Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • January 2012
  M T W T F S S
   1
  2345678
  9101112131415
  16171819202122
  23242526272829
  3031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

የረር ጽርሃ ሥላሴ ተዓምርና ምስጢር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 16, 2012


 

 

ሰሞኑን ወደ የረር በር ሥላሴ ገዳም ጎራ ብየ ነበር። እንደሚታወቀው ይህ ገዳም የተሰራው ከ6 ዓመታት በፊት፤ ሁለት ግለሰቦች የተለያዩ ራዕዮች ከታዩአቸው ጊዜ በኋላ ነበር።

የመጀመሪያውን ራዕይ ያዩት አንዲት ሴትዮ ነበሩ። እኚህ ክርስቲያን ኢትዮጵያዊት አሁን ገዳሙ የሚገኝበትን ቦታ በወቅቱ በመግዛት አነስተኛ የሆነ ቤት ሠርተው መኖር ጀመሩ። ነገር ግን ይህን ቦታ ለቀው እንዲሄዱ የሚጠቁም ራዕይ በተደጋጋሚ ይታያቸው ነበር። ሴትዮዋም ይህን ራዕይ ቸል በማለታቸውና ኑሮአቸውንም እዚያው ቦታ ላይ ለመግፋት በመወሰናቸው እያበዱ መጡ። በዚህም ምክኒያት ከዓመት በኋላ ግቢውን ለቅው ለመውጣት ተገደዱ።

ቀጥሎም ራዕይ ለማየት የበቁት ግለሰብ አሁን ገዳም የሚገኝበት አካባቢ ላይ መሬት ገዝተው ከባለቤታቸው ጋር የሚኖሩት ሙስሊም ኢትዮጵያዊ፡ አቶ ቃሲም ናቸው። በራዕይ ተገለጠለት፡ ይመልከቱ

አካባቢው፡ በጣም ልዩ የሆነ፡ ባለታሪክ እና የተቀደሰ እንደሆነ ለእኝህ ሰው በራዕይ ይታያቸው ነበር። እዚህ ቦታ ላይ መሬት ሥር ተደብቆ የሚገኝ አንድ የጥንት ቤተክርስቲያን ሕንፃ እንዳለ እመቤታችን ድንግል ማርያም ለኚህ ግለሰብ በራዕይ ደጋግማ ትገልጽላቸዋለች።

ራዕያቸውንም ለሚያውቋቸውና ለሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ ለማጫወት ከበቁ በኋላ መጨረሻ ላይ ቤተ ክርስቲያኗ አለችበት ወደተባለው ቦታ ሁሉም አምርተው ቁፏሮ ይጀምራሉ። ግለሰቡ በራዕይ የታዩዋቸው ነገሮች ሁሉ መሬት ውስጥ ተቀብረው ይገኛሉ፡ ከነዚህም ውስጥ ጥንታዊ አጽሞች፡ መስቀላት እና ቅርሳቅርሶች ይገኙበታል።

4ኛው ምዕተ ዓመት ላይ በኢትዮጵያና አካባቢዋ ነግሥው ሲያስተዳድሩ የነበሩት አብርሃወአጽበሃ በሥላሴ ስም ይህችን ቤተከርስቲያን አሰርተዋት እንደነበር አሁን በደንብ ለማወቅ ተችሏል። ባካባቢው ገና ብዙ ምስጢራዊ የሆኑ ነገሮች እንደሚገኙ ይታመናል። ሣርና ዛፎች በሚገኙበት ቦታ ላይ ከየት እንደሚመጣ የማይታወቀው የሚጤስ ዕጣን ሽታ አልፎ አልፎ እንደሚሸታቸው ሰዎች ይናገራሉ። በጣም ቅዱስ የሆነ ጽላትም አሁን ቤተክርስቲያን የተሰራበት ቦታ አካባቢ ጥልቅ መሬት ውስጥ ተደብቆ እንደሚገኝ ነገር ግን እሱን እስካሁን ለማውጣት እንዳልተቻለ የኃይማኖት መሪዎች አውስተውኛል።

አሁን ቤተክርስቲያኗ በነበርችበት ቦታ ላይ የረር ጽርሃ ሥላሴ ገዳምበቆንጆ መልክ ተሰርቷል።

ቀደም ሲል የጠቀስኳት ሴትዮ መጀመሪያ ትኖርበት በነበረው ቦታ ላይ አንድ አነስተኛ ቤተመቅደስ ተሠርታለች።

ሴትዮዋም ሥላሴ ገዳም አጠገብ አንድ ቤት ተሠርቶላት ከልጅዋ ጋር እየኖረች እንዳልች ባለፈው መስከረም 2004፡ ልክ በሥላሴ ዕለት ፡ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታናለች። (እግዚአብሔር አምልክ ቀበላት!)

አቶ ቃሲም ከገዳሙ አጠገብ ከቤተሰባቸው ጋር አንድ አነስተኛ ሱቅ ከፍተው ይኖራሉ። አቶ ቃሲም ከቤተክርስቲያን ሰዎች ጋር በየጊዜው ይገናኛሉ፡ ነገር ግን ተባብሮ ለመስራት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ እሳቸው እና ያነጋገርኳቸው የቤ/ክርስቲያን አገልጋዮች አውስተውኛል።

በቤተክርስቲያን በኩል አቶ ቃሲምን ለማስጠመቅ የተሞከረው ሙከራ ሁሉ ከሽፏል። አቶ ቃሲም ለመጠምቅ እና ክርስትናን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደሉምና። እንዲያውም፡ እሳቸው፡ በድፍረት የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን እንደሚሳደቡ፡ “ቄሶቹ የገንዘብ አፍቃሪዎች ናቸውእያሉ ስማቸውን እንደሚያጠፉ ነው የተነገረኝ።

አቶ ቃሲም፡ እኔ አሁን ለመጠመቅ ዝግጁ አይደለሁም!” “አባቶች በሚባሉትታሪክ አምናለሁ፡ ነገር ግን እኔን ለማጥመቅ ብቃት ያላቸው ቄሶች የሉም፡ ሁሉም የገንዘብ አፍቃሪዎች ናቸው…. በነገራችን ላይ ሙስሊም ራዕይ አይታየውምእየተባለ አይደለም አዲስ አበባ በየመንገዱ የሚወራው!?” እያሉ በማፌዝ አጫወቱኝ ነበር።

ይህም ሁኔታ በጣም ስላሳዘነኝ ነገሮችን ጠለቅ ብዬ ለመመርመር ሞከርኩ፤ ሁሉም የተወሳሰበ ስለሆነ ጉዳዩ ብዙዎቻችን ልናስብ እንደምንችለው ሆኖ መቀመጥ እንደማይኖርበት አሁን ተረዳሁ።

ይህ ቦታ ብዙ ታላላቅ ምስጢሮች የተደበቁበት እና መንፈሳዊ የሆኑ ጉዳዮች የሚገኙበት ቦታ ስለሆነ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትግል ይካሄድበታል። ሰይጣን ከቅዱሳን ቦታዎች አይርቅምና ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ተንኮልን እየፈጠረ ቅዱስ መንፈስን (ሥላሴን) ለመፈታተን ይሞክራል።

አቶ ቃሲም ከጥሩ የኢትዮጵያ ክርስቲያን ቤተሰብ የወጡ፡ አባት እና እናታቸው ታማኝ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እንደነበሩ፡ ባለቤታቸውም ክርስቲያን የሰሜን ሴት እንደሆኑ ተነግሮኛል።

50 ዓመት ዕድሜ የሚሆናቸው አቶ ቃሲም በወጣትነት እድሜአቸው ወደ አረብ አገር ሄደውና ሰልመው ከተመለሱ በኋላ ነበር ለዚህ የራዕይ ጸጋ ለመታደል የበቁት። የአባቶቻቸውን እና የእናቶቻቸውን እምነት የከዱት አቶ ቃሲም እስልምናን በመቀበል የኢትዮጵያን አምላክ ጨምረው ነበር የከዱት፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ቻይ፡ መሐሪ እና ሩህሩህ ነውና ለአባቶቻቸው፡ ለእናቶቻቸውና ለባለቤታቸው ሲል አንድ ሌላ እድል ሰጣቸው። እሱም፡ ፈጣሪአችን የኢትዮጵያ አምላክ እና ሥላሴ መሆኑን በእመቤታችን አማካይነት ገለጸላቸው፡ የተገለጸላቸውም ሁሉ ከነማስረጃው ፊታቸው ላይ ቀረበ፡ አቶ ቃሲም ግን ጥመቅትን የመሰለ ታላቅ ስጦታ ለመቀበል ወይም ለመጠመቅ ፈቃደኛ አይደሉም። እንዲያውም ሳዑዲ ዓረቢያ ሄጄ ሸሆችን ማማከር አለብኝ እያሉ በማቅማማት ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ አምላኩ ታጋሽ፡ መሐሪ እና ሩህሩህ ስለሆነ፡ ተጠምቀህ ብትድን ጥሩ ነው፡ መዳን ትፈልጋለህን?” ብሎ ከመጠየቅ ሌላ ማንንም አስገድዶ ወደ እግዚአብሔር ኃይማኖት የመቀየር ፍላጎቱም የለውም። አቶ ቃሲም ያው ሥላሴ ቤተክርስቲያን አጠገብ ቤት ሠርተው ይኖራሉ። እዚያም ሆነው የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን መሳደብና መገለማመጥ ችለዋል፡ ሆኖም ክርስቲያኑ ተገርሞ ራሱን ከመነቅነቅ በቀር ማንም ትንፍሽ ብሎ ሊነካቸው የቃጣ የለም።

ክርስቲያኖች እስላም በሆኑ አገሮች የሚደርሱባቸውን በደሎች ዓለም ሁሉ የሚያውቀው ነው። አረብ አገር የሚገኝ አንድ ክርስቲያን፡ እንኳን ሸሆችን እና ኢማሞችን እንዲህ በግልጽ ሊሳደብ እና መስጊድ አጠገብ ቤት ሰርቶ ሊኖር፡ መጽሐፍ ቅዱስን ይዞ፡ መስቀል አንጠልጥሎ ወደ አገራቸው ከገባ እንኳ ለእስራት፡ ለስቃይና ለግድያ ይበቃል።

ከዕለታት አንድ ቀን በግብጽ አገር ያሉ አንድ ሙስሊም ሸህ ፡ ታዋቂ የነበረውን ግብጻዊ ክርስቲያን መሀንዲስ መስጊድ እንዲሰራላቸው ይጠይቁታል። እርሱም በደስታ ፈቃደኝነቱን ይገልጽ እና መስጊዱን በደንብ አሳምሮ ይሰራላቸዋል። በዚህም ሥራው በጣም የተደሰቱት ሸህ ወደ መሀንዲሱ ዘወር ይሉና አሁን እስልምናን ተቀበል!” ብለው ይጠይቁታል፤ መሀንዲሱ ግን አይ አይሆንም እልምናን አልቀበለዐም በማለቱ አስገደሉት።

ክርስቶስ አምላክ፤ ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ሳያዩየሚያምኑ ብፁዓን ናቸውብሎ አስተምሮናል። ስለዚህ አሁን አቶ ቃሲም ታላቅ ፈተና ላይ ነው የሚገኙትክርስቶስን ወይም ሥላሴን የሚቀበሉት ቄሶቹን ወይም ሌላውን ለማስደሰት ብለው መሆን የለበትም፡ እግዚአብሔርን እንጂ። መዳን መፈለግ አለመፈለግ የራሳቸው መብት ነው፤ ግን ለጠፉት ሙስሊም ወገኖቻቸው አርአያ በመሆን ወደ ክርስቶስ መንግሥት እንዲመጡ ቀጥተኛውን መንገድ መምረጥ ነበረባቸው። በስድስት ዓመታት ውስጥ ስንት ሙስሊም መዳን በቻለ ነበር! የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ጥፋት ወይም ድክመት የለባቸውም ማለት አይደልም፡ ሁላችንም ድክመት አለብን፡ ኃጢአተኞችም ነን፡ ነገር ግን እንኳን ከውጭ ሆነው ለሚታዘቡት አቶ ቃሲም ቀርቶ ክርስቲያኖችም እንኳ ቢንሆን በቤተክርስቲያን አገልጋዮች ላይ ምንም ዓይነት ስድብና ዘለፋ እንዲሁም ተቃውሟዊ ኃይለ ቃል የመሠንዘር መብት ሊኖረን አይገባም። የስድብና ፌዝ መንፈስ ከእግዚአብሔር አይደለምና!

አንድ ሌላ የታዘብኩት አሳዛኝና በጣም አደገኛ የሆነ ነገር የሚከተለው ነው፤

የሥላሴ ገዳምን አድራሻ ፈልጌ ለማግኘት በሞከርኩበት ወቅት የረር ሠፈር አንዳንድ ሰዎችን እጠይቅ ነበር። በአንድ ወቅት እስላማዊ አለባበስ የነበራቸው አንዲት ሲትዮ ወደኔ ጠጋ ብለው መጡና፡ “ “ቃሲም ሥላሴን” ነው እየፈልግክ ያለኽው? በዚህ በኩል ስትሄድ ታገኘዋለህ” ብለውኝ አለፉ። “ቃሲም ሥላሴ?” ፤ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ብዬ እጅግ በጣም ተቆጣሁ። ወደ 20 የሚጠጉ የአካባቢውን ነዋሪዎችና ጎብኝዎች፤ “የዚህ ቦታ ስም መጠሪያ ምን ይባላል?” ብዬ መጠያየቅ ጀመርኩ። “ሥላሴ” “የረር ሥላሴ” “ሠፈራ ሥላሴ” ተብሎ እንደሚጠራ ነው በብዛት የተነገረኝ። “ቃሲም ሥላሴ” በማለት አንዳንዴ ለመጥራት እንደሚሞከርም ግለሰቦቹ በሃዘንና በንዴት ገልጸውልኛል። በርግጥም ገዳሙን በዚህ ዓይነት መልክ ለመጥራት መሞከሩ በጣም መጥፎ ብቻ ሳይሆን እጅግ ኃይለኛ መቅሰፍት አምጪም ነው።

ከዚህ በተረፈ ሦስት ዓብያተክርስቲያናት በነዋሪው ብርታት በሥላሴ ዙሪያ፡ ትንሽ ራቅ ራቅ ብለው ተሠርተዋል። ብዛት ያላቸው ሙስሊሞችም በቤ/ክርስቲያን አገልጋዮች ጥረት በየረር ጽርሃ ሥላሴ ተገኝተው በመጠመቀ እየዳኑና ክርስቶስንም እየተቀበሉ እንደሆነ ለማወቅ ችያለሁ።

ሥላሴ የተመሰገኑ ይሁኑ!

__________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: