Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • May 2012
  M T W T F S S
   123456
  78910111213
  14151617181920
  21222324252627
  28293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Archive for May 1st, 2012

ቅዱስ ጊዮርጊስ – ተአምራታዊ ኃይላቸውን የገለጹ ጽላቶች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 1, 2012

 

በደቡብ ጎንደር ሃ/ስብከት በፋርጣ ወረዳ በጋሣይና በክምር ድንጋይ መካከል የሚገኘው ጥንታዊው የድድም ደብረ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የካቲት 19 ቀን 1982 .. ከቀኑ 3 ሰዓት በሰው ሠራሽ መሣሪያ ከተቃጠለ በኋላ የአጥቢያው ካህናትና ምእመናን አዲስ ለሚሠራው ቤተ ክርስቲያን ቦታ በመቆፈር ሲያደላድሉ የቅ/ጊዮርጊስ፥ የኪዳነ ምሕረት፥ የቅ/ሚካኤል፥ የታቦተ ጽዮን የታቦተ ሩፋኤል ጽላቶች ጥላሸት ሳያርፍባቸው በተአምር መገኘታቸውን ከሰበካ ጽ/ቤት ለመረዳት ተችሏል።

ይህ ቤተ ክርስቲያን የተተከለው በ13ኛው ክፍለ ዘመን ሲሆን ለአራት ጊዜ ተሠርቶ አምስተኛው የተቃጠለው ቤተ ክርስቲያን እንደ ነበር በዕድሜ የገፉ የታሪክ ባለቤት የሆኑ አባቶች ይናገራሉ፤ ቤተ ክርስቲያኑ እንደተቃጠለ ቢቀር የሰበካ ክርስቲያኖችን ብቻ ሳይሆን መላ ምእመናንን የሚያሳዝን እንደሆነ በመገመት አዲስ ቤተክርስቲያን በአራት ዓመታት ሥራው ተጠናቆ ሚያዝያ 23 ቀን 1988 .. ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል። ለዚህም ቤተ ክርስቲያን አቶ ዓለማየሁ የአምር ከሃያ ሺህ ብር በላይ የሚገመት አንድ የብረት መንበር ሰጥተዋል።

በዚህ ቤተክርስቲያን ቀደም ያሉ አባቶች እንደሚናገሩት የተለያዩ ተአምራት ይነገሩበታል፡ በቦታውም የሚገኙ ሕሙማን ይድኑበታል፣ ሥዕለት ሰሚ በመሆኑም ክርስቲያኖች የለምኑትን ያገኙበታል አንዳንዶችን ለመጠቆም ያህል ከአንድ ድንጋይ ላይ ጐማዳ መስቀልና ትልቅ ጭራ እንደተገኘ በየጊዜው ይተረካል። ከዬት አቅጣጫ እንደመጣ የማይታወቅ ጠበል ከጭንጫ ላይ ይወርዳል፡ ሕመምተኞች በዚህ ጠበል ተጠምቀው አፍጡነረድኤት ተደግሞላቸው በጐማዳው መስቀል ሲታሹ ከልዩ ልዩ በሽታ የሚድኑ ሕመምተኞች ሥፍር ቁጥር የላቸውም።

በተለይ በየዓመቱ በዚህ በዛሬው እለት፤ በሚያዝያ 23 ቀን የቅ/ጊዮርጊስ ጽላት በክብር ታጅቦ በመውጣት ጠበሉ ስለሚባረክ በበዓሉ የሚገኙት ሁሉ ሰለሚጠመቁ የተለየ ሀብተ በረከትና ፈውስ ይታያል፡ የሚገኙትም ምእመናን ከክብረ በዓሉ ሲመለሱ በየደረሱበት ቦታ መንፈሳዊ ዜናውንና ተአምራታዊ ታሪኩን ይመሰክራሉ።

የአረጋዊው መነኩሴ እንባዎች

በስድሳዎቹ ዓመታት ውስጥ አንድ አረጋዊ መነኩሴ እስክንድርያ ስፓርቲንግ ውስጥ ወደሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አዘውትረው ይመጡ ነበር። እኚህ አረጋዊ መነኩሴ ቅዳሴው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፊታቸውን በሁለት እጃቸው በመሸፈን ምርር ብለው ያለቅሱ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ይህ ሁኔታውን የተመለከተ አንድ ወጣት ከቅዳሴ በኋላ በመኪናው ወደ ዘመዶቹ ይዟቸው ይሄድና ከእነዚህ እንባዎች በስተጀርባ ያለውን ምክንያት አጥብቆ ይጠይቃቸዋል።

አረጋዊው መነኩሴም ለወጣቱ እንዲህ አሉት፦ በወጣትነት ዘመኔ ከሴት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አልነበረኝም፤ የተሳሳተ ስሜትም አላውቅም ነበር። በቅድስናና በንጽሕና መኖር ያስደስተኝ ነበር። ወደ አንድ ገዳም ገብቼም በእውነተኛ ደስታ ውስጥ እኖር ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ስለ ታመምሁ በገዳሙ ውስጥ ያሉት ሰዎች ወደ ሆስፒታል መሄድ እንዳለብኝ አጥብቀው ጠየቁኝ። በሆስፒታሉ ውስጥ ሳለሁም አንዲት ነርስ እንደ አባቷ አድርጋ ትንከባከበኝ ነበር እንክብካቤዋ እየጨመረ ሲመጣም የረከሱ አሳቦች በሕሊናዬ ይመላለሱ ጀመር። በዚህ ጊዜ ከሆስፒታሉ እንዲያስወጡኝ ግድ አልኋቸው። ከዚህ ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ ዘወትር ስለ ድካሜ እያለቀስሁ ነው። ከእንግዲህ በኋላ ድጋሚ እንዳልወድቅም ኃጢአቱን ከፊቴ አስቀምጬዋለሁ።

ወጣቱም ለአረጋዊወ መነኩሴ እንዲህ በማለት ይጠይቃቸዋል፦ እነዚህ አሳቦች የተከሰቱት ከብዙ ዓመታት በፊት ነው። ታዲያ አሁን ይህን ሁሉ እንባ ማፍሰስ ለምን አስፈለገ?”

የእኔ የረከሱ አሳቦች የወደደኝንና እስከ አሁን ድረስ የሚወደኝን ጌታዬን አሳዝነውታልና ለምን አላለቀሰም? ዘላለማዊነቱ እጅግ ውድ ስለሆነች በእግዚአብሔር ዘንድ ያለኝን ክብር እንዳላጣ እሰጋለሁ።

እንባዎችዎ ሰላምዎትን አያስጡብዎትም?”

እንባዎቹ በደስታና በሰላም ይሞሉኛል፤ ሰላምንም በአባቱ እቅፍ ውስጥ ስፍራ ባዘጋጀልኝ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ያድሉኛል።

አቤቱ ጌታ ሆይ፦ ንጹሕ እንባዎችን አድለኝ።

የንስሓ እንባዎቼን ከደስታ ዕንባዎቼ ጋር ቀላቅላቸው።

ኃጢአቶቼንና ድካሞቼን ሁልጊዜ አስባቸዋለሁ።

የአንተንም ታላቅ ፍቅር ዘወትር አስታውሳለሁ።

የአንተ መንፈስ ደስታና ሰላምን ያጎናጽፈኛል።

በእውነተኛ የንስሓ እንባዎች ልቤን ደስ አሰኛት።

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: