Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • November 2011
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for November, 2011

‘Little’ Great Britain: Christian Worker Loses Her Job After Being Targeted by Islamic Extremists

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 30, 2011


Nohad Halawi, who worked at Heathrow Airport, is suing her former employers for unfair dismissal, claiming that she and other Christian staff at the airport were victims of systematic harassment because of their religion.

She claims that she was told that she would go to Hell for her religion, that Jews were responsible for the September 11th terror attacks, and that a friend was reduced to tears having been bullied for wearing a cross.

Continue reading…

____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Life | Tagged: , , , , , , , | 1 Comment »

Human Resources: Social Engineering in the 20th Century

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 30, 2011

Here is part 1/9..the other parts are on the sidebar…

Human Resources explores the rise of mechanistic philosphy and the exploitation of human beings under modern hierarhical systems.

Topics covered include behaviorism, scientific management, work-place democracy, schooling, frustration-aggression hypothesis and human experimentation.

The education of the masses in order to ‘create’ good consumers, good soldiers, and the effect of the proper ‘training’ on the human being as an animal to be USED by the PTB. The film covers mind control, and behavior..

______________________________________

Posted in Ethiopia, Psychology | Tagged: , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያ የተስፋው ቃል ሕዝብ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 24, 2011


የነብዩ ኤርምያስ ምስክርነት

ኢትዮጵያ የተስፋው ቃል ሕዝብ” በሚል ርዕስ ከታተመው የ ዶ/ር ዘላለም እሸቴ መጽሐፍ የተወሰደ።

ከታላቅ አክብሮትና ምስጋና ጋር

ነብዩ ስለ ተስፋው ቃል ሕዝብ እንዲህ ሲል ይመሰክራል።

በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዥንጉርጉርነቱን ይለውጥ ዘንድ ይችላልን?” (ኤርምያስ 1323)

ይህን የትንቢት ቃል በጥልቀት ከማየታችን በፊት ነብዩ ኤርምያስ ስላለበት ሁኔታና ነብዩ ስለ ኢትዮጵያ የነበረውን ግንዛቤ ከእግዚአብሔር ቃል እንመልከት።

በመጀመሪያ በኤርምያስ 387-13 ያለውን ታሪክ እናጥና። ኤርምያስ የፍርድን ቃል ለእስራኤል ከእግዚአብሔር ያስተላልፍ ነበር። በዚህም የፍርድ ቃል ያልተደሰቱት ሕዝብ ኤርምያስ እንዲገድል ንጉሡን ለመኑት። ንጉሡም ኤርምያስን “እነሆ በእጃችሁ ነው” ብሎ አሳልፎ ሰጣቸው። ሕዝቡም ኤርምያስን በጉድጓድ ውስጥ እንዲሞት ጣሉት።

በዚህን ጊዜ በባዕድ አገር ይኖር የነበረ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ስለ ኤርምያስ ማለደ። ወደ ንጉሡም ገብቶ ሕዝቡ በነብዩ ላይ ክፉ እንዳደረጉና ኤርምያስ በረሃብ ሊሞት እንዳለው በማስረዳት ጠበቃ ቆመለት። ንጉሡም በኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ምክንያት ሀሳቡን ለውጦ ኤርምያስን እንዲታደገው ፈቀደለት።

ከዚህ ታሪክ እንደምንረዳው ነብዩ ስለ ኢትዮጵያዊው መልካም ምስክርነትን በሕይወቱ እንዲሰርፅ እግዚአብሔር በር እንደከፈተለት ነው። ታሪኩ የአጋጣሚ ሳይሆን እግዚአብሔር እንኳን ለራሳችን ለሌላም ለመትረፍ የሚያስችል ሞገስ ከጌታ የተሰጠን ሕዝብ እንደሆነ ያመለክታል። በተጨማሪም ከሁለቱ ኢትዮጵያውያን ጃንደረቦች ታሪክ የምንረዳው በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን ከጌታ የተቀበልነው ጥሪ (መልክ) ሊለውጥ እንደማይችል ነው።

መልካችንን መለወጥ አለመቻላችን አንድም ተለዋዋጭ ሕዝብ አለመሆናችንን ያሳያል። ስለዚህም ይሆናል በስደት ለረዥም ዓመታት ስንኖር ኑሯችንና ነገራችንን ያየ ሁሉ እዚያው አገር ቤት እንዳለን ያህል ሳንለወጥ የሚያገኘን። ታዲያ ይህ ባህሪያችን ለጎጂ ባሕል ቢያጋልጠንም ለበጎ ነገር ዓይነተኛ ጎናችን ነው። ስለሆነም ጊዜው ሞልቶ እጃችንን ያነሳንለት ወደ ኋላ የሚመልሰን (መልካችንን የሚለውጥ) ነገር አይኖርም። ያኔም ለጌታ የምንመች ባስቀመጠን ቦታ የምንገኝ ሕዝብ እንሆንለታለን።

ቀጥሎ የምናየው ነብዩ ለኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ከእግዚአብሔር ያመጣለት የተስፋ ቃል ነው። እንዲህ ይነበባል፦

ፈጽሜ አድንሃለሁበእኔም ታምነሃልና፤ ይላል እግዚአብሔር” (ኤርምያስ 3918)

ይህም የሚያሳየው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ለበጎ ሥራ የተነሳሳው በእግዚአብሔር ላይ ስለታመን ነው። ኢትዮጵያም እጆቿን የምትዘረጋው በጌታዋ ላይ ስለምትታመን ነው። ይህ በአምላክ የመታመን ባህርያችንን ምን ጊዜም (መልካችንን) ሊለውጥ የሚችል ነገር አይደለም።

በመጨረሻ ኤርምያስ ስለ ኢትዮጵያ ያለውን ግንዛቤ በቃሉ እንዲህ ተገልጧል፦

ጋሻንም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና ኃያላን” (ኤርምያስ 469)

ይህ ኢትዮጵያውያን የያዙት የጦር መሳርያ ጋሻ ለመከላከያ የሚያገለግል ሲሆን በቃሉ ውስጥ እንዲህ የሚል ትርጉም እናገኛለን፤ “በሁሉም ላይ ጨምራችሁ የሚንበለበሉትን ፍራፃዎች ሁሉ ልታጠፉ የምትችሉበትን የእምነት ጋሻ አንሱ” (ኤፌሶን 616)

በኢትዮጵያ ላይ ያለውን መለኮታዊ ጥሪ ለማኮላሸት ለዘመናት የተዋጋን ክፉ የሆነው አንዱ ዲያብሎስ ነው። በዚህም አጥፊያችን በሆነው ጠላት ላይ የእምነት ጋሻችንን እንድናነሳ ይናገረናል። ለኢትዮጵያ መጐብኘት ቁልፉ ያለው ድል የምንነሳበትን የእምነት ጋሻን መታጠቃችን ላይ ነው። በገሀዱ ዓለም ደም እያፈሰሰ እርስ በርስ የሚያዋጋን ጠላታችን ላይ ሰማያዊ (መንፈሳዊ) ጦርነት ማካሄድ እንጀምራለን። በጦር ሜዳ የታወቅንበት ጀግንነታችንን (መልካችንን) ዕውቅ እንደነበረ ሁሉ በሰማያዊውም ፍልሚያ ልናሳየው ያለው የእምነት አርበኝነታችንን (መልካችንን) እንዲሁ ሳይለወጥ ይቀጥላል።

መልካችን” በቀጥታ ሲተረጎም – አንድም ጥቁርነታችንን ያሳያል። በአንዳንድ የእንግሊዘኛው መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ኩሽ የኢትዮጵያን መልከዓምድርና ዳርድንበር የሚያዋስኗትን ሌሎች የአፍሪካ አገሮች የሚጨምር እንደሆነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም ጥቁር ማለት ነው።

የኢትዮጵያ ወርድና ስፋት በየጊዜው እየተለዋወጠ በዙሪያዋ አዳዲስ መንግሥታት መመስረታቸው እርግጥ ነው። ይሁን እንጂ

  1. ቃሉ መልካችንን (መለኮታዊ ጥሪያችንን) ሊለውጥ የሚችል ነገር እንደሌለ ይናገረናል።

  2. እጃችንን ስንዘረጋ መልካቸውን የለወጡ ሁሉ ከእግዚአብሔር የሚለቀቅልንን በረከት ተካፋይ ለመሆን ይሰበሰባሉ።

  3. እጃችንን ስንዘረጋ ከዘራችን ወጥተን በኢትዮጵያዊነታችን ብቻ መመካት እንጀምራልን።

  4. በዚያም ሳንረካ ከጥቁር ሕዝብነታችን ባሻገር የእግዚአብሔር ሰው በመሆናችን ሀሴትን እናደርጋለን። ለዓለምም ብርሃን እንሆናለን። ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቆረጠልን መልካችን ነውና ይህን ሊለውጥ የሚችል ማንም የለም።

በድክመቶች ፈንታ መልካም ፍሬዎችን በመተካት ንስሀ እንገባለን። ሌላውን ከራሳችን ይልቅ የተሻለ አድርጎ በመቁጠር ዘረኝነትን እንገድላለን። የሌላውን የልብ ትርታ እናዳምጣለን። በአባቶቻችን ያጣነውን የሌላውን አመኔታ እናገኛለን።

በፍቅር ላይ የተመሠረተ እውነተኛ አንድነት ለማግኘት የሚያስከፍለውን ዋጋ ለመክፈል ራሳችንን እናዘጋጃለን። የሌላውን ወገናችንን ቋንቋና ባህል ችላ ብለን ብለን በመኖራችን እናፍርበታለን። እጃችንን ወደ እግዚአብሔር አንስተን በቅን ልቡና ብንጠቀምበት ጌታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ተነጥቀው ከሰው በታች ተቆጥረው ለዘመናት የተሰቃዩት ወገኖች የሚታሰቡበትን መልካም ዘመን ያመጣል።

ኢትዮጵያ የብዙ ብሔርና ብሔረሰብ የጋራ ርስት እና ቤት ነች። ኢትዮጵያ የተጠራችው አንድ ትልቅ በፍቅር የተሳሰረ ቤተሰብ እንድትሆን ነው። ይሁን እንጂ እጆቻችንን ስንዘረጋ ነው ከእግዚአብሔር በታች ያለ አንድ ቤተሰብ የምንሆነው። ያን ጊዜም የኢትዮጵያ ገጽታ ይለወጣል። ገጽታውም ለእኛም ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሁሉ ይታያል።

አዲሲቷ ኢትዮጵያ

እግዚአብሔር ስለ ተስፋው ቃል እንዲህ ሲል ይናገራል።

አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጥቅጠህ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።” (መዝሙር 7414)

ምድራችን የመሪዎቻችንን ክብር ስታስተናግድ ለዘመናት ኖራለች። እጃችንን ስንዘረጋ ደግሞ አዲሲቷ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔርን ክብር ታስተናግዳለች።

የኤደን ገነት እግዚአብሔር ለሰው ልጅ በምድር ያዘጋጀው በረከት ነበረች። ኢትዮጵያም ከኤደን ጋር ተያይዛ በቃሉ ውስጥ ትገኛለች (ዘፍጥረት 213)። ዲያብሎስ ግን በኤደን የነበረውን በረከት ወደ መርገም ለወጠው።

ልናስተውለው የሚገባን ጉዳይ እሥራኤል እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ያዘጋጀው ዘላለማዊ በረከት መንገድ መሆንዋን ነው። ለዚህም ምስክር የሚሆነን ከአብራሃምና ከዳዊት ዘር የወጣውና የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ለሰው ልጅ ሁሉ መዳን ሆነ (ሐዋ. 412)

ኢትዮጵያ ደግሞ እግዚአብሔር በምድር ለሰው ልጅ በመጨረሻው ዘመን ያዘጋጀውን መነቃቃት ልታሳይ የተጠራች ምድር ብትሆንስ? ያለነገር ጌታ ዘንዶውን እየቀጠቀጠ ምግባቸውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይሰጣል ተብሎ አይፃፍም። ደግሞስ እጃችንን ማንሳታችን ለዚሁ በረከት ቢሆንስ? ይህም የሚሆነው ኢትዮጵያውያን ለበረከት የተጠራን የተለየን ሕዝብ ስለሆንን ሳይሆን ከእግዚአብሔር ቸርነት የተነሳ አምላክ አስቀድሞ ቃሉን ስለሰጠን ነው። ዘንዶው በአሸነፈበት ምድር ይጋለጥ ዘንድ አለውና ኢትዮጵያ እጆቿን እንድትዘረጋ ተጠራች።

በኤደን ገነት ዘንዶው (ጠላት) የእግዚአብሔርንና የሰውን ልጅ ግንኙነት አበላሸ። እግዚአብሔርም ለሰው ልጅ የዘንዶውን ራስ የሚቀጠቀጥ መሲህ እንደሚልክ ቃል ገባላት (ዘፍጥረት 315)። የጌታ ቀንም ሲደርስ አዳኙ ወደ ገዛ ወገኖቹ (እስራኤል) በመምጣት የዘንዶውን ራስ ቀጠቀጠ። ነገር ግን እስራኤል ንጉሧን አልተቀበለችም።

ከአህዛብ ወገን የሆንነው የጠላትን ተሸናፊነት ያስመሰከረ በሕዝብ ደረጃ በምድር ላይ አልተገኘም። ሌላው ቀርቶ በሃይማኖት ላይ የተመሰረቱ መንግሥታት እንኳን ለሕዝባቸው መንፈሳዊና ሥጋዊ ችግር መፍትሔ ለማምጣት ለዓለም እንደ ሞዴል ሲሆኑ አልታዩም።

ስለዚህም ዓለም መንግሥትን ከሃይማኖት ነጥላ “ሴኩላር/secular” መንግሥትን መመስረት መረጠች። ይህም አዲሱ ምሪት በመባል ይታወቃል። ታዲያ እነዚህ ሴኩላር (ዓለማዊ) መንግሥታት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ ላለመግባት ሲሸሹ እግዚአብሔርንም አብረው ደህና ሰንበት አሉት። ስለሆነም የዘንዶው አሠራር እስከዛሬ በዓለም ተንሰራፍቶአል (መዝ. 10426)

እጆቻችንን ስንዘረጋ ግን ከምድር መጨረሻ በሆነችው ምድረ ኢትዮጵያ መንፈስ ቅዱስ የተሰበረችውን የጌታ አካል ተጠቅሞ በሙላት ይገለፃል።

ሁሉም በየቤተ ሃይማኖታችን እግዚአብሔር ወደ እውነት እንዲመራን እጆቻችንን ወደ እግዚአብሔር እንዘረጋለን። አንዳችን አንዳችንን ወደ የግል እምነታችን ለመቀየር ከመሮጥ ይልቅ ሁላችንንም በያለንበት ወደራሱ ወደ እግዚአብሔር ልብ እንዲያቀርበንና እንዲቀይረን እንጸልያለን። ሁላችንም በያለንበት ሁኔታ ለያለንበት ሥፍራ ብርሃን ሆነን እንቆማለን።

እግዚአብሔር የሰጠን ተስፋ ዓይናችንን ከራሳችን ላይ አንስተን ጌታችን ላይ እንድናደርግ ይጠራናል። የሚያስተሳስረንም በእግዚአብሔር ያለን እምነት ብቻ ነው። አምላክ የለሹ “ሴኩላሪዝም” ዓይናችንን ጨፍነን ከመነዳት እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ጥሪ እናስተውላለን። እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የማንኛውም አንድ ሃይማኖት አገር ሳትሆን የአንዱ እግዚአብሔር አገር ትሆናለች።

ከላይ ባነበብነው ምንባብ ውስጥ የተጠቀሰው የዘንዶው ራሶች በእየሩሳሌም ከተቀጠቀጠው ከዘንዶው ራስ ይለያል። የዘንዶው ራስ በቀራንዮ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በክርስቶስ ደም የአንዱን ጠላት ሽንፈት ሲያመለከት የዘንዶው ራሶች ደግሞ በተለያየ መልክ የሚከሰተውን የጠላት አሰራሮች ሽንፈት በታላቅ መንፈስ ቅዱስ መነቃቃት ይታያል።

የእስራኤል ሕዝብ ጥሪ በአንድ ሰው ያውም በአብርሃም ላይ የተመሰረት ነው። ስለሆነም ያዕቆብ እስራኤል በመሆን የቃል ኪዳኑን ሕዝብ መሰረተ። ከእስራኤልም ሕዝብ አንድ አዳኝ የሆነ ክርስቶስ ወደ ዓለም መጣ። እስራኤል ግን አዳኙን አልተቀበልችም። ስለዚህም እንደ እግዚአብሔር ሕዝብ ልትቆም አልተቻላትም።

የኢትዮጵያ ጥሪ ግን በሕዝብ ላይ የተመሰረተ ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያ እጆቿን በመዘርጋት የተስፋው ቃል ሕዝብ ትሆናለች። ጌታም በዚህ ሕዝብ በመጠቀም የጠላትን አሰራር በሕዝብ ደረጃ በማጋለጥ በመንፈሱ ይቀጠቅጠዋል። ለሕዝቡም ምግባቸውን ይሰጣቸዋል። ይህም ተጽፏል። ስለተጻፈው ይፈጸም ዘንድ ግድ ነው።

በርግጥ በመንግሥተ ሰማይ እግዚአብሔር ይከበራል። ሰይጣንም ይጣላል። ነገር ግን በኤደን ገነት ነገርን ሁሉ ያበላሸው ዛሬ ደግሞ ዓለምን የሚገዛው ዘንዶ እንዲሁ እንደንተሰራፋ የዓለም ፍጻሜ አይሆንም። ስለዚህ በምድር ሰይጣን ዓይኑ እያየ እግዚአብሔርን በድል እንድታከብር ኢትዮጵያ ተጠራች። ዘንዶው ራሱ እየተቀጠቀጠ ሕዝቡ ግን ምግባቸውን ከአምላካቸው ሲቀበሉ ፍጥረት ያያል። ትልቁ ድግስም ወንጌል እንደሆነ አንዘንጋ።

ዳዊት በእግዚአብሔር ቃል ሲናገር “በፊቴ ገበታን አዘጋጃለህኝ። በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ። ጽዋዬም የተረፈ ነው ይላል (መዝ 235)። ስለዚህም ጠላታችን እያየ በፊት ለፊቱ ምግባችንን እረኛችን የሆነው እግዚአብሔር እንዲሰጠን እጆቻችንን ወደ እርሱ ለማንሳት እንፍጠን።

ኮሚኒዝም አምላክን ክዶ አገር አጥፍቶ እርሱም ተሰባብሮ ከዓለም ጠፉ። በምትኩም በምድር ላይ የገነነው ሴሉላሪዝም አማራጭ ስለጠፋ ተቀባይነትን በዓለም አገኘ። ይሁን እንጂ በተራው የጌታን ፍርድ የሚጠብቅ ነው። ምድራችን በዘንዶው ሴራ የሚከሽፍበትና የጌታ ኃይል የሚገለፅበት አዲሲቷ ኢትዮጵያ ትሆናለች።

የማታ ማታ አምላክ የተሻለውን ክብርና በጎነት በምድራችን ሊገልጥ እንዳለው እንመን።

በችግርና በስደት ሕዝባችን በዓለም ዙሪያ ተበትኗል። ዓለምም እጇን ከፍታ አስተናግዳናለች። በጌታ ስንጎበኝ ግን ታሪክ ይቀየራል። ያኔ አምላክ ዘንዶውን እየቀጠቀጠ ምግባችንን ስለሚሰጠን እንጀራ ፍለጋ አንሰደደም፡ ይልቁንስ በምድራችን የተለማመድነውን ክብር እንድናካፍላቸው ዓለም ትለምነናለች። እኛም ያኔ ሃያል አምላክ ለሆነው እግዚአብሔር ምስክር አብሳሪ ለመሆን ወደ ዓለም ሁሉ ቃሉን ይዘን እንወጣለን።

ሁላችንም የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በዓለም ዚሪያ ተበትነናል። በሀገር ቤትም ያለው መውጫ ቀዳዳ ይፈልጋል። በሌላ በኩል ስናየው በውጭ ያለውም ሕዝብ በሥጋ ቢመቸውም ልቡ ያለው ሀገር ቤት ነው። ለመመለስ የፈለገም የኑሮ አባዜ አስሮት በምኞት ብቻ እየዋለለ ይገኛል። አገር ቤት በሥራችም ስንፍናን ያሳየን በስደት ስንኖር ሠራተኝነታችን በገሀድ ወጣ። ወንዞቻችን ለዓለም ሲሳይ እንጂ ለምድራችን እንዳልታደሉ ሁሉ ጉልበታችንም ለዓለም ሲሳይ እንጂ ለኢትዮጵያ እንዳልታደለ በሁሉም መስክ የተረጋገጠ ሆኗል።

እጃችንን ስናነሳ ይህ መርገም ከምድራችን ላይ ይነሳል። የጌታ ሞገስ በምድራችን ስለሚገን ሰዎች ሁሉ ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ይፈጥኑ ዘንድ ታሪክ ይቀየራል። በስደት ያለነውም እስራታችን ተፈቶ ለአገራችን ልማት ወደ አገራችን እንመለሳለን። መኖር ማለት በኢትዮጵያ ነው እስኪባል ድረስ ስለምትባረክ ዓለም ዓይኑን ወደ ኢትዮጵያ ያቀናል። በምድረ ኢትዮጵያ አምላክን ስንከተል ምህረቱና ቸርነቱ ይከተለናል።

ዓይናችን ተከፍቶ ከእስራት ተፈተን እጆቻችን ለተገለጠልን ስጦታዎች በሥራ ሲበረቱ እግዚአብሔርም ሰምተንም አይተንም በማናውቀው ሥጦታዎች ይባርከናል። በአምላክ ጥሪ ጥላ ሥር ያለችው ምድራችን በውስጧ አምቃ የያዘችውን ድብቅ በረከት ማን አውቆት? በፊታችን የሚፈሱትን ወንዞችና ጅረቶች በመጠቀም ታማኝነታችንን ካሳየን በበለጠ ቸርነት ሊያስደንቀን አምላክ የታመነ ነው።

ኢትዮጵያ የዓለም ሞዴል

እግዚአብሔር ስለተስፋው ቃል እንዲህ ሲል ይናገራል።

የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደ ኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን?”

ይላል እግዚአብሔር (አሞጽ 97)

ይህ ቃል የተገላቢጦሽ የተጻፈ ይመስላል። ምክኒያቱም እስራኤል የእግዚአብሔር ሕዝብ በመባል ሲታወቅ፦ ኢትዮጵያ ደግሞ እንደ አህዛብ ስለምትታወቅ ነው። ሲሆን ሲሆን ኢትዮጵያውያን እናንተ እንደ እስራኤል ልጆች አይደላችሁምን? ማለት በተገባው ነበር። ለምንድንነው ታዲያ እዚህ ላይ ኢትዮጵያን ከእስራኤል ይልቅ ወደራሱ ጌታ ያቀረበው? ደግሞስ ለምንድነው እስራኤል እንደ ኢትዮጵያ መቆጠሯ የሚያፅናናት?

ጥቅሱ የተወሰደበት አጠቃላይ ዐውድ ስንመረምረው እስራኤል በብዙ መከራ በምትገኝበት ወቅት ነው። የእስራኤል ሰላም አሁንም መልስ ያልተገኘለት ጥያቄ ነው። እስራኤልም ለእየሩሳሌም መጐብኘት መልስ የሚያመጣለትን የሰላም አለቃ አልተቀበለችውም። ስለዚህም ሰላምን ለኢየሩሳሌም ሊያመጣ የሚችል ሰው ሊመጣለት አይችልም።

ስለዚህም የተስፋ ቃሉ ተፈጽሞ ኢትዮጵያ እጆቿን አንስታ ከጌታ ስትባረክ እስራኤል በኢትዮጵያ ትደነቃለች። ጌታ ረሃብና ጦርነት ያጠቃትን የኢትዮጵያን ታሪክ ቀይሮ ለዓለም ብርሃንና ሞዴል ሲያደርጋት እስራኤል ስለ ሰላሟ ትጮሃለች። ያኔ ጌታ እናንተስ እንደ ኢትዮጵያ ልጆቼ አይደላችሁምን? የተባለው ቃል ትርጉም ይሰጣል። እነሱም ወደ ልባቸው እንዲመለሱ ኢትዮጵያ በረከት ትሆንላቸዋለች።

አርማችን

ባንዲራችን እኛን ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ኩራት እንደሆነ ይታወቃል። በባንዲራችን ላይ ያለው አርማችን ግን መንግሥት በተቀየረ ቁጥር እየተቀየረ ፈተና ላይ ይገኛል። ኢትዮጵያ በታሪክ የበለፀገች አገር ብትሆንም አርማችን ዕድሜው በመንግሥታት ዕድሜ ልክ ብቻ የሚቆጠር መሆኑ ይታወቃል።

እጆቻችንን ስንዘረጋ ግን ኢትዮጵያ ከጥሪዋ ጋር የሚሄድ አርማ እንዲኖራት ዕድል ቢሰጣት የተዘረጉ እጆች እንዲያርፍባት ታደርጋለች የሚል ምኞት አለን።

ይህ ዓርማ ታሪካዊ በሆነው ባንዲራችን ላይ ቢቀመጥ ሊሰጠን ያለውን በረከት በጥቂቱ እንመልከት።

1. የተሰጠን ዓርማ ከአምላክ የተወሰነልንን የበረከት ጥሪ ለመቀበል እሺ በማለት እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እንዲባርካት ፍቃደኝነታችንን ያሳያል።

2.የተሰጠን ዓርማ የኢትዮጵያን ሕዝብ ማንነት ያንፀባርቃል። የሰዎች ምኞት የሚያንፀባርቅ ሳይሆን የተስፋው ቃል ሕዝብ ለመሆናችን ምስክር ይሆናል።

3. የተሰጠን ዓርማ ከማናቸውም መንግሥታት ጋር ስለማይወግን ዘላቂነት ይኖረዋል።

4. የተሰጠን ዓርማ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን ሃሳብ እንጂ ኢትዮጵያዊ ሰው የፈጠረው አይደለም። ስለዚህም ከአምላክ የተሰጠን ስጦታ ነው።

5. የተሰጠን ዓርማ በሺህ የሚቆጠር ዘመን ታሪክ ያለው ታሪካዊ ነው። ስለዚህም ታሪካዊ በሆነው ባንዲራችን ላይ ታሪካዊ ለሆነችው አገራችን ምቹ ነው።

6. የተሰጠን ዓርማ ለኢትዮጵያ ብቸኛ መለያ ይሆናል። በሌላ በኩል ግን የብዙ አገሮች ባንዲራ ኮከብ አለበት።

7. የተሰጠን ዓርማ ከማናቸውም ሃይማኖት ጋር አይወግንም። ከማናቸውም ሃይማኖት ምልክቶች ጋር አይያያዝም።

8. የተሰጠን ዓርማ በፊት ለአፍሪካ ኩራት የነበረውን ባንዲራችንን ለዛሬ የአፍሪካ ተስፋ በማድረግ ይበልጥ ያከብረዋል።

9. የተሰጠን ዓርማ በዓለም የሰለጠነውን አዲሱን የሴሉላሪዝምን ምሪት እያጋለጠ የእግዚአብሔር ምሪት ምን እንደሚመስል ለዓለም ያበስራል።

10. የተሰጠን ዓርማ እግዚአብሔር አዲሲቷን ኢትዮጵያ ገፅታ ለውጦ የዓለም ሞዴል ሲያረጋት ለእግዚአብሔር ታማኝነትና ታላቅነት መታሰቢያ ይሆናል።

ጥቁር ሕዝብ

ቃሉ ሰይጣን የብርሃን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣል ይላል (2ኛ ቆሮንቶስ 1114)። ዓለም ግን ሰይጣንን ቀንድ ያወጣ ጥቁር ሰው አድርጎ ይስለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ቃሉ ስለ ክርስቶስ እንዲህ ሲል ይናገራል፤ “መልክና ውበት የለውም ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም (ኢሳያስ 532)። ዓለም ግን ክርስቶስን ቆንጆ ፈረንጅ አድርጎ ይስለዋል። እኛም በራሳችን ተስፋ ቆርጠን እግዚአብሔር ፈረንጅን እጁን አጥቦ ነው የፈጠረው ብለን እንድንደመደም አድርጐናል።

አፍሪካ የጨለማው አህጉር ተብላ ትታወቃለች። ጨለማነቷ በቆዳዋ ጥቁረት ብቻ ሳይሆን በሁሉም መስክ ነው። በቅኝ አገዛዝ ዘመን እንደ ዕቃ በብር ተሽጠናል ተለውጠናል። ጥቁር ሕዝብ በሰይጣን መልክ የወጣን ይመስል ጨልሞብናል።

ኢትዮጵያ የተጠራቸው ለብቻዋ ብርሃን ሆና በጨለማው አፍሪካ አህጉር እንድትኖር አይደለም። ኢትዮጵያ ኩሽ ስለሆነች የአፍሪካና የጥቁር ሕዝብ ተስፋና ፋና እንድትሆን እንጂ። እጆቻችንን ስንዘረጋ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር በእርግጥ እንዳለ ብርሃናችን ይታያል።

ዓለም ከፍልስፍናዋ የተነሳ ሰዶማዊነትን በፀጋ ተቀብለዋለች። መንግሥታት ወንድና ወንድን ወይም ሴትና ሴትን ሲያጋቡ አይተን ተገርመን ሳንጨርስ የምዕራቡ ዓለም አንዳንድ ቤተ ክርስቲያናት ሰዶማዊነትን ሲቀበሉ እያየን ነው። ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም እንዲሉ ነገ በአደባባይ ልናይ ያለው የትዳር ዓይነቶች ገና ጉድ ያሰኘናል።

ዓለም ተፈጥሮ ሰልችቷት በራሷ ፍልስፍና ኢተፈጥሯዊ ነገርን ስታበራ ኢትዮጵያ የእግዚአብሔርን ክብር በመግለጥ የጥቁር ሕዝብን ታሪክ ፋና በመሆን ትለውጣለች። ዓለም ያረጀውንና ያፈጀውን የጠላት አሰራር እንደ አዲስ በመቁጠር ደስ ተሰኝተንበት ይሆናል። ኢትዮጵያ ደግሞ ጆሮ ያልሰማውን ዓይን ያላየውን የጌታ ድንቅ ሥራ ታስተናግዳለች። በኢትዮጵያ የጀመረውም ይህ ብርሃን አፍሪካን ሁሉ ያበራል።

ዓለም ከጥበቧ የተነሳ እንደባቢሎን ዘመን የፈጣሪን ሥራ እየተገዳደረች ነው። ለዚህም ምሳሌ የሚሆነን ሰውን “ክሎን” ለማድረግ መነሳሳታቸው ነው። በምናለበት ዛሬ ይህ ተጀመረ እንጂ የነገውን ጉድ ማን አውቆት። ባቢሎንን ንግግሯን ደባልቆ በምድር እንደበተናት ሁሉ ዛሬም ዓለም ራሷን ለሌላ ለፍርድ እያዘጋጀች ናት።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ እጆቿን በመዘርጋት ለእግዚአብሔር የተሰጠች ናት። ዕድል ፈንታችንን በእግዚአብሔር ችሎት ላይ መጠቅለላችን እንደ መሃይምነትና ተስፋ መቁረጥ በዓለም ዘንድ ችሎት ላይ ይቆጠር ይሆናል። በሰዎች አቅምና መላ ላለመመርኮዝ ተስፋ መቁረጣችን እውነት ነው። የእግዚአብሔርን ጥበብ ለመውረስ ሞኝነትን መርጠናል። በዚህ የተነሳም የሰለሞን ጥበብን ለመስማት ፍጥረት ሁሉ ኢየሩሳሌም እንዳልተጓዘ ሁሉ የክርስቶስን ክብር ለማየት ወደ ምድራችን የሚፈጥንበት ዘመን በደጅ ነው።

መፍትሔ

ዓለም በየጊዜው በብርና ወርቅ እንዲሁም በሃይልና በጥበብ ገናና ለመሆን በመጣር ላይ ትገኛለች። ገንዘብንም አምላክ አድርጋ ታመልከዋለች። ይሁን እንጂ በዓለም አንድ ክፍል የሚገኙ ህፃናት በረሃብ ሲኖሩ በሌላ በኩል ደግሞ ስንዴ ተርፏቸው ባህር ውስጥ እንደሚጥሉ እንሰማለን። በርካታዎች በበሽታና በረሃብ ተይዘው መንገድ ዳር በሚተኙበት ምድር ባንዲራ ማርስ ላይ ለመስቀል ትሯሯጣለች። ዓለም ጥበቧም ሆነ ሀብቷ ለችግረኞች ጩኸት መልስ እንድትሰጥ ግድ ሲላት አላየንም። ምክንያቱም ለድሃ መድሃኒት ለመሆን የድሃ አምላክ ልብና ሃይል ያስፈልጋልና ነው። ለዚህም ነው የድሃ አደግ አባት ለሆነው አምላክ እጆቻችንን በፍጥነት መዘርጋት ያለብን።

በችግረኛነት በዓለም የምትታወቀው ኢትዮጵያ እጆቿን ስትዘረጋ ለዓለም እንቆቅልሽ የሆነ ፍትህን በምድሯ በማስፈን ሞዴል እንድትሆን ተጠርታለች። መሃይምነትና ኋላ ቀርነት የገነነባት ኢትዮጵያ ስትጎበኝ ለፍጥረት መፍትሔ ማፍለቂያ ምንጭ ትሆናለች።

እግዚአብሔር በዘመን መጨረሻ ሊሰራው ስላለው ድንቅ ሥራ ኢትዮጵያን አስቀድሞ የተስፋ ቃል በመስጠት ወደ ራሱ ጠርቷታል። በሥጋዊ አስተሳሰብ ካየን ኢትዮጵያን ለሞዴልነት የሚያበቃት ምንም ነገር የለም። እንዲያውም ከሰልፉ የመጨረሻ ጭራ ሆና ትገኛለች። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ግን የራሱን ክብር ለማሳየት የዓለም ዝቃጭ ሆና የምትቆጠረውን ኢትዮጵያን መርጧል።

የኤርትራ ባህር አምላክ እስራኤልን ከውጭ ጠላት የታደገበት ምስክር ነው። ዛሬ ቀይ ባህር ለኢትዮጵያ መሰበር ዓይነተኛ ምስክር ነው።

የዛሬ የኢትዮጵያ ከቀይ ባህር ጋር በመልከዓምድር የተለያየች ብትሆንም ልቧ ግን አሁንም አንድ እንደሆነ ጌታ ያውቃል። የዓለም አስታራቂዎች ወጥተው ወርደው ሊያደርጉ ያልቻሉትን ነገር ወደ እግዚአብሔር ከኤርትራውያን ጋር ወንድማማች ስለሆንን በጥሪያችን መሰረት እጃችንን እናነሳለን።

የኤርትራ ሕዝብ ከጥሪያችን የተነሳ በኢትዮጵያ ላይ ያለውን የአምላክ በረከትና ሞገስ ያስተውላሉ። ለብቻቸውም ከአምላክ ፍቃድ ውጭ ሆነው መኖሩ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝንባቸው ይገነዘባሉ። ከጥሪያችን በረከት ለመካፈልና ለኢትዮጵያ አንድነት ራሳቸው ኤርትራውያን በጌታ ሃይል ይነሳሉ። ቀይ ባህርም ዳግም የአምላክ ክንድ የሚታይበትና የኢትዮጵያ አንድነት በፍቅር የሚታደስበት ምስክር ይሆንልናል።

እግዚአብሔር በኢትዮጵያ ታላቅነቱን ሊያሳይ አስቀድሞ ራዕይን ሰጥቶናል። ይህንንም ለመረዳት ቅዱስ ቃሉን በጥሞናና በተከፈተ ልብ እናያለን።

ኢትዮጵያ የተስፋው ቃል ሕዝብ ናት። ስለሆነም የተሰጠንን መለኰታዊ ጥሪ በሙሉ ልብ እንቀበላለን። የእግዚአብሔር ዓላማ በምድራችን እንዳይከናወን እንቅፋት የሚሆን ሰይጣናዊ አሠራር ሁሉ በጌታ ኃይል ይሻራል። አምላክም ክብሩን በምድራችን በመግለጥ ኢትዮጵያን ለበረከት ያደርጋታል።

ወሳኝ ምርጫ

ታዲያ ይህ ሁሉ በረከት ከአርያም ታዞልን ምድራችን ለምን በጦርነትና ችግር ደቀቀች ብለን ብንጠይቅ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ይመሰክራል፦

እናንተ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በሰይፌ ትገደላላችሁ” (ሶፎንያስ 212)

ቁጣውንስ አየን። ተስፋችን ግን ወዴት አለ ብለን ስንጠይቅ ያ የእኛ ወሳኝ ምርጫ እንደሆነ ቃሉ ያስረግጥልናል። እግዚአብሔር በቃሉ ሁልጊዜ ታማኝ ነውና።

ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔርእሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፥ እንቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና” (ኢሳያስ 118-20)

የእግዚአብሔር ቃል እውነት ነው። ዛሬም ምርጫችንን ካላስተካከልን በረከቱ አባቶቻችንን እንዳለፈ ሁሉ እኛንም ያልፋል። ሰይፉን በበረከት ለመለወጥ ምርጫው የእኛ ፈንታ ነው። አንድ ቀን ኢትዮጵያ የጌታን አሸናፊነት ልታሳይ ተጠርታለችና ይህ መሆኑ አይቀሬ ነው። ዘመኑን ለመዋጀት ብንነሳ የበረከቱ ተካፋይ ሆነን ክብሩን ባየን ነበር። የጌታ ቃል እንዲህ ይነበባልና፦

በስሜ የተጠሩት ሕዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢፀልዩ ፊቴንም ቢፈልጉ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ ኃጢያታቸውንም ይቅር እላለሁ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ።” (2ና ዜና 714)

ኢትዮጵያ ሆይ! ዛሬስ ምርጫሽ የቱ ይሆን?

Please download the fileEthiopiaYetesfauAger to read in PDF

___________________________________

Posted in Faith | Tagged: , , , , , , , | 1 Comment »

Abdirizak Mohamed Mohamoud, “Even if I got a visa for Europe…I wouldn’t go”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 22, 2011

The only safe place to sleep was on graves”

Abdirizak Mohamed Mohamoud, 30, returned to his home village of Lafaisa, in the Jijiga zone of eastern Ethiopia, six months ago, after his attempt to reach Europe and a better life turned into an ordeal. He talked to IRIN, as well as a roomful of curious neighbours and friends, about his experiences as a migrant in Libya.

“I wasn’t satisfied with life here. I was a teacher, but I wasn’t earning enough to support my family. I had friends who had gone to Libya and then to Italy, but I only got as far as Libya.

“I crossed the border of Ethiopia into Sudan; then I crossed the Sahara in a lorry with 160 other people. All of the others were from Somalia – I was the only Ethiopian. One lorry broke down, then another came and took us the rest of the way.

“I paid the driver US$1,000 – money I got from all of my family and friends – but when we arrived in Libya, the driver wanted another $1,200 and held all of us hostage in his home on a big farm for two days.

“He gave me a cell phone and told me to call my family to get the money. He only got money from 10 individuals, even though he tortured us with electric shocks. I told my mother to send money but before it came, the Libyan police came and arrested all of us, including the driver.

“We were taken to a prison in Benghazi where there were about 900 Africans – Nigerians, Somalis, Eritreans and Congolese. After three months we thought we were going to die there. Some were tortured and some tried to kill themselves. We broke out by force, overwhelming the guards, and escaped, but some local people caught me and returned me to the jail. I spent one more month there before they transferred me to a Tripoli prison, where I spent two months.

“Then they transferred me again to a place called Katron, near the border with Niger, in the Sahara. I was there for a month with 320 Somali people before we escaped again. I found some people from Chad in Katron and stayed with them for 15 days and called my family to send money. My brother sent $300 to someone he knows in Tripoli, but that money paid only for me to be smuggled from Katron to Tripoli.

“I worked as a porter in Tripoli for 18 months, just to save money to get home. I couldn’t sleep at night because I was so afraid of being robbed; the only safe place to sleep was on graves. I managed to save $700 and pooled my savings with 14 friends to pay a smuggler to take us through Niger and into Chad. We left just before the uprising [in Libya] started.

“In Chad, people were dying of hunger and UNHCR [the UN Refugee Agency] refused to help us because they were busy helping the local people who were starving. We went on to Darfur in Sudan and UNHCR flew us to Khartoum and then to the Ethiopian border. I was very happy to get home after two years and two months.

“By the time I got back, one of my sisters had already left for Saudi [Arabia] to work as a housemaid. If I had got back in time, I would have told her not to go.

“I’m an example for my village – if I had succeeded, all the others would have gone. I don’t have a job now, I’m surviving by Allah, but even if I got a visa for Europe or the United States, I wouldn’t go – I’m dying here.”

May you survive up to Christ, brother!

Source: IRIN

_________________________________________

Posted in Ethiopia, Life | Tagged: , , , | 4 Comments »

ቅ/ሚካኤል የአሥር ዓመት ዓይነ-ሥውር አበራ — Miracles of Archangel Michael

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 20, 2011

የአገራችንን ዓብያተ ክርስቲያናት ልዩና ቅዱሳዊ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መካከል የቤተክርስቲያኖቹ ሕንፃዎች ዛፎችንና አእፅዋታትን ከተፈጥሮ ጋር በተስማማ መልክ አብቀለው ለምዕመናኑ አመች የሆነ ሁኔታ መፍጠር መቻላቸው ነው።

እላይ ቪዲዮው ላይ በከፊል እንደሚታየው ምዕመናኑ የቤተክርስቲያኖቹ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኙት ውብ የተፈጥሮ ሣሮች፡ አበቦች ወይም ዛፎች አጠገብ በመሆን እንዲሁም ቀዝቀዝ ያለውንና ነፋሻማውን ንጹህ አየር እየተቀበለ ለፈጣሪው ጸሎቱን ያደርሳል።

ብዙ ዓብያተ ክርስቲያናትን በመላው ዓለም ተዘዋውሬ ለማየት በቅቻለሁ፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር በቀላሉ ሊያገናኙ የሚችሉትና ለመንፈሳዊ ሕይወት በጣም አመቺ የሆኑ ዓብያተ ክርስቲያናት በኢትዮጵያ እንደሚገኙ አሁን ለመገንዘብ በቅቻለሁ። ይህን ለመሰለው ጸጋ እግዚአብሔርን ልናመሰግነው ይገባል። ምናልባት ይህ እድል አሁን በእጃችን ስላለ ላንገነዘበው እንችል ይሆናል፡ ሆኖም ግን በመልክአምድር እንደ አዲስ አበባ ከፍ ብለው በሚገኙ ቦታዎች ላይ የቤተክርስቲያኖች ቁጥር በዓለም በብዛት የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው። ይህ እራሱ እንደ አንድ ትልቅ ምልክት ሊሆነን ይገባል፡ ቤተክርስቲያን ልጆቿን ለመጭው ጊዜ እያዘጋጀች ነውና!

በዘመኑም ፍጻሜ የእግዚአብሔር ቤት ተራራ በተራሮች ራስ ላይ ጸንቶ ይቆማል፥ ከኮረብቶችም በላይ ከፍ ከፍ ይላል፥ አሕዛብም ሁሉ ወደ እርሱ ይሰበሰባሉ።” {ኢሳያስ 22}

/ሚካኤል የአሥር ዓመት ዓይነሥውር አበራ

የደወሌ ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከድሬዳዋ ማሥራቃዊ ክፍል በኢትዮጵያና በጅቡቲ ወሰን አቅራቢያ በረሃማ በሆነችው ከተማ ነው።

በደወሌ በረሃማ ሥፍራ ላይ በተመሠረተው የቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ልዩ ልዩ ተአምራት ታይቷል።

ከነዚህም አንድ ዓይነሥውር ከማየቱም በላይ ሁለተኛው ሊቀ መላእክት ቅ/ሚካኤል የተወሰደበትን ቆርቆሮ በተአምር ወደ ቤተ መቅደሱ መመለሱ ነው።

ዓያናቸው የበራው ግለሰብ አቶ ጥላሁን ታደሰ የሚባሉ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ ለዓይናቸው መታወር መነሻው በውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የቦኖ ውሃ አስቀጂ ሆነው በሚሠሩበት ወቅት ቢርካውን ሲከፍቱ እንደ ደም ያለ ነገር ይታያቸዋል ከዚህም ጋር የጋዜጣ ንባብ ሱስ ስለነበራቸው አዘውትረው ጋዜጣ ያነቡ ነበር። በእነዚህ ሁለቱ ምክንያቶች በየትኛው ዓይናቸው እንደጠፉ በትክክል ባይታወቅም ዓይናቸው ደም ካየበት ጀምሮ እየደከመ መምጣቱን በዝርዝር ገልጸዋል።

አቶ ጥላሁን እንዳስገነዘቡት ከልጅነቴ ጀምሮ ቅ/ሚካኤልን እወደዋለሁ አከብረዋለሁ እዘክረዋለሁ ግን ዓይኔ በመታወሩ ምክንያት ከሥራ ተወገድኩ ለመኖር ስል አንድ መሪ ልጅ ይዤ ከድሬዳዋ ደወሌ በመመላለስ የጫት ንግድ ጀመርኩ በዚህም ምክንያት በሄድኩ ቁጥር በረኸኛው ቅ/ሚካኤል በድርሳንህ እንደሚነገረው ብዙ ተዓምር ሠርተሃል በእኔም ላይ ተአምርህን አሳይ እለው ነበር። በንግዱ የዕለት ጉርሴን የዓመት ልብሴን በሚገባ እያገኘሁ የደወሌን ቅ/ሚካኤል አጥብቄ እማፀነው ነበር። ዕለቱ ማክሰኞ ሐምሌ 12 በዚሁ ዕለት የደወሌው ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ተባርኮ እንደሚገባ ባለቤቴ ነገረችኝ እኔ ግን እጄም እግሬም በመተሣሠሩ ምክንያት አንቺ ሄደሽ አክባሪ አልኳት ሄዳ አክብራ ተመለሰች።

በዚሁ የቅ/ሚካኤል ዕለት ልጄን ይዤ ዳቦዬን አቅርቤ ከዘከርኩ በኋላ ከጐረቤቶቼ ጋር ጠበሉን ጸዲቁን ቀምሰን ቅ/ሚካኤልን አመስግነን ጐረቤቶቼ ሲወጡ ጋደም አልኩ እንቅልፍ ያዘኝ በእንቅልፍ ላይ እንዳለሁ አንተ አንተ የሚል የጥሪ ድምፅ ሰማሁ ድምፁም ተደጋግሞ መጣ ብድግ አልኩ ልጁን ብጠራው የለም ነገሩ ግራ አጋባኝ በቤቴ ወለል ላይ በመተከዝ እንዳለሁ አንተ አንተ አታየኝም እንዴ? አለኝ እኔም መልሼ እኔ እኮ ዓይን የሌለኝ በመሆኔ ላይህ አልችልም አልኩ፤ መልሶም እኔ የደወሌው የመቶ አለቃ ኃይለ ሚካኤል ነኝ እንዴት አታውቀኝም አለኝ እኔም በደወሌ የማውቀው መቶ አለቃ ገበየሁን ነው አልኩት ዕለቱ ቅ/ሚካኤል በመሆኑ ከልጅነት የምማፀነው ቅ/ሚካኤል ይሆናል በዬ አስብ ነበር።

ሆኖም የደወሌው መቶ አለቃ ኃይለ ሚካኤል ነኝ ሲለኝ ልቤ በደስታ እየመላ መጣ እሱም በመቀጠል የለበስኩት ምንድር ነው? የእኔስ መልክ ምን ይመስላል? ሲል ጠየቀኝ፤ እኔም የለበሰው ልብስ በኮከብ የተጥለቀለቀ መሆኑንና መልኩም ቀይ እንደሆነ ነገርኩት ከዚህ በኋላ ለ10 ዓመታት ብርሃን አጥቶ የኖረው ዓይኔ ለማየት በመታደሉ በደስታ ተመላሁ ከዚሁም ቀጥሎ መሉ እንደ ብርሃን የሚያበራው ይኽ ሰው በቀጥታ እያየሁት የወርቅ ኃብል በአንገቴ ላይ አጠለቀልኝ የዓይኔን ብርሃን አረጋግጦ የድሮውን የወታደሮች ካኪ ልብስ አለበሰኝ ወርቁንም ሆነ ልብሱን ለማንም እንዳትሰጥ በማለት አስጠነቀቀኝ ከእኔ ተሠወረ።

ከተሠወረ በኋላ ለእኔም ሆነ ለጐረቤቶቼ ነገሩ እውነት አልመሰለም ባለ 50 ባለ 25 ባለ 10 ሳንቲም ገንዘብ በእግሬ ሥር እየጣሉ ይኽ ምንድር ነው? እያሉ ፈተኑኝ ሁሉንም ነገርኳቸው ይህን ሲያረጋግጡ ደስታው ልዩ ሆነ።

እግዚአብሔር ይመስገን የቅ/ሚካኤል ተረዳኢነት አማላጅነት በሁሉም ሰዎች ዘንድ ለዘለዓለም ይኑር” ማለታቸውን የሀ/ስብከቱ ጽ/ቤት በወቅቱ ገልጿል።

ከዚህም ሌላ ከባድ ነፋስ የተቀላቀለ ኃይለኛ ዝናብ ጥሎ በከተማ ውስጥ የሚገኙ ታላላቅ ሕንፃዎች ተሰነጣጠቁ፥ በላያቸው የነበረው የጣራ ቆርቆሮ የነፋሱ ኃይል ተገነጣጠሎ ሲወስድ ቀደም ሲል ከቤተ መቅደሱ ላይ ተወስዶ የነበረውና ግለሰቦች በራስ ወዳድነት ይጠቀሙበት የነበረው ቆርቆሮ በዚሁ ከባድ ነፋስ ተጭኖ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ በመምጣት በቅጽረ ግቢው ውስጥ ተቀመጠ፤ የተወሰደው ቆርቆሮ ተመልሶ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ በመገኘቱ ቅ/ሚካኤል የሠራውን ገቢረ ተአምር ሕዝበ ክርስቲያኑ በአድናቆት ተመልክቶታል።

___________________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ምን ጐደለን? እንጦጦ ቁስቋም ማርያም – Addis Church

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 16, 2011


መላካም ወላጅ ልጁ ከመወለዱ በፊት ለልጁ የሚያስፈልጉ ነገሮችን እንደሚያዘጋጅ፣ አሳድጎ ርስት ሰጥቶ፣ የጨዋ ልጅ ድሮ ጎጆ እንደሚያወጣው እግዚአብሔርም ለሰው ልጅ መኖሪያውንዓለም፣ የፍላጎቱን ግብ፣ አጽናኝ ጓደኛ ሰጥቶ ፈጥሮታል ከዚህ ባሻገር እግዚአብሔር ማንንም ሰው ያለ ወዳጅ አልተወውም። ክፉ ቢሆን እንኳ የሚወዱትን ሰዎች አዘጋጅቶለታል ይህም የእግዚአብሔር በጎ ስጦታ ነው

የሚበልጠውን ይዘናል? ከበረከት ሁሉ የሚበልጠው በረከት የዕድሜ በረከት ነው። ብዙ ጊዜ የምንኖረው መኖር መብታችን ስለሆነ ይመስለናል። መኖር ግን የእግዚአብሔር ስጦታ ነው። ወላጆቻችን ረጅም ዘመን ስለኖሩ እኛም እንደ እነርሱ ረጅም ዘመን ኖረን የምናልፍ ይመስለናሎ። መኖር የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑ የሚገባን ግን መኖርን የሚቋቋሙ ነገሮች ሲገጥሙን ነው። ስንታመም፣ በምርኮ ውስጥ ስንሆን እያንዳንዱን ቀን ዋጋ እንሰጠዋለን። እኛ ግን ለመኖር እርግጠኞች ሆነን ለመኖሪያው እንጨነቃለን። እስቲ መጀመሪያ ስለ መኖራችን እናመስግን! ከእኛ የተሻሉ ቆንጆዎች፣ ከእኛ የተሻሉ አዋቂዎች፣ ከእኛ የበለጡ ኃብታሞች፣ ከእኛ የተሻሉ ኃያላን አልፈዋል። እኛ የቀረነው በብልጠታችን ሳይሆን የእግዚአብሔር ምሕረት ስለበዛልን ነው።

ብዙዎች ይጨነቃሉ። ዓለም በቃኝ ያሉ መነኮሳት ሳይቀር ከወለዱት እኩል በፍርሃት ይናጣሉ የቪዛ ወሬ የብዙ አገልጋዮችን አፍ ሞልቶታል። ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ እጆቻቸውን ወደ እግዚአብሔር ሳይሆን ወደ አሜሪካ ዘርግተዋል። መንኮሳቱ እንኳ የሚመኩበትን ገዳም ትተው አሜሪካ ገዳማቸው ሆኗል። አሜሪካ ግን ከአንድ ሰው ጋር ተጣልታ የምትባረር አገር በመሆኗ ዋስትና ልትሰጥ አትችልም። በአሜሪካ ምድር ከሦስት ሰው አንድ ሰው በመንፈስ ጭንቀት በሽታ የተያዘና መድኃኒት ተጠቃሚ ነው። በምድረ አሜሪካ ሰው በዓይኑ የሚሰማ በስሜቱ የሚያይ ሆኗል። ስለዚህ የምንሸሽባቸው እነዚህ ኃብታምየተባሉ አገሮች ራሳቸው የሚበላ እንጂ የሚያረካ ወይም ዘላለማዊውን ነፍስ የሚያስደስት ነገር የሌላቸው ባዶሰዎች ናቸው

መንፈስ ቅዱስን የለበስን ስለሆንን አብዛኛው የምድር ሰው የሌለውንና የሚበልጠውን ነገር ለመጎናጸፍ በቅተናል፣ ታድለናልም፡ ማንም በደግነት ለማንም የማይሰጠው የዘላለም ሕይወት አለን። መንፈሳዊ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር ቤተሰብ የምትሆን መንፈሳዊ ኅብረት አለን። የመረጃ እጥረት ያለብን እንጂ ብዙ ያጣን ሰዎች አይደለንም። ስለ ኑሮ መባነን ከበዛብን ግን የጤናችን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ዶክተር ኢሳያስን ልኮ ከምዕራፍ 49:13-16 ፍቱን መድኃኒት አዞልናል።

“ጽዮን ግን፥ እግዚአብሔር ትቶኛል ጌታም ረስቶኛል አለች። በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን! እርስዋ ትረሳ ይሆናል፥ እኔ ግን አልረሳሽም። እነሆ፥ እኔ በእጄ መዳፍ ቀርጬሻለሁ፥ ቅጥሮችሽም ሁልጊዜ በፊቴ አሉ።

_________________________________________

Posted in Faith | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

Ethnic Cleansing in Libya – የሊቢያ በደል በጥቁር ሕዝብ ላይ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 14, 2011

ሊቢያ ውስጥ ጠቆር ባሉ ሕዝቦች ላይ የሚፈፀመው በደል አሁን አልጀመረም። በቀድሞው የሊቢያው ፕሬዚደንት በኮሎኔል ጋዳፊም ጊዜ በጥቁር አፍሪቃያን ላይ አድሎ ይፈጸም ነበር። ኮሎኔሉ የአውሮፓውያን መንግሥታት ለማስደሰት ሲል ወደ አውሮፓ ለመግባት የሚመኙትን አፍሪቃውያን ስደተኞች በየካምፑና እስር ቤቱ እያጎረ ያሰቃያቸው ነበር።

አሁን ደግሞ በአውሮፓውያን እርዳታ ጋዳፊን የፈነቀሉት ሀይሎች የሰሜን አትላንቲኩ ውል ድርጅት አለቃዎቻቸው እያዩ “ጥቁር” አፍሪቃውያንን መንጥረው መጨፍጨፉን ቀጥለውበታል።

NATO እንደነ ቢቢሲ፡ ሲኤንኤን እና አልጀዚራ በመሳሰሉት ቀጣፊ የዜና ማሰራጫዎች አማካይነት ጸረ ጥቁርአፍሪቃ የሆነ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት አፍሪቃውያኑ የኮሎኔል ቀጣፊ ቅጥሮች እንደሆኑ ስማቸው እንዲጠፋ አስተዋጽኦ አድረጓል። የአፍሪቃ አገሮች የጋዳፊ ደጋፊዎች እንደሆኑ፡ ኮሎኔሉም በአፍሪቃውያን ዘንድ ተወዳጅ እንደሆነ አድርገው ነው የዜና ማሰራጫዎቹ እስካሁን ደግመው ደጋግመው የሚቀባጥሩት።

በጥቁሮች ላይ እየተካሄደ ስላለው አሰቃቂ ጭፍጨፋ የሚናገሩ ብዙ ቪዲዮች ዩቲውብ ላይ ማየት በምንችልበት ወቅት፡ እነ ኦባማ፡ ሳርኮዚና ካሜሮን እንዲሁም የ “ሰብዓዊ መብት” ተሟጋች ነን የሚሉት ድርጅቶች ሁሉ የተቃውሞ ድምጻቸውን እስካሁን አላሰሙንም፡ ሊቢያ ውስጥ የሊቢያ ተወላጅ የሆኑ ጥቁር ሊቢያውያን እንዳሉ መናገርም አይፈልጉም። እንዲያውም ሊቢያ የአፍሪቃ ክፍለ ዓለም ውስጥ እንደማትገኝ አድርገው ነው ዜና ማሰራጫዎቻቸው የሚለፍፉት።

በሊቢያ የተካሄደው የአውሮፓውያኑ ዘመቻ በጥንቃቄና በፕላን ታቅዶ የተዘጋጀ ዘመቻ ነው። ሁለት ወፍ ባንድ ድንጋይ ለመግደል በማቀድና አፍሪቃውያኑ ስደተኞችም በሊቢያ በኩል አድርገው ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ “የጋዳፊ ቅጥረኞች” የሚል ስም በመስጠት ገና ሊቢያ እያሉ በሰፊው እንዲገደሉ እየተደረገ ነው። “ውሻውን መጥፎ ስም ሰጥተህ ግደለው” እንዲሉ። ስርሰደድ የሆነው የአረብዘረኝነት በሽታ በጣም አመቺ እንደሆነ የተረዱት “ብልጥ” አውሮፓውያን ድንበራቸውን ኢሰብዓዊ በሆነ መልክ ድንበሮቻቸውን “ለመከላከል” ወስነዋል። አፍሪቃውያን ሞቱ አልሞቱ ግድ እንደማይሰጣቸው ዲያብሎሳዊ ድርጊቶቻቸው ሁሉ በግልጽ ይናገራሉ።

ምንም እንኳን ደቡብ አፍሪቃ እና ናይጀሪያ የኔቶን ወረራ መጀመሪያ ላይ በመደገፍ አሳፋሪ የሆነ ድርጊት ለመፈጸም ቢበቁም፡ ይህ የአውሮፓውያን የባርነት እና አዲስ የቅኝ ገዥነት መንፈስ ወደ አፍሪቃ እየመጣ እንደሆነ የአፍሪቃው ህብረት ገና ከመጀመሪያው ተገንዝቦት ነበር። ድምጹ አልተሰማም እንጂ!

የሊቢያ ሕገ መንግሥት በእስልምና ላይ የተመሠረተ እንደሚሆን የአዲሱ ሊቢያ መስተዳደር መሪዎች በግልጽ ተናግረዋል። ታዲያ እነዚህ በሙስሊምነታቸው እንደሚኮሩ የሚናገሩት ሊቢያውያን ልክ ሱዳን በዳርፉር ጥቁር ሙስሊሞች ላይ እንዳካሄደችው ዓይነት ጭፈጨፋ አሁንም ጎረቤት በሆነችው ሊቢያ በጥቁር ሙስሊሞች በጥቁር አፍሪቃውያን ሙስሊሞች ላይ የሚዘገንን የግድያ ዘመቻ እያካሄዱ ነው፡ የዓለም ማሕበረሰብም እንዳላየና እንዳልሰማ ዝም ማለቱን መርጧል።

 

____________________________________________

Posted in Ethiopia, Media & Journalism | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Shocking Things You Now Realize To Be True

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 13, 2011


“Truth shall spring out of the earth; and righteousness shall look down from heaven.” Psalm 85:10

 

We are living through a time of great awakening. The people of our world are beginning to open their eyes and realize the stunning depth of the scams and collusion taking place all around them. These scams that steal their wealth, poison them with chemicals, enslave them with financial trickery and control their minds with propaganda. These scams are the very fabric of modern government, the mainstream media, universities and so-called “science” institutions.

 

 

Here are 9 of those scams that you probably never would have believed just 2-3 years ago; but now you probably realize these are true!

#1 – Most of the honey you buy in the grocery store contains no actual honey whatsoever

It’s true, the so-called “honey” isn’t even technically honey. Most of it is made of cheap “mystery” sweeteners, illegally imported from China, right under the nose of the FDA.

http://www.naturalnews.com/034123_h

http://www.naturalnews.com/034102_h

#2 – The fluoride that’s dripped into municipal water supplies is actually a highly toxic industrial chemical byproduct.

This scam is exploding in the faces of all the ignorant dentists and doctors who have been pushing this poison for years. Once again, they were wrong; the “conspiracy theorists” were right.

http://www.naturalnews.com/033753_w

http://www.naturalnews.com/031547_f

http://www.naturalnews.com/031602_f

#3 – Flu vaccines often contain live flu viruses and actually cause the flu as a way to worsen the flu season and scare more people into buying vaccines.

It’s also true with MMR vaccines, which cause the measles. Flu vaccines are the greatest medical hoax that has ever been perpetrated on the world:

http://www.naturalnews.com/033998_i

http://www.naturalnews.com/033816_s

http://www.naturalnews.com/029641_v

http://www.naturalnews.com/031043_f

#4 – Prestigious U.S. hospitals are widely engaged in black market organ trafficking and organ transplants.

And why not? It’s profitable, and they can claim they’re “saving lives!” Make no mistake: the organ transplant industry is steeped in dark, psychopathic criminal activity.

http://www.naturalnews.com/028994_o

http://www.naturalnews.com/034060_o

#5 – The child sex slave industry is huge, highly profitable, and found everywhere across America (and the world).

You wouldn’t have believed this, probably, until the whole Penn State scandal recently made headline news around the world. As everybody now knows, Penn State sports officials routinely raped young children, even pimping them out to other criminal rapists who paid big money to rape young boys. This went on for 15 years right inside a prestigious university, right here in America.

Are you shocked? You shouldn’t be. Alex Jones has been sounding the alarm about this for a decade. Nobody listened to him. They couldn’t believe it was real. People would rather bury their heads in the sand than face reality.

And yet, this Penn State scandal just scratches the surface. The far deeper horrifying truth of all this is that Child Protective Services routinely kidnaps young American children and sells them into sex slavery — so-called “white slavery.” That story has not yet been covered by the mainstream media.

http://www.naturalnews.com/032501_M

http://abcnews.go.com/US/penn-state

http://www.prisonplanet.com/archive

http://www.cnn.com/2011/11/10/justi

http://www.pennlive.com/midstate/in

#6 – Commercial chickens are routinely fed arsenic, and commercial cows are routinely fed chicken poop.

Oh, you didn’t know that? When you eat conventional beef, you’re eating meat from cows who created that meat by consuming chicken poop. Yumm! Can I have some more poop on that burger, please?

http://www.naturalnews.com/032659_a

http://www.naturalnews.com/000987.html

http://www.naturalnews.com/028675_b

#7 – “Natural” foods and cereals are routinely made with genetically modified ingredients

Oh, you thought “natural” meant better than organic? Non-GMO? Stop getting suckered by the cereal companies and dishonest food conglomerates. Know what you’re really eating:

http://www.naturalnews.com/033838_b

http://naturalnews.tv/v.asp?v=15C9C

#8 – The global banking industry is a criminal racket that steals wealth from working class People and redistributes it to the global wealthy elite

You wouldn’t have believed this five years ago, but now, looking at your own bank account, the job you lost, the house you can’t sell and the health care you can’t afford, it’s all sinking in: The global financial system is an engineered con that suckers working-class people into giving up all their wealth, piece by piece, until they die bankrupt. Indentured servitude…

http://www.naturalnews.com/News_000

http://www.naturalnews.com/025672_m

http://www.prisonplanet.com/goldman

#9 – The U.S. government routinely conspires with pharmaceutical giants to conduct criminal, inhumane medical experiments on innocent people.

Recent revelations about the U.S. government’s secret medical experiments in Guatemala are just the tip of the iceberg here. Dr. Jona Salk, inventor of the polio vaccine, also ran unethical medical experiments on people. In fact, the entire history of modern medicine (pharmaceuticals, vaccines, chemotherapy and more) is something of a “house of horrors” of inhumane medical experiments on innocent victims.

http://www.naturalnews.com/033483_G

http://www.naturalnews.com/031564_J

http://www.naturalnews.com/033988_a

http://www.naturalnews.com/019189.html

http://www.naturalnews.com/019187.html

 

Source: Naturalnews.com

________________________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia | Leave a Comment »

አንጎልና ጦርነት – No pain, No Brain

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 6, 2011

አንጎልህን መመልከት አትችልም

በሩስያ አብዮት አንድምታ መሠረት መምህሩ እምነትንና የእግዚአብሔርን ሕልውና ስለ መካድ ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንዲህ እያለ ያስተምር ነበር፦

እነዚህ ምንድር ናቸው?”

የዐይን መነፅሮች ናቸው!”

የዐይን መነፅሮቹን ታዩአቸዋላችሁ?”

አዎ፥ እናያቸዋለን!”

በእርግጥም የዐይን መነፅሮቹን ታዩአቸዋላችሁ። በመሆኑም መነፅሮቹ አሉ ማለት ነው። ይሁን እንጂ እግዚአብሔርን ታዩታላችሁ?”

አናየውም!”

እዚህ ላይ ሲደርሱ አንድ ልጅ ተነሣና “የአንተን አንጎል ማየት አንችልም። ስለሆነም አንተ አንጎል የለህም ማለት ነው።” አለ።

ምስጋና እና እግዚአብሔርን መካድ።

እግዚአብሔርን የከዳ ሰው ምስጋና ማቅረብ አይችልም። የዚህ ምክንያቱ እርሱ በበረከት ሲጥለቀለቅና ለዚህ ምስጋናውን ለማቅረብ ሲፈልግ ማንን ማመስገን እንዳለበት ስለማያውቅ ነው።

በእግዚአብሔር የማያምንን ሰው ለመግለጽ የሚመረጠው መንገድ ለእርሱ የሚጣፍጥ ምግብ ካቀረቡለት በኋላ “ይህን ምግብ ያዘጋጀች ምግብ አብሳይ እንዳለች ታምናለህ?” ብሎ በመጠየቅ ነው።

ከዚህ ምግብ በስተጀርባ ምግብ አብሳይ መኖሯ እርግጥ ከሆነ ይህ ዓለም በውስጡ ከሚገኙት ድንቅ ሕግጋቶቹ ጋር ሊቆይ የቻለው በአጋጣሚ ነው ማለት ነው።

ጦርነት እንዴት ይጀምራሉ?

አንድ ልጅ አባቱን “ጦርነቶች እንዴት እንደሚጀምሩ ንገረኝ።” ብሎ ጠየቀው።

አባቱም እንዲህ ብሎ መለሰለት፦ “እንደ ምሳሌ አድርጌ የምነግርህ የአንደኛውን የዓለም ጦርነት ነው። ይህ ጦርነት የተጀመረው ጀርመን ቤልጂየምን በወጋች ጊዜ ነበር።”

በዚህ ጊዜ የልጁ እናት በቁጣ ቃል የባሏን መልስ አቋረጠችና እንዲህ አለች፦ “ለልጅህ እውነተኛውን ነገር ነገረው።” ጦርነቱ የተጀመረው ጥቂት ሰዎች እርስ በእርሳቸው በተገዳደሉ ጊዜ ነው።”

አባት የልጁ እናት እንዲህ ባለ ሁኔታ በመካከል ጣልቃ ገብታ ስላቋረጠችው ተበሳጨና ወደ እርሷ እየተመለከተ በተግሣጽ ቃል “የጠየቀው እኔን እንጂ አንቺን ስላልሆነ ለምንድር ነው የምታቋርጭኝ?” አላት።

በዚህ ጊዜ እናትየዋ በጣም ስለ ተናደደች የቤቱን መዝጊያ በሃይል ወርውራ ስትወጣ በግድግዳው ላይ የታሰረው መደርደሪያ ተናጋ። በዚህ ጊዜ በላዩ ላይ ከተደረደሩት ውድ ዕቃዎች መካከል ጥቂቶቹ ወለሉ ላይ ወድቀው ተሰባበሩ።

በዚህ ጊዜ ጥቂት ነግሦ የቆየው ፀጥታ በልጁ ንግግር ተቋረጥ፦ “አሁን አባዬና እማዬ ጦርነት እንዴት እንደሚጀምር ስላሳዩኝ ለጠየቅሁት ጥያቄ መልስ አልሻም።

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: