Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • May 2012
  M T W T F S S
   123456
  78910111213
  14151617181920
  21222324252627
  28293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

የግብጽ ምርጫ፡ ወይ ወረርሽኝ ወይ ኮሌራ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 31, 2012

ግብጽ ውስጥ 50 ሚሊየን የሚሆኑ ግብጻውይን የመምረጥ መብት ሲኖራቸው፡ ከዚህም ግማሽ የሚሆነው በአሁኑ ምርጫ ላይ ተካፍሏል። ከ18 ሚሊየን ክርስቲያኖች (እንደ ኮፕት ቤተከርስቲያን ዘገባ) 6 ሚሊየኑ ድምጽ ሰጥተዋል። አቶ ሻፊክ እና ሸህ ሙርሲ እያንዳንዳቸው 5 ሚሊየን ድምጽ አግኝተዋል። በሁለቱ መካከል ከሁለት ሣምንት በኋል ምርጫ እንደገና ይካሄዳል።

ፓርላማው በእስልምና አርበኞች ቁጥጥር ስር ሲሆን፡ በፕሬዚደንት ወንበሩ ላይም እነርሱ ራሳቸው ሊቀመጡበት እየተዘጋጁ ነው።

የአረብ ጸደይ ተብሎ ሲለፈፍለት በነበረውና የካይሮው ታሂር አደባባይ ላይ ሲካሄድ በነበረው እንቅስቃሴ ሌት ተቀን ሲቁነጠነጡ፣ ሲጮሁና የተጋነነ ትኩረት ሲያገኙ የነበሩት የሙባረክ ተቃዋሚ ግብጻውያን፡ ለነጻነት፣ ለፍትህና ለእኩልነት ነው የምንታገለው እያሉ መፈክሮች ሲያሰሙ ነበር። የዚህ አብዮትተሳታፊዎች በእስላም ፓርቲዎቹ የማይወክሉ፤ ከተለያየ የሕብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ፡ ሊበራልአለማውያንየሚል ቅጽል ስም የተሰጣቸው ተሳታፊዎች ነበሩ። በኋላ ግን ይህን እንቅስቃሴ በመጥለፍ ስልጣኑን ለመያዝ የበቁት የፖለቲካ እስላም ሃይሎች ነበሩ።

ሙስሊም ወንድማማችነትእያለ እራሱን የሚጠራው የእስላሞች አንድነት ማኅበር / ፓርቲ ከ6 ወራት በፊት ለሥልጣን ወይም ለፕሬዝደንትነት ስፍራው ምንም ዓይነት ፍላጎት እንደሌለው፤ ለምርጫ ተወዳዳሪም እንደማያቀርብ ቃል ገብቶ ነበር፡ ነገር ግን ይህን ቃል ኪዳን በማፍረስ ተዋካያቸው ያው አሁን በእጩነት ለመቅረብ በቅቷል። ቀደም ሲል የእስላሞቹን ግንባር የሚወክሉትና ተስፋ ተጥሎባቸውም የነበሩት ሳላህ አቡ እስማኤል ለእጩነት ብቃት እንደሌላቸው በአስመራጩ ኮሚሽን ጸደቆ ነበር። ምክኒያቱም፡ የአክራሪ እስልምናን ወገን የሚወክሉትና በምዕራቡ፡ በተለይ በአሜሪካ ላይ ከፍተኛ ጥላቻ እንዳላቸው በአደባባይ በግልጽ ሲያስታውቁ የነበሩት እኚህ ሰውም ቀጣፊና አታላይ ናቸውና፤ የኝህ የአሜሪካ ቀንደኛ ጠላት እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሰው እናት የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው የግብጽ ተወላጅ ሆነው ተገኝተዋል።

ከሺህ በላይ የሚሆኑ ግብጻውያንን ለሞት ያበቃው ይህ የግብጽ አብዮት አሁን ምን አመጣ? ብለን ብንጠይቅ ፤ ያመጣው መተረመማስን፣ ብጥብጥን፣ አክራሪነትንና ተስፋዓልባነትን ነው። አሁን የፕሬዝደንቱን ስልጣን ለመያዝ የተዘጋጁት የቀድሞው ፕሬዚደንት በሁስኒ ሙባረክ የመጨረሻው ካቢኔ ለ1ወር ያህል በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለው የነበሩት፡ ፓይለት ሻፊክ እና የፖለቲካ እስላሙ አርበኛ ሸህ ሙርሲ ናቸው። እያንዳንዳቸው 5ሚሊየን የሚሆኑትን ግብጻውያን ድምጽ አግኝተዋል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ተዓምር ነው! ግብጽ በእጃችን ናት ብለው ከረባት ማንጠልጠል የጀመሩት የሙስሊም ወንድማማችነት ፓርቲ ተወካዮች አሁን ተደናግጠዋል፤ አብዛኛው ሕዝብ ይደግፈናል የግብጽ ሠራዊት ጀነራሎችም እኛን ይሻሉ ብለው ሲያስቡ የነበሩት እነዚህ የእስላም አርበኞች አሁን ቶሎ ብለው ክርስቲያኖችን መውቀስ ጀምረዋል። ክርስቲያኖች የሙባረክን ሰው ነው የመረጡት፡ የቀድሞውን መንግሥት እንደገና ሊያመጡብን ነው ብለው ግብጻውያንን በማስፈራራት ላይ ናቸው። ይህ ውንጀላ በስተጀርባው ሌላ ምስጢር አለው። ይኽውም፡ ኮፕቲክ ክርስቲያኖች የቀድሞው የሙባረክ መንግሥት ደጋፊዎች ናቸው ብሎ በመጠቆም ለመጪው ጭፍጨፋ / ጀነሳይድ መንገድ ለመክፈት ነው። ይህ የአረብ ሙስሊሞች ዓይነተኛ ባሕርይ ነው። ተመሳሳይ ሁኔታም በሶርያ እየተከሰተ ነው። በሶሪያ ተቋዋሚ ነን የሚሉት የእስላም ተዋጊዎች ክርስቲያን ሶሪያውያን የሃፌዝ አልአሳድ ደጋፊዎች ናቸው እየተባሉ እንደዚሁ ለመጪው ጀነሳይድ እየተዘጋጁ ነው። እንዲያውም አላዊዎች ወደ መቃብራት፤ ክርስቲያኖች ወደ ቤይሩትየሚል መፈክር በማሰማት ላይ ናቸው። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ከሙሶሊኒ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ላይ ብዙ በደል ፈጽመው ነበር፤ ሰለዚህ አሁን መጨፍጨፍ አለባቸው ብሎ እንደማሰብ ማለት ነው። ከማን ጋር ዓለምን እንደምንጫረት እንታዘብ!

ወደ ግብጽ ስንመለስ፡ የሙስሊም ወንድማማችነት ፓርቲ አባላት የፕሬዚደንትነት ስልጣኑን፡ ባጠቃላይ የፖለቲካውንና የሕጉን ስልጣን በመቆጣጠር እ..አ ከ1928 ጀምሮ ያለሙለትን ህልም እውን ለማድረግ በመወራጨት ላይ ናቸው። ለዚህም የተለመደውን የቅጥፈት ታክቲክ (ታኪያ) ይጠቀማሉ። በዚህ በአንድ ሳምንት ውስጥ እንኳን፡ ባንድ በኩል ክርስቲያኖች የቀድሞውን የሙባረክን ምኒስትር፡ አቶ ሻፊክን መርጠዋል እያሉ ሲወንጅሉ በሌላ በኩል ደግሞ ክርስቲያኖች ሙሉ በሙሉ የግብጽ ዜጎች ናቸው፡ የፕሬዚደንት ስልጣን እንዲይዙ ባንፈቀድላቸውም በአማካሪነት ሁላችንንም ማገልገል ይችላሉ፣ ሴቶችም እንዲሸፋፈኑ አናስገድድም ወዘተ፤ እያሉ አሥቂኝ የሆነና ጮሌነት የተሞላባት ቅጥፈታቸውን ለግጻውያን ክርስቲያኖች ለመሸጥ ይሞክራሉ። የአቶ ሻፊክን ፕሬዚደንትነት ፈጽሞ እንደማይቀበሉ ገና ካሁኑ ማስፈራራት እንዲሁም ጥቃቶችን መፈጸም ጀምረዋል። አቶ ሻፊክ ከተመረጡ የአባይ ወንዝ ደም በደም ይሆናል፣ ውሃው ልክ ሙሴ ቀይሮት የነበው ዓይነት ቀለም ይይዛል።

ሸህ ሙርሲና አጋሮቹ ስልጣኑን ሙሉ በሙሉ ከያዙ ደግሞ የሻርያ ህግ የግብጽ መተዳደሪያ ይሆናል፤ ሴቶችና ክርስቲያኖችም ወይ ወደ ባርነት ይመለሳሉ ፣ ወይ እስልምና መቀበል ሊኖርባቸው ነው ፣ ወይ አገራቸውን ለቀው መውጣት ካልሆነም መሞት ብቻ ነው ምርጫቸው። እስላማዊ መስተዳደር ለንዑሳን ሕዝቦች ብቻ ሳይሆን ጠንቅነቱ፡ ለራሳቸው ለሙስሊሞችም አስከፊ እንደሚሆን ሩቅ መሄድ አያስፈልግም በኢራን ማየት ይቻላል። ሆኖም ሕዝቡ፡ አይ! የለም! ከረባት ያሠሩትን ሼሆቹን ነው የምንመርጠው ካሉ መብታቸው ነው፣ ምርጫቸውም ነው። በዚህ ምርጫ ወቅት ጠላትከሚሉት የውጩ ዓለም የተደረገ ምን ዓይነት ተጽእኖ የለም። ስለዚህ በኋል የተለመደው ዓይነት ሰበብ ሊኖራቸው አይችልም። ግን የሚገርመው፤ ለሰብዓዊ መብትና ለዲሞክራሲ ቆመናል እያሉ ምርጫ በሚያካሂዱ የአፍሪቃ ሃገሮች ላይ እራሳቸውን ደግመው ደጋግመው የሚያስተዋውቁት የምዕራባውያን ቡድኖች ግብጽን በተመለከተ ጸጥ ማለታቸው ነው፤ ግብጽ ለሺህ ዓመታት ዲሞክራሲን ተክና እንደኖርች! የዜና ማሰራጫውም ጥሩ ጥሩውን እንጂ መጥፎውን ነገር ከግብጽ፤ ስለ ግብጽ አያወራም።

በመጪዎቹ አመታት፤ የኢትዮጵያ ጎረቤት አገር በሆኑትና እንደ ግብጽ ባሉት አገሮች በክርስቶስ ተከታይ ሕዝቦች ኢትዮጵያውያንላይ አድሎና ግድያ ሲፈጽምባቸው የዓለም ማህበረሰብ ምንም ማድረግ አይችል/አይፈልግ ይሆናል፣ የዘመኑ ደካማ የኢትዮጵያውያን ትውልድም ምን አገባኝማለቱን ይቀጥል ይሆናል፤ ነገር ግን፡ ፈጠነም ራቀም፡ የኢትዮጵያ አምላክ ዝም አይልም፣ መጪው የኢትዮጵያ ትውልድም በሱዳን፣ በግብጽና በአረቢያ በክርስቶስ ተከታዮች ላይ እንዲሁም በሴቶች ላይ ለተፈጸመው በደል ሁሉ አስፈላጊውን መልስ ይሰጣል፤ ይበቀላል፤ በዚህ አንጠራጠር!

(ማቴ. 13:15 )በዓይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል፡ ዓይናቸውንም ጨፍነዋል የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።

 

_____________________________________________

 

One Response to “የግብጽ ምርጫ፡ ወይ ወረርሽኝ ወይ ኮሌራ”

 1. Lillie said

  Have you ever thought about writing an e-book or guest authoring on other blogs?

  I have a blog based upon on the same topics you discuss and would really
  like to have you share some stories/information.
  I know my viewers would enjoy your work. If you’re even remotely interested, feel free to shoot me an email.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: