Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World

ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን

Posted by addisethiopia on April 21, 2011

ከአምስቱ አዕማደ ሃይማኖት መካከል፡

፩ኛ፡ ምስጢረ ሥላሴ

፪ኛ፡ ምስጢረ ሥጋዌ

፫ኛ፡ ምስጢረ ጥምቀት

፬ኛ፡ ምስጢረ ቍርባን

፭ኛውን ምስጢረ ትንሣኤ ሙታንን


እንመለከታለን።

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትከሚለው ከንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ ሁለተኛ መጽሐፍየተወሰደ። ከታላቅ አክብሮትና ምስጋና ጋር።


ሥጋና ደም፡ የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፡ የሚበሰብሰውም፡ የማይበሰብሰውን አይወርስም! በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት፡ በማይሞተውና በማይበሰብሰው፡ በማይለወጠውና በማይጠፋው፡ ሊገለጽና ሊሰወር በሚችለው፡ ለዘለዓለም በሚኖረው፡ በአዲሱ የትንሣኤ መንፈሳዊ አካል ነው።

ለሰው ልጆች ከሙታን ተለይቶ የምነሣት ጸጋና ክብር የተገኘው ሰው የሆነው አምላክ፡ እኒህን ፈተናዎችና መከራዎች፡ ሰለእናንተና ሰለእኛ፡ እኛን ስለመሰሉ የሰው ልጆች ሁሉ ሲል፡ እስከመጨረሻ በጸና ትዕግሥት በመቀበሉ መሆኑን፡ ዘወትር ማስታወስ ይገባናል። ሁሉ፡ በአዳም እንደሚሞቱ፡ እንዲሁ፡ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ፡ ሕያዋን ይሆናሉና።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ከመጨረሻ ምጽአቱ ጋር በሚከሠታው የሙታን ትንሣኤ፡ የሰው ልጆች ዕድል ፈንታ፡ ምን ዓይነት እንደሚሆን፡ ያም ትንሣኤ፡ እንዴት እንደሚካሄድ፡ መልካም ዘርን በዘራ ገበሬና ክፉ ዘርን በዘራ ጠላት፡ በእርሻና በዘር፡ በስንዴና በእንክርዳድ፡ በአጫጆችና በመክር እየመሰለ ባስተማራቸው ትምህርቶች አስረድቷል።

ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ!” ያለው ጌታ፡ እነዚህን የምሳሌ ትምህርቶቹን ሲተረጕም፡ መልካምን ዘር የዘራው፡ የሰው ልጅ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ነው፡ እርሻውም፡ ዓለም ነው፡ መልካሙም ዘር፡ የመንግሥት (የእግዚአብሔር) ልጆች ናቸው፡ እንክርዳዱም፡ የክፉው (የዲያብሎስ) ልጆች ናቸው፡ (ክፉውን ዘር) የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፡ መከሩም፡ የዓለም መጨረሻ ነው፡ አጫጆችም፡ መላእክት ናቸው።

እንግዴህ፡ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፡ በዓለም መጨረሻም እንዲሁ ይሆናል።አለ። ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ይህንኛውን ትርጓሜውን የጨረሰው፡ እናንተና እኛ፡ እኛንም የመሰሉት ሁሉ፡ ልብ ብለን እንድናስተውለው በሚፈልገው፡ የሚሰማ ጆሮ ያለው፡ ይስማ!” በሚለው የማስጠንቀቂያ ቃሉ ስለሆነ፡ ይህ መለኮታዊ ቃል የዘወትር ማንቂያ ደወል ሊሆነን ይገባል።

በራእየ ዮሐንስ ላይ የተጠቀሰው የሺ ዓመቱ ምስጢር ላይ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ በትንሣኤውና በዕርገቱ የክፋትን፥ የኃጢአትንና የሞትን ኃይላት ድል ነስቶ፡ መንፈስ ቅዱስ በዓለሙ ላይ እንዲወርድ በማድረጉ፡ የእግዚአብሔር ልጆች የተቀዳጁትን ድል የሚገልጸውን ይህንኑ ምስጢር፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሓንስ እንዲህ አብራርቶ ጽፎታል፦

የጥልቁን መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት፡ በእጁ የያዘ መልአክ፡ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። የቀደመውንም እባብ፥ ዘንዶውን፥ እርሱም፡ ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው! ሺ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፡ በእርሱ ላይ ዘግቶ፡ ማኅተም አደረገበት! ከዚያም በኋላ፡ ለጥቂት ጊዜ ይፈታ ዘንድ ይገባዋል።

ከዚህ በኋላ፡ ዙፋኖች ተዘርግተው፡ የሰው ልጅ (ኢየሱስ ክርስቶስ) በላያቸው ተቀምጦ አየሁ! ሰለኢየሱስ፥ ስለስሙና ስለእግዚአብሔር ቃል ሲሉ ስለተገደሉ ሰዎች ነፍሳትም፡ ቅን ፍርድን ፈረደላቸው! ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን፥ ምልክቱንም፡ በግምባራቸው ላይ ያልጻፉትን፥ በእጆቻቸውም ያልተቀበሉትን አየሁ! እኒህ ከክርስቶስ ጋር፡ በዚህ ሺ ዓመት፡ ሕያዋን ሆነውና ነግሠው ይኖራሉ! የቀሩቱ ሙታን ግን፡ ይህ ሺ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፡ ተነሥተው በሕይወት አይኖሩም። ይህ በመንፈስ ትንሣኤ የምትገኘው፡ የፊተኛዪቱ ሕይወት ናት! አስቀድማ በምትመጣው፡ በዚች ሕይወት፡ ዕድል ፈንታ ያለው፡ ብፁዕና ቅዱስ ነው! ሁለተኛው ሞት በእኒህ ላይ፡ እንግዴህ ወዲህ፡ ሥልጣን የለውምና! የእግዚአብሔርና የክርስቶስ አገልጋዮች ይሆናሉ እንጂ! ከእርሱም ጋር ይህን ሺ ዓመት ይነግሣሉ!”

ሽሁም ዓመት ሲፈጸም፡ ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል! በአራቱም፡ በምድር ማዕዘናት ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን እንዲያስታቸው፥ ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ቁጥራቸውም እንደባሕር አሸዋ የሚያህል ነው። ወደምድርም ስፋት ወጡ! የቅዱሳን መሰባሰቢያ የሆነችውንም ቅድስት አገር (ኢትዮጵያን) ከበቡ! ከዚህ በኋላ፡ ከሰማይ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ፡ እሳት ወርዳ በላቻቸው! ያሳታቸውም ዲያብሎስ፡ አውሬውና ሓሰተኛው ነቢይ ወደሚገኙበት፡ ወደእሳቱና ወደዲኑ ዐዘቅት ተጣለ! በዚያም፡ ለዘለዓለም እስከዘለዓለም፡ በመዓልትና በሌሊት፡ ሲሰቃዩ ይኖራሉ።” (ራእ. 201-10)

ከዚህ በላይ የሠፈረው የእግዚአብሔር ቃል አያሌ ቁም ነገሮችን የያዘ ነው፡ ነገር ግን ትንሣኤ ሙታንን በሚመለከተው ላይ ብናተኩር ሁለት ትንሣኤዎች እንዳሉ እንረዳለን። የመጀመሪያው ትንሣኤ ተነሥተው የሚኖሩት ሕይወት ሲሆን፡ ሁለተኛው ትንሣኤ ደግሞ፡ በመጨረሻ፡ በክርስቶስ ምጽአት ጊዜ፡ በመንፈሳዊው የትንሣኤ አካል፡ ለዘለዓለም የሚነሱት፡ የኋለኛው ትንሣኤ ነው፤ እኒህ የእግዚአብሔር ወገኖች፡ በፊተኛው የመንፈስ ትንሣኤ፡ በሕይወት ሥጋ እየኖሩ ሳሉ፡ ምናልባት፡ የክርስቶስ ምጽአት የሆነ እንደሆነ በቅጽበት ተለውጠው፡ ለዘለዓለማዊው የሕይወት ትንሣኤ የሚበቁ መሆናቸውን፡ መለኮታዊው ቃል ያመለክታል።

በዚሁ መለኮታዊ ቃል መሠረት፡ በአንድ በኩል፡ የእግዚአብሔር ወገኖች፡ ይህን በመሰለ የብቅዓት ሕይወት ላይ ሲገኙ በሌላ በኩሉ ደግሞ የቀሩት የሰው ዘሮች ቅዱሱን ኪዳን ለመቀበል ፈቃደኞች ባለመሆናቸው፥ የተቀበሉትም በእርሱ ላይ፡ ክህደትና ዓመፅ በመፈጸማቸው፡ በሕይወተ ሥጋ እያሉ፡ እንደሙታን ይቆጠራሉ፤ ራሳቸውንም፡ በፈቃዳቸው፡ ከእግዚአብሔር ሕይወት አግልለው፡ ለሰይጣን ወገንነት ስላቀረቡ፡ በክርስቶስ ምጽአት ጊዜ፡ በሕይወተ ሥጋ የሚገኙት ጭምር፡ በፃዕር፡ የመጀመሪያውን የሞት ጽዋቸውን ከተቀበሉ በኋላ፡ ሁለተኛውንና ነፍሳዊውን ሞት ለሚያስከትልባቸው፡ ለዘለዓለማዊው ኵነኔ ትንሣኤ ይነሳሉ።

Tensae-Continue reading…

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: