Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • December 2011
  M T W T F S S
   1234
  567891011
  12131415161718
  19202122232425
  262728293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

ኢትዮጵያ የ Armenian Genocideን በይፋ መቀበል አለባት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 30, 2011

 

..አ ከ1914 እስከ 1917 .ም ባለው ጊዜ፡ 1.5 ሚሊየን የሚሆኑ አርመናውያንን በቱርክ ምድር በመጨፍጨፍ ለመፍጀት የበቁት ኦቶማን ቱርኮች ይህን አሳዛኝ ታሪካቸውን ስህተት እንደሆነ ለመቀበል እስካሁን ድረስ ፈቃደኞች አይደሉም።

ቀደም ሲል የግብጽን፡ ሱዳንና ሱማሊያን ሙስሊሞች በማገዝ በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ መከራና ሥቃይ ያደረሱት ኦቶማን ቱርኮች አሁንም፣ በቁጥር አነስተኛ በሆኑት ክርስቲያን ቱርኮች፣ በአረመናውያን፣ ወንድማቸው በሆነው በኩርድ ሕዝብ ላይ፣ እንዲሁም ባዳርፉርና ደቡብ ሱዳን ሕዝቦች ላይ ጂሃዳዊ ጭፍጨፋቸውን በረቀቀ መልክ ቀጥለውበታል።

ባለፈው ሳምንት ወደ ቱርክ ጎራ ብዬ ነበር፡ በዚህች አገር በክርስትና እና በክርስቲያኖች ላይ የሚታየውን ጥላቻ ለመግለጽ ብዙ ቃላቶች ያስፈልጉኛል፡ ለማንኛውም፤ ቱርኮች እጅግ በጣም አሳዛኝና አደገኛ የሆነ ሁኔታ በአገራቸው ላይ በመፍጠር ላይ ይገኛሉ። በቅርብ ተደርጎ የነበረው ጥናት እንደሚናገረው፡ 2/3ኛ የሚሆነው የቱርክ ነዋሪ የክርስቲያን ጎረቤት እንዲኖረው አይሻም።

ቱርክ በ 1970ዎቹ ዓመታት የቆጽሮስ ደሴትን ህገወጥ በሆነ መንገድ በመውረር ሰሜናዊውን ክፍል ለመያዝ ከበቃችበት ጊዜ ጀምሮ፡ ብዛት ያላቸው የግሪክ ኦርቶዶክስ ተከታዮች ተጨፍጨፈዋል፡ አብያተ ክርስቲያኖቻቸው፡ አድባሮቻቸው እና ገዳሞቻቸው ቀስበቀስ ፈራርሰው እንዲጠፉ እየተደረገ ነው።

ቱርክ በአገራችንም ትምህርት ቤቶችንና ፋብሪካዎችን እንድትከፍት እየተፈቀደላት ነው። እነዚህ ትምህርት ቤቶችና ፋብሪካዎች ኢትዮጵያውያንን በክርስቲያን እና እስላም ሰፈር በመከፋፈል፡ ክርስቲያን ተማሪዎችንና ተቀጣሪዎችን ባገራቸው ለመቀበል ፈቃደኞች አይደሉም። ገንዘባቸውን ከፍለው ወደ ቱርክ ትምህርት ቤቶች ለመግባት የበቁት “ክርስቲያን” ኢትዮጵያውያን ሕጻናት ቁራእንን እንዲያነበንቡ፡ እንደ እስላም እንዲሰግዱ ይገደዳሉ። ይህን አሳፋሪና አሳሳቢ ጉዳይ የአዲስ አበባ ነዋሪ በሚያስገርም ትእግስት እየታዘበ ነው። የሚመለከታቸው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፡ በተለይም በውጩ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ይህን እንደ አፓርታይዷ ደቡብ አፍሪቃ በአገራቸው ሕዝብ ላይ አድሎ እየፈጠረ ያለውን ሁኔታ በእንጭጩ የመቅጨት፡ ብሔራዊና መለኮታዊ ግዴታ አለበት። እዚህ ዓይነት ደረጃም ላይ ለመድረስ መብቃታችን እጅግ በጣም አሳዛኝ ነገር ነው። ይህን ያህል ሞኞች እንድንሆን ያበቃን ምን ይሆን?

እንደሚታወቀው፡ ቱርክ ወዳጃችን ሆና አታውቅም፡ ወደፊትም ልትሆን አትችልም፡ የራሷ ችግሮች ምናልባት ከኛ እየከፉ ሊመጡ ይችላሉ፡ መምጣታቸውም የማይቀር ነው። ስለዚህ ቱርክን ሆነ ባካባቢው የሚገኙትን ጠላቶቻችንን በጣም ማስጠጋት ትልቅ ስህተት ነው። ጠላትህን ከራስህ አብልጠህ ውደድ የሚል ነገር ያለው ምናልባት በኢትዮጵያን ዘንድ ብቻ ሳይሆን አይቀርም የተለመደው። ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ ልዩ የሆነና በጊዜው መሪ ከነበረው ዓለም ጋር የሚወዳደር ሥልጣኔ የነበራት እኮ ካካባቢው ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ግኑኝነት አቋርጣ የክርስትያኖች ደሴት ለመሆን በበቃችበት ዘመን ነበር። “ወዳጅህን ቅረብ፤ ጠላትህን ደግሞ በጣም ቅረብ!” የሚለው ስልታዊ አባባል፡ እንደ አዳምና ሔዋን ዘመን ለሞኝነት ለበቃነው ለኢትዮጵያውያን አይሰራም። የሚሰራው እንደ እስራኤል ነቅተው እራሳቸውን ለመቻል ለበቁት ብልጥ አገሮች ነው።

የእስራኤል ፓርላማ (ክነሰት) ኦቶማን ቱርኮች በአርመን ሕዝብ ላይ ያካሄዱትን ፍጅት “Genocide” ነበር ብሎ ለመወሰን ሰሞኑን እየተነጋገሩበት ነው። እስካሁን አለማጽደቃቸው የሚገርም ነው፡ ከሁሉም በፊት መቅደም የነበረባቸው እነርሱ ነበሩ፡ ምክኒያቱም የአርመን ጀነሳይድ በሂትለር እንደምሳሌነት ተወስዶ ድሞቻቸውና እህቶቻቸው በናዚዎች ለመጨፍጨፍ በቅተው ነበርና።

ይህን የአርመኖች ፍጅት “Genocide” እንደነበር፡ ይህንም የሚክድ ለብዙ ዓመታት እስራት እና ለገንዘብ መቀጮ እንደሚበቃ የፈረንሳይ ፓርላማ ባለፈው ሳምንት ወስኗል።

በመጪው የአሜሪካ ምርጫም ይህ ጉዳይ ቁልፍ የሆን ሚና ሊጫወት ይችላል። ፕሬዝደንት ኦባማ እጩ በነበሩበት ወቅት ገብተው የነበረውን ቃልኪዳን እስካሁን ለመተግበር አለመቻላቸው አሳዛኝ ነገር ነው።

እስካሁን ድረስ የሚከተሉት አገሮች የአርመኑ እልቂት፤ “Genocide” እንደነበር በይፋ አስታውቀዋል፦

 • Argentina
 • Armenia
 • Austria
 • Belgium
 • Canada
 • Cyprus
 • France
 • Greece
 • Italy
 • Lebanon
 • Lithuania
 • The Netherlands
 • Poland
 • Russia
 • Slovakia
 • Sweden
 • Switzerland
 • Uruguay
 • Vatican City
 • Venezuela

በተጨማሪም 39 የተባበሩት አሜሪካ ግዛቶች ተቀብለውታል፡ መንግሥቱ ግን ወለም ዘልም በማለት ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያና አርሜኒያ ሕዝቦች በታሪክ፡ በእምነት እና በቋንቋ በጣም የተሳሰሩ ናቸው። የአርመን ፊደለታ (የጆርጂያ አገር ፊደላትን ጨምሮ) ከኢትዮጵያኛው ቋንቋ (ግእዝ) እንደተዋሰ የቋንቋ ሳይንስ ጥናት ተመራማሪዎች አሳውቀዋል፡ አርጋግጠዋል። አርመናዊቷ ቅድስት አርሴማ ከአርመንያ ይልቅ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በጣም ከፍተኛ ክብር አላት፡ ባማልጅነቷም ብዙ ኢትዮጵያውያን ተዓምራትን አይተዋል፤ ይህም የሚያሳየው በዓለም የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያን ሕዝቦች የሆኑት አርመናውያንና ኢትዮጵያውያን በመንፍስም በጣም የተሳሰሩ መሆናቸውን ነው።

ከሁለት ሣምንታት በፊት በኢትዮጵያ አገራችን ሙስሊሞች የቅድስት አርሴማን ቤተክርስቲያን ለማቃጠልና ለማፍረስ በቅተው ነበር። ይህን አሳዛኝና ሰይጣናዊ የሆነ ድርጊት ቅዱሳን ዝም ብለው የሚያልፉት ይመስለናል? በፍጹም! ቅድስት አርሴማ ሥራዋን እየሰራች ነው፤ ያው የአርመኖች ጉዳይ ይህ ድርጊት ከተፈጸመ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነበር በፈረንሳይና በእስራኤል የተቀሰቀሰው። በቱርክ ላይ እየመጣ ያለው መዘዝ ቀላል አይደለም፤ ስህተቱን፡ ኃጢአቱን ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆነ፡ ሊማርና ሊታረም ብሎም ለንስኅ ሊበቃ አይችልም፡ ሌላውን እየወነጀለ የዘራትን መርዝ መልሶ ይቅማታል እንጂ።

ኢትዮጵያ የአርመናውያንን እልቂት፡ አዎ! ጀነሳይድ ነበር ብላ የማወጅ ግዴታ አለባት።

 

_____________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: