አንጎልህን መመልከት አትችልም
በሩስያ አብዮት አንድምታ መሠረት መምህሩ እምነትንና የእግዚአብሔርን ሕልውና ስለ መካድ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲህ እያለ ያስተምር ነበር፦
“እነዚህ ምንድር ናቸው?”
“የዐይን መነፅሮች ናቸው!”
“የዐይን መነፅሮቹን ታዩአቸዋላችሁ?”
“አዎ፥ እናያቸዋለን!”
“በእርግጥም የዐይን መነፅሮቹን ታዩአቸዋላችሁ። በመሆኑም መነፅሮቹ አሉ ማለት ነው። ይሁን እንጂ እግዚአብሔርን ታዩታላችሁ?”
“አናየውም!”
እዚህ ላይ ሲደርሱ አንድ ልጅ ተነሣና “የአንተን አንጎል ማየት አንችልም። ስለሆነም አንተ አንጎል የለህም ማለት ነው።” አለ።
ምስጋና እና እግዚአብሔርን መካድ።
እግዚአብሔርን የከዳ ሰው ምስጋና ማቅረብ አይችልም። የዚህ ምክንያቱ እርሱ በበረከት ሲጥለቀለቅና ለዚህ ምስጋናውን ለማቅረብ ሲፈልግ ማንን ማመስገን እንዳለበት ስለማያውቅ ነው።
በእግዚአብሔር የማያምንን ሰው ለመግለጽ የሚመረጠው መንገድ ለእርሱ የሚጣፍጥ ምግብ ካቀረቡለት በኋላ “ይህን ምግብ ያዘጋጀች ምግብ አብሳይ እንዳለች ታምናለህ?” ብሎ በመጠየቅ ነው።
ከዚህ ምግብ በስተጀርባ ምግብ አብሳይ መኖሯ እርግጥ ከሆነ ይህ ዓለም በውስጡ ከሚገኙት ድንቅ ሕግጋቶቹ ጋር ሊቆይ የቻለው በአጋጣሚ ነው ማለት ነው።
ጦርነት እንዴት ይጀምራሉ?
አንድ ልጅ አባቱን “ጦርነቶች እንዴት እንደሚጀምሩ ንገረኝ።” ብሎ ጠየቀው።
አባቱም እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ “እንደ ምሳሌ አድርጌ የምነግርህ የአንደኛውን የዓለም ጦርነት ነው። ይህ ጦርነት የተጀመረው ጀርመን ቤልጂየምን በወጋች ጊዜ ነበር።”
በዚህ ጊዜ የልጁ እናት በቁጣ ቃል የባሏን መልስ አቋረጠችና እንዲህ አለች፦ “ለልጅህ እውነተኛውን ነገር ነገረው።” ጦርነቱ የተጀመረው ጥቂት ሰዎች እርስ በእርሳቸው በተገዳደሉ ጊዜ ነው።”
አባት የልጁ እናት እንዲህ ባለ ሁኔታ በመካከል ጣልቃ ገብታ ስላቋረጠችው ተበሳጨና ወደ እርሷ እየተመለከተ በተግሣጽ ቃል “የጠየቀው እኔን እንጂ አንቺን ስላልሆነ ለምንድር ነው የምታቋርጭኝ?” አላት።
በዚህ ጊዜ እናትየዋ በጣም ስለ ተናደደች የቤቱን መዝጊያ በሃይል ወርውራ ስትወጣ በግድግዳው ላይ የታሰረው መደርደሪያ ተናጋ። በዚህ ጊዜ በላዩ ላይ ከተደረደሩት ውድ ዕቃዎች መካከል ጥቂቶቹ ወለሉ ላይ ወድቀው ተሰባበሩ።
በዚህ ጊዜ ጥቂት ነግሦ የቆየው ፀጥታ በልጁ ንግግር ተቋረጥ፦ “አሁን አባዬና እማዬ ጦርነት እንዴት እንደሚጀምር ስላሳዩኝ ለጠየቅሁት ጥያቄ መልስ አልሻም።
_________________________________