Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2011
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    27282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ምስጢረ ጰራቅሊጦስ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 12, 2011

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

ዘንድሮ የጰራቅሊጦስ (ጰንጠቆስጤ) በዓል በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ሰኔ ፭ ቀን በመላው አብያተ ክርስቲያናት ተከብሮ ይውላል። ከጌታ ዘጠኙ ዐበይት በዓላት አንደኛው የጰራቅሊጦስ በዓል ነው። ይህ በዓል በኦሪቱ በዓለ ሠራዊት ይባላል። የእሸት በዓል ማለት ነው። ከፋሲካ ሰንበት በኋላ እሑድ በሃምሳኛው ቀን ላይ ስለሚውል በዓለ ሃምሳ ተብሎ ይታወቃል። ይህንን ዕለት ጽርአውያን በቋንቋቸው ጸንጠቆስጤ ይሉታል። የሃይማኖት ስም አይደለም። በዘመናችን በተለይም እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር ከ ፲፱፻፮ ዓ.ም ጀምሮ በዚህ ስም ራሳቸውን የሰየሙ ቡድኖች የሃይማኖታቸው መታወቂያ በማድረግ ሲጠሩ ይሰማል። በመጽሐፍ ቅዱሱም ሆነ በጥንታዊት ቤተክርስቲያን ታሪክ በጰንጠቆስጤ ስም የሚታወቅ የሃይማኖት ድርጅት አልነበረም አይታወቅም።

ቤተክርስቲያናችን ይህን በዓል የምታከብረው መጽሐፍ ቅዱስንና ትውፊተ ሐዋርያትን መሠረት አድርጋ ነው። በግብረ ሐዋ.፪፥ ፩ – ፳፪ ተጽፎ እንደምናገኘው አይሁድ ከመላው ዓለም ተሰብስበው በዓለ ሃምሳን ሲያከብሩ ጰራቅሊጦስ የተባለው መንፈስ ቅዱስ ድምፁን እንደ አውሎ ነፋስ እያሰማ ጸጋውን እንደ ባዘቶ በእሳት ላንቃ አምሳል ከፍሎ ከፍሎ በጸሎት ጽሙዳን ለሆኑት መቶ ሃያ ቤተሰብ አድሏቸዋል። (ሐዋ.፪፥፲፬–፲፭) ሐዋርያትም ከሦስቱ ክፍላተ አህጉር ለመጡት አይሁድ መንፈስ ቅዱስ በገለጸላቸው ቋንቋ ለማስተማር በቅተዋል።

በሚያውቁት በአንድ የዕብራይስጥ ቋንቋ ላይ ሰባ አንድ ቋንቋ ስለተጨመረላቸው እንደ ልባቸው የክርስቶስን አምላክነትና ትንሣኤውን ያለ ፍርሃት መስክረዋል። በተገለጸላቸው ቋንቋ ለሰው ሁሉ ስላስተማሩ ሰሚዎቹ ተአምራቱን በማድነቅ የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ በልሳኖቻችን ሲናገሩ እንሰማቸዋለንበማለት ተገርመዋል። የመንፈስ ቅዱስን ሥራ የተጠራጠሩ ሰቃልያን ክርስቶስ አይሁድ ግን የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ለጉሽ ጠጅ ሰጥተው ማፌዝ ስለጀመሩ ቅዱስ ጴጥሮስ ነቢዩ ኢዮኤል በምዕራፍ ፪ ከቁጥር ፳፰—፴፪ የተናገረውን ትንቢት በመጥቀስ በተግሳፅ አሳፍሯቸዋል። ኢዮኤል የተናገረው ትንቢት ለአንድ ጊዜና ለመጨረሻው በዘመነ ሐዋርያት ተፈጽሟል። መንፈስ ቅዱስ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በቤተክርስቲያን አድሮ ለምእመናን እንደ ሃይማኖታቸው ጽናት፥ እንደ ምግባራቸው ቅንነት ጸጋውን ሲያድል ይኖራል። የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በጥምቀተ ክርስትና በሜሮን ሲሰጥ በመጠኑ ነው። ምዕመናን ጸጋው እየተጨመረላቸው እንዲሄድ በገድል በትሩፋት ተወስነው የክርስቲያንን ተግባር እየፈጸሙ ሲሔዱ ጸጋው እየተጨመረላቸው እንዲሄድ በገድል በትሩፋት ተወስነው የክርስቲያንን ተግባር እየፈጸሙ ሲሔዱ ጸጋው እየተጨመረላቸው ከነጽሮተ ሥሉስ ቅዱስ፥ ከከዊነ እሳት ማዕረግ ለመድረስ ይበቃሉ። በዚህን ጊዜ እንደሐዋርያት በጥላቸው በልብሳቸው ሕሙም መፈወስ፣ ጋኔን ማውጣት፣ ሙት ማንሳት

ይቻላቸዋል። ቤተክርስቲያናችን ጠቅለል ባለ መልኩ ስለ መንፈስ ቅዱስ ለቤተ ክርስቲያን እንዳልተሰጠ ተቆጥሮ አንዳንድ መናፍቃን በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የሚሰነዝሩት ጉንጭ አልፋ ዘለፋ መሠረት የሌለው ስለሆነ አንደነቅበትም። እነዚህ የሚያለያዩ ሥጋውያንም የሆኑ።መንፈስም የሌላቸው ሰዎች ናቸውና። (ይሁዳ ፩፥፲፱) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በመጀመሪያይቱ የቆሮንቶስ ክታቡ የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት አምነው በተጠመቁ ክርስቲያኖች መንፈስ ቅዱስ አድሮባቸው እንዳለ ገልጾልናል። በተጨማሪም የመንፈስ ቅዱስ አካሉ አንድ ሲሆን ጸጋው (ሀብቱ) ግን ልዩ ልዩ በመሆኑ ለምዕመናን ሁሉ አንድ አይነት ጸጋ የላቸውም ብሏል። (፩ቆሮ. ፲፪፥፩—፲፩) ጸጋውንም እነርሱ እንደወደዱት ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ እንደፈቀደ እንደሚጠቅማቸው አድርጎ ይሰጣቸዋል። ከመንፈስ ቅዱስ ሥጦታዎች ከእምነትና ከፍቅር የሚበልጥ ጸጋ አለመኖሩን ዐውቀን በየሰፈሩ እየተሹለከለኩ መንፈስ ወርዶብናል እያሉ ከሚያጭበረብሩ ቢጽ ሐሳውያን ሁሉ መጠበቅ ይገባናል።

እነዚህ ሰዎች የጵጵስናም ሆነ የቅስና ማዕረግ ክህነት ሳይኖራቸው ራሳቸውን በራሳቸው ሾመው እጆቻችንን እየጫንን መንፈስ ቅዱስ እናሳድራለን በማለት ብዙዎቹን የዋሆች የመንፈስ ርኩስ ቁራኛ ስላደረጉዋቸው ምዕመናን ሆይ በተዋሕዶ ሃይማኖታችሁ እስከመጨረሻው እንድትጠበቁ እንመክራችኋለን። (፩ቆሮ.፲፪፥፫፧ ፩ቆሮ.፲፫፥ ፩—፲፫) በጸሎተ ሃይማኖታችን ስለ መንፈስ ቅዱስ ያለን እምነት እንደሚከተለው ይጠቃለላል፡

በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን። እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረፀ፣ ከአብና ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን። እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረ ነው።መንፈስ ቅዱስ እንዳይለየን በመናፍቅነትና በእልከኝነት ልባችን እንዳይደነድን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ሃይማኖታችን አጽንቶ በክርስቲያናዊ ሕይወት ለመመላለስ ያብቃን፡ አሜን።

MenfesQedus

 

ምንጭ፡ ethiopianorthodox.org

Speaking In Tongues: An Orthodox Perspective

Fr. George Nicozisin

Speaking in Tongues, “Glossolalia,” a popular practice with many Churches today, is a phenomenon which can be traced to the days of the Apostles. A decade ago, Speaking in Tongues was encountered only in Pentecostal Churches, Revival Meetings, Quaker gatherings and some Methodist groups. Today, Glossolalia is also found in some Roman Catholic and Protestant Churches.

Serapion of Egypt, a fourth century contemporary of St. Athanasios summarized Eastern Orthodox theology:

“The Anointing after Baptism is for the Gifts of the Holy Spirit, that having been born again through Baptism and made new through the laver of regeneration, the candidates may be made new through the gifts of the Holy Spirit and secured by this Seal may continue steadfast.”

Bishop Maximos Aghiorghoussis, Greek Orthodox Diocese of Pittsburgh and world-reknowned Orthodox theologian on the Holy Spirit states it this way: “For Orthodox Christians, Baptism is our personal Paschal Resurrection and Chrismation is our personal Pentecost and indwelling of the Holy Spirit.”

There are two forms of Glossolalia:

Pentecost Glossolalia happened this way: Fifty days after the Resurrection, while the disciples were gathered together, the Holy Spirit descended upon them and they began to speak in other languages. Jews from all over the civilized world who were gathered in Jerusalem for the religious holiday stood in amazement as they heard the disciples preaching in their own particular language and dialect (like in a United Nations Assembly). They understood!

Corinthian Glossolalia is different. St. Paul, who had founded the Church of Corinth, found it necessary to respond to some of their problems, i.e., division of authority, moral and ethical problems, the Eucharist, the issue of death and resurrection and how the Gifts of the Holy Spirit operated. In chapter 12, St. Paul lists nine of the Gifts of the Holy Spirit, i.e., knowledge, wisdom, spirit, faith, healing, miracles, prophecy, speaking in tongues and interpreting what another says when he speaks in tongues.

Specifically, Corinthian Glossolalia was an activity of the Holy Spirit coming upon a person and compelling him to external expressions directed to God, but not understood by others. In Pentecost Glossolalia, while speaking in several different tongues, both the speaker and the listener understood what was uttered. The Glossolalia manifested in Corinth was the utterance of words, phrases, sentences, etc., intelligible to God but not to the person uttering them. What was uttered needed to be interpreted by another who had the gift of interpretation.

GlossolaliaOrthodoxPerspective

TheTruthOfOurFaith

A Neuroscientific Look at Speaking in Tongues

2 Responses to “ምስጢረ ጰራቅሊጦስ”

  1. In case your kitchen is equipped with a gas array or electric coil burners, there is
    no superior tasting burger than one cooked in a cast iron skillet.

    Together with the rise inside the demand of
    premium good quality cookware products, a substantial number of manufacturers have joined the league; even
    so, as an alternative to focusing as well considerably on the brand, you must concentrate around the top quality and
    also the cost effectiveness offered from the contenders currently
    being offered in the market place.

  2. If that isn’t the situation, then I’m glad I didn’t spend a lot more than I had to. Quickly following my obtain, I began an accredited, qualified baking program wherever the entire school (aside through the floor model machines) made use of both the Kitchen – Support 5 quart Artisan or even the Kitchen – Support 6 quart Pro 600.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: