Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2012
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    272829  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 5, 2012


ሞኑን በአዲስ አበባ ከታዘብኳቸውና አሳሳቢ ሆነው ካገኘኋቸው ነገሮች መካከል፡ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን የሚክዱ፡ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ የጥላቻ መርዝ የሚረጩ ኃይሎች በተጠናከረ መልክ እየተነቀሳቀሱ መሆናቸውን ነው። በተለይ የፕሮቴስታንት እና የሙስሊሙ ማሕበረሰቦች የኢትዮጵያን ታሪክ ከልሰው በመጻፍ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻቸውን በጽሑፍና በቪዲዮ መልክ በየቦታው በማቅረብ ላይ ናቸው።

ለምሳሌ ወደ መርካቶ ጎራ ብላችሁ በአኑዋር መስጊድ አካባቢ የሚገኙትን መጻሕፍት መሸጫ መደብሮች ብትቃኙ በጣም ከእውነት የራቁና ዑዑ! የሚያሰኙ ጽሑፎችን በቀላሉ ተደርድረው ማየት ትችላላችሁ፤ ከነዚህም ውስጥ የክርስትና እምነትን የሚያጠቁ፣ የክርስቶስን ክብር ዝቅ የሚያደርጉ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያንን የሚያጥላሉ፣ ጀግኖች እና አኩሪ የነበሩትን ቅድመ ኢትዮጵያውያን ታሪክ የሚያንቋሽሹ፣ አብዛኞቹም በአርብ አገሮች የድጎማ እርዳታ ተተርጉመው የቀረቡ ጽሑፎች፣ ጋዜጦች፣ ካሴቶችና ቪዲዮዎች ይገኙበታል። ስለ እራሳቸው እምነት ወይም ታሪክ (ከሌላው ኢትዮጵያዊ የተለየ ታሪክ ካላቸው) ለሽያጭ ከሚቀርቡት ጽሑፎች እስላም ስላልሆነው ዕምነት እና ታሪክ የተጻፉት መጻሕፍት በተለይ ጸረክርስትያን የሆነው መጽሐፍ ቁጥር ይበዛል ብል አላጋነንኩም።

በውዲቷ አገራችን አሁን ይህ እንዴት ሊከሰት ቻለ?

በሰፊዋ ዓለማችን ስንኖር በየቦታውና በአካባቢያችን የሚደረገውን እንቅስቃሴ፡ የምናየውን የማናየውን ነገር የምንከላከልበት ሁለት ምድብ አለን። በቀድሞ ኢትዮጵያውያን የማቲማቲክ ዓለም የሚታወቀው ይህ መንትያዊ (dual) ምድብ፦ ሞትና ሕይወት፤ ማግኘትና ማጣት፤ ደስታና ሐዘን፤ ኔጋቲቭና ፖሰቲቭ፤ ፍቅርና ጥላቻ፤ የተማረና ያልተማረ ድሃና ሀብታም፤ እምነት ያለውና የሌለው ወዘተ እያልን ዙሪያችን ያሉትን ክስተቶች መቁጠር እንችላለን።

ያለፈው 20ኛ ምዕተ ዓመት በፖለቲካዊው ርዕዮትዓለም ላይ ትኩረት አድርጎ የቆየ ዘመን ሲሆን የያዝነው የ21ኛው ምዕተ ዓመት ደግሞ ሃይማኖታዊ ሕይወት ከፍተኛ ሚና የሚጫወትበት ዘመን እንደሆነ ሁላችንም የምናየው ነው። አሁን፡ ጥሩው ከመጥፎው፣ ሐቁ ከውሸቱ ተበጥሮ የሚወጣበት ጊዜ ስለሆነ፡ ከምንጊዜውም በላይ በሐቅ ላይ ከፍተኛ ዘመቻ በመካሄድ ላይ ነው። ፖለቲከኞች፤ ባለሥልጣኖች እና የዜና ማሰራጫዎች በሐቅ ላይ የሚካሄደውን ዘመቻ በረቀቀ መልክ ተያይዘውታል። የሰው ልጅ ባብዛኛው መንፈሳዊ የሆነ ፍጡር ነውና ትኩረቱ የተደረገው በተለይ እምነትን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ነው።

ዓለማችን ከእምነት አመለካከት አኳያ በሁለት ሰፊ ክልሎች ትከፈላለች፤ እነርሱም በጥቅል ሲገለጡ የፈጣሪን አምላክ መኖር የሚቀበልና የሚያመልክ እንዲሁም የፈጣሪን መኖር የማይቀበልና የማያመልክ በማለት ልንለያያቸው እንችላለን።

በዚህች ዓለም ለሰው ልጅ እውነተኛውን የሕይወት ትርጉም የሚያስጨብጥ መልእክት አለን የሚሉ እምነቶች በርካታ ቢሆኑም እንደምሳሌ አድርገን የምንወስዳቸው ክርስትናና እስልምና ናቸው። በእነዚህ ሁለት እምነቶች መካከል የማያቋርጥ ፍልሚያ ሲካሄድ ቆይቷል። ሁሉም እምነቶች የሰውን ልጅ ከተዘፈቀበት የኃጢአት ማጥ ውስጥ የሚያወጣው የምሥራች አለን በማለት የየበኩላቸውን እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ቆይተዋል፤ እያደረጉም ነው።

የሌላውን እምነት ዝም ብሎ ከማጥላላትና ከማራከስ ይልቅ ሌላው እምነቴ፤ ዓላማዬ ብሎ የያዘውን እምነት በጥሞና ከመረመሩ በኋላ ምርቱን ከግርዱ፤ ፍሬውን ከገለባ፤ እውነቱን ከስህተት መለየት የእውነተኛነትና የትክክለኛ ዳኝነት ዓየነት ባሕርይ ነው።

አገራችን ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ዕድሜ እና አኩሪ ታሪክ ያላት ቀደምት ከሚባሉት ሀገራት ተርታ የምትመደብ ሉዓላዊት አገር ናት። የኢትዮጵያ መንግሥት እስከ ልደተ ክርስቶስ 1000 ድረስ ህልውና ስለነበረው ኢትዮጵያ 2 ሺህ የሕገ ልቡና ዘመናት 3 ሺህ ዓመታት በብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን እምነት በድምሩ የ5 ሺህ የነፃነት እድሜ ይቆጠርላታል።

በሃይማኖትም በኩል በዘመነ ኦሪት ብሉይ ኪዳንን እንደተቀበለች ሁሉ ሐዲስ ኪዳንንም ለመቀበል የቀደማት አገር የለም። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስረጅነት (ሐዋ. 8:26) የክርስትና ሃይማኖት ወደ ኢትዮጵያ የገባው ወንጌላዊው ቅዱስ ፊልጶስ ኢትዮጵያዊውን ጃንደርባ ባጠመቀው ጊዜ ነው። ይህም በ34 .ም መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሁለት ሺህ ዘመን ታሪክ ያላት እንደመሆኗ ታሪኳ ከአገራችን ኢትዮጵያ ታሪክ ጋር በእጅጉ የተሰናሰለ አንዱን ካንደኛው ለመለየት የሚያዳግት ነው። ቤተክርስቲያኗ ለአገራችን ያበረከተችው አስተዋጽኦ ብዙ ነው። ከነዚህም ሙሉ ትምህርት፣ ፍጹም ቋንቋ ከነፊደሉ፣ ሥነ ጽሑፍ ከነጠባዩና ሙያው፣ ኪነጥበብ በየዓይነቱ፣ ሥነ ጥበብ በየመልኩ፣ ታሪካዊና ጥንታዊ ቅርስ፣ እምነት ከነፍልስፍናው፣ ነፃነት ከነክብሩ፣ አንድነት ከነጀግነነቱ፣ አገር ከነድንበሩ ከነፍቅሩ ወዘተ፤ አሁንም ቢሆን ትውልዱ አገር ወዳድነትን፣ ለባህልና ለሃይማኖት ተቆርቋሪነቱን ይዞ እንዲያድግ በማስተማርና በማበረታታት ቤተክርስቲያን የበኩሏ ድርሻ አላት። ዛሬ ኢትዮጵያ በበጎ ጎኗ ስትነሳ እንግዳ ተቀባይነቷ፣ የሕዝቦቹ ሰውን አክባሪነትና ትሕትና አብሮ መነሳቱ ከቤተክርስቲያኗ ትምህርት የተነሳ ነው።

በእርግጥ ይህ የሰላም መሻትና እንግዳ ተቀባይነት ባህል አሁን ለሚታየው የእምነት ምስቅልቅል አስተዋጽኦ ስላደረገ ጎጂ ጐን እንደነበረው የተገነዘብነው ዘግይተን ነው።

በሌላ በኩል ከዚህ በተለየ መልኩ ፍጻሜው እልቂትና ሽብር የሆነ አክራሪ የእስልምና እንቅስቃሴ ነበር። የአክራሪዎች እንቅስቃሴ የጀመረው ድሮ በአክሱም ዘመነ መንግሥት ጊዜ ነው። አቀነባባሪዎቹ አንድም በዘር ኢትዮጵያዊ ሆነው ለጥፋት ራሳቸውን በቅጥረኝነት የመለመሉ አልያም ኢትዮጵያንና መታወቂያዋ የሆነውን ክርስትናን ለማጥፋት ከኋላ ሆነው ነገሮችን የሚያቀነባብሩ፣ መሳሪያ የሚያስታጥቁ አረባውያን ናቸው።

አገራችን ኢትዮጵያ አሁን ላለንበት ዘመን የደረሰችው ያለ መታደል ሆኖ ብዙ ውጣ ውረዶችን አልፋ፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ጦርነቶች አስተናግዳ ነው። የቀድሞ ነገሥታትም ዘመነ መንግሥታቸው የሚያልቀው ከወራሪ ጠላት ጋር በመዋጋት ነበር። ስለሆነም አገራችን ግዛቶቿንና ሕዝቦቿን (ሱዳን፣ ሶማሊያ፤ ኤርትራ) ቀስበቀስ እንድታጣ፡ በሥልጣኔ የኋልዮሽ እንድትጓዝና በኢኮኖሚ ኋላ ቀር እንድትሆን ተገድዳለች። ከታሪክ እንደምንረዳው አብዛኞቹ ጦርነቶች የተከፈቱብን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በአረባውያን አገራት፡ በተለይም ከግብጽ፣ ከየመን፣ ከሱዳንና ቱርክ ኃይሎች ነው።

የቀድሞ ነገሥታት በእስልምና ስም ድንበር እየዘለሉ የኢትዮጵያን ምድር ለመቁረስ ካሰፈሰፉ እስላም አክራሪዎች ጋር በየዘመኑ እጅግ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያዎችን ሲያደርጉ ኖረዋል። ውድ ሕይወታቸውን ለአገራቸው ዳር ድንበር መጠበቅ ሲሉ ሰውተዋል። በተለይ የግብፅና ሱዳን አክራሪ እስላማውያን ኃይሎች በአገራችን ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት አድርሰዋል። ደቡብ አረቢያና ቱርክ ደግሞ ድንቅና ትጥቅ በማቅረብ፣ ለአሸባሪ ኃይሎች ወታደራዊ ሥልጠና በመስጠት፣ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ ፀረኢትዮጵያዊ አቋም የነበራቸው አገራት ናቸው።

የታሪክ ድርሳናትን ስናገላብጥ በየጊዜው የተደረጉ የአክራሪ እስልምና ዘመቻዎች ሲመሩ የነበሩትን፦ የአህመድ በድላይን (ግብጽ) የመሀፉዝን (የመን) የኑር መጀሀድን (ግብጽ) ስሞች በዋነኝነት እናገኛለን። በሌላ ወገን የአክራሪ እስላሞችን እንቅስቃሴ ከተጋፈጡ ኢትዮጵያውያን ነገሥታት ውስጥ፦ ንጉሥ ላሊበላ፣ አፄ አምደጽዮን፣ አፄ ዳዊት፣ አፄ ቴዎድሮስ ቀዳማዊ፣ አፄ ይስሃቅ፣ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ፣ አፄ በእደ ማርያም፣ አፄ ናዖድ፣ አፄ ልብነ ድንግል፣ አፄ ገላውዲዮስ፣ አፄ ሠርፀ ድንግል እና አፄ ዮሐንስ ይገኙበታል።

አፄ ዮሐንስ በግራኝ አህመድ ወረራ የጠፋውን ሀገር ለማቅናት አገሩን ሁሉ ሲያስሱ የወሎውን ባላባት መሐመድ ዓሊን አገኟቸው ከዚያም ወደ ጥንቱ የአባት እናታቸው የቅድመ አያቶቻቸው እምነት ተመለሱ፤ ንጉሠ ነገሥቱ ራሳቸው የክርስትና አባት ሆነው አስቀመጧቸው። “ሚካኤል” የሚል ስም ተሰጥቷቸው በባለሟልነት ተስማምተው ኖረዋል።

አሁን አሁን አክራሪ እስላሞች ሰላማዊውን ክርስቲያን በግፍ ለመጨፍጨፋቸው እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት “አፄ ዮሐንስም በእኛ ላይ እንዲሁ አድርጐብናል” በማለት ነው። እነሱ ይህን ይበሉ እንጂ ኢትዮጵያዊው የታሪክ ምሁር ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ እ... 1991 .. ባሳተሙት መጽሐፍ (A History of Modern Ethiopia: 1855-1991) ገጽ 48 ላይ የሰፈረው ታሪክ እንዲህ የሚል ነው፦

አፄ ዮሐንስ ከቦሩ ሜዳ የሃይማኖት ጉባኤ በኋላ ሁለት አዋጆችን አወጡ። የመጀመሪያው “የጸጋና” “የቅባት” ኑፋቄ የሚከተሉ ይህንን እንዲያስተምሩ የሚከለክል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እስላሞች ወደ ክርስትና ዞረው እንዲጠመቁ የሚያዝ ነው። (ይህ ሁኔታ ወደፊትም ቢሆን መደገሙ አይቀሬ ነው)። አዋጁን የተላለፉ እስላሞች እንኳን ቢኖሩ የጭፈጨፋ ድርጊት ፈጽሞ አልተፈጸመባቸውም።

እንዲያውም አስገራሚው እውነታ በእንግሊዟ ለንደን Public Records Office F 095-738-12-99 ተጠብቆ በሚገኝ ሰነድ ላይ የሰፈረው በእርሳቸው ዘመነ መንግሥት ከእስልምና ወደ ክርስትና የመጡ አብዛኛዎቹ በፈቃዳቸው መሆኑን ነው። ምክንያቱም በግራኝ ወረራ ጊዜ ተገደው ሃይማኖታቸውን እንዲለውጡና እንዲሰልሙ ተደርገው ስለነበር ነው።

የጥንቱ “ቤተአምሐራ” የዛሬው “ወሎ” በግራኝ አህመድ ወረራ በግዳጅ እስከሰለመበት ድረስ ጥንተ መሠረቱ ክርስትና ነው። ይህ ሕዝብ በግራኝ ዘር ማንዘሩ በግፍ የተጨፈጨፈበት አለዚያም ተገዶ የሰለመበት መሆኑን የተረዳ ስለነበር የአፄ ዮሐንስን መንግሥታዊ አዋጅ ተቀብሎ ወደ ቀድሞ ዘመዶች እምነት፡ ወደ ክርስትና ተጠምቆ ተመለሰ። ታዲያ የዘመናችን አሸባሪዎች የእምነት ወንድሞቻቸው ለፈጸሙት ጽንፈኛ ተግባር ይቅርታ ጠይቀው፡ ንስኅ ገብተው እንደመኖር የሙት አጥንት ያለምንም ታሪካዊ ማስረጃ በመውቀስ ላይ ይገኛሉ። እኛስ በተረዳ ነገር አፄ ዮሐንስ ታላቅ የአገራችን መሪ ነበሩ እንላለን። ሌሎቹም አፄዎች በሃይማኖት ማስለወጥ ጉዳይ አንድም ሰው እንዳልገደሉና መንደርም እንዳላቃጠሉ አያሌ ማስረጃዎች አሉ። እንዲያውም አንድ እስላም ክርስትናን ለመቀበል እድሉን ሳያገኝ ለሞት እንዲጋረጥ አይፈልጉም ነበር፡ ነፍሱ ለዘላለሙ እንደምትጠፋ ይታወቃቸዋልና።

አፄ ምኒልክ በዘመነ መንግሥታቸው ወሎ ድረስ መጥተው በታላቅ ሥነ ሥርዓት ለቀድሞው የወሎ ባላባት መሐመድ አሌ የንግሥና ማዕረግ በመስጠት “ራስ ሚካኤል” ብለው ሾሟቸው። ከዚህም በኋላ ሚካኤል በራስነት ማዕረግ ወሎን ማስተዳደር ያዙ። በሰላሙ ዘመን ሠርተው ካቆዩልን ቅርሶች መካከል “አይጠየፍ” ይገኝበታል። ንጉሡ ግብር ሲያበሉ ሕዝቡን የሚጋብዙበት አዳራሽ ነው። በዚህ እጅግ ግዙፍ አዳራሽ፡ በ21ኛው ክፍለዘመን በአረብ አገር በወገን ላይ እንደሚደርሰው አድሎ ሳይሆንና ትልቅ ትንሽ፣ ድሃ ሃብታም፣ እስላም ክርስቲያን፣ ሳይለይ ሁሉም በእኩልነት ይስተናገድበት ነበር። “አይጠየፍ” መባሉም ስለዚህ ነው። ንጉሥ ሚካኤል እስከዚህ ድረስ ሁሉን በእኩልነት የሚያስተዳደሩ ቅን መሪ ነበሩ። የሀገሪቱ ዳር ድንበር ሲደፈር ደግሞ በተለያዩ የጦር ግምባሮች (የአደዋን ጨምሮ) በመዝመት ከሌሎች ስመጥር ጀግኖች ጋር በጀግንነት ጠላቶችን የተፋለሙ ናቸው። ታዲያ ለእኝህ ስመ ጥር ንጉሥ በሚለኒየሙ ወሎ ሃውልት ታቁምላቸው ሲባል ሙስሊሙ ተለይቶ ተቃውሞውን አሰማ።

አንድ እምነት ሌላውን በእምነት ከቦ ያለውን ያህል ክርስትናም ቁጥራቸው በጣም በርካታ በሆኑ ሌሎች እምነቶች ተከቧል። ከእንዲህ ዓይነቱም መከባበብ (የአንዱ ሌላውን መክበብ) የተነሳ አንዱ ለሌላው እውነቴ፣ እምነቴ፣ ዓላማዬ ብሎ ያከበረውን እምነቱን ለማካፈል ሲጥር መቆየቱ የሚታወቅ ነው። በመሆኑም ሰዎችን ሁሉ የሚያድነውን አስደናቂ እውነት ይዣለሁ የሚል ክርስቲያን ሁሉ በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሁሉንም በአንድነት የተቀበለች እንደመሆኗ የኛ ብለን የያዝነውን እውነት ከዚህ እውነት ለራቁ ሰዎች ማካፈሉ በዚህ ዘመን የሁላችንም ኃላፊነት ሆኖ ነው መወሰድ ያለበት። ክክርስቶስ መራቅን የመሰለ በጣም አሳዛኝና አስከፊ የሆነ ነገር የለምና፣ ከክርስቶስ ማዳን ርቀው ክፉ በሆነችው በዚህች ዓለም የጥፋት አካሄድ ውስጥ የሚገኙትን መድረስ ከምንግዜውም በላይ አሁን በጣም አስፈላጊ ነው።

አንዳንዶች ተከራካሪዎችንም ውቀሱ፥ አንዳንዶችንም ከእሳት ነጥቃችሁ አድኑ(ይሁዳ 122)

 

___________________________

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: