የዓለም ዜና ማሰራጫዎች የሉሲፈርን ዳንስ ሲደንሱ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 31, 2012
በፊደላት ሰላጣ የታጀቡት እንደ ሲ ኤን ኤን፤ ቢቢሲ፤ አልጀዚራ፤ ፍራንስ 24፤ ራሽያ ቱደይ፤ የመሳሰሉት የዜና ማሰራጫ ድርጅቶች በተገልጋዩ ዘንድ ያላቸው ተሰሚነት ከቀን ወደቀን እየቀነሰ መጥቷል። ተጠቃሚው የዓለም ማህበረሰብ የነዚህን ድርጅቶች ቀጣፊነት፣ አምታችነት አሁን እየተረዳው ነው። ሃቅ/ፋክት፡ 1/10ኛ ፤ ግምት፡ 4/10ኛ፤ ፕሮፓጋንዳ ደግሞ 5/10ኛውን ነው በዜና ማሰራጫዎቹ የሚንጸባረቀው። እነዚህ ድርጅቶች ለተለያየ ተመልካች ወይም አድማጭ የቆሙ መስለው ቢታዩንም፡ የቆሙት ግን ለአንድ አጀንዳ፤ ዓለምን ለአንድ ዓለም የሉሲፈር ሥርዓት ለማዘጋጀት መሆኑን መገንዘብ አለብን። ለዚህ እቅዳቸው ተባባሪዎች ሆነው ያገኟቸው የካውካስ ‘ዘር‘ ናቸው የሚባሉት መካከለኛ ምስራቃውያን፣ አለፍ ብሎም ደቡብና ምስራቅ እስያውያን ናቸው።
እግዚአብሔር ልጆቼ በማለት የመረጣቸው ሕዝቦች/እስራኤላውያን እንዳሉ ሁሉ፤ ሉሲፈር ሰይጣንም የእኔ ናችሁ ብሎ የመረጣቸው ሕዝቦች ከጎናችን አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት አጋራውያን እና አማሌቆች ሰይጣን የኔ ናቸው የሚላቸው ሕዝቦች ናቸው። አረቢያ የሰፈሩት የአማሌቅ ዘሮች የጭካኔ ባሕርያቸው ልክ ዘጽአት 17 ላይ የተገለጠውን ባሕርይ ያንጸባርቃል። በሙሴ ጊዜ በሲናይ በርሃ ሲካሄድ የነበረው ዓይነት አመጽና ጭካኔ አሁንም በወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ላይ እዛው ሲናይ በርሃ ላይ እየተፈጸመ ነው፤ ሰሞኑን የምንሰማው የኩላሊት፣ የጉበት፣ የልብ ዘረፋ ይህን ሰይጣናዊ ተግባር ይጠቁመናል። ለማንኛውም ሰይጣን የእኔ ናችሁ ብሎ የተቀበላቸው ሕዝቦች አረቢያ መገኘታቸው የሚያጠራጥር አይደለም፡ ብዙ ምልክቶች አሉና።
እነዚህ ህዝቦች አሁን ከምዕራቡ ጋር በመተባበር አለምን በማወክ ላይ ይገኛሉ። አሁን የምናየውን ወግ/ባህል አጥባቂነታቸውን አንመለከት፡ ህሊናቸው በቀላሉ መታጠብ የሚችልባቸው ህዝቦች ናቸው። እግዚአብሔር ልጁን ለይቶ እንደሚያውቅ ሰይጣንም ልጆቹን ለይቶ የማወቅ ችሎታ/ፈቃድ አለው። በሉሲፈር የምትደዳደረው ዓለማችን ለእነዚህ ሕዝቦች ከሁሉም አቅጣጫ በሁሉም መስክ ወደር የሌለው አትኩሮት ሰጥቷቸዋል ፤ ለዚህም ነው እነ ቢቢሲ እነዚህን አገሮች በተመለከተ ስሜታዊ በሆነ ወይም ፍቅር በተሞላበት መልክ ዘገባዎቻቸውን እንዲያቀርቡ ‘ምርጥ‘ የሚባሉት ጋዜጠኞቻቸው ወደዚያ የሚልኳቸው።
አሰቃቂና በጣም አሳዛኝ የሆኑ በደሎች በኮንጎ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በደቡብ ሊቢያ፣ በሰሜን ማሊ እየተካሄዱ ናቸው፤ ታዲያ ስለነዚህ ሕዝቦች ማን ግድ ሰጥቶት? ለግብጽና ለሶሪያ የሚሰጡት ትኩረት፡ ለግብጻውያንና ለሶሪያውያን ደህነንት ልባቸው ሲመታ ማየቱ ግን በሁላችን ዘንድ የተለመደ ሆኖአል። የሶሪያ ሕጻናት ሞተው ሲታዩ እምባቸው ዱብዱብ ይላል፣ የጥቁር አፍሪቃውያን ልጆች እንደ ቅጠል ሲረግፉ ግን “እነዚህ ኋላ ቀሮች፡ የታባታቸው፡ እርስበርሳቸው ቢጨራረሱ እኛ ምን አገባን? እንዲያውም ማዕቀብ እናድርግባቸው፤ ፍርድ ቤት አቋቁመን መሪዎቻቸውንም በውንጀላ እናዋርዳቸው!” ከማለት ሌላ ነገር አያውቁም፡ ማወቅም አይፈልጉም።
እነዚህ የዜና ማሰራጫዎች እውቀት ያላቸውን፣ የነቁትንና፣ ተደማጭነት ሊኖራቸው የሚችሉትን አፍሪቃውያንን በፍጹም አይጋብዙም፤ ከጋበዙም ሃሳባቸውን በግልጽ እንዲያቀርቡ እድሉን አይሰጧቸውም። “ኮኒ 2012” የሚለውን ‘ጥናታዊ‘ የፕሮፓጋንዳ ቪዲዮ አስመልክቶ ብልሹው ቢቢሲ ብልህ የሆነችውን እህታችንን፡ ሰሎሜ ለማን ጋብዟት ነበር። ከተጋበዙት 4፣ 5 እንግዶች መሀከል ብልህ በሆነ መልክ የምትናገር፣ አሳማኝ በሆነ መልክ ነገሮችን በሚገባ ለመግለጽ ብቁ የነበረች እሷ ብቻ ነበረች፡ ነገር ግን ብልሹው ቢቢሲ፡ ሆን ብሎ እድሉን ሊሰጣት ዝግጁ አልነበረም። ቢቢሲ እድሉን የሚሰጠው ድንቁርና ብቻ ለሚያስተምሩት “አል–ቁድስ” የሚባለውን የአረብ ጋዜጣ ከለንደን ሆኖ ለሚያትመው ደባሪ ‘ጋዜጠኛ‘ ለመሰሉት ዓየነት ሰዎች ነው። አንዳንዴ ደግሞ የአጀንዳቸውን ብርጭቆ የሚሞሉላቸውን፡ “እንደ ጨቅላ የሚያወሩትን” (እንደዚያ ነው አፍሪቃውያንን የሚሉን) ከጋና ወይም ከኬኒያ የመጡትንና ነጭን መኮረጅ የሚወዱትን አፍሪቃውያንን ነው።
ከጥቂት ሣምንታት በፊት በአንድ የሞቃዲሾ ሆቴል ውስጥ በተደረገው የአጥፍቶ ማጥፋት የቦምብ ጥቃት ሳቢያ የሶማሊያ ኦሊምፒክ ኮሚቴና የእግርኳ ፌዴሬሺኑ ሊቃነመናብርት ባጠቃላይ 10 የሚሆኑ ሌሎች ሶማሊያውያን መገደላቸው ይታወሳል። ይህን አስመልክቶ ‘ብዙ ጊዜ የቆዩ ናቸው ከሚባልቱ የቢቢሲ ጋዜጠኞች አንዱ፡ “እንዴት ነው በሶማሊያ ሰላም ማምጣት ያልተቻለው?” ለሚለው ጥያቄ መልስ ሲያቀርብ፡ “ሶማሊያ ውስጥ የኢትዮጵያና የኬኒያ ወታደሮች አሉ፤ ኬኒያውያን ብዙ ልምድ የላቸውም፤ የኢትዮጵያ ወታደሮችም የተሻለ ልምድ ቢኖራቸውም፤ የአልሸባብን ተዋጊዎች አይችሏቸውም” ብሎ የአልቄይዳን አርበኞች በብሔራዊው የቢቢሲ ቴሌቪዥን ሲያሞግሳቸው ነበር። በተለይማ “HardTalk” በተባለው ፕሮግራም ላይ አፍሪካውያን እንግዶችን ንቀት በተሞላበት መልክ እያንቋሸሹ ለማዋረድ ሲሞክሩ ማየቱ በጣም ነው የሚያሳዝነው፤ ጥላቻው በግልጽ ነው የሚታየው።
አይ የነዚህ ሰዎች ድንቁርና በማልት ከታዘብኩ ከጥቂት ቀናት በኋላ፡ በአፍጋኒስታኗ ካቡል ውስጥ የታሊባን ተዋጊዎች በምዕራባውያንና የሩስያ ኢምባሲዎች አካባቢ ጥቃት አድርሰው ብዙ ሰዎች ሊያልቁ በቅተው ነበር። ይህ ጥቃት እንደ ሞቃዲሾው የአጥፍቶ ማጥፋት ዓይነት ጥቃት ሳይሆን፡ ደንበኛ የጎሬላ ዓይነት ታክቲክ የነበረው ጥቃት ነበር። የዜና ማሰራጫዎች፣ ቢቢሲን ጨምሮ፡ ስለዚህ ጥቃት ብዙም ሪፖርት በጊዜው አላቀረቡብም፡ “እንዴት ነው በአፍጋኒስታን ሰላም ማምጣት የሚቻለው? ወይም የእንግሊዝና የኔቶ ወታደሮች ብቃት አላቸውን?” የሚል ጥያቄም በጭራሽ አላቀረቡም፤ ሊያቀርቡትም አይችሉም። ላለፉት 10 ዓመታት ያ ሁሉ አገር በህብረት የዘመተመበት፤ ትሪሊየን ዶላር የወጣለት፤ የብዙ ወታደሮችን ሕይወት የጠየቀውን የአፍጋኒስታንን ጦርነት ለማውገዝ ሳይቃጣቸው፤ ድሃዋ ኢትዮጵያ በቀጥታ ከሚመለከታት ጉዳይ ጋር ስትፋለም፡ ለምንድን ነው አፍሪቃውያንን/ ኢትዮጵያውያንን የሚያጥላሉት? የተሻሉ ሯጮች ስለሆኑ፤ ምናልባትም የተሻሉ ተዋጊዎች ስለሆኑ?
ሶርያን በተመለከተ የአንዱ ዓለም ሥርዓት ቱልቱላዎች በተቻላቸው መጠን በሥልጣን ላይ ያለውን
ባሽር አል አሳድን መንግሥት ለመገርሰስ በሚደረገው ትግል ላይ በተቻላቸው መንገድ ሁሉ የሚቻላቸውን አስተዋጽዖ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ድብቅ የሆነው ተቀዳሚ ዓላማቸው ጥንታዊ የሆኑትን ክርስቲያን ማሕበረሰቦች ማጥፋት ነውና በኢራቅ፣ በቦስኒያና በሰርቢያዋ ኮሶቮ እንደተጠቀሙት ዓይነት ስትራቴጂ በሶሪያ ለመጠቀም ነገሮችን በመቆስቆስ ላይ ይገኛሉ። ሶርያ ውስጥ በ አላዊ (ሺያ) እስላም አስተዳዳሪዎች ለዘመናት በመጠኑም ቢሆን በሰላም ሲኖሩ የነበሩት ክርስቲያኖች ልክ እንደ ሳዳም ኢራቅ ዓይነት እጣ እየደረሳቸው ነው። ሶርያን ካካባቢው ለየት የሚያደርጋት፤ በሶርያ ንኡሳን የሆኑት አላዊያን ለዘመናት ስልጣን ላይ መቆየታቸው ነው። እነዚህ አላውያን በሱኒ እስላሞች የተጠሉ ናቸው፤ ስለዚህ እነ አሳድ ከስልጣን ከተወገዱ የሶርያ አላውያን፤ ከዚያም የሊባኖን ሺያዎች፣ ከዚያም የየመን ሺያዎች፣ ከዚያም የባህሬይን፣ ከዚያም የኢራን ተራ በተራ ለእልቂት ይበቃሉ። ይህ ጦርነት በሺያና ሱኒ እስላሞች መካከል የሚካሄድ ጦርነት ነው። ለዚህም ነው፣ ሳውዲ አረቢያ ወታደሮቿን ወደ ባህሬን ወዲያው የላከችው (እነ ቢቢሲ ስለዚህ ጸጥ ብለዋል)። ለዚህም ነው ሱኒዎቹ ሳውዲዎች፣ ኳታሮችና ቱርኮች አሳድን ለመገርሰስ ከምዕራቡ ድጋፍ እንዲሰጣቸው የሚሯሯጡት። ምዕራቡ በማይመለከተውና በማያውቀው ጉዳይ እጁን ለማስገባት ይፈልጋል።
ንጉሥ ሰለሞን ደግሞ እንዲህ ይለናል፡
“አልፎ በሌላው ጥል የሚደባለቅ ውሻን በጅራቱ እንደሚይዝ ነው።” (ምሳ. 26፡17)
የዚህ ዓይነትም ቅሌት አለ፡
ከ መካው ጥቁር ድንጋይ ጋር ምን ያገናኘዋል?
የመካው ጥቁሩ ድንጋይ ከመለኮታዊ አመለካከት አንጻር ብዙ ምስጢራዊ የሆኑ ነገሮችን የያዘ ድንጋይ ነው። አንድ ሕንዳዊ ጓደኛየ ሰሞኑን ስታጫውተኝ፡ “ሂንዱዎች ከእስልምና በፊት ጥቁሩን ድንጋይ በተመለከተ ዓይነተኛ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡ እንደነሱ እምነትም ከሆነ፣ ከዋናዎቹ አማልክቶቻቸው አንዷ “ሺቫ” እዚያ ጥቁር ድንጋይ ውስጥ በእስር ላይ ትገኛለች ብለው ያምናሉ፡ ታዲያ ከ “ጋንጅስ” ወንዝ ውሃ ወደ መካ ወስደን ጥቁሩ ድንጋይ ላይ ብንረጭበት ሺቫ ነጻ ትወጣለች፤ በዚህ ጊዜ የእስልምና ተከታዮች ሁሉ ወይ እስልምናን ይተዋሉ ወይ እንደቅጠል ይረግፋሉ፡ ብለው ያምናሉ“. ወቸው ጉድ! ለማንኛውም፡ “ሺቫ” ፤ “ሳባ‘ን ፤ ወሃው ደግሞ ጸበልን አስታወሰኝ።
እግዚአብሔር የወደደውን፡ የኔ ነው ለሚለውና ለሚወደው ልጁ በፈለገው ጊዜ በመለኮታዊ ጥበቡ እንደሚሰጥ፡ ሰይጣንም የኔ ነው ለሚለው ስጦታውን ያበረክታል። ጥቁር ወርቅ ወይም የሰይጣን ወርቅ በመባል የሚታወቀው የነዳጅ ዘይትም አንዱ የሰይጣን ስጦታ ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? ይህን ጥቁር ወርቅ / የነዳጅ ዘይትን በበላይነት ሆኖ የሚቆጣጠረው ጥቁሩ ድንጋይ ሳይሆን አይቀርም። ዘይቱ ከወጣበት ብሎም ገበያና ግልጋሎት ላይ እስከዋለበት ወቅት ድረስ አንቀሳቃሹ ሞተር ጥቁሩ የመካ ድንጋይ ነው። ልብ ብለን ብንታዘብ ይህ ጥቁር ወርቅ ወጥቶ በግልጋሎት ላይ የዋሉባቸው አገሮች ወይ እስላም አገሮች ናቸው ወይ ከእስላም አገሮች ጋር በወዳጅነት የቆሰሉ ፤ እንደ እንግሊዝ፤ ኖርዌይ፣ ሩስያ እና ቬኔዝዌላ የመሳሰሉት አገሮች ናቸው። አሜሪካና ካናዳም ብዙ ክምችት አላቸው ነገር ግን ብዙ አያወጡም፡ ማውጣት አልቻሉም። ዘይት ወደ ሚያወጡባቸው የሰሜን አሜሪካ አካባቢዎች (ሚነሶታ፣ ማኒቶባ) ቀርብ ቀረብ የሚሉትም የእስማኤል መንፈስ ያደረባቸው ሶማሊያውያን ወይም አረቦች መሆናቸውን ማየት ይቻላል። ሚናሶታ = ማኒቶባ = ሞቃዲሾ = ሙሶሊኒ = ሙሀመድ = ሙስሊም = መናፍቅ… ኧረረ ይኽ በ “መ” ፊደል የሚጀምር ነገር መዘዘኛ ነው! ያም ሆነ ይህ፡ ካለ “ካባው” ፈቃድ ነዳጅ በማውጣት ሃብት ለማካባት የሚሞክሩ አገሮች/ሕዝቦች ጦርነት እና መተላለቅ ብቻ ነው የሚጠብቃቸው፤ ሱዳንና ናይጀርያን እንደምሳሌ መውሰድ ይቻላል። የነዳጅ ዘይት፡ አየርን፡ ውሃንና ምድሩን በሙሉ ከማበላሸቱ ሌላ የሰውን ህሊና ይበክላል፤ ያሰክራል። በናይጀሪያ ብቻ እስክ 500 ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ የዘይት ገንዘብ በግለሰቦች፤ በፖለቲከኞች ተሰርቋል፡ ነዳጁ የሚገኘው ክርስቲያኑ በሚኖርበት የደቡቡ ክፍል በመሆኑ። በሌላ በኩል ኡጋንዳ ኮሎኔል ጋዳፊ በ “ስጦታ” መልክ አበርልተውላት አንድ ትልቅ መስጊድ ካምፓላ ላይ ሰራች፣ አሁን ነዳጅ ማውጣት ተፈቀደላት።
የቀድሞዋ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ወ/ሮ ጎልዳሜየር አንድ ጊዜ ሲቀልዱ ምን ብለው ነበር፡ “ሙሴ እስራኤላውያንን ከግብጽ ባርነት አውጥቶ ወደ ከነዓን ምድር ሲወስድ፡ “ኑ የእግዚአብሔር ልጆች ይህችን ምርጥ ቦታ ልስጣችሁ፣ ምንም የነዳጅ ዘይት የላትም!” “ ብለው ነበር። አዎ! በሙስሊሞች የተከበቡ ሁለት የአይሁድና ክርስቲያን አገሮች ቢኖሩ እስራኤልና ኢትዮጵያ ብቻ ናቸው። እነዚህ አገሮች የነዳጅ ዘይት ሳይኖራቸው ቀርቶ አይደለም፡ እስራኤልን አዋሳኝ ባህር ውስጥ ብዙ የጋዝና የነዳጅ ዘይት ክምች እንዳለ ይታወቃል፡ በኢትዮጵያም ተወዳዳሪ የሌለው የነዳጅ ዘይት ሆነ የጋዝ ክምችት ተቀብሮ እንደሚገኝ አያጠራጥርም፤ ግን ማውጣት አልተፈቀደም፡ ባለሙያ የሚባሉ ወደዚያ እየተላኩ ጥናት ያደርጋሉ፡ ሁልጊዜ የሚመጡት ግን ባዶ እጃቸውን ነው፡ ግን ምን ያህል የበዛ ምድራዊ ‘ሃብት‘ እዚያ እንደተቀበረ አውቀው ከወጡ በኋል ልክ “Men In Black” ላይ እንደሚታየው የአእምሮ ማጥፊያና ማብሪያ፡ የማስታወስ ችሎታቸውን የሚያጠፋባቸው ኃይል አለ። ማን/ምን ይሆን የሚያጠፋባቸው? የጥቁሩ ድንጋይ መንፈስ? ለማንኛውም ኢትዮጵያም የነዳጅ ዘይት መኖር ጭምጭምታ የሚሰማው አካባቢው በእስላሞች ቁጥጥር ሥር በመሆኑና፡ በሸህ አላሙዲን የጥቁሩ ድንጋይ መልዕከተኛነት መስጊዶች በየቦታው ብቅብቅ ለማለት በመብቃታቸው ነው።
ጎበዝ ወገን ተጠንቀቅ! የነዳጅ ዘይት ለቅድስት አገራችን መቅሰቱን ሊያመጣባት ይችላል።
ሳውዲ ዓረቢያ የፈለገቺው ዓይነት ሰብዓዊ መብት ብትረግጥ ምዕራብ ያሉት ሃይሎች ጸጥ ነው የሚሉት፡ እነ ሂውማን ራይትስ ዋች (HW)፡ እነ ሲ ኤን ኤን ወይም ፎክስ የመሳሰሉት ድርጅቶች ገንዘባቸውን የሚያገኙት ከነሳውዲ ነው። ፕሬዚደንት ኦባማ ለሳውዲ ንጉሥ መስገዳቸው ዓለምን ሁሉ አስገርሞ ይሆናል፡ ነገር ግን ከበስተጀርባው ሌላ ነገር ስለሚኖር ወደፊት ይገለጥልን ይሆናል። አቶ ኦባማ ከእስራኤል መሪዎች ጋር ሲገናኙ የማኩረፍ ዓየንት ገጽታ አሳይተው ነው፤ ከአረቦች ጋር ግን በሞቅታ ነው። እስካሁንም ወደ የአረብ አገር፣ አፍጋኒስታን፣ ቱርክ እና ኢንዶኒዢያ ብዙ ጊዜ ሲመላለሱ እስራኤን እስካሁን አልጎበኙም፡ ኢትዮጵያንማ የሚጎበኝ የአሜሪካ ፕሬዚደንት የለም። ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ግን ሁሉም ወደ ኢትዮጵያ ነው በቅድሚያ የሚጓዙት። ምስጢሩ ምን ይሆን?
ጥቁሩ የመካ ድንጋይ ምዕራባውያኑን በጥቁሩ ወርቅ ለማሰር መኪና የሚባል ተንቀሳቃሽ ገና ዱሮ እንዲሰሩ አደረገ። የሚገርመው ከዚህ ነዳጅ ተጽእኖ ነጻ ለመውጣት ከፍተኛ ጥናት በማድረግ ላይ የነበሩትና ኤሌክትሮ መኪናዎችን በብዛት ማምረት የጀመሩት እንደ “ቶዮታ” የመሳሰሉ አንጋፋ ኩባንዮች በኢንዱስትሪያዊ አሻጥር ቴክኒካዊ ጉድለት እየፈለገባቸው በየጊዜው መመታታቸው ፤ መሬቱ እንዲንቀጠቀጥ እይተደረገባቸው ለመድከም መብቃታቸው ከዚህ ጋር የተያያዝ ሊሆን ይችላል። ልክ አውሮፕ አንዳንድ አገሮች ፈጣን መኪና የሚሰሩ ኩባንያዎች እንዳይከስሩ ፈጣን መንገዶች ላይ የኪሎሜትር ገደብ ከማድረግ እንደሚቆጠቡት፤ ከነዳጅ ዘይት ነጻ ለመሆን የሚሞክሩ ኩባንያዎች ይኮረኮማሉ።
ጥቁሩ ድንጋይ የተቀረውን ዓለም በተባበሩት መንግሥታት (UN) እና በ ኦፔክ (OPEC) በኩል እየተቆጣጠረ ነው። 52 የዓለም እስላም አገሮች አባላት በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ የሚያካሄዱትን እንቅስቃሴ በጥሞና ብንከታተል ብዙ ነገር ሊያሳየን ይችላል።
ኒው ዮርክ ከተማ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጽሕፈት ቤት ህንፃ ውስጥ፡ ስዕሉ ላይ የሚታየውን ሳጥን ቅርጽ ያለው ጥርብ ድንጋይ የያዘ ክፍል አለ፤ ይህም ክፍል “ጸሎት ቤት” የሚል ስም ተሰጥቶታል። ይህን 6.5 ቶን የሚመዝን “ጥቁር” ድንጋይ ያሰሩት የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ (1953 – 1961፟)፡ የስዊድን ተወላጁ Dag Hammerjsköld ናቸው። እንደ እሳቸው ከሆነ “ይህ ሳጥን የሁሉም ሰው አምላክ ነው” የዚህ ክፍል መግቢያ 18 ጫማ ስፋት አለው፡ በቁጥር ጥናት 18 = ሦስት 666 ነው። ክፍሉ ግርግዳ ከፊት ለፊት የተለያዩ አብስትራክት ስዕሎች ይታያሉ፡ አንዱ ላይም ዘንዶ ይታያል። ይህን ክፍል የጎበኙ አንዳንድ ታዛቢዎች በጣም የሚስብና ማግኔታዊ የሆነ ነገር ከጥቁሩ ድንጋይ እንደሚፈልቅ፡ ክፍሉም የሚቀፍ መንፈስ ውስጥ እንደሚከት ይናገራሉ። የዓለም መሪዎች ከእዚህ ዓይነት ቦታ ነው ብቅ ጥልቅ የሚሉት። ወስላታው ኮፊ አናንን ከስዊድናዊቷ ሚስታቸው ጋር የጋብቻ ስነሥርዓት የፈጸሙት እዚህ ክፍል ውስጥ ነበር።
በነገራችን ላይ፡ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጽሕፈት ቤት ከኒው ዮርክ ተነስቶ ወደ አዲስ አበባ እንዲዛወር አንዳንድ የዓለም መሪዎች ጥሪ አቅርበው ነበር።
ለተጨማሪ መረጃ እዚህች ላይ ይጫኑ
____________________________________________
Eden H said
betam yigermal. thanx
addisabram said
As F1s Sebastian Vettel would say, “That’s What I’m Talking About!” . Oil could be a curse, therefore, Instead of Oil and Co, Africa, Ethiopia in particular, should do more in the agriculture sector. The world will soon go thirsty and hungry, and organic food, and the traditional private Ethiopian farming system could be the only solution — if, of course, everything is done in an effective and developed manner.
AfDB Chief Warns Resource Curse May Lead to Civil Wars
http://allafrica.com/stories/201206060097.html
–More and more countries in Africa are discovering oil, recently. It is part of the 122 billion barrels of oil that experts from the AfDB estimate the continent to possess in proven reserves as well as 500 trillion cubic feet of natural gas deposits, estimated to be worth 605 billion dollars.
–Discovering oil in Ethiopia is within reach, according to reliable sources
–Africa’s real hidden treasury is not oil, not gas, not rare minerals, but its youth, its demographic dynamics,