ሁለት የኦሎምፒክ ወርቆች ለአገሯ ካስገኘች ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ፤ ውድድሩን ሲያስተላልፍ የነበረው የአሜሪካ የቴሌቪዥን ጣቢያ (NBC) ዝንጆሮውን ጂምናስቲክ ሲሠራ የሚያሳይ የማስታወቂያ ፊልም ወዲያው አቀረበ። ይህን መሰሉን ድርጊትበቀላሉ ማየት አያስፈልግም፤ የስድብ መልዕክት ከማስተላለፉ ሌላ በፈረንጆች የስፖርት ዓለም ውስጥ ገብታ ለማሸነፍ የበቃችው ጥቁሯ አትሌት ተፈጥሮዋ እንደ ዝንጆሮ ከዛፍ ወደዛፍ መዝለል ነው፡ ስለዚህ ድሏ የኛን የበላይነት ዝቅ አያደርገውምየሚል ሥውራዊ መልዕክት ህሊናቸው ለታጠበባቸው የቴሌቪዥን ተመልካቾች ማስተላለፋቸው ነበር። በዚህ አላባቃም፡ ህሊናቸውን ለነጭ ርዕዮተዓለም የሰጡ ጥቁሮች ራሳቸው፡ የራሳቸውን ድንቅ ልጅ፡ ፀጉሯ አስቀያሚ ነውእያሉ ሲያንቋሽሿት ሰንብተው ነበር። ጋቢ በኋላ ላይ በተደረጉት የተናጠል ውድድሮች እንደገና ለማሸነፍ አለመቻሏ፡ እንዲያውም መጨረሻ መውጣቷ የዚህ ቆሻሻ የቅናት ዘመቻ ጉዳተኛ ለመሆን መብቃቷን ነው የሚያሳየው፤ እጅግ በጣም ያሳዝናል!

ባጠቃላይ ለነጮች ብቻ ተመድበዋል በሚባሉት የስፖርት ዓይነቶች፤ እንደነ ታታይገር ውስድ (ጎልፍ) የዊልያምስ እህትማማቾች (ቴኒስ) ፤ ሉዊስ ሃሚልተን (ሞተር ስፖርት) እንዲሁም በ ዋና እና በበረዶ የስፖርት ዓይነቶች ሁሉ ጥቁር ስፖርተኞች ብቅብቅ ማለታቸው አንዳንድ ፈረንጆችን በጣም እያስኮረፈ ነው። በአትሌቲክሱ ዓለምማ ባብዛኛው ጥቁሩ ለዘመናት የበላይነቱን ስላረጋገጠ አውሮፓዊው ተስፋ እየቆረጠ መጥቷል፤ አሁን ለንደን ላይ ነው እንጂ ተመልካቹ ስቴዲየሙን ሞልቶ የሚታየው በሌላ ጊዜማ ወደ ቢራ ቤት ለ ዳርትስፖርት የሚጎርፈው ተመልካች ከአትሌቲክሱ ይበዛል።

የፈረንጁን ዓለም በይበልጥ እልህ እያስያዘ የሚያናድዳቸው የስፖርት ዓይነት የረጅም ርቀት ሩጫ ነው። የረጅም ርቀት ሩጫ የግለሰቦችን ብሎም የሕዝቦችን ኢቮሊሽናዊ የበላይነትና ጥንካሬ ያሳያል ብለው ያምኑ ስለነበር ከጥቂት ዓመታት በፊት ጥቁር ለረጅም ርቀት ሩጫ ብቃት የለውም፡ እኛ ምርጦቹ ነጮች ነን የበላይነቱን የያዝነውየሚል ደረቅ ፍልስፍና ነበራቸው። በጊዜው የቼክ፣ የፊንላንድ፣ የእንግሊዝ ወይም የጣሊያን የረጅም ርቀት ሯጮች አሸናፊዎች ስለነበሩ። አሁን ግን ኢትዮጵያውያንና ኪኒያውያን የበላይነቱን ስለያዙ ፍልስፍናቸው ሁሉ ውድቅ ሆነ፣ ይህም አናደዳቸው። ጥቁር ሕዝቦች የበላይነቱን ስለያዙ እኛ እንበልጣለንእያሉ ሌላውን ሲያንቋሽሹ ተሰምቶም ታይቶም አይታወቅም። በ1968 የሚክሲኮው ኦሎምፒክስ ወቅት “Black power” ብለው እጆቻቸውን አንስተው የነበሩት ጥቁር አሜሪካውያን ሁኔታው የጊዜውን የአፓርታይድ ሥርዓት ጭቆና ያንጸባርቅ ስለነበር ነበር ለዚያ ያበቃቸው።

2012 .ም ግን ግሪኳ አትሌት ጣሊያኑ እግር ኳስ ተጨዋች ሲሠነዝሩት የነበረው ዘረኝነት የተሞላበት ስድብ ከበታቸኝነት ስሜት የመነጨ ነው። የፈረንጅ ሥልጣኔ ባጠቃላይ ከዚህ የበታቸኝነት ስሜት ፈልቆ የወጣ ሥልጣኔ ነው። ብዙ የሚደነቅ ነገር እንዳላቸው ሁሉ ለክፋት፣ ለሸርና ለጥፋት የሚያነሳሳ መንፈስም እንዳላቸው የሚታወቅ ነው። ስለዚህ ድሆቹንስፖርተኞቻችንን ከመተናኮል ወደኋላ አይሉም። ከሦስት በላይ የኢትዮጵያ አትሌቶች የጡንቻ ችግር ውስጥ መግባታቸው፤ ወንዶቹ ሯጮቻችን መደካከም፣ የኬኒያውያን ሯጮች ይህን ያህል መድከም ሊያሳስበንና እንድንጠራጠር ሊያደርገን ይገባል። የጡንቻ ህመም በምስራቅ አፍሪቃውያን ዘንድ ያልተለመደ ነው። የሶማሊያው ተወላጅ ሞ. ፋራም ኢትዮጵያውያኖችን ያዋርድ ዘንድ ተዘጋጅቶ የቀረበ የእንግሊዝ ዞምቢ ነው። እንግሊዝ ኢትዮጵያን በሁሉም መስክ ለመተናኮል ሶማሊያውያንና መሰሎቻቸውን ነው ሲጠቀሙ የቆዩት፣ አሁንም አዲስ ነገር አይኖርም። ታዝበን ከሆነ፤ ሞ. ፋራ ድሉን ከተቀዳጀ በኋላ ቀድሞ በመሄድ አቅፎት የነበረው ለ አዘርበጃን የሮጠውን ከዳተኛ ኢትዮጵያዊ ነበር፣ ኢትዮጵያውያኖቹን ግን ሰላምታ እንኳን ሊሰጥ አለመፈለጉ በግልጽ ይታይ ነበር።

በተረፈ፣ ውዲቷ አገራቸውን በመክዳት በተለይ አረብ ለሆኑ አገሮች የሚሮጡ ኢትዮጵያውያንእየበዙ መምጣታቸው በጣም አሳሳቢ ነው። እናት አባቶቻቸው የሰጧቸውን ስም በመቀየር ብሎም ኃይማኖታቸውን በመካድ ለኢትዮጵያ ጠላቶች የተሰለፉት ስፖርተኞች የሚጠብቃቸው ፍርድ ቀላል እንደማይሆን ማወቅ አለባቸው።

ገንዘቡ የሚመች ፍራሽ ሊገዛላቸው ይችል ይሆናል፤ ጥሩውን እንቅልፍ/ዕረፍት ግን አያገኙትም!

___________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , | 1 Comment »

የ አውሮፓ–አሜሪካና የ ዐረቦች ጥፋታዊ ኅብረት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 1, 2012

በምድር ላይ የመጨረሻዋ መንግሥት ዋነኛዎቹ አስር አገሮች

አውሮፓ በአራት መንግሥታት ነበር የተነሣችው

አዉሬይቱ አስር ቀንዶችም ነበሯት።

አውሬይቱ አውሮፓ፣ አስሩ ቀንዶች፦ አስር ኃያላን ተዋጊ መንግሥታቷ ናቸው።

አሁኑ መልክና ስም የምናውቃቸው የአውሮፓውያን መንግሥታት አገሮች በአንድ ጊዜ ይህንን ቅርጽና ስም በትክክል አልያዙም። አሁን ያሉበት የሀገር ቅርጽና የሚጠሩበትን ስሞች ለመያዝ ከመካከለኛው ዘመን ጀምሮ እስከ 19ኛውና እስከ 20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ድረስ ፈጅቷል።

በረጅም የታሪክ ዘመን ውስጥ እንኳንስ የአገሮችን የአንድን አገር ትክክለኛ ክልልና ስም ወስኖ ለመናገር በጣም ከባድ ነው።

ለምሳሌ ሲጀመር ኢትዮጵያ ተብላ የተጠራችው አገር ኩሽ በመባል የታወቀች ሳለች መካከላዊ መነሻዋ የግዮን መፍለቂያ ቆላ ደጋ ዳሞት፥ ሰከላ፤ ቅርጽዋም ግዮን (አባይ) ወንዝ የሚከበው መሪት አሁን ጎጃም የምትባለው ክፍለ ሀገር እንደ ነበረች በግልጥ ተቀምጧል። (ዘፍ.213) በኋላም ሕዝቡ መንቀሳቀስ ሲጀምርና በየአቅጣጫው ሲሄድ አሁን ሱዳን የምትባለው ኑቢያ እስከ ደቡብ ግብጽ ድረስ ሁሉም የኢትዮጵያ ክልል እንደነበሩ ይታወቃል። ግብጽ በኢትዮጵያ ድንበርተኝነት በኢሳያስ 203 በሕዝ. 29-10 ተመዝግቦ እናያለን። እስከ ኢርትራ፣ ጂቡት፣ ሶማሊያ ሁሉ የኢትዮጵያ ግዛቶች ነበሩ።

ታዲያ በምድር ላይ ያሉ አገሮች ሁሉ እንዲሁ በብዙና በተለያዩ ምክንያቶች የተወሰነና ቋሚ ቅርጽና ስም ይዘው አልኖሩም።

በትክክል አዉሮፓን አዉሮፓ ያሰኙዋትና ተግባራቸውንም ማከናወናቸውን ግልጽ ያደረገው በ1941 .ም የአቋቋሙት የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን አገሮች፦ የ

1. እንግሊዝ

6. ዴንማርክ

2. ፈረንሳይ

7. አይስላንድ

3. ቤልጂየም

8. ኢጣሊያ

4. ኔዘርላንዶች

9. ኖርዌና

5. ሉክሰንበርግ

10. ፖርቱጋል

ሕብረት ነው።

ካናዳና የተባበሩት የአሜሪካ ክፍለ ግዛቶች (USA) አባል ቢሆኑም የአውሮፓ ማሕበረሰብ ስለአይደሉ አይካተቱም። የአባላቱ ቅደም ተከተልነት አስፈላጊ ነው፤ ምክኒያቱም በዓለማችን ላይ ለሚደረጉት አውሮፓዊ ተጽዕኖዎች ሁሉ የመሪነቱን ሚና የምትጫወተው በእንግሊዝ የምትተዳደረዋ ታላቋ ብሪታኒያ ነች።

አሜሪካ = እንግሊዝ

ካናዳ = ስኮትላንድ

አውስትራሊያ / ኒውዚላንድ = አየርላንድና ዌልስ

መሆናቸው ነው። 

በምድር ላይ ባሁኑ ጊዜ ተንሠራፍቶ የሚታየው የፓለቲካ፣ የኅይማኖት፣ የባህል እንዲሁም የምጣኔ ኅብት ችግር ሁሉ የተፈጠረው በእንግሊዝ (ታላቋ ብሪታኒያ) ቆሽቋሽነት ነው። ታላቋ ብሪታኒያ ግዛቶቿን በአንድነት ለመያዝና የተቀረውንም ዓለም ለመቆጣጠር ያመቻት ዘንድ በጣም ጠንካራና በሕዝቦቿ ዘንድ ተቀባይነት ያላትን የንጉሣዊ ሥርዓት ትንከባከባልች፤ እንደ ኢትዮጵያ ባሉት አገሮች ግን የንጉሣዊ ሥርዓታት እልም ብለው እንዲጠፉ ከፍተኛ ሚና ትጫወታለች/ተጫውታለች። ልብ ብለን ከታዘብን፤ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን እንድትወር ከወረረችም በኋላ የዓለም ማሕበረስብ ወረራውን እንዳያወግዝ ያደረገችው እንግሊዝ ነበረች። በዚህ ወቅት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በእንግሊዟ ሳውዝሃምፕተን ጥገኝነት አግኝተው በኢትዮጵያ የብዙ ሺህ ዓመታቱን የነገሥታት ሥርዓትን ለመገርሰስ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ፀረንጉሣዊ ተል ዕኳዋን ቀስበቀስ በሥራ ላይ ለማዋል በቃች።

በኋላም፡ አፄ ኃይለሥላሴን በማድከም እና በማታላል እሳቸው ከአረቦች ጋር፤ ከኢራኑ ሻህ ጋር ያላቸውን ግኑኝነት እንዲያጠናክሩ በዚህም ሰበብ ከእስራኤል ጋር እንዲኳረፉና እንዲረቁ ተደረገ። የንጉሡ መውደቂያቸው የሆነውን የወሎንና የትግራይን ሰው ሰራሽ ድርቅ ካመጡባቸው በኋላ፡ በንግሥቲቷ የዜና ማሠራጫ፡ በቢቢሲ እንዲጋለጡና እንዲዋረዱ ተደረጉ። ከዚያም፡ እላይ የተጠቀሱት የ ናቶ አባላት እንዲሁም ጀርመን በእርዳታሰጭዎች ስም ወታደሮቻቸውን ወደ ወሎና ትግራይ አሠፈሩ። በእንግሊዞች የሚመራው የአውሮፓውያኑ ሠራዊት በዓየር ሲያበራቸው የነበረው አውሮፕላንና ሄሊኮፕተር በጣም ብዙ ነበሩ ፡ በምድርም ወታደሮቹ በሠፈሩባቸው ቦታዎች ሁሉ የተለያዩ ሰፋፊ ካምፖችን በመገንባት ሲንቀሳቀሱ፡ ኢትዮጵያውያን ልጃገረዶችን እያታለሉ ሲደፍሩ ነዋሪው ትንፍሽ እንኳን ለማለት አለምብቃቱን በጊዜው በቦታው የነበሩ አንድ ባለሥልጣን በሃዘን አጫውተውኛል። ሁሉም ለርዳታ የመጡ መስሏቸው ነበር። ብዙም አልቆየም አፄ ኃይለሥላሴ ከውጭ በተቀነባበረው የንጉሣን ሥርዓት ግልበጣ ዘውዳቸውን እንዲያስቀምጡ ተገደዱ።

ቀደም ሲልም እንግሊዝ፡ ታሪካዊ ጠላቶች አድርጋ በምታያቸው፤ በፈረንሳይ፡ በሩሲያና በጀርመን የሚገኙትን የንጉሣን ሥርዓታት ተራበተራ እንዲገረሰሱ አድርጋ ነበር። አሁን ዓይኗን በስፓኙ እና በሳውዲው የንጉሣውያን ሥርዓቶች ላይ ነው ያሳረፈችው። ካቫቲካኑ ጳጳስ ጋር የሚደረገው ሽኩቻም እንደቀጠለ ነው። በዓለም ላይ አንድ ንጉሥ/ንግሥት መኖር አለበት/አለባት እነሱም ከለንደን ሆነው የበላይነቱን ማሳየት አለባቸው የሚል ተልዕኮ ነው የዳን ዘሮች የሆኑት እንግሊዛውያን ተልዕኮ። በቅርቡ የተካሄደው የንግሥት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ የኢዮቤልዮ በዓል አከባበር፡ እንዲሁም በመካሄድ ላይ ያሉት የኦሎሚፒክ ጨዋታዎች ይህን ነው የሚያመለክቱት። በለንደን ስቴዲየም የተካሄደውን የመክፈቻ ስነሥርዓት ታዝበን ከሆነ፡ ስቴዲየም የነበረው 80ሺህ ሕዝብ ከፍተኛ ጭብጨባ ሲደረግላቸው የነበሩት ተሰላፊ አገሮች፤ አሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ኒውዚላንድ ብሎም በክሪኬት ስፖርት የደም ትስስር ውስጥ ለገቡት የሕንድና ፓኪስታን ተሰላፊዎች ነበር። ኢትዮጵያና የተቀሩት የአፍሪቃ አገሮች ተሰላፊዎች ስማቸው ሲጠራ የግዴለሽነት ፀጥታ ሰፍኖ ነበር።

በመላው ዓለም የሚፍተለተለው ገንዘባዊ እንቅስቃሴም ቢሆን የሚውጠነጠነው ከለንደን ከተማ ሆኖ ነው። ሰሞኑን ባንዳንድ ባንኮች (ባርክሌይስ፥ HSNBC) የታየው ቅሌት እነዚህ በለንደን ተቀማጭነት ያላቸው የገንዘብ ተቋሞች ምን ያህል ብልሹና ኢሰብዓዊ (አውሬአዊ) የሆነ ድርጊት እንደሚፈጽሙ ነው የሚያሳየው። እነዚህ ባንኮች ለ ዋሃቢ ሽብር ፈጣሪዎች ቢሊየን ዶላር ይለግሳሉ፣ እንደ ሶሪያና ሊቢያ ባሉት አገሮች የአልቃይዳን ተዋጊዎች እንዲያሰለጥኑ የሚላኩትን እንግሊዛውያን ባለሙያዎች ይደጉማሉ። እዚህች ይመልከቱ፡“Club of the Isles”

እነዚህ ደም መጣጮች በየቦታው ህውከትና ሽብር በመፍጠር አንዱ በሌላው ላይ እየተነሳ ሕዝቦች ሁሉ እንዲበጣበጡና እንዲተላለቁ የማድረግ ኃይል/ፍላጎት አላቸው። የዓለም ሕዝብ ቁጥር ከአሁኑ ከ7ቢሊየን ወደ 1ቢሊየን ለማውረድ የተቻላቸውን ተንኮል ሁሉ በመጠንሰስ ላይ ይገኛሉ። በተለይ ዋናው ትኩረታቸው በአፍሪካ ላይ ነው፤ አፍሪካውያንን በድህነት እንዲማቅቁ፤ እንደ ኮሙኒዝምና እስልምና በመሳሰሉ ጠንቀኛ ርዕዮተ ዓለሞች እንዲታሠሩ ብሎም በበሽታዎች እየተለከፉ እንዲያልቁ በማድረግ ለዘመናት ብዙ ሞክረዋል፤ ነገር ግን ይህ አልተቻላቸውም፤ እንዲያውም የአፍሪቃውያኑ የሕዝብ ቁጥር በጣም እየጨመረ ፡ የክርስትና እምነትም በይበልጥ እየተስፋፋ ነው የመጣው፤ ስለዚህ አሁን አፍሪቃውያኑን በክህደት ማዕበል በማጥለቅለቅ፤ ገንዘብ አፍቃሪ፣ በእንግሊዝኛ የከረባት ባህልና ቋንቋ ኮሪ፣ ሰዶማዊነትን እንደዘመናዊነት ቆጣሪ እንዲሁም የአክራሪ እስልምና ተቀባይ እንዲሆን በማድረግ እየበጠበጡት ነው። እነርሱ ላቆሙት ምስል ያልሰገዱት አፍሪቃውያን፤ ከነርሱ ጋር ያልተባበሩትና፡ ሉሲፈራዊ ተልዕኳቸውን ለመዋጋት የሚቃጡትን አፍሪቃውያን መሪዎችን በድብቅ እየመነጠሩ ያስወግዳሉ፤ ይገድላሉ።

ላይ ከተጠቀሰው የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ጋር ጎን ለጎን በመተባበር የሚጓዘው በ1949 .ም የተቋቋመው የአውሮፓ የምጣኔ ሀብት ኮሚሽን (European Economic Commission) ወይም የአውሮፓ ማሕበረሰብ (European Community) የሚባለው ነው። በመጨረሻም የአውሮፓ ሕብረት (European Union) ተብሏል። እነርሱም፦

1. እንግሊዝ

7. ኢጣልያ

2. ፈረንሳይ

8. ፖርቱጋል

3. ቤልጂየም

9. ጀርመን

4. ኔዘርላንዶች

10. ስፔን

5. ሉክስምበርግ

11. ግሪክ

6. ዴንማርክ

12. አየርላንድ

ናቸው።

የአውሮፓው የጦር ቃል ኪዳንም ሆነ የአውሮፓውያን የምጣኔ ሀብት (የኢኮኖሚ) ኅብረተሰብ አባል አገሮች መጽሐፍ በዳን. 78-24 በራእ. 131 1712 በሚለው ቁጥር (ከአሥር ቀንዶች)በልጠው ቢታዩም አንዳንዶች አባላት በማሕበሩ አገልግሎት ምንም ያህል አስተዋጽኦ የሌላቸው ናቸው። ለምሳሌ ፖርቱጋልና ግሪክ የመሰሉም አርጅተውና አብቅተው የተቀመጡት አገሮች ናቸው።

ላላፉት ወራት በአውሮፓ የሚታየው የኢኮኖሚ ቀውስ የሚያሳየንም የአንዳንድ ማኅበርተኞች አገሮችን የማኅበሩ አስተዋጽኦ ዝቅ ያለ (ግሪክ፣ ምስራቅ አውሮፓ) ያንዳንዶቹን አገልግሎት ደግሞ የበረታ (ጀርመን)፤ ያንዳንዶችን ደግሞ ገለልተኛ እንደሆነ(ታላቋ ብሪታኒያ)ነው የሚያሳየን። ስለዚህ በማኅበሩ ከልብ የሚሳተፉ አገሮች ቁጥር ከፍና ዝቅ ሲል ይታያል። እስያዊቷ ቱርክ ደግሞ ለጦር ከቃልኪዳኑ ኅብረት ያላት አስተዋጽኦ ቀላል አይደለም። የአውሮፓው የኢኮኖሚ ኅብረተሰብ አባል ለመሆንም ትሻለች።

በአውሮፓውያን ኅብረተሰብ አንድነት መካከል አንዳንድ የሀሳብ ልዩነት ቢኖርም በጽኑ ኅብረት (አንድነት) እንዲያውም ከቱርክና አረብ አገሮች ጋር ሳይቀር በመተባበር ለጥፋት መቆማቸው አይቀሬ ነው።

ከአውሮፓ ግዙፍ ምድር ጋር በእግሯ አውራ ጣት ብቻ የምትገኘው ቱርክ ከሁሉም ይበልጥ ከፍተኛውና ውስብስቡን ሚና ተጫውታለች። በቀዝቃዛው ጦርነት ጊዜ የአሜሪካ የጦር ተዋጊ ጠያራዎች ከቱርክ እየተነሱ በመብረር የሶቪየት ግዛት በነበሩት በጆርጂያ፣ አርሜኒያና አዘርበጃን እንዲሁም በእስያው ክፍል ብዙ የስለላ በረራዎችን ሲያካሂዱ ነበር። በኢራቅ ጦርነትም ጊዜ ብዙ በረራዎች ከቱርክ ተነስተው ነበር ወደ ኢራቅ የሚላኩት። ለዚህም አገልግሎት ቱርክ ከ15 ቢሊየን ዶላር በላይ የገንዘብ ስጦታ እንዳገኘች ማስረጃዎች ይናገራሉ።

የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳንና የአውሮፓ ኅብረት (የካውካስ ዘሮች) እየተጠናከሩ መምጣታቸው በግልጽ እየታየ ነው፤ ይህም ትንቢት ጊዜውን ጠብቆ መፈጸም ለመጀመሩ ግልጽ የሆነ ማረጋገጫ (ምስክር) ነው።

ስለዚህ ወደ አሜሪካ ሄደው የሠፈሩት ሕዝቦች የተነሱባቸው አገሮች በአሁኑ ቅርጾቻቸውና ስሞቻቸው እንዲህ ሆኖ ተበጥሮና ተንጠርጥሮ በምናያቸውና በምናውቃቸው በሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን አገሮች እነርሱም የአውሮፓ ኅብረት በሚባሉት አሥር አገሮች ልብና ፍሬ ሆነው ተጠቅለው ያሉ ስለሆኑ፤ ትንሹን ቀንድ፡ አሜሪካን ያበቀለችው ባለ አሥር ቀንድ አውሬ (አራተኛ መንግሥት) አውሮፓ ሆና ተገኝታለች።

ይህች አውሬ (አውሮፓ)የምድርን ሕዝብ ሕይወት እያደቀቀች ንብረቱን ሁሉ ለዘመናት በመብላት ላይ ትገኛለች። እ..አ በ1872 .ም ታላላቅ አውሮፓውያን (የአውሬይቱ አሥር ቀንዶች)በበርሊን ከተማ በመሰባሰብ በእስያ እንዳደረጉት የአፍሪካንም አሕጕር ከነሕዝቦችዋ ለመከፋፈል ወሰኑ። ከ1877 እስከ 1892 .ም ድረስ የተካሄደው የአፍሪካ መሬትና ሕዝብ ክፍፍል ውጤት በሆነው የቅኝ ግዛት (የባርነት ሥርዓት) የአውሮፓውያን ግዥዎች በተቻለ ፍጥነት ብዙ ሀብት የማግኘት ፍላጎት የአገሬውን ሕዝቦች በሀብታም መሬቶቻቸው ላይ የተመሠረቱ መንደሮቻቸውን እንዲለቁ ሲያደርጋቸው ለገዥዎችም መሬት ጎርጉሮዖዖኦ ናዳ እስኪቀብረው ድረስ መቋቋም በማይችል ቃጠሎ ውስጥ ሥራ ቀን ከሌት ትጋትን የሚጠይቅበት የሲዖል ኑሮ ሆኖበት ነበር። እንዳያልፍ የልም ይህ ሁሉ መዓት አልፏል በቅን የማይታዘዝ ቢኖር በግርፋት የማይቀናም አሟሟቱ የከፋ ነበር። እግዚአብሔር በሰጠውና ባሰፈረው መሬት(አገር)ላይ መኖር ካልተቻለ የት መሄድ እንደሚቻል እስካሁን ድረስ መልስ የሌለው ጥያቄ ሆኖ ቀርቷል።

ይህንን አውሮፓውያን ከአሜሪካ አሕጉሮች እስከ እስያ ዳርቻ እስከ አውስትራሊያና አፍሪካን በሙሉ በአጠቃላይ በምድር ሕዝብ ላይ ማለት ነው የፈጸሙትን የግድያ፣ የዘረፋ ግፍና በደል ተንኮል ለሚያስበው ያቅለሸልሻል፣ ያሳምማል፡ አዙሮ ይጥላል።

የአውሮፓውያን አበላል በዚህ አላበቃም። ሌላውን እንተወውና ከቅኝ ግዛት በኋላ በተለይ እንግሊዝ በቀየሰችው መሠረት የአገሮች ድንበር (ወሰን)አከፋፋይ ሆነች። በዚያም ጥል የተነሳ እስከ አሁን ለምናየው የጦርነት እልቂት የጦር መሣሪያ ሽያጭ ከፍተኛ የደም ገንዘብ እየጋበሱ ነው። አንዱ ይህን ሌላው ደግሞ ያንን የወገነ በመምሰል የየዋሀንን ደም እያፈሰሱ የድህነት ሀብቱን ይበላሉ፤ አገሮቻቸውንም ያደቅቃሉ። የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝ (ባርነት) አልቀረም።

አራተኛይቱ አዉሬ በምድር ላይ አራተኛ መንግሥት ትሆናለች፤ እርሱም ከመንግሥታት ሁሉ የተለየ ይሆናል፥ ምድሪቱንም ሁሉ ይበላል፥ ይረግጣታል፥ ያደቃትማል። አሥሩም ቀንዶች ከዚያ መንግሥት የሚነሡ አሥር ነገሥታት ናቸው።” (ዳን.7 23-24)

ለመሆኑ የፈረንጆች እምነቶች፣ ሕይወት፣ ታሪክና ፍሬ በትንቢት መጽሐፍ ምን ይመስላል? የትኛውስ እምነት ነው ትክክል ሊባል የሚችለው?

በእርግጥ የእምነቶችን መለያ ወይም መጠሪያ ስም በቀጥታ ጠቅሶ እከሌ የተባለው ሃይማኖት ትክክል ነው፤ እከሌ፥ እከሌ የሚባሉት እምነቶች ግን ትክክለኞች አይደሉም፤ የሚሉ ቃሎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኙም። ምክኒያቱም የእምነቶች ስሞች ከጊዜ በኋላ በሰዎች እየተሰጡ የመጡ ሰለሆኑ።

ነገር ግን በነቢያቱ እኔ ሳልፈጠር አይኖችህ አዩኝ፥ የተፈጠሩ ቀኖች ሁሉ፤ አንድ ስንኳ ሳይኖር በመጽሐፍ ተጻፉ።” (መዝ. 13815-16፤ ራእይ 138 17 8 20 5)ብሎ እንዳስነገረው የሚሆነውን ሁሉ አስቀድሞ ስላየው የአገሮችና አካባቢዎችን ምግብረ ሥራቸውን ሁሉ በሕጉ መሠረት እያንጠረጠረ፥ በስፋት እንደቀረበው፥ ከባቢሎን መንግሥት አንስቶ በተዋረድ እስካለንበት ዘመን አምጥቶ የመረጡትን እምነቶቻቸውን ፍሬዎቻቸውን፥ እጣ ፈንታቸውን አስቀምጦታል። ከፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ።በተባለው መሠረት በማቴዎስ 717-20። የእምነት ዓይነቶች ደግሞ በዋነኝነት በአገር በአካባቢና በዘር ተዋረድ እየተስፋፋ እንደመጡ በማስተዋል በግልጥ ማየት የሚቻል ነው። መካከለኛው ምስራቅ፦ አይሁድ ፡ ኢትዮጵያ፦ ተዋሕዶ ክርስቲያን፤ ዐረቦች፦ እስላም፤ ምሥራቅ አውሮፓ፡ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን፤ ምዕራብ አውሮፓ፦ ካቶሊክና ፕሮቴስታንት ከነዘርፉ፤ ምሥራቅ እስያ፦ ሂንድ፥ ቡዳ ወዘተ ናቸው። በእነዚህም ሁኔታ ስለ እስራኤል፣ ዐረቦች፣ አውሮፓ እና አሜሪካ የተፃፈውን በእምነቶቻቸው ፍሬነት የተጠቃለለውን የረዥም ዘመናት ሕይወት ታሪካቸውን ተመልክተናል፤ ቀጥሎ ደግሞ የእምነቶቻቸውን ማንነት ገላጭ የሆኑትን ዐረፍተ ነገሮ (ሐረጎችን) ሰፋ አድርገን እንመለከታለን።

የዐረቦች ሠራዊት አለቃ የሚሆነው፦ ተመልሶም ሃይማኖታቸውን (ክርስትናን) ከካዱት ሰዎች ጋር (ከዐረቦች ጋር)ይወዳጃል። ሠራዊቱም ቤተመቅደሱንና አካባቢውን ያረክሳሉ፤(የድንጋዩ ጉልላት መስጊድ) የዘወትር መሥዋዕትም እንዳቀርብ ያደርጋሉ፤ አሰቃቂና አስጸያፊ የሆነ ርኩስ ነገር እንዲቆምበት ያደርጋሉ። ንጉሡም (ኢየሩሳሌምን የያዘው የዐረቦች ሠራዊት አለቃም)ቀደም ብለው ሃይማኖታቸውን (ኦርቶዶክስ ተዋህዶን)የካዱትን ሁሉ (አውሮፓውያንን)በማታለል የእነርሱን ድጋፍ ያገኛል።ዳን. 1130-32)የኢትዮጵያ መ..ማህበር መ.ቅ።

ቅዱስ ቃል ኪዳን (አዲስ ኪዳንን)የተውት ሰዎች፤” “ቅዱስን ቃል ኪዳን (አዲስ ኪዳንን)የሚበድሉት፤በሚሉት ፍሬ ሐረጎች የዕረቦችና አውሮፓውያን እምነቶች፡ ማለትም የእስልምናና የካቶሊክፕሮቴስታንት ምንነት ተገልጿል።

ዐረቦች ሙስሊሞች የጌታ ኢየሱስን የእግዚአብሔር ልጅነት፣ አምላክነቱንና አዳኝነቱን፤ ከውኃና ከመንፈስ ዳግም ልደትንና ሙታን ትንሳኤውን መተዋቸውና አለመቀበላቸውም በግልጽ የታወቀ ነገር ስለሆነ የሚያነጋግር አይደለም። ትኩረት የሚሰጠው ስለፈረንጆች፤ ካቶሊክፕሮቴስታንት ቃል ኪዳኑን የሚበድሉ ሰዎችተብሎ ስለ መሠረተ እምነቶቻቸው የተጻፈላቸው ቃል ነው።

በደል፦ ክፋትን በማድረግ ማመፅ፡ ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ ከፍርድም ፈቀቅ ማለት። ዳን 95። በዚህ መሠረት የአዲስ ኪዳንን መበደል። በክርስትና ሃይማኖት ላይ ማመፅ፥ ትዕዛዛትን መጣል፤ ክፋትን ማድረግ፤ ሕግን መቃወም።

አዎ! ንጉሡ የተባለው ኢየሩሳሌምን የሚይዛት የዐረቦች ሠራዊት አለቃ ቀደም ብለው ሃይማኖታቸውን የካዱትን ሁሉ፡ማለትም፡ ቃል ኪዳኑን የሚበድሉትን፡አውሮፓአሜሪካን በማታለል ለርኩሱ ጥፋት ጦርነት የእነርሱን ድጋፍ ያገኛል፡ ያስታቸዋልም።

ዐረቦቹ ምዕራባውያኑን እንዴት እያታለሏቸው እንደሆነ የዛሬው የዓለማችን ሁኔታ በግልጽ ያሳየናል። ምዕራባውያኑ፡ ዐረብና እስላም በሆኑት አገሮች ከፍተኛ የገንዘብና የሰው ሕይወት መስዋዕት በማድረግ ላይ ናቸው። ሙስሊሞቹ ምዕራባውያኑ ላይ የሽብር ፈጣሪነት ተግባር በፈጸሙ ቁጥር፡ ምዕራብውያኑ ወደ ዐረቦቹ አገሮች በመግባት ትርፍ ለሌለው የብድር መላሽነት ተግባር ይጋበዛሉ፡ አገሮቻቸውንም ለሙስሊሞቹ ይከፍታሉ። በኢራቅና አፍጋኒስታን፡ እንዲሁም በሰሜን አፍሪቃ የወጣው ወጭ በጣም ብዙ ነበር፤ በሙስሊሞቹ ሽብር ፈጣሪዎች ጥቃት በተካሄደባት በኒውዮርክ ከተማም፡ ሰማይ ጠቀሶቹ ህንፃዎች በፈራረሱበት ቦታ ላይ መስጊድ ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ማሳወቃቸው ምን ያህል ግራ እንደተጋቡና እንደተታለሉ ነው የሚያሳየው። እዚህ ላይ ልብ ልንል የሚገባን፤ ግጭቶች በበዙባቸው በመካከለኛው ምስራቅ አገሮች፤ አንድም የአረብ ማህበረሰብ (አረብ ሊግ)አባል ወታደር ወደ ጦር ሜዳ አለመላኩን ነው። ሊቢያ፤ ግብጽ፤ ቱኒዚያ፤ የመን፤ ሶማሊያና ሶሪያ ሁሉም የዐረብ ሊግ አባላት አገሮች ናቸው። ነገር ግን የዐረብ ሊግ ወይም መንግሥታቱ ወደነዚህ አገሮች የገንዘብና ቁሳቁስ ድጎማ ከማደረግ በቀር ወታደሮቻቸውን(ፀጥታ አስከባሪዎችን)ለመላክ ፈቃደኞች አይደሉም። ሳውዲ አረቢያም ወደ ባሕሬን ሠራዊቷን ስትልክ ቀጥተኛ የወታደራዊ ፍጥጫ ባለመኖሩ፡ ቢኖርም ከሺያ እስላሟ ኢራን ብቻ ሊሆን እንደሚችልና እሷም ለጦርነት አሁን ዝግጁ እንዳልሆነች በመገንዘብ ነበር።

ቀደም ብለው ሃይማኖታቸውን ኦርቶዶክስ ተዋህዶን የካዱት ሁሉ የተባሉት አውሮፓአሜሪካ ተታለው የዐረቡ ሠራዊት ለሚያስነሳው ርኩስ ጥፋት ድጋፍ የሚሄዱት እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አጻጻፍ መንፈስ ንጉሡን (እየሩሳሌምእን የያዘውን የዐረቦችን ሠራዊት አለቃ)ለመወገን ሳይሆን፡ ትክክለኛ ታሪኩ በተቃራኒነት ነው። ዳሩ ግን ንጉሡ የተባለው ወይም የዐረቦች ሠራዊትና ሃይማኖታቸውን የካዱት ሁሉ የተባሉት አውሮፓውያን በተቃራኒነት ጦርነት ቢያካሂዱም ሁለቱም ወገኖች አንድ የርኩስ ጥፋት ዓላማ ጦርነት ስለሚያካሂዱ አጠቃላይ ታሪኩን ከሥር ከመሠረቱ በግልጥ ላልተረዱና ለተምታታባቸው፡ ተባባሪዎች ናቸው የሚለው ሃሳብ ያስኬዳል። እንደተገለጸው ግን ሃይማኖታቸውን የካዱት ለንጉሡ ተቃራኒዎች ሳሉ ርኩሱን ጥፋት ለማካሄድ ግን ደጋፊዎቹ ተባባሪዎቹ ናቸው። አንድ የጥፋት መንፈስ ነውና። ወደ ርኩስ ጥፋት የሚዘምተውን የምዕራቡን ወገን (መሪ) ዳን.825 ላይም በመታለሉ ተንኮል በእጁ ያከናውናል፤ በልቡ ይታበያል።ይለዋል።

አንድ መስተዋል ያለበት ትልቅ ምስጢር፦ የእነዚህ ሁለት ወገኖች፡ ማለትም የዐረቦችና የፈረንጆች፥ አጠቃላይ ሕይወት ታሪክ በዋና ዋና ነጥቦች ጠቅለል ተደርጎ ይታያል። በሰዎች ቋንቋ፡ ፖለቲካም ሃይማኖትም ይበሉት ይህ ጽሁፍ ግን የዐረቦችን ከባቢሎኑ ናቡከደነፆር፤ የፈረንጆችን ከግሪኩ እስክንድር መንግሥታት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ዘመን ፍሬአቸው ድረስ ባጭሩ የቀረበው በሃማኖት ነው።

ይህን ሁሉ ነገር ስለ እነርሱ እንደሚናገር ብዙዎቻችን አላስተዋልነውም፤ ዓለማችንም አስፈላጊውን ትኩረት አልሰጠችውም። እነርሱ ግን ምድሪቷን የምንቆጣጠር፤ ዓለሙን የምንሰብክ እስራኤል እኛ ነን ይላሉ። የሚሉሽን በሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ፤ይላል ያገራችን ሰው። ራስን ትንሽ ቅንጣት ታህል እንኳ አለማወቅ እጅግ የሚያሳዝን ነገር ነው። ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።ምሳሌ 47

ነገር ግን ይህን ሁሉ መመልከት ያለብን በአብዛኛው፣ በዋንኛነት ወይም በአመዛኙ ነው እንጂ በአውሮፓውያንም ሆነ በሌሎች ሕዝቦች ዉስጥ እጅግ ሩህሩህና ለሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ለተፈጥሮ ሁሉ የሚቆረቆሩ ሕይወታቸውን ሳይቀር የሚሰው ብዙ ሰዎች እንዳሉ ግልጽ ነው።

ነገር ግን እነዚህ ልዩየሆኑት የእግዚአብሔር ሰዎች በተለይ እኛን አፍሪቃውያኑን በሚመለከት ጉዳይ ብዙም ሚና አይጫወቱም፤ ከኛ ጋር ግንኙነት ያላቸው እኛን ለመቆጣጠር፡ ባሪያ ለማድረግ ብሎም ለማጥፋት የሚፈልጉት የአውሬው ኃይሎች ናቸው። ሲያስፈልጋቸው የኤድሱንና የኢቦላውን ቫይረስ፤ ሲያሰኛቸው ረሃቡን፣ የማጥፊያ ክትባቱንና የርስበርስ ጦርነቱን ይልኩብናል። ይህን ሁሉ ጉድ የዓለም ማሕበረሰብ እንዴት ዝም ብሎ እንደሚያልፈው እጅግ በጣም የሚገርምና የሚያሳዝን ነገር ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ እየተካሄደ ያለው ጦርነት በይበልጥ በክርስትና እምነት ላይ ነው ትኩረቱን ያደረገው። የአውሮፓን የበላይነት በምድር ላይ ለማስፋፋት ሲባል የክርስትና እምነትን ለማጥፋት ዘመቻ ውስጥ የሚሳተፉት፡ ልባቸውን ለአውሮፓአሜሪካና ዐረቦች ዓላማ የሚሰጡት ወገኖች ሁሉ የአውሬው አገልጋይ እንደሆኑ ተደርገው ነው የሚቆጠሩት። አውሮፓውያኑአሜሪካኑ ከሙስሊሞቹ ዐረቦች ጋር በመተባበር በክርስቲያን ሕዝቦች ላይ የሚያካሂዱትን ዘመቻ፤ በግብጽ፤ በኢራቅ፤ በሶሪያ በግልጽ የምንታዘበው ነው።

በሶሪያ በ አላዊ እስላም መንግሥታዊ መስተዳደርና ደፈጣ ተዋጊዎችበሚባሉት የሱኒ እስላም አክራሪዎች መካከል የሚካሄደው ጦርነት ወደ አሌፖ ከተማ መዘዋወሩ ያለ ምክኒያት አይደለም። አሌፖ ጥንታዊ የክርስቲያኖች ከተማ ናት። በዚህች ከተማ 47 ጥንታውያን ዓብያተክርስቲያናት አሉ፤ አሁን ግን በጦርነቱ ሳቢያ በቦምብ ለመፈራረስ ይበቃሉ፤ በዚህም የዲያብሎስ አርበኞች ዓላማቸውን ከግብ ያደርሳሉ። ከ100 ዓመታት በፊት፡ እ..አ በ1860 .ም በአሌፖና አካባቢዋ ተካሂዶ በነበረው የድሩዝ ሙስሊሞች ጸረክርስቲያን ዘመቻ እስከ 20.000 የሚጠጉ ክርስቲያኖች ተጨፍጭፈዋል። በዚያን ጊዜም ቢሆን ምዕራባውያኑ ከቱርክና ዐረብ ሙስሊሞች ጋር በመተባበር ነበር ክርስቲያኖችን በመካከለኛው ምስራቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ ሲጨፈጭፉ የነበሩት። በዓፄ ዮሐንስ ዘመነ መንግሥት ኢትዮጵያን ወረርው የነበሩትን የግብጽና ቱርክ ሠራዊቶች በሰው ኃይልና በጦር መሣሪያ ሲደግፉ የነበሩት እንግሊዛውያንና አሜሪካውያን እንደነበሩ ስንገነዘብ እጅግ በጣም እያዘንን ነው፤ ክርስቲያን ነን የሚሉ ኃያላን አገሮች ከእስላም አገሮች ጋር በመተባበር ሌላዋን ድሃ የክርስቲያኖች አገር፤ ኢትዮጵያን ለመጨፍጨፍ ሲበቁ። እነዚህ ከታሪክ ለመማር ፈቃደኞች ያልሆኑት ምዕራባውያን በሁለተኛው የዓለም ጦርነትም ይህን ትልቅ ስህተት ደግመውታል፤ አሁንም እየደገሙት ነው። ባሁኑ ሰዓት ልዩ የውትድርና ውል ከአሜሪካ ጋር ለማድረግ የበቁትና በጣም የረቀቁትን የጦር መሣሪያዎች ከአሜሪካ ለማግኘት ዕድል ያገኙት፤ ከኔቶ ዓባላት ሌላ፤ ግብጽ፣ ፓኪስታንና አፍጋኒስታን ናቸው።

የሚቀጥለው የዚህ አውሬ ሠራዊት ዒላማም የመጨረሻዋ የክርስትና ትልቅ ምሽግ የሆነችው ኢትዮጵያ እንደሆነች መገንዘብ ይኖርብናል።

 

የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅልን!

በ PDF ለማንበብ እዚች ይጫኑ EndTimesConstellation

______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: