Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2012
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    272829  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for February 1st, 2012

በባዶ እግሩ ከሚሄደው ተጠንቀቅ፤ ጫማ ያገኘ እለት ይረግጥሃል።

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 1, 2012

ርዕሱ ላይ ያለው ይህ አባባል የሚመለከተው ሳውዲ ዓረብያን ነው። ሳውዲ ዓረብያ በነዳጅ ዘይት ከመስከሯ በፊት የገንዘብ ምንጯ ከመካና መዲና የሚገኘው የሃጅ ንግድ ብቻ ነበር። ዘይቱ ባይወጣ ኖሮ ልክ እንደ ሶማሊያ፣ የመንና አፍጋኒስታን ዓይነት አገር ትሆን ነበር።

አሁን ግን ሳውዲ አረቢያ ገንዘብ አላት፣ ብዙ የዘይት ዶላር። በዚህ ገንዘብ ለስጋቸው ብቻ የሚኖሩትን ሀይሎች በቀላሉ ለመቸብቸብ በቅታለች። ፖለቲከኛውን፣ ፕሬዚደንቱን፣ ሚንስትሩን፣ ዲፕሎማቱንና ስፖርተኛውን እንደ ጫማ ትሸምታለች። በውጥንቅጧ ዓለማችን ውስጥ የሚሽሎከለኩት እነዚህ  ጭስ ያለቀባቸው ባለሥልጣናት በሳውዲ አረብያ ስለሚፈጸመው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ምንም ነገር እንደማያውቁ፡ ዓይኖቻቸውን እንዲጨፍኑና ዝም እንዲሉ ተደርገዋል።

የክርስቶስን ልደት በጂዳ ከተማ ለማክበር ተሰባስበው የነበሩት 35 ኢትዮጵያውያን (29 ሴቶች እና 6 ወንዶች)ተጨናንቀው ከሚኖሩበትና ከሚጸልይቡት ቤታቸው በፖሊስ እየተደበደቡ ወደ እስር ቤት እንዲገቡ ከተደርጉ ያው ወር አለፈው።

በእሥር ቤት ቆይታቸው ከሳውዲ ፖሊስ፡ ስድብ፣ ግርፊያና ውርደት በየቀኑ ይደርስባቸዋል። የእጅ ጓንት ያደረጉ ፖሊሶች ተራ በተራ እየዞሩ በኢትዮጵያውያኑ ሴቶች ኅፍረተ-ሥጋ ላይ እጅግ ዘግናኝ፣ አሳፋሪና ዲያብሎሳዊ የሆነ ተግባር ይፈጽማሉ። ሴቶቹ በአካል እንዲታሙ መንፈሳቸውም እንዲረበሽ ተደርጓል።

ለመሆኑ የወገኖቻችን ጥፋት ምን ይሆን? ክርስቲያኖች በመሆናቸው? የክርስቶስን ልደት ቤታቸው ውስጥ ስላከበሩ?

ከታሰሩት ወንድሞቻችን መካከል አንዱ ዝርዝር ሁኔታውን እንደሚከተለው ይገልጻል፡

“አንድ ከፍ ያለ-ማዕረግ ያለው ጸጥታ “አስከባሪ” “እናንተ እምነት የሌላችሁ እንስሶች ናችሁ።” ( ትዝብቱ የኔ ነው) ቀጠል አድርጎም፡  “እናንተ የአይሁዶችና የአሜሪካ ደጋፊዎች ናችሁ።” ( የንጉሱን ቤተሰቦችስ የምትጠብቀው ማን ናት? አሜሪካ አይደለችምን? ትዝብቱ የኔ ነው።)

ለመሆኑ እዚህ ላይ ማነው እንስሳው? 100 ቢሊየን ዶላር የሚያወጣ የጦር መሣሪያ ከአሜሪካን የሚገዛው ማን ነው? ከትዊተር እስከ ሲ ኤን ኤን እነሱ ያልገቡበት የአሜሪካ ባለ አክስዮን ድርጅት የለም!

“እኛ ሁሉንም እንወዳለን፡ አምላካችን እያንዳንዱን ሰው እንድንወድ ነው የሚያስተምረን! ብለን መለስንላቸው” አለ፡ ይህ እስር ቤት የሚማቅቀው ጀግና ወገናችን።

አዎ! ይህ የአብርሃም፣ የይስሐቅና ያዕቆብ አምላክ፡ አመጸኛ፣ ጨካኝ፣ ሴቶችን የሚያንቋሽሽ የሻሪያ ባርነትን የሚፈቅድ አምላክ አይደለም።  ሙስሊሞች “ኢሳ” ብለው ቁራአናቸው ላይ ያስቀመጡት በምንም ተዓምር የመጽሐፍ ቅዱሱ እየሱስ ክርስቶስ ሊሆን አይችልም። “ኢሳ በኛ ዘንድ እጅግ በጣም የተከበረ ነው” እያሉ “የኢሳ ተከታዮች” የሚሏቸውን ክርስቲያኖችን በአድሎ መለየት፣ መግረፍና መግደል ምን ሊባል ይችላል? “ክርስቲያን ኢትዮጵያ ለነብያችንና ተከታዮቹ ከፍተኛ ውለታ የዋለች አገር ናት” እያሉ የኢትዮጵያን ልጆች እንደ ውሻዎቻቸው ማስቃየት፣ ማጎሳቆልና ደማቸውን ማፍሰስ ምን ሊባል ይችላል?

በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በወገኖቻችን ላይ በየአረብ አገሩ የሚደርስባቸውን በደል ፈጽሞ ዝም ብለን ልናልፈው አይገባንም።

እነ ቢቢሲ፣ ሲ ኤን ኤን፣ አልጀዚራ ወይም ኒውዮርክ ታይምስ ዜናዎቹን ደግመው ድጋግመው እስኪያቀርቡልን እጆቻችንን አጣጥፈን ቁጭ ልንል አይገባንም።

በተለይ በአሜሪካና አውሮፓ ተንደላቅቆ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ አጋጣሚው ሁሉ ስላለው በዚህ መሰሉ ድርጊት ላይ ሊያስብበት፣ ሊወያይበት ብሎም መፍትሄ ሊያገኝበት ይገባል።

ይህ አሳዛኝና ረባሽ ሁኔታ፣ ከጓዋንታናሞ ወይም ጋዛ በከፋ ሁኔታ ሰብዓዊ መብት የተረገጠበት ሁኔታ ተደርጎ ነው ሊወሰድ የሚገባው። እነዚህ እህቶቻችን ማንንም ያልተፈታተኑ፣ ኑሮአቸውን በሰላማዊ መልክ በመግፋት ነፍሳቸው ላይ ታላቅ ፈተና የሚደርስባቸው ተጠቂዎች ናቸው። ስለሆነም በተለይ ከኢትዮጵያ ውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ነኝ ባይ ሁሉ እስራኤል ውስጥ መዘነጫ ቤት ለመግዛት በመመኘት አድሎ በተደረገባቸው ጥቁር እስራኤላውያን ላይ ሳይሆን ትኩረቱን በይበልጥ ማድረግ ያለበት፣ በኢትዮጵያዊነቱና በክርስቲያናዊ ሕይወቱ በአረብ አገር ያለተቋረጠ ስቃይ ላይ በሚገኘው፣ እንደባሪያና እንስሳ በሚቆጠረው ኢትዮጵያዊ ወገኑ ላይ መሆን አለበት።

ዓለማችን በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያኖች በኩል እንደምትፈተን ሁሉ፣ እኛ ውጭ ያለነው ኢትዮጵያውያንም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያኖች በምናሳየው ፍቅር ወይም ተግባራዊ ሥራ፡ እንፈተናልን። እነዚህ ኢትዮጵያውያን ለስጋቸው ብቻ ለመኖር ባለመሻት ክርስትናቸውን ሳይከዱ፣ ስሞቻቸውን ሳይቀይሩ ባጠቃላይ ፈጣሪ የለገሳቸውን ውድ ክርስቲያናዊ መንፈስ ሳያባክኑ፡ ሳይሸጡ ለዚህ ውርደት መብቃታቸው በእግዚአብሔር ዘንድ ለፃድቃን የሚገባ ከፍተኛ ዋጋ ያገኙበታል። ብዙዎቻችን በአውሮፓ ወይም አሜሪካ ያለነው ግን፡ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ፣ ወደንም ሆነ ሳንወድ ቅዱስ መንፈስ ለራቃቸውና የአውሬው ቱጃር ለሆኑት ለአብዛኞቹ የካውካስ ዘር ልጆች፡ ነፍሳችንን  “እንኩ!” እያልን እንዲያው በከንቱ ለምስጠት ፈቃደኞች እንሆናለን። ይህም ግድየለሽነታችን በወደፊቱ ትውልድ ዘንድ፣ በአምላካችን ዘንድ በጣም ያስጠይቀናል፤ ማንነትን መቀየር ነፍስን መሸጥ በመሠረቱ የኢትዮጵያውያን ባሕርይ ሊሆን አይችልምና።

“በወንጌል አላፍርምና፤ አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን ነውና።

ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና።

እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና፤ እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና።

የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ።

የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ።

ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥ የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ።

ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው፤
ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን።” (ሮም. ፩፡ ፲፮ – ፳፭)

__________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: