Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • October 2011
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
    31  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for October 26th, 2011

አረብ በመሀረብ አርብ፡ “የመጨረሻ ተስፋየ የአገሬ ፀበል ብቻ ነው”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 26, 2011

ታች ላይ የሚገኘውን ፊልም በቅርብ የቀረጸው የፌደራል ጀርመን ብሔራዊ የቴሌቭዥን ጣቢያ ነበር። ፊልሙ ላይ ከቀረቡት ዋና ዋና ቁምነገሮች መካከል የሚገኙትን መልእክቶች እናገኛለን፦

  • 600.000  የቤት አገልጋዮች በትንንሾቹ የተባበሩት የአረብ ኢሚራቶች ይኖራሉ።

  • 80%  የሚሆነው የኢሚራቶች ነዋሪ ስደተኛ ሠራተኛ ነው።

  • ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ወደ አረብ አገር የሚልኩት የአዲስ አበባ ወኪሎች የሚገኙት በመርካቶ ገባያ አካባቢ ነው። ብዙዎቹ ወኪሎች ፈቃድ የላቸውም። ለምሳሌ፣ ፋይዛ የጉዞ ወኪል

  • አብዛኛዎቹ ወደ አረብ አገር የሚሄዱ ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ሴቶች ስማቸውንና ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ ይደረጋሉ።

  • እንደ ትርንጎያሉት ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ዱባይ ሲገቡ ገና በአውሮፕላን ማረፊያው ነው ፓስፖርታቸውና ተንቀሳቃሽ ስልካቸው በአስቀጣሪዎቹና በቀጣሪዎቹ የሚነጠቀው።

  • ኢትዮጵያውያን የቤት አገልጋዮች በየቀኑ እስከ 20 ሰዓት፡ ሳምንቱን ሙሉ እንዲሰሩ ይገደዳሉ፡ ምግብም በቀን አንዴ ብቻ ያገኛሉ።

  • የወር ደምወዛቸው ከ120 ዩሮ አይበልጥም፡ እሱም አንዳንዴ ጭራሽ አይከፈላቸውም።

  • ከጨካኝ አሰሪዎቻቸው በደል ያመለጡ 400 የሚሆኑ ሴቶች በዱባይ እስር ቤቶች ውስጥ ይማቅቃሉ። ለመብታቸው የሚከራከርላቸው ማንም የለም። እንዲያውም የእስር ቤት ጠባቂ ፖሊሶች ሴቶቹን በየጊዜው ይደፍሯቸዋል።

  • ዱባይ ውስጥ ተቃውሞን ወይም ብሶትን መግለጽ አይፈቀድም፥ ለመስማትም ሆነ ለመርዳት ዝግጁ የሆነ መንግሥታዊ ወይም መንግሥታዊ ያልሆነ ዓለም ዓቀፍ ድርጅት የለም።

  • የቤት ሠራተኞችን ኢሰብዓዊ የሆነ አኗኗር ለመከታተል ዱባይ የሚገቡ ጋዜጠኞች ክትትል ይደረግባቸዋል፡ ይህ የጀርመን ቴሌቪዥን በድብቅ የቀረጻቸው ፊልሞች በዱባይ ባለስልጣናት እንዲደመሰስ ተደርጓል። (የፖሊስ አገር!)

  • በኢትዮጵያ ሙስሊሞች የሚተዳደረው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ትርንጎን ለመሳሰሉት የኢትዮጵያ ተወላጆች ግልጋሎት አይሰጥም፡ እሷን በሚመለከት ከእዚህ የቴሌቪዥን ቡድን ጋርም ለመተባበር ፈቃደኛ አልነበረም፡ እንዲያውም ኢትዮጵያውያንን በመርዳት ፈንታ እነርሱን ለዱባይ ባለሥልጣናት አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ሪፖርቱ ያመለክታል።

  • ኢትዮጵያውያኑን ለመርዳት ፈቃደኛ ሆኖ የተገኘው በዱባይ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ሳይሆን፡ አጠገቡ የሚገኘው የፊሊጲንስ ኢምባሲ ነው። (ሐዋርያው ፊሊፖስ የኛ አምባሳደር ተንከባካቢ ስለነበር ይሆን?)

  • በፊሊጲንስ አገር የቤት ሠራተኞች ተጨማሪ የቤተሰብ አባል እንደሆኑ ተደርገው ነው የሚቆጠሩት ፡ በዱባይ ግንባሪያየሚል ስም እየተሰጣቸው ይገረፋሉ፡በፈላ ውሃ ይቃጠላሉ።

ትዕቢተኛዋ ባቢሎን ሰማይ ጠቀስ ፎቆችን መስራት ትወዳለች፤ ብልጭልጭ በሆኑ ነገሮች ታሸበርቃልች፤ በጥቁር ወርቅም ሰክራለች፤ ለቅንጦትና ምድራዊ ለሆነ ምቾትም እንቅልፍ አጥታ ትኖራልች፡ ሰውን የመሰለ ክቡር ፍጡርን ግን ትንቃለች፣ ታንቋሽሻለች።

ትርንጎ የት እንደደረሰች ለማወቅ የቴሌቪዥን ቡድኑ አልቻለም። ግን የትም ትድረስ የትም፡ እነዚህ አረማዊ የአረብ ማህበረሰቦች በዚህች ምድር ላይ የተሰጣቸውን የቤት ስራ እየሰሩ አይደሉም፡ ምናልባትም የመጨረሻውን ፈተና በኢትዮጵያውያኑ አማካይነት ለመውደቅ እየበቁ ነው ፤ እንዲያውም የመጥፊያ ጊዚያቸው መቃረቡን በአገሮቻቸው እየተቀጣጠለ ያለው እሳት ፈጋ አድርጐ እያሳየን ነው።

በጣም የሚያሳዝነው፡ በእነ አባ ጂፋር ጊዜ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያትን በባርነት ሲሸጡ የነበሩት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች አሁንም በተመሳሳይ መልክ ይህን አጸያፊ ድርጊት በመፈጸሙ ረገድ ክፍተኛ ሚና ለመጫወት መብቃታቸው ነው። እስላም በሆኑ አገሮች ኢትዮጵያን እየወከሉ የሚሄዱት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ናቸው። እነዚህ ኢትዮጵያ አገራችንና ኢትዮጵያውያትን ያገለግሉ ዘንድ ዱባይን በመሳሰሉ የአረብ ከተሞች በየቪላው የተቀመጡት ዲፕሎማቶች የሚሰቃዩ ወገኖቻቸውንለመርዳት ፈቃደኞች አይደሉም።

90ዎቹ ዓመታት የአዲስ አበባ ከንቲባ እንዲሆን ተሹሞ የነበረው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ስልጣኑን ያለአግባብ በመጠቀም ባጭር ጊዜ ውስጥ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የመስጊድ ግንባታ ጂሃዳዊ ዘመቻ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አካሄደ። ከዚህ ድርጊት በኋላ ይህ ግለሰብ ምንም ዓይነት መንግሥታዊ ኃላፊነት ሊወስድ አይገባውም ነበር፡ ነገር ግን በሱዳኗ ካርቱም የኢትዮጵያአምባሳደር ሆኖ ለመሾም በቃ፡ ባለፈው መስከረም ላይም አንድ ታላቅ የኪነጥበብ በዓል እዚያው አዘጋጀ። ይህን መሰሉ ዝግጅት ነፃ በወጣችዋና በአዲሲቷ ሱዳን መቅረብ ሲገባው፡ በክርስቲያኖችና በዳርፉር ጥቁር እስላሞች ላይ ጭፍጨፋውን ስታካሂድ ለነበረችው፡ እንዲሁም የኢትዮጵያን መከፋፈል ለምትመኘዋ ለካርቱም ተሰጠ። ከዚያም ወደዚህ የኪነጥበብ ትዕይንት በዓል ሲያመሩ የነበሩ የትግራይ ኪነጥበብ ቡድን ዓባላት በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን አጡ። ለመሆኑ ይህ በካርቱም የተቀመጠው አምባሳደር በጋበዛቸው ዘፋኞች ሕይወት መጥፋት ላይ ምን ዓይነት ሚና ተጫውቶ ይሆን?

ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?” [ማር. 836]

ስቃይ በዱባይ #1


ስቃይ በዱባይ #2

ስቃይ በዱባይ #3


ስቃይ በዱባይ #4

ስቃይ በዱባይ #5


__________________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: