Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • June 2011
  M T W T F S S
   12345
  6789101112
  13141516171819
  20212223242526
  27282930  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

የበግ ለምድ የለበሱ ነጣቂ ተኵላዎች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 16, 2011

አባ በዝብዝ ካሣ (አፄ ዮሐንስ) ለደጃዝማች ኃይሉ እንዲህ አሏቸው፡

አባቶቻችን ሲጋደሉላት በኖረችው አገራችን ላይ የሠፈሩትን ቱርኮችና ግብጦች ካገራችን ለማስወጣት ከኔ ጋር እንደመተባበር ፈንታ ከእነሱ ጋር ተሰልፈው እኔን ለመውጋት መዘጋጀትዎን ደርሼበታለሁ። ይህ ምኞትዎና ሐሳብዎ ደግሞ እኔና እኔን የመሳሰሉ የኢትዮጵያ ቆራጥ ልጆች እያለን አይሳካልዎትም። የአባቶቻችንና የጀግኖቻችን አጥንትም እሾህ ሆኖ ይወጋዎታል።

የግብጽ ዋናው ዓላማዋ የቀይ ባሕርንና የአባይን ወንዝ አካባቢ ጭምር ለጥቅሙዋ ማዋል ነበር። ለዚህም ዓላማዋ መሳካት ሃይማኖትን ሽፋን አድርጎ ደጋፊን ማብዛትና ተቃዋሚንም በመጀመሪያ እርስ በርሱ ማፋጀት ነበር።

ግብጦች ቢመጡ በመጀመሪያ የምንዋረደው እኛ ነን። ከዚህም ቀደም ቱርኮች ወደ አገራችን ሲገቡ ያደረሱት ጥፋትና በደል ተወርቶ አያልቅም። የአረመኔነት ሥራ ነው የሠሩት።” (ዮሐንስ፡ በ ታላቁ ማሞ ውድነህ፡ ፲፱፻፹፭ ዓ.መነበብ ያለበት መጽሐፍሌላ ጊዜ እምለስበታለሁ)

በዐሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን ቱርኮች በቀይ ባሕር አካባቢ ማተኮር ከጀመሩ በኋላ፡ የኢትዮጵያውያን መከፋፈልና የእርስ – በርሱ ግጭትም እየከረረና ሥር እየሰደደ ነበር የመጣው። በተለይም ቱርኮች በሰሜንና በምሥራቅ ኢትዮጵያ እጃቸውን አስገብተው የለኮሱት እሳት ኢትዮጵያን እስካሁን እየለበለባት ነው።

በአባቶቻችንና በእናቶቻችን ላይ ይህ ነው የማይባል ጭካኔ የተሞላበት በደል ሲፈጽሙ የነበሩት ቱርኮች አሁን ደግሞ መልካቸውን ቀየር እያደረጉ ወደ ውዲቷ አገራችን በመግባት ላይ ናቸው። ይህም፡ በቀላሉ የማንመለከተው አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ቱርክ ጎረቤታችን አይደለችም፡ ቱርክን ከኛ ጋር የሚያዛምዳት ምንም ነገር የለም። የቱርክኛ ቋንቋ፡ የቱርክ ባሕል ወይም የእስላምና እምነቷ ለሕዝባችን የሚጠቅመው አንዲት ቅጣት ነገር የለችም። ቱርክ ገና አዳጊ አገር፡ ግማሹ ሕዝብዋም ከኢትዮጵያ ባላነሰ በከፋ ድህነት የሚሮርባት አገር ነች። ቱርክ ባገሯ በሚገኙት ንዑስ ሕዝቦች፡ ክርስቲያኖችና ኩርዶች ላይ አድሎና በደል የምትፈጽም አገር ነች። ይህ ሆኖ ሳለ፡ ባሁኑ ወቅት፡ ቱርክ በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙት የቀድሞ ቅኝ ግዛት ሕዝቦች ጋር በመተባበር ብሎም የመሪነቱን ሚና ለመጫወት በመንጠራራት ላይ ትገኛለች። ቱርክ፡ የቀድሞዋ ወዳጇን፡ እስራኤልን መተነኳኮል እና ማስቆጣቱን መርጣለች።

መጽሐፍ ቅዱስ፡ አንዳንዴ “Sythian” (እስኩቴስ)እያለ የሚጠራት ቱርክ፡ እና ሕዝቧ፡ በመላው ዓለም እንደ መቅሰፍት የሚላኩ

ኃይሎች መሆናቸውን አሁን ሁላችንም የምንታዘበው ነገር ይመስላል።

... 1950ቹ ዓመታት የሰሜን አውሮፓ አገሮች ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በደረሰባቸው የኗሪዎች ወይም የሠራተኞች እጥረት ሳቢያ፡ አገሮቹ መጀመሪያ ከደቡብ አውሮፓ፤ ከጣሊያን፡ ስፓኝ፡ ፖርቱጋል እና ግሪክ ሠራተኞችን ወደ አገሮቻቸው ማስገባት ጀመሩ። ከዚያም፡ ልክ አሁን ሳዑዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች ይላኩልኝ እንደምትለው፡ አውሮፓውያኑ፡ በተለይም ጀርመን፡ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞችን ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ እንዲልኩላቸው ጠየቁ፡ ነገር ግን ንጉሡ እኔ ሥራ አጦች የሉኝምበማለት የአሻፈርኝ መልዕክት ስለላኩና፡ እግዚአብሔርም ስላልፈቀደ፡ እነዚህ የአውሮፓ አገሮች ቱርካውያን ሠራተኞችን በሚሊየን ወደአገሮቻቸው ለማጉረፍ በቁ።

በዓለም ሕዝቦች ላይ በታሪክ ይህ ነው የማይባል ከፍተኛ ጭካኔ እና በደል ሲፈጽሙ የነበሩት እነዚህ የአውሮፓውያን አገሮች አሁን ውስጣዊ ሰላሙን አጥተው ለሚያረካ ኑሮ ሊበቁ ያልቻሉት፡ መቅሰፍቱ በቱርኮች እና በአረቦች አማካይነት ስለመጣባቸው መሆኑን እየተረዱት ነው። ገና ብዙ ጣጣ እንደሚጠብቃቸው አካሄዳቸው ያስታውቃል። ለስፓኝ እና ለፖርቱጋል፡ በስተደቡብ ሞሮኮና ማውሪታኒያ ተመድቦላቸዋል። ለፈረንሳይ፡ በስተደቡብ አልጀሪያ ተመድቦላታል፡ ለጣልያን፡ በስተደቡብ ሊብያና ቱኒስያ ተመድበውላታል፡ ለግሪክ፡ በስተደቡብ ግብጽ ተመድባታለች፡ ለተቀረው አውሮጳ፡ በስተደቡብ ቱርክ ተመድባላቸዋለች። አንድ የ ሁኔታ ክፍል (Situation Room) ከፍቶ ሁሉን መታዘብ ነው።

ወደኛም ዘወር ስንል፡ ያሁኑ ከዳተኛና አመጸኛ የኢትዮጵያ ትውልድ ከፈጣሪው ከእግዚአብሔር ያገኘውን ተወዳዳሪ የማይገኝለት ፀጋ ተቀብሎ ለመኖር አሻፈረ በማለቱ፡ ጥሩውን ከመጥፎው ለይቶ ለማየት እየከበደው ነው፡ ቀጥተኛውን መንገድም መርጦ ለመጓዝ አልተቻለውም፡ ሦስተኛው ዓይኑ እየታወረ ነውና።። ይህን የተረዱትም እባብ ጠላቶቹ፡ መሸፈኛ ቆዳዎቻቸውን እየቀያየሩ ና ወደኔ፡ ነይ ወደኔ እያሉ ሊያታልሉት ሲሞክሩ ይታያሉ።

ከግራኝ መሃመድ ሰይጣናዊ የጥፋት ዘመን አንስቶ ቱርክ በኢትዮጵያ ላይ የጥፋት ተልዕኮዎችን በመያዝ ሕዝባችንን ስትፈታተን መቆየቷን፡ ወደ አገራችንም ለበጎ ነገር ገብታ እንደማታውቅ ያሁኑ ትውልድ ደግሞ ደጋግሞ ሊያውቅና ሊያሳውቅ ይገባል። በተለይ ኢትዮጵያዊ ሕጻናት ይህን ታሪካዊ ትምሕርት በየቤቱ፡ በየትምሕርት ቤቱ መቅሰም ይኖርባቸዋል።

በተለይ፡ ሕጻናት፡ ምክኒያቱም የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች በአሁኑ ጊዜ ትኩረቱን እያደረጉ ያሉት በሕጻናቱ ላይ ነውና። ልጅህን 7 ወይም 8 ዓመት እስኪሞላው ስጠኝ ከዚያ ውሰደው የፈለግከውን ማድረግ ትችላለህየሚለውን አባባል በደንብ የተረዱት እነዚህ የእፉኝት ልጆች፡ ለጨቅላ አያሌው እና ለጣፋጭ አየለች በመርዝ የተቀመመ ከረሜላቸውን ኑና ምጠጡ በማለት ላይ ይገኛሉ።

ባሃይለሚባለው መጤ የእስልምና እምነት አምባሳደር ለመሆን የበቃችው እህታችን፡ የውጭ ሰው አግብታ ወደ አገራችን ከተመለሰች በኋላ የኢትዮጵያውን ሕጻናትን ህሊና ለማጠብ ፀሀይየሚል የሕፃናት ፕሮግራም በብሔራዊው ቴሌቪዥን በማቅረብ ላይ ትገኛለች።

ኢትዮጵያዊ መልኩንና ማንነቱን ቀይሬአለሁ የሚል ወገን ከቱርኩ እና ከአረቡ የከፋ ድርጊት ሊፈጽም እንደሚችል እንዴት ተሳነን?

ኢትዮጵያን በመሳሰሉ አገሮች ውስጥ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኝ አንድ የ ቱርክ ድርጅት አለ፡ ይህም ጉለን እንቅስቃሴተብሎ የሚታወቀው ነው። ይህ እንቅስቃሴ በቱርኩ ኢማም፡ በ ፋቱላ ጉላንነው የተጀመረው። ይህ እንቅስቃሴ ምስጢራዊ በሆነ መልክ ለመስራት ቢነሳሳም፡ ተልዕኮው ወይም ዓላማው ምን ሊሆን እንደሚችል አሁን እየታወቀ ነው።

ከቱርክ ውጭ በመላው ዓለም እስከ 10 ሚሊየን የሚጠጉ ተከታዮች እንዳሉት የሚነገርለት ይህ የ ጉላን እንቅስቃሴ፡ የቱርክ መንግሥት አባት በሆኑት በ አታቱርክ መሪነት ጸረእስላም፡ ዘመናዊ እና ዓለማዊ ለመሆን የበቃችውን የቱርክ አገር ቀስ በቀስ ወደ እስልምና ለመለወጥ እየተቻለው ነው። 20% የሚሆነው የቱርክ ነዋሪ የዚህ እንቅስቃሴ አባል መሆኑም ይታወቃል። ቱርክን በማስተዳደር ላይ ያለው የኤርዶዋን እስላማዊ ፓርቲም (AKP) በዚህ ድርጅት የሚደገፍ ነው። ይህ ድርጅት እስከ 25 ቢሊየን ዶላር ያህል ንብረት አለው።

የአሁኒቷ ቱርክ መንግሥት መስራች የነበሩት ሙስጠፋ ከማል አታቱርክ የእስልምና ጠላት ነበሩ። በአንደኛው የዓለም ጦርነት አካባቢ፡ በብዙ ሚሊየን ክርስቲያን አርመኖች እና ግሪኮች በቱርክ መንግሥት በጭካኔ ከተጨፈጨፉ በኋላ፡ ቱርክ የምትባል አገር ከምድር ካርታ ልትጠፋ ጥቂት ነበር የቀራት። ነገር ግን አገሪቱ ለኦርቶዶክሳውያን ግሪኮችና አርመኖች እንዳትመለስ እንግሊዝና ጀርመን እንቅፋት ሆኑ። በአንደኛው የዓለም ጦርነት የኦርቶዶክሳዊዋ ሩስያ ተባባሪ የነበረችው እንግሊዝ ሩስያን በመክዳት ከውጭ በኩል ለማድከም የኦርቶዶክስ ክርስትና ጠላቶች የሆኑትን ኃይሎች መርዳት ጀመረች። ከኦስትሪያሀንጋሪ ሌላ የቱርክ ተባባሪ የነበረችው ጀርመን ደግሞ በሩሲያ የኮሙኒዝም አብዮት እንዲፈነዳ በማድረግ ሩስያን ከውስጥ ለማድከም በቃች። ይህ አመቺ ሁኔታ ስለተፈጠረ ነበር ቱርክ የምትባል አገር ልትመሠረት የቻለችው። ባጠቃላይ፡ ምዕራባውያን ኮንስታንቲኖፕል በእስላም ወራሪዎች እንድትያዝ ከረዱበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን ድረስ፡ በባልካን፡ በካውካስ ሆነ በግሪክና በሩስያ እንዲሁም በግብጽና በኢትዮጵያ፡ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ጥቃት በማድረስ ላይ ይገኛሉ። ይህን ሰይጣናዊ ድርጊት በጥሞና መከታተል ይኖርብናል።

ከምዕራቡ ዓለም ድጋፍ አግኝተው ስልጣን ለመያዝ የበቁት ከማል አታቱርክ፡ ቱርክ አገራችው ልትዳብር እና መሠረቶቿም ሊጠነክሩ የሚችሉት ከእስልምና ርዕዮተ ዓለም ለመላቀቅ ስትበቃ ብቻ መሆኑን በመገንዘብ፡ እስላምና አረብ በሆኑ ነገሮች ላይ ሁላ ትግሉን ጀመሩ።

ስለዚህም፡ ለምሳሌ፡ የቱርክኛ ቋንቋ በዐረብኛ ፊድል መጻፉ ቀርቶ በላቲን እንዲተካ፤ ቀን መቁጠሪያው ከእስልምናው ወደ አውሮፓዊው የግሪጎሪያን ካላንደር እንዲቀየር፤ እስላማዊ አለባበሶች እንዲከለከሉ፤ መስጊዶች እና መድረሳዎች እንዲፈራርሱ፡ አድርገው ነበር፡ ከማል አታቱርክ። በተለይ ቱርክ ከእስራኤል ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖራት ታላቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱት እኝህ የቱርክ መሥራች ነበሩ። ለዚህም ነው ቱርክ ላለፉት 30 ዓመታት በልጸግ በልጸግ ለማለት፡ ሰላምና መረጋገትን ለማግኘት የቻለችው። (ዘፍ. 122-3)

80% በሚሆኑ የዘመኑ ቱርኮች ተወዳጅነት ያላቸው አታቱርክ ስለ እስልምና የሚከተሉትን ተናግረው ነበር፡

 • It is claimed that religious unity is also a factor in the formation of nations. Whereas, we see the contrary in the Turkish nation. Turks were a great nation even before they adopted Islam. This religion did not help the Arabs, Iranians, Egyptians and others to unite with Turks to form a nation. Conversely, it weakened the Turks’ national relations; it numbed Turkish national feelings and enthusiasm. This was natural, because Mohammedanism was based on Arab nationalism above all nationalities.

 • Those who use religion for their own benefit are detestable. We are against such a situation and will not allow it. Those who use religion in such a manner have fooled our people.

 • If our religion did not conform to reason and logic, it would not be the perfect religion, the final religion.

 • I am not leaving a spiritual legacy of dogmas, unchangeable petrified directives. My spiritual legacy is science and reason. … What I wanted to do and what I tried to achieve for the Turkish nation is quite evident. If those people who wish to follow me after I am gone take the reason and science as their guides they will be my true spiritual heirs.

 • The evils which sapped the nation’s strength had all been wrought in the name of religion.

 • Islam, this absurd theology of an immoral Bedouin Arab, is a rotting corpse which poisons our lives.

David Lloyd George: ስለ ሙስጠፋ ከማል አታቱርክ ይህን ተናግረው ነበር፡

The genius of our century – centuries rarely produce a genius. Look at this bad luck of ours, that great genius of our era was granted to the Turkish nation.”

የአሁኗ ቱርክ በፈጠነ መልክ እየተለወጠች ነው፡ ወደ እስልምናው እየተመለሰች ነው፡ አምባገነን የፖሊስ አገር ለመሆን እየበቃች ነው፡ ነፃነት እየጠፋ ነው፡ መብት እየተረገጠ ነው፡ ገለልተኛ የሆኑ ጋዜጠኞች፡ ተቃዋሚዎች፡ በተለይ ክርስቲያኖች በየቀኑ በደል እየተፈጸመባቸው ነው።

ለማንኛውም በኢስታንቡል ከተማ የሚገኘው እና አታቱርክ አውሮፕላን ማረፊያተብሎ እስከ አሁን የሚጠራው ዋናው የአውሮፕላን ማረፊያ ስሙን ቀይሮ ሌላ ስም ከተሰጠው፡ ቱርክ ወዴት እያመራች እንደሆነ ለማወቅ እንበቃለን ማለት ነው። ይህን ማድረጋቸው የማይቀር ነው፡

የታላቁ ከማል አታቱርክ ጠላት የሆነው የ ፋቱላ ጉለንእንቅስቃሴ፡ የአታቱርክን ቅርስ ለማፈራረስ ቆርጦ ተነስቷል፡ ቀስበቀስም ይህ ተልዕኮው እየተሳካለት ነው። ድርጅቱ የዜና ማሰራጫዎች፡ የትምህርት ተቋሞች፡ ባንኮችና የሕይወት ዋስትናዎች ባለቤት ነው። በቱርክኛው ቋንቋዘመን‘ (ከኢትዮጵያኛ የተወሰደ ነው) ተብሎ የሚጠራው ታዋቂ ጋዜጣ የዚሁ ድርጅት የፕሮፓጋንዳ ዋና ሰሌዳ ነው። እንቅስቃሴው እስከ 30የሚጠጉ ዩኒቨርስቲዎችን በመላው ዓለም የማቋቋም ዕቅድ አለው። የገንዘብ ምንጩ ከየት እንደሆነ ግን በትክክል አይታወቅም። ድርጅቱ ዕጽ ነክ ከሆነ ንግድ ጋር የተያያዝ የገቢ ምንጭ እንዳለው አንዳንድ ምንጮች ይናገራሉ።

ይህ ድርጅት ልክ እንደ አሜሪካዊው ጎጂ የአምልኮት እንቅስቃሴ እንደ ሳይንቶሎጂዓይነት መዋቀር ያለው ይመስላል። ተልዕኮውም፡ እስልምናን እንደ መሣሪያ አድርጎ በመጠቀም፡ ኃብትን አካብቶ ሥልጣን ላይ መውጣት ነው። ይህንንም ዓላማውን የሚያራምደው፡ እንደነ ኦሳማ ቢንላድን ወደ ቀይ የጦር ግንባር ሄዶ በመዋጋት ያዙኝ ልቀቁኝዓይነት የጦር ስልት በመጠቀም ሳይሆን፡ ዓለማዊ መንግሥታት በዘረጉለት የነፃነት ጎዳና ላይ በመንሸራሸር ደካማ የሆኑትን የህብረተሰብ ክፍሎች፡ በተለይም፡ ህጻናትን ለስለስ ባለ መልክ ቀርቦ በእጁ ስር ማስገባት ነው።

ኢማም ፋቱላ ጉለን በተለያየ ጊዜ ባደረጉት ስብከታቸው፡ እንቅስቃሴያቸው፡ ቱርክን ወደ እስልምና ሙሉ በሙሉ መቀየር፡ ብሎም እስላማዊ የሆነ አንድ የዓለም መንግሥት የማቋቋም ዓላማ እንዳለው አልደበቁም። በቅርቡ ዊኪሊክስ የተባለው የሕዋ ሰሌዳ ፤ የፋቱላ ጉለን ድርጅት በተለይ ህጻናት ላይ ትኩረት ማድረጉን አሜሪካውያንን እንዳሳሰባቸው ጠቁሞ ነበር።

አንድ የአሜሪካ ኢምባሲ ሠራተኛ በ2005 .. ይህን አሳሳቢ ጉዳይ አውስቶ ነበር፡

We have multiple reliable reports that the Gülenists use their school network (including dozens of schools in the U.S.) to cherry pick students they think are susceptible to being molded as proselytizers,” U.S. Embassy officials in Ankara said in a 2005 report.

And we have steadily heard reports about how the schools indoctrinate boarding students,”

ሙሉው ሪፖርት እዚህ ይገኛል

በተጨማሪ፡ የአሜሪካ ፌደራል የምርመራ ቢሮ(FBI) ኢማም ፈቱላ ጉለን ላይ ክትትል በማድረግ ላይ ይገኛል

... 1999 ኢማም ፋቱላ ጉለን የእንቅስቃሴያቸውን ዓላማ የቱርክ ቴሌቪዥን ባቀረበው ስብከታቸው ላይ እንደሚከተለው በግልጽ አስቀምጠው ነበር፡

You must move in the arteries of the system without anyone noticing your existence until you reach all the power centers … until the conditions are ripe, they [the followers] must continue like this. If they do something prematurely, the world will crush our heads, and Muslims will suffer everywhere, like in the tragedies in Algeria, like in 1982 [in] Syria … like in the yearly disasters and tragedies in Egypt. The time is not yet right. You must wait for the time when you are complete and conditions are ripe, until we can shoulder the entire world and carry it … You must wait until such time as you have gotten all the state power, until you have brought to your side all the power of the constitutional institutions in Turkey … Until that time, any step taken would be too early—like breaking an egg without waiting the full forty days for it to hatch. It would be like killing the chick inside. The work to be done is [in] confronting the world. Now, I have expressed my feelings and thoughts to you all—in confidence … trusting your loyalty and secrecy. I know that when you leave here—[just] as you discard your empty juice boxes, you must discard the thoughts and the feelings that I expressed here.

ቀጥለውም፡

When everything was closed and all doors were locked, our houses of isik [light] assumed a mission greater than that of older times. In the past, some of the duties of these houses were carried out by madrasas [Islamic schools], some by schools, some by tekkes [Islamist lodges] … These isik homes had to be the schools, had to be madrasas, [had to be] tekkes all at the same time. The permission did not come from the state, or the state’s laws, or the people who govern us. The permission was given by God … who wanted His name learned and talked about, studied, and discussed in those houses, as it used to be in the mosques.”

The philosophy of our service is that we open a house somewhere and, with the patience of a spider, we lay our web to wait for people to get caught in the web; and we teach those who do. We don’t lay the web to eat or consume them but to show them the way to their resurrection, to blow life into their dead bodies and souls, to give them a life.” [1]

ለድርጅቱ ሰይጣናዊ ተልዕኮ ከዚህ የበለጠ ምንም ማስረጃ ሊኖር አይችልም።

በነገራችን ላይ፡

ይህ ድርጅት ትምህርት ቤቶችን በመላው ዓለም ከፍቷል። ሩስያና ኡዝቤኪስታንን በመሳሰሉት አገሮች እንቅስቃሴው በጥብቅ የተከለከለ ነው፡ እንደ ጎጂ አምልኮት ተመዝግቧል። ኔዘርላንድስም የእንቅስቃሴውን በሮች በማጥበብ ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ አራት የእስላም ትምህርት ቤቶችን (ዘመናዊ መድረሳዎች)ከፍቷል። መቼም፡ በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ጭፍጨፋ ሲያደርግ የነበረውን የኦቶማን ቱርክን ስርዓት እንደገና ለመጥራት ቆርጦ የተነሳው ይህ እንቅስቃሴ ወደ ከፈታቸው መድረሳዎች ልጆቹን የሚልክ የክርስቲያን ወላጅ አለ ብየ አልገምትም። ግን ሙስሊሞቹስ? የክርስቶስን ብርሃን እያዩ ከክርስቲያን ወገኖቻቸው መማር ይሻላቸዋል ወይስ የተሳሳተውን የሙሃመድ ትምህርት አጥብቀው በመያዝ በ ጉለን እና በ ባሃይ በኩል ወደ ጨለማው ዓለም መሄድ?

ለአራት መቶ ዓመታት ያህል፡ በኢትዮጵያውያን የክርስቲያን ፍቅር እና ቻይነት በሰላም እና በፍቅር ለመኖር በቅተው የነበሩት ኢትዮጵያዊ ሙስሊሞች መጤ ከሆኑት ጂሃዳዊ ትምሕርት ቤቶች ተመልምለው በመውጣት ኢትዮጵያን ወይስ ቱርክ እና ሳውዲ አረቢያን ሊያገለግሉ የሚበቁት? ይህን በቅርቡ ያሳዬን።

[1] Turkish channel ATV, June 18, 1999

http://vimeo.com/3927140

WolvesInSheep’sClothing

PDF ለማንበብ ይህን ፋይል ያውርዱ

One Response to “የበግ ለምድ የለበሱ ነጣቂ ተኵላዎች”

 1. […] በፊት አቅርቤው በነበረው በዚህ ምስል ላይ ከሚታዩት አራት የኢትዮጵያ ዋና ዋና ጠላቶች መካከል ልክ አቶ ኮርኑክን የመሰለው ሰው ይገኝበታል። ይህ […]

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: