Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2012
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ግብጽ፡ በ ፌስቡክ በኩል ወደ ሻርያ ባርነት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 27, 2012

በዓለም ዓቀፍ ዜና ማሰራጫዎች ቆስቋሽነት ተነስቶ የነበረውና የ አረብ ጸደይወይም የአረብ አብዮትእየተባለ ዓመቱን ሙሉ ሲወራለት የቆየው የአረብ እንቅስቃሴ ማዕበል በእስላማውያን የርዕዮተዓለም ቱጃሮች ተጠለፈ።

... በጃንዋሪ 25 2011 ላይ በካይሮው ታሂር አደባባይ ላይ ድንኳናቸውን ተክለው ለቀድሞው ፕሬዚደንት፡ ለሁስኒ ሙባረክ ከስልጣን መውረድ ምክኒያት የነበሩትና ዲሞክራሲ” “ነፃነትና” “ፍትሕናፍቆናል በማለት የተቃውሞ ድምጻቸውን ሲያሰሙ የነበሩት ዓለማዊ ሊበራልየሆኑት ግብጻውያን የተመኙትን የራሳቸውን ዲሞክራሲአሁን ለማግኘት በቅተዋል።

በዚህ ዲሞክራሲያዊ ሂደት፡ በታሂር አደባባይ አንድም ቀን ወጥተው ድምጻቸወን ለማሰማት ያልፈለጉት፡ ሙስሊም ወንድማማቾች እና ሳላፊዎች፡ ከሙባረክ እስር ቤት በመውጣት 70% የሚሆነውን የፓርላማ መቀመጫ እንዲረከቡ ተደርገዋል።

የግብጽ ሠራዊት በድብቅም ሆነ በግልጽ ከነዚህ የእስላም እንቅስቃሴዎች ጋር በመተባበር አሁን ሥልጣኑን ለማስረከብ መዘጋጀቱ እንግዳ ነገር ሊሆንብን አይችልም፤ ገና ከመጀመሪያው ጀምሮ ግብጽ ወዴት እንደምታመራ የታወቀ ነበርና። ባንዳንድ ነገሮቹ ይህ ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ በ1974 .. አካባቢ የነበረውን ሁኔታ ትንሽ መሰል ይላል።

የግብጽ ወደፊት ምን ይመስላል?

ሙስሊም ወንድማማቾቹና ሳላፊዎቹ (ልዩነታቸው ታክቲካዊ/ስትራቴጂካዊ አካሄድን በሚመለከት ጉዳይ ብቻ ነው) ስልጣኑን ከተረከቡ በኋላ የሚፈልጉትን እስላማዊ የሻርያ ሕግ መመሪያቸው አድርገው በይፋ ያጸድቃሉ። ይህን ለመቃወም የምእራቡ ደጋፊ የሆኑት ዓለማውያን የተቃውሞ ድምጻቸውን ለማሰማት ይሞክራሉ፡ ነገር ግን ዲሞክራሲየብዙኅኑን ፍላጎት መከተል ስላለበት ምንም ማድረግ አይችሉም። በጣሊያንና በጀርመን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ሥልጣን ላይ ወጥተው የነበሩት ፋሽስቶች እና ናዚዎች፡ ሙሶሊኒንና ሂትለርን የመሳሰሉትን አምባገነን መሪዎች አፍርተው በኋላ ለጭካኔና ለእልቂት መብቃታቸውን ከታሪክ እንማራለን። በኛም ዘመን፡ በኢራን እንዲሁም በጋዛ በሕዝቡ ፍላጎት ሥልጣኑን የያዙት ኃይሎች ሕዝባቸውን በጣም አስከፊ ለሆነ ሁኔታ ማጋለጣቸው የምናየው ነው።

85% የሚሆነው ግብጻዊ እስልምናን ይመርጣል፣ የግብጽ መተዳደሪያ የእስላም ሻርያ ሕግ እንዲሆን ይፈልጋል፣ የሚሰርቅ ሰው እጆቹ እንዲቆረጡበት ይመኛል፣ ሴቶች እና ክርስቲያኖች እንደሁለተኛ ዜጎች ሆነው እንዲኖሩ ያቅዳል። ይህንንም የግብጻውያንን የልብ ትርታ በደንብ የተረዱት የእስላም ፓርቲዎች ሴቶች እና ክርስቲያኖች ፕሬዚደንት መሆን እንደማይገባቸው፡ እንዲያውም ቁልፍ የሆኑ የሥልጣን ቦታዎችን መያዝ እንደሌለባቸው በመተዳደሪያዎቻቸው አስቀምጠዋል። አሁንም ቢሆን፡ ክርስቲያን ግብጻውያን፡ ፖሊስ መሆን፣ በውትድራን ማገልገል፣ የእስላም ትምህርት ተቋሞች ውስጥ ገብቶ መማር ወይም ማንኛውም የብሔራዊ የስፖርት ቡድን ውስጥ የመሳተፍ መብት የላቸውም። ይህን አሳፋሪ ሁኔታ የዓለም ማሕበረሰብ እንደማያውቅ ሆኖ ዝም ብሎታል፣ እግዚአብሔር ግን አይረሳውም።

እነዚህ የእስላም ፓርቲዎች አንዴ ስልጣን ላይ ከወጡ ተመሳሳይ ምርጫ ከአራት ወይም አምስት በኋላ ለማድረግ ዝግጁዎች አይሆኑም። ስለዚህ ይህ የሰሞኑ ምርጫ ለመጀመሪያና ለመጨረሻ ጊዜ ተካሄደ ማለት ነው። ምዕራብውያን የዜና ማሰራጫዎች ዓመቱን ሁሉ በጥሩ መንፈስ ሲለፍፉለት የነበረው ይህ የአረብ ጸደይ” “እስላማዊ አብዮትእንደሆነ ዓለም ሁሉ ይረዳል፣ ምዕራቡ ታይቶ የማይታወቅ ትኩረት ሲሰጠው የነበረውና እኔ ግብጻዊ በመሆኔ ገና አሁን ኮራሁ” “እኛ ግብጻውያን አስተዋዮች ነን፡ የተማርን ነን፡ ማርና ወተት በሚፈስባት አገራችን ነጻነትና ዲሞክራሲ በቅርቡ እናስፍናለን!” እያሉ ጉራቸውን ሲነዙ የነበሩት ግብጻውያን ሁሉ ለቅሶአቸውን የሚያሰሙበት ቀን በቅርቡ ይመጣል።

የአረቦችን ዲያብሎሳዊ ተልእኮ እስካሁን ያልተገነዘቡት/መገንዘብ ያልፈለጉት ሞኝ አውሮፓውያን ተበድለናል!” በማለት ከግብጽ፣ ከሊቢያ፣ ከቱኒዝያ በቅርቡም ከሞሮኮና አልጀሪያ የሚፈልሱትን ስደተኞች በአገሮቻቸው ተቀብለው ለማስተናገድ ይገደዳሉ፣ የዚህ ሁሉ እባባዊ እንቅስቃሴ መሪ ሰይጣን ነውና።

የዲሞክራሲያዊ ምርጫ ተካሄደ፡ የተመረጡት እስላማዊ ፓርቲዎች ግን ለነጻነት፣ ለእኩልነት እና ለፍትሕ የቆሙ ኃይሎች አይደሉም፤ ሃይማኖታችን እስላም፣ ሕገ መንግሥታችን ሻሪያ፣ መሪያችን ሙሀመድ ነውየሚል ነው መመሪያቸው። ስለዚህ ዲሞክራሲ ሙስሊሞች በብዛት በሚኖሩባቸው አገሮች ሊሠራ አይችልም።

ብዙ ኃብትና ንብረቶች ያሉት፣ እንዲሁም በአሜሪካ እርዳታ እስከ አፍንጫው ድረስ የታጠቀው የግብጽ ሠራዊት ስልጣን የሚመኝ ከሆነ፣ በመጀመሪያ የእስላም ኃይሎች ፓርላማውን አሁን ለመያዝ እንደበቁት ሁሉ ለወደፊቱም የፕሬዚደንቱን ቦታ ከመካከላቸው መርጠው እንዲይዙ ያደርጋል፤ ከዚያም፡ በእስላም ፓርቲዎች መስተዳደር ሥር ግብጽ በሁሉም መስክ ወደ ውድቀት ስለምታመራ፣ ሠራዊቱ ተቃውሞውን በማሰማት፡ “እነዚህ ፓሪዎች 80 ሚሊየን የሚሆኑትን ግብጻውያን ለማስተዳደር ብቃት የላቸውም በሚል ሰበብ የመንግሥት ግልበጣ ለማድረግ ያስብ ይሆናል። ስለዚህ እነዚህ እስላማዊ ፓርቲዎች በመጀመሪያ የሠራዊቱን ዋና ዋና መሪዎች የተለያዩ ምክኒያቶች እየፈለጉ ካጠገባቸው ያስወግዳሉ። በቱርክም የምናየው ይህን ነው። ጄነራሎቹን ከመነጠሩ በኋላ ለዛባየሚባሉት ሙስሊም ወንድማማቾች ትክክለኛውን ገጽታቸውን ያሳያሉ። ሻርያ በሥራ ላይ ይውላል፤ ምንጠራና እጅ ቆረጣ ይጧጧፋል፣ ልክ እንደ ኢራን ግብጽም የእስላም ሪፓብሊክ የሚል ስያሜ ይሰጣታል። ይህም ሁኔታ በግብጽ የምጣኔ ሃብት ቀውስ እንዲፈጠር ይገፋፋል። ሳውዲ አረቢያና ኢራን ዘይት ባይኖራቸው ኖሮ የእስልምናው ሥርዓት ገና ዱሮ በጠፋ ነበር። ግብጽ ግን የተፈጥሮ ኃብት የላትም፣ መተዳደሪያዋ ከአሜሪካ የሚገኘው የገንዘብ ስጦታ፣ ከአውሮፓውያን ቱሪዝም የሚገባው ገቢ በተለይ ደግሞ የአባይ ውሃና የኢትዮጵያ አፈር ነው።

አሁን ግብጻውያን ይህን መርጠዋል፣ ሴቶቹም ይህን ተመኝተዋል። የመረጡትንና የተመኙትን አግኝተው ከራሳቸውና ከአካባቢያቸው ጋር እንዴት እንደሚኖሩ ከውጭ ሆነን ለምንታዘብ ይህ ትልቅ ትምህርት ነው። ኢትዮጵያን በሚመለከት በተለይ በኮፕት ክርስቲያኖች ላይ በደል ይፈጸማልና፡ የአባይ ባለቤት የሆነችው ኢትዮጵያ በዚህ አጋጣሚ እንደ እነ አፄ ዳዊት ዘመን ቁልፍ የሆነ ሚና መጫወት ትችላለች፡ መጫወትም ይኖርባታል፡ ይህ ጥሩ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው።

በዚህ የቀውጥ ጊዜዋ፡ አሜሪካ ጥሩ መሪ ካገኘች ድጎማዋን ልታቆም ትችላለች፣ የቱሪዝሙም መስክ ሙሉ በሙሉ ገደል ሊገባ ይችላል። ለዚህ ሁሉ ጥፋት ሰበብ ይፈለጋል፣ ሰበበኞቹም 15 ሚሊየን የሚሆኑት ኮፕት ክርስቲያኖች ይሆናሉ፣ በደልና ግድያ በኮፕቶች ላይ ይቀጥላል፣ ዓብያተ ክርስቲያናት ይቃጠላሉ፣ ብዙዎችም ለመሰደድ ይገደዳሉ። የክርስቲያኖችን በአርብ አገሮች መገኘት የማይፈልጉትና፣ 15 ሚሊየን ያህል ኮፕቶች እስካሁን በግብጽ መኖራቸውን እንደ ኃፍረት አድርገው ሲወስዱት የነበሩት የእስላም ማሕበረሰቦች፡ ግብጽ ቀስበቀስ ከክርስቲያኖች መጽዳት ስለበቃች ይደሰታሉ፣ ይህንም እንደ ትልቅ ድል አድርገው ይቆጥሩታል።

ግብጽ፡ ላገሪቱ ብልጽግና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ የነበሩትን፡ ቀደም ሲል፡ አይሁዶችን አሁን ደግሞ ክርስቲያኖችን ካጠፋች በኋላ ሙሉ በሙሉ በእስልምናው መንፈስ ሥር ትወድቃለች። ሴቶች እንዲሸፋፈኑ ይታዘዛሉ፣ ሴቶች የወሊድ ፋብሪካ ብቻ እንዲሆኑና ልጆች ብቻ እንዲፈለፍሉ ይገደዳሉ፣ በግብጽ የሕዝብ ቁጥር ጣራ ላይ ይወጣል፣ መንግስቱ አገሪቷን በደንብ ማስተዳደር ያቅተዋል፤ ድህነት፣ ረሃብ የእርስ በርስ ጦርነት በአገሪቱ ይንሰራፋል፣ አክራሪዎች አጋጣሚውን በመጠቀም ሕዝቡ እንዲከፋ ያደርጋሉ፣ ጦርነት ከእስራኤል ጋር ይጀመራል፣ ብዙ ግብጻውያን ወደ አውሮፓ ለመሰደድ ይበቃሉ። በአውሮፓም ሰው የስደተኞች ነገር ያንገፈግፈዋል፣ በስደተኞች ላይ ያማርራል፤ በዚህም ምክኒያት ቀኝ እና ብሔራዊ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ስልጣኑን አሁን ካሉት ሶሺያል ዲሞክራቶች እና አረንጓዴዎች መረከብ ይጀምራሉ። በአውሮፓ ብሔራዊ አምባገነንት በየአገሩ ይንሰራፋል። በምጣኔ ኃብት ያልታደሉት አውሮፓውያን ወራሪ ሠራዊቶቻቸውን ወደ አፍሪካ እንደገና መላክ ይጀምራሉ።

 

________________________________

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: