Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • April 2011
  M T W T F S S
   123
  45678910
  11121314151617
  18192021222324
  252627282930  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Archive for April, 2011

ሊበሏት ያሰቧትን ቆቅ፡ ዥግራ (ዶሮ) ነች ይሏታል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2011

የሚገርም ነው፡ ይህን ጽሑፍ ልክ ስጨርስ፡ ፎቶው ላይ ያለው ክቡር ሰንደቅ ዓላማ ከፊቴ ተደቅኖ ይታየኝ ነበር…

መብራት ከብትማ የተባለች እህታችን ባለፈው ሣምንት ላይ በቤይሩት፡ ሊባኖስ ሕይወቷን አጥታለች። ገዳዮቹ: የመብራትን አንገት ብዙ ጊዜ በጭካኔ  ደጋግመው በመውጋት ነበር ለዚህ ሰይጣናዊ ተግባር የበቁት(እግዚአብሔር ነፍሷን ይማርላት!)

እንደ ሌባኖስ፡ ሳውዲ ዓረቢያ፡ ዱባይ እና የመሳሰሉት የአረብ አገሮች የሚገኙት እህቶቻችን በመንፈሳቸው፡ በነፍሳቸውና በአካላቸው ላይ አሰቃቂ የሆነ ጥቃት ያለማቋረጥ እየደረሰባቸው ነው።

በሰሜናዊው አፍሪቃ በኩል የመካከለኛውን ባሕር ተሻግረው በመሄድ የተሻለኑሮ በአውሮፓ ለማየት የሚሹት፡ በግብጽ በኩል የሲናይ በረሃን በማቋረጥ ነፃነትን በእስራኤል ለመቅመስ የሚመኙት ወገኖቻችን ሁሉ የባሕር ሞገዶች ላይ ጠውልገው እንዲቀሩ፡ በየበረሃው ለጨካኝ የአረብ ድንበር ጠባቂዎች የተኩስ መለማመጃ ለመሆን እየበቁ ነው።

ለዚህ ሁሉ አሳፋሪ ሁኔታ በመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂዎች የምንሆነው እኛው ኢትዮጵያውያን ነን። ማንነታችንን አጠንቅቀን ለማወቅ ባለመቻላችን ወይም እንዳንችል ለጠላት በራችንን በመክፈታችን፡ ከፈጣሪያችን ያገኘነውን ውድ ስጦታ በምስጋና ተቀብለን በሥራ ላይ ለማዋል አልፈቀድንምና። እራሳችንንም እየተንከባከብን እስከመጨረሻው ለመጽናት ዝግጁ በመሆን የጠላቶቻችንን ትሪክ ለማጥናት ስለሰነፍን፡ የደንቆሮውና የእውሩ፡ የተንኮለኛውና የጨካኙ ኃይል ሁላ መጫወቻዎች ሆነናል፡ ለዲያብሎስ ጥቃት በቀላሉ ለመጋለጥ በቅተናል።

ሆኖም ፈጣሪያችን አዛኝ፡ ቸር እና መሐሪ ነው፡ ለንስሐም የሚያበቃን አንድ አምላክ ነው፡፡ ስለሆነም፡ በተለይ በውጩ ዓለም በምንገኘው ኢትዮጵያውያን አማካይነት፡ በየቦታው በሚጠነሰሱት ሰይጣናዊ ሤራዎች ላይ ፍልሚያውን እንድንያያዝ ጥሪውን አቅርቦልናል። በዚህም፡ ቀደም ሲል ከፈጸምናቸው ስህቶቻችን እየተማርን ከበደሎቻችን ሁሉ ነፃ እንድንወጣ ሌላ ትልቅ እድል ሰጥቶናል።

አገራችንን በመልቀቅ በመላው ዓለም ለመበታተን የተገደድንበት ምክኒያት እንደምናስበውና እንደምንመኘው ዓለማዊ የሆኑ ፍላጎቶቻችንን ለማሟላት፡ ወይም እኔ እበልጣለሁ/እሻላላሁ፡ አንተ ታንሳለህ/አትሻለም እየተባባልን የኩራት ደም ሥራችንን ለመወጠር ሳይሆን፥ ለዓለሙ ሁሉ መፈራጃ ለመሆን እንድንበቃ፥ በአባቶቻችንና እናቶቻችን፡ በወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የተጋረደውን የሰይጣን ግድብ ከውጭ ሆነን ለመቦርቦር ብሎም ለማፍረስ እንችል ዘንድ እውቀቱንና መረጃውን የመሰብሰብ ዕድሉ እንዲኖረን ነው። ይህን ዕድል ያልተጠቀመ፡ ተረገመ!

የሊቢያው ጦርነት፡ በየዜና ማሰራጫው ሁሉ እንደሚወራው፡ የነዳጅ ዘይትን ወይም የተቀናጣውን የኮሎኔል ጋዳፊ መንግሥትን የተመለከት መስሎ ሊታየን ይችል ይሆናል፡ ነገር ግን ይህ እንደ አንድ ሰበብ እንጂ እንደ ዋና ምክኒያት ተደርጎ መወሰድ የለበትም። የዚህ ጦርነት ዓላማ ሌሎች ብዙ የተወሳሰቡ ነገሮችን ያካተተ ነውና።

እግዚአብሔር አምላካችን፤ በልጆቼ ላይ በደል የሚፈጽሙ ሰዎች፡ ዕምነት የሌላቸው ወይም እግዚአብሔርን ያልተቀበሉት ኃይሎች ለጥፋት ይላኩባቸዋልብሎ እንዳስተማረን፡ ኮሎኔል ጋዳፊ እና ከርሱ ጋር ለዘመናት አብረው ሲንደላቀቁ የቆዩት ሊቢያውያንም ለዚህ ክፉ ጊዜ በመድረስ፡ ጨነቀኝ ጠበበኝለማለት የበቁት፡ በተለይ፡ ኮሎኔሉ በክርስቲያኖች አምላክና በመንፈስ ቅዱስ ላይ ደግሞ ደጋግሞ ትዕቢት የተሞላባቸውን ስድቦች ለመሠንዘር በመቃጣቱ፡ እንዲሁም የሊቢያው ሕብረተሰብ፡ በተለይ በሃገረ ኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ ለዘመናት ሲፈጽመው ከነበረው ዲያብሎሳዊ አድራጎቱ የተነሳ ነው።

የኢትዮጵያና እስራኤል ግኑኝነት እንዲሻክርና ቀዳማዊ ኃይለሥላሴም እ... 1973 .ም ከእስራኤል እንዲርቁና ወደ አረቦች ጠጋ ጠጋ በማለት የመውደቂያ ጉድጓዳቸውን ለመቆፈር የበቁት የጋዳፊዋ ሊቢያ በ አፍሪቃ አንድነት ድርጅት በኩል ኢትዮጵያ ፀረእስራኤል የሆነ አቋም እንድትይዝ በርሷ ላይ ተጽእኖ ለማድረግ በመቻሏ ነበር። ልክ ከዚህ ጊዜ በኋላ ነበር በአገራችን ላይ ያ ሁሉ ታሪክ የማይረሳው መዓት ሊደርስባት የቻለው።

ከጥቂት ዓመታት በፊት ከአውሮፓውያን መሪዎች (ቶኒ ብሌር፡ ኒኮላስ ሳርኮዚ፡ ሲሊቪዮ ቤርሉስኮኒ) ጋር ጥብቅ ግኑኝነት መሥርቶ የነበረው እባቡ ጋዳፊ፡ ከኢትዮጵያ፡ ከኢርትራ ወይም ከሶማሊያ የሚመጡትን ስደተኞች በሊቢያው የሳሓራ በርሃ አፍኖ ለመያዝ እና አውሮፓን ከጥቁር ሕዝቦች ለመከላከል እንድትችሉ ለመርዳት ዝግጁ ነኝበማለት ፈቃደኝነቱን አሳየ፡ ለዚህም ተልዕኮው በቢሊየን ዩሮ የሚቆጠር የገንዘብ ስጦታ ከአውሮፓው አንድነት ሊሰጠው እንደሚገባው ገለጠ።

... 1988 .. በስኮትላንዷ ሎከርቢ ላይ የአሜሪካን አየር መንገድ በማፈንዳት270 መንገደኞች ሕይወት ማጣት ተጠየቂ የነበረውና በስኮትላንድ ፍርድ ቤት የዕድሜ ልክ እስራት ፍርድ የተሰጠው ሊቢያዊ የጋዳፊ የግድያ ወኪል፡ አብደልባሰት አልመግራሂ፡ ከ 8 ዓመት እስራት በኋላ እ... 2009 .. ከስኮትላንድ እሥር ቤት ወጥቶ ወደ ሊቢያ እንዲመለስ ተደርጓል። ይህ ሊቢያዊ ገዳይ የነቀርሳ በሽታ አለበት፡ ለመኖርም በጣም ጥቂት ቀናት ነው የቀሩትበሚል ሳቢያ ከእሥር ቤት እንዲወጣ ቢደረገም፡ በተለይ ከአሜሪካ በኩል ትልቅ ተቃውሞ መቅረቡ የሚታወስ ነው። ይህ ገዳይ እንደተባለው በጥቂት ቀናት አልሞተም፡ ያው እስካሁን በሕይወት እንዳለ ይነገራል።

ነገር ግን አንድ መጠየቅ የሚኖርብን ነገር፡ የሊቢያው ጦርነት በእውነት ከዓመታት በፊት ታቅዶ የቆየ ጦርነት ከሆነ የዚህ ሊቢያዊ ገዳይ ሚና ምን ይመስል ይሆን? እንደ አንድ የ ማንቹሪያ እጩየሮቦት ዓይነት ሥራ ተሰጥቶት፡ የጋዳፊን ዓለም ለመሰለል እና ለመጭው የሊቢያ ወረራ በእንግሊዛውያኑ ተዘጋጅቶ የተላከ ሰው ይሆን?

በመካከለኛው ባሕር ላይ የጦር መርከቦች እንቅስቃሴ፡ ገና ኖቬምበር 2010 ላይ ነው መታየት የጀመረው። በያዝነው ዓመት መግቢያ ላይ፡ መጀመሪያ በቱኒዚያ፡ ከዚያም በግብጽ የታየው የሕዝቦች እንቅስቃሴ፡ ምናልባት ሆን ተብሎ በውጭ ኃይሎች የተዘጋጀ፡ በተለይ በሁለቱ አገሮች መካከል በምትገኘው ሊቢያ ላይ ዋና ትኩረት ያደረገ እንቅስቃሴ መሆኑ አሁን አያጠራጥርም፡ ለዚህም በሊቢያ ላይ በ ፈረንጅ ሕዝቦች ክበብበሆነው በNATO መሪነት እየተካሄደ ያለው የውትድርና ጥቃት ያሳየናል።

መቼም የፈረንጁ ዓለም የኢትዮጵያንና የአፍሪቃን ስም መጥፎና አስቀያሚ ከሆኑ ድርጊቶች ጋር በማያያዝ ብቻ መጥራቱን እንደሚወዱ አሁን ሁላችንም እናውቃለን። የአፍሪቃው አንድነትም በግርግሩ ምንም ሚና እንዳይጫወት፡ “ለምንም የማይበቃ ድርጅት ነው” በሚል፡ ስም አጥፊ የሆነ አሮጌ ፕሮፓጋንዳ የዓለምን ማሕበረሰብ ለማታለል እየሞከሩ ነው። 

ሊበሏት ያሰቧትን ቆቅ፡ ዥግራ(ዶሮ)ነች ይሏታልእንዲሉ፡ የፈረንጁ ዓለም፡ በወዳጅ ጠላቱ፡ በኮሎኔል ጋዳፊ ላይ ጥቃት ከጀመረበት ዕለት አንስቶ፡ ጋዳፊ በጥቁር አፍሪቃውያን ቅጥረኞች ይደገፋልሲባል ነበር። እነ ቢቢሲና አልጀዚራም ለምንድን ነው አፍሪቃውያን ብቻ ኮሎኔል ጋዳፊን የሚደግፉት?” የሚሉ የፈጠራ ወሬዎችን በመንዛት፡ በጋዳፊ ላይ ተቃውሞ የነበራቸው ሊቢያውያን ጥቁር በሆኑ አፍሪቃውያን ላይ የጥላቻ መርዝ እንዲረጩ ተደረገ። ከዚያ፡ ነፃ አውጪዎች ተብለው በቢንጋዚ ከተማ መሠረት የያዙት ተዋጊዎች (ግማሹ የአልቄይዳ ወኪል ነው) በጥቁር ሰዎች ላይ (በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጭምር) ጥቃት እንዲፈጽሙ ተደረገ፥ አሁን የጋዳፊ ቅጥረኞችበሚል መጠሪያ ስማቸው የጠፋው እነዚህ ጥቁር ስደተኞች ባካባቢው በሚገኙት ቱኒዚያና ግብጽ በኩል አልፈው በጀልባ ወደ አውሮፓ ለማለፍ እንዳይችሉ በቱኒዚያናውያንና ግብጻውያን ተመነጠሩ፡ ተለይተው በአንድ ላይ እንዲሰበሰቡ ተደረጉ። (በየበረሃው ወድቆ ለሞት የበቃው ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው)

እንደምንም ብለው ቱኒዚያና ግብጽ የደረሱት ከዚያም ለአውሮፓ የጀልባ ጉዞ የበቁት ወገኖቻችን ደግሞ ልዩየሆነ ጀልባ እየተመደበላቸው የአሣ ነባሪ ቀለብ እንዲሆኑ ተደርገዋል።

ይህን እጅግ የሚያሳዝንና የሚያስቆጣ ተግባር በ21ኛው ምዕተ ዓመት ዓይናችን እያየ፡ ጆሮአችን እየሰማ ዕለት ተዕለት ይከሰታል።

እስቲ እግዚአብሔር ይይላቸው፡ በጣሊያን ደሴቶች በኩሉ አሁን በመላው አውሮፓ እንዲሠፍሩ የተደረጉት ከ 30 እስከ 50 ሺህ የሚጠጉ ስደተኞች ከቱኒዚያ ያመለጡ አረቦች ናቸው። (ከዚህም ግማሹ የአልቄይዳ ወኪል እንደሆነ ይነገራል)

በሌላ በኩል ግን፡ ኢትዮጵያውያኑና ኤርትራውያኑ የበሰበሰ ጀልባ ላይ እየተመነጠሩ ተለይተው እንዲወጡ ከተደረጉ በኋላ ተቀባይ አጥተው በኢንዱስትሪ ቆሻሻ በተበከለው በመካከለኛው ባሕር ወስጥ ለሚገኙት ዓሣዎች ምግብ ለመሆን ይበቃሉ።

ከሃያ ዓመታት በፊት በቀድሞው የደርግ መንግሥት ሰራዊቶች እና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል አባይ ወንዝ አካባቢ ከፍተኛ ዕልቂት የጠየቀ ጦርነት መካሄዱን በወቅቱ ባካባቢው ከነበሩት ወገኖች ለመረዳት ችየ ነበር። እኔን በጣም ያሳዘነኝ፡ የረበሸኝ፡ የዘገነነኝ እና ያናደደኝ፤ የወገኖቻችንን ሬሳ ወደ አባይ ወንዝ እየተጣለ የወንዙ ቀለም በደም ቀይ ሆኖ ባካባቢው የነበሩት እናቶች፡ እህቶችና ሕፃናት ለሣምንታት ያህል ዋይዋይዋይ!” እያሉ ሃዘናቸውን በጩኸት ሲገልጹ የነበረበት ሁኔታ ነው። ይሄም ሁኔታ ፊቴ ላይ እንደ አንድ መሳጭ የፊልም ስዕል እስካሁን ድረስ ይታየኛል።

የተባረከው የወንዛችን ውሃ፡ በብዙ ውድ ማዕድናት የተካነውን አፈራችንን ይዞ በመጓዝ የጠላቶቻችንን መቅኒ ለዘመናት ማዳበሩ እንዳይበቃ፡ አሁን ደግሞ ይህ ውሃ በኢትዮጵያውያን ደም ተቀምሞ እንዲፈስስላቸው እናደርጋለን!

ዓየር መንገዳችን መካከለኛው ባሕር ላይ እንዲወድቅ ይደረጋል፡ እናት ዓባያችን መሬታችንን እየሸረሸረ ወስዶ የተበከለውን የመካከለኛውን ባሕር ውሃ ይቀልባል፡ ይህ አልበቃም ስላለ ደግሞ በረሃ ለበረሃ ተንከራትተን በስቃይና በመከራ ወደዚያው ተጉዘን ከደረስን በኋላ፡ ትኩስ ሥጋችንን፡ ንጹሕ ደማችንን በነጭ ሳሕን ለባሕሩ መናፍስት እንኩ ብለን በቦታው እናቀርብላቸዋለን።

በቅርቡ ከሊቢያ ወደ ጣልያን ለመግባት ከቻሉት ጥቂት ኢትዮጵያውያን (ኤርትራውያን) መካከል TIME magazine ካቀረበው ዘገባ የተወሰደ ጥቅስ፡

Desperate Tsegay: “Whatever abuse a normal person gets, you get twice as much if you’re Christian”

Pregnant Helen: “We’re so happy, it’s like we’ve been born for the second time.”

Sensational TIME: “Italy should listen to its better angels.


ቅኑ እና ንቁ መንፈስ ይስጠን!

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ምስጢረ ትንሣኤ ሙታን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 21, 2011

ከአምስቱ አዕማደ ሃይማኖት መካከል፡

፩ኛ፡ ምስጢረ ሥላሴ

፪ኛ፡ ምስጢረ ሥጋዌ

፫ኛ፡ ምስጢረ ጥምቀት

፬ኛ፡ ምስጢረ ቍርባን

፭ኛውን ምስጢረ ትንሣኤ ሙታንን


እንመለከታለን።

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትከሚለው ከንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ ሁለተኛ መጽሐፍየተወሰደ። ከታላቅ አክብሮትና ምስጋና ጋር።


ሥጋና ደም፡ የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፡ የሚበሰብሰውም፡ የማይበሰብሰውን አይወርስም! በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት፡ በማይሞተውና በማይበሰብሰው፡ በማይለወጠውና በማይጠፋው፡ ሊገለጽና ሊሰወር በሚችለው፡ ለዘለዓለም በሚኖረው፡ በአዲሱ የትንሣኤ መንፈሳዊ አካል ነው።

ለሰው ልጆች ከሙታን ተለይቶ የምነሣት ጸጋና ክብር የተገኘው ሰው የሆነው አምላክ፡ እኒህን ፈተናዎችና መከራዎች፡ ሰለእናንተና ሰለእኛ፡ እኛን ስለመሰሉ የሰው ልጆች ሁሉ ሲል፡ እስከመጨረሻ በጸና ትዕግሥት በመቀበሉ መሆኑን፡ ዘወትር ማስታወስ ይገባናል። ሁሉ፡ በአዳም እንደሚሞቱ፡ እንዲሁ፡ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ፡ ሕያዋን ይሆናሉና።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ከመጨረሻ ምጽአቱ ጋር በሚከሠታው የሙታን ትንሣኤ፡ የሰው ልጆች ዕድል ፈንታ፡ ምን ዓይነት እንደሚሆን፡ ያም ትንሣኤ፡ እንዴት እንደሚካሄድ፡ መልካም ዘርን በዘራ ገበሬና ክፉ ዘርን በዘራ ጠላት፡ በእርሻና በዘር፡ በስንዴና በእንክርዳድ፡ በአጫጆችና በመክር እየመሰለ ባስተማራቸው ትምህርቶች አስረድቷል።

ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ!” ያለው ጌታ፡ እነዚህን የምሳሌ ትምህርቶቹን ሲተረጕም፡ መልካምን ዘር የዘራው፡ የሰው ልጅ (ኢየሱስ ክርስቶስ) ነው፡ እርሻውም፡ ዓለም ነው፡ መልካሙም ዘር፡ የመንግሥት (የእግዚአብሔር) ልጆች ናቸው፡ እንክርዳዱም፡ የክፉው (የዲያብሎስ) ልጆች ናቸው፡ (ክፉውን ዘር) የዘራውም ጠላት ዲያብሎስ ነው፡ መከሩም፡ የዓለም መጨረሻ ነው፡ አጫጆችም፡ መላእክት ናቸው።

እንግዴህ፡ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል፡ በዓለም መጨረሻም እንዲሁ ይሆናል።አለ። ኢየሱስ ክርስቶስ፡ ይህንኛውን ትርጓሜውን የጨረሰው፡ እናንተና እኛ፡ እኛንም የመሰሉት ሁሉ፡ ልብ ብለን እንድናስተውለው በሚፈልገው፡ የሚሰማ ጆሮ ያለው፡ ይስማ!” በሚለው የማስጠንቀቂያ ቃሉ ስለሆነ፡ ይህ መለኮታዊ ቃል የዘወትር ማንቂያ ደወል ሊሆነን ይገባል።

በራእየ ዮሐንስ ላይ የተጠቀሰው የሺ ዓመቱ ምስጢር ላይ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ፡ በትንሣኤውና በዕርገቱ የክፋትን፥ የኃጢአትንና የሞትን ኃይላት ድል ነስቶ፡ መንፈስ ቅዱስ በዓለሙ ላይ እንዲወርድ በማድረጉ፡ የእግዚአብሔር ልጆች የተቀዳጁትን ድል የሚገልጸውን ይህንኑ ምስጢር፡ ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሓንስ እንዲህ አብራርቶ ጽፎታል፦

የጥልቁን መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት፡ በእጁ የያዘ መልአክ፡ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። የቀደመውንም እባብ፥ ዘንዶውን፥ እርሱም፡ ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው! ሺ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፡ በእርሱ ላይ ዘግቶ፡ ማኅተም አደረገበት! ከዚያም በኋላ፡ ለጥቂት ጊዜ ይፈታ ዘንድ ይገባዋል።

ከዚህ በኋላ፡ ዙፋኖች ተዘርግተው፡ የሰው ልጅ (ኢየሱስ ክርስቶስ) በላያቸው ተቀምጦ አየሁ! ሰለኢየሱስ፥ ስለስሙና ስለእግዚአብሔር ቃል ሲሉ ስለተገደሉ ሰዎች ነፍሳትም፡ ቅን ፍርድን ፈረደላቸው! ለአውሬውና ለምስሉም ያልሰገዱትን፥ ምልክቱንም፡ በግምባራቸው ላይ ያልጻፉትን፥ በእጆቻቸውም ያልተቀበሉትን አየሁ! እኒህ ከክርስቶስ ጋር፡ በዚህ ሺ ዓመት፡ ሕያዋን ሆነውና ነግሠው ይኖራሉ! የቀሩቱ ሙታን ግን፡ ይህ ሺ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ፡ ተነሥተው በሕይወት አይኖሩም። ይህ በመንፈስ ትንሣኤ የምትገኘው፡ የፊተኛዪቱ ሕይወት ናት! አስቀድማ በምትመጣው፡ በዚች ሕይወት፡ ዕድል ፈንታ ያለው፡ ብፁዕና ቅዱስ ነው! ሁለተኛው ሞት በእኒህ ላይ፡ እንግዴህ ወዲህ፡ ሥልጣን የለውምና! የእግዚአብሔርና የክርስቶስ አገልጋዮች ይሆናሉ እንጂ! ከእርሱም ጋር ይህን ሺ ዓመት ይነግሣሉ!”

ሽሁም ዓመት ሲፈጸም፡ ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል! በአራቱም፡ በምድር ማዕዘናት ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን እንዲያስታቸው፥ ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ቁጥራቸውም እንደባሕር አሸዋ የሚያህል ነው። ወደምድርም ስፋት ወጡ! የቅዱሳን መሰባሰቢያ የሆነችውንም ቅድስት አገር (ኢትዮጵያን) ከበቡ! ከዚህ በኋላ፡ ከሰማይ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ፡ እሳት ወርዳ በላቻቸው! ያሳታቸውም ዲያብሎስ፡ አውሬውና ሓሰተኛው ነቢይ ወደሚገኙበት፡ ወደእሳቱና ወደዲኑ ዐዘቅት ተጣለ! በዚያም፡ ለዘለዓለም እስከዘለዓለም፡ በመዓልትና በሌሊት፡ ሲሰቃዩ ይኖራሉ።” (ራእ. 201-10)

ከዚህ በላይ የሠፈረው የእግዚአብሔር ቃል አያሌ ቁም ነገሮችን የያዘ ነው፡ ነገር ግን ትንሣኤ ሙታንን በሚመለከተው ላይ ብናተኩር ሁለት ትንሣኤዎች እንዳሉ እንረዳለን። የመጀመሪያው ትንሣኤ ተነሥተው የሚኖሩት ሕይወት ሲሆን፡ ሁለተኛው ትንሣኤ ደግሞ፡ በመጨረሻ፡ በክርስቶስ ምጽአት ጊዜ፡ በመንፈሳዊው የትንሣኤ አካል፡ ለዘለዓለም የሚነሱት፡ የኋለኛው ትንሣኤ ነው፤ እኒህ የእግዚአብሔር ወገኖች፡ በፊተኛው የመንፈስ ትንሣኤ፡ በሕይወት ሥጋ እየኖሩ ሳሉ፡ ምናልባት፡ የክርስቶስ ምጽአት የሆነ እንደሆነ በቅጽበት ተለውጠው፡ ለዘለዓለማዊው የሕይወት ትንሣኤ የሚበቁ መሆናቸውን፡ መለኮታዊው ቃል ያመለክታል።

በዚሁ መለኮታዊ ቃል መሠረት፡ በአንድ በኩል፡ የእግዚአብሔር ወገኖች፡ ይህን በመሰለ የብቅዓት ሕይወት ላይ ሲገኙ በሌላ በኩሉ ደግሞ የቀሩት የሰው ዘሮች ቅዱሱን ኪዳን ለመቀበል ፈቃደኞች ባለመሆናቸው፥ የተቀበሉትም በእርሱ ላይ፡ ክህደትና ዓመፅ በመፈጸማቸው፡ በሕይወተ ሥጋ እያሉ፡ እንደሙታን ይቆጠራሉ፤ ራሳቸውንም፡ በፈቃዳቸው፡ ከእግዚአብሔር ሕይወት አግልለው፡ ለሰይጣን ወገንነት ስላቀረቡ፡ በክርስቶስ ምጽአት ጊዜ፡ በሕይወተ ሥጋ የሚገኙት ጭምር፡ በፃዕር፡ የመጀመሪያውን የሞት ጽዋቸውን ከተቀበሉ በኋላ፡ ሁለተኛውንና ነፍሳዊውን ሞት ለሚያስከትልባቸው፡ ለዘለዓለማዊው ኵነኔ ትንሣኤ ይነሳሉ።

Tensae-Continue reading…

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , | Leave a Comment »

የግብጽ ክርስቲያኖች የኢትዮጵያ ሙስሊሞች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 12, 2011


ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ታላቁን ግድብ ለመስራት ካላት ዕቅድ የተነሳ የተጨነቁት ግብጻውያንና መንግሥታቸው ኢትዮጵያ ከዚህ አንጋፋ ፕላን እንድትቆጠብ ይገፋፉ ዘንድ የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጳጳስን፡ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኑዳ 3ትን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ ተዘጋጅታለች። የ88 ዓመቱ አዛውንት አቡነ ሰኑዳ፤ ምንም እንኳን በቅርቡ በአሜሪካ የሕክምና እርዳታ አግኝተው ወደ ግብጽ ከተመለሱ በኋላ በማገገም ላይ የሚገኙ ቢሆኑም ለአገራቸው ደህንነት ሲሉ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው በግብጽ መንግሥት ስም አቤቱታቸውን ለኢትዮጵያውያን ለማሰማት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጠዋል።

እጅግ በጣም የሚገርም ነገር ነው፡ በትውልድ አገራቸው ለዘመናት እንደ ሁለተኛ ዜጋ የሚቆጠሩት ግብጻውያን ክርስቲያኖች ከሙስሊም ወገኖቻቸው ጋር አብረው በመሆን ለአገራቸው ደህንነት ሲታገሉ ስናይ፡ ምን ያህል የታደለች አገር ናት እንድንል ያስገድደናል። ምክኒያቱም፡ በአገራችን ኢትዮጵያ የሚገኙ ሙስሊሞች፡ ከጥቂቱ በስተቀር፡ አብዛኛዎቹ ታማኝነታቸው ለአረቦች እና ለእስልምናው ኡማ ነው እንጅ ለጎረቤቶቻቸው፡ አስተናግደው በሰላምና በፍቅር ለመኖር እንዲችሉ ለፈቀዱላቸው ኢትዮጵያውያን አይደለም። ይህም ሁኔታ በታሪክ ተደጋግሞ የተከሰተ ሁኔታ ነው። በግብጽ፡ በቱርክ፡ በጣልያንና በሶማሊያ ወረራዎች ጊዜ ታማኝነታቸው ተፈትኗል።

እስኪ የግብጽ ክርስቲያኖችንና ሙስሊም ኢትዮጵያውያኖችን እናነጻጽር፡

ክርስቲያን ግብጾች፡ ከ10-15ሚልየን ይሆናሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን፡ ከ10-15 ሚሊየን ይሆናሉ
ክርስቲያን ግብጾች ከሙስሊም ግብጾች በፊት ግብጽ ነበሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በእንግድነት ወደ ኢትዮጵያ ገቡ
ክርስቲያን ግብጾች እንደ ሁለተኛ ዜጎች ሰለሚቆጠሩ ብዙ ይበደላሉ፡ ሰላምም የላቸውም ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከክርስቲያኑ ጋር በእኩልነት በሰላም ይኖራሉ
ግብጻውያን ክርስቲያኖች ወደ እየሩሳሌም እንዳይሄዱ በህግ ይከለከላሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ወደመካና መዲና እንዳፈቀዳቸው መጓዝ ይችላሉ
ግብጻውያን ክርስቲያኖች አዲስ ቤተክርስቲያን መሥራት አይፈቀድላቸውም፡ ለማደስም ቢሆን ከመንግሥት ፈቃድ ማግኘት አለባቸው ሙስሊም ኢትዮጵያውያን መስጊድ መሥራት ሆነ ማደስ ይችላሉ፡ ሙስሊሞች በማይገኙበት ቦታዎች ሁላ መስጊዶቻቸውን ይሠራሉ
በካይሮ፤ ከ10ሺህ በላይ መስጊዶች፡ እስከ 2 መቶ የሚጠጉ ቤተ ክርስቲያኖች አሉ። 30% ነዋሪ ክርስቲያን በሆነባት ከተማ በ አዲስ አበባ፤ 180 መስጊዶች 130 ቤተ ክርስቲያኖች አሉ። 85% ነዋሪ ክርስቲያን በሆነባት ከተማ
ግብጻውያን ክርስቲያኖች በሙስሊሞች በየጊዜው ሰይፍ ይመዘዝባቸዋል፡ ይጨፈጨፋሉ፡ይገደላሉ፡ ዓብያተ ክርስቲያኖቻቸው፡ ገዳሞቻቸው፡ ንብረታቸው ይቃጠልባቸዋል ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ላይ በየጊዜው ሰይፍ ይመዝዛሉ፡ ዓብያተ ክርስቲያናትን፡ ገዳማትን ያቃጥላሉ
ሙስሊም ግብጻውያን ለግብጽ ክርስቲያኑ ከፍተኛ ጥላቻን ያሳያሉ ኢትዮጵያዊው ክርስቲያን ለሙስሊሙ ሕብረተሰብ አክብሮትና ፍቅር ሳይነፍግ ይኖራል
ግብጻውያን ክርስቲያኖች ከሙስሊም ግብጻውያን ጋር አብረው በመሰለፍ በእስራኤል ላይ ጥቃት አድርሰዋል ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከፋሺስት ሙሶሊኒ እንዲሁም ከሶማሊያ ጋር በመተባበር በኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት አድርሰዋል
ግብጻውያን ክርስቲያኖች የሙስሊሞችን አምላክ ባይቀበሉትም፡ የኮፕቲክ መጠሪያውን ትተው እንደ ሙስሊሞች፡ አላህእያሉ ይናገራሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን አምላክ አይቀበሉም፡እግዚአብሔር ብለውም አይጠሩትም፡ የአረብኛውን አላህእንጂ
ግብጻውያን ክርስቲያኖች የእስልምናን አዲስ አመት ከሙስሊሞች ጋር አብረው ያከብራሉ፡ እንኳን አደረሳችሁም ይላሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት አያከብሩም፡ የእስልምናን እንጂ፡ ለኢትዮጵያውንም እንኳን አደረሳችሁ አይሉም
የግብጽ ክርስቲያኖች የባህል አለባበስ እንደ ሙስሊሙ ሁሉ የአረብን ባህል የተከተለ ነው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን አለባበስ ኢትዮጵያዊ ሳይሆን የአረብን ባህል የተከተለ ነው
የግብጽ ክርስቲያኖች ፀሎታቸውን፡ በግብጽኛ ሳይሆን በዐረብኛ ቋንቋ ነው የሚያደርሱት፡ ለሰላምታም እንዲሁ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፀሎታቸውን የሚያደርሱት በኢትዮጵያ ቋንቋዎች ሳይሆን በዐረብኛ ነው፡ ለሰላምታም እንዲሁ
የግብጽ ብሔራዊ ሃይማኖት እስልምና ነው ኢትዮጵያ ይፋ የሆነ ብሔራዊ ሃይማኖት የላትም
የግብጽ ክርስቲያኖች የምርጫ እድል ቢሰጣቸው ቅዱስ ማርቆስን በመሪነት እንዲያገለግላቸው ይመርጣሉ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የምርጫ እድል ቢሰጣቸው፡ ግራኝ አህመድን በመሪነት እንዲያገለግላቸው ይመርጣሉ
የግብጽ ክርስቲያኖች ልባቸው ለግብጽ ይመታል የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ልብ ለሳዑዲ ዐረቢያ ነው የሚመታው
የግብጽ ቤተክርስቲያን ምእመኗ እየተበደለ እንኳ መቻቻልንና መተሳሰብን ታስተምራለች የሙስሊም ኢትዮጵያ መስጊዶች የሙስሊሙን እና የመስጊዶችን ቁጥር ለማብዛት ኃይል የተሞላበት ጂሃዳዊ ትግል መካሄድ እንዳለበት ያስተምራሉ
የግብጽ ክርስቲያኖች የሚሌኒየም ግድብ በዓባይ ወንዝ እንዳይሰራ ይፈልጋሉ፡ ለመታገል ብሎም በክርስቲያን ኢትዮጵያ ላይ ለመነሳትም ዝግጁ ናቸው ሙስሊም ኢትዮጵያውያንስ? ይህን የግድብ ዕቅድ ይደግፉታልን? ኢትዮጵያን እንደ አገራቸው በመቁጠር ለመከላከልስ ዝግጁ ናቸውን?

Sources from the Egyptian Coptic Church said its leader, Pope Shenouda III, is communicating with the Ethiopian church in an effort to help resolve the water crisis, which erupted after Ethiopia began constructing a Millennium Dam on the Nile.

Sources said that a trip by the Pope to Ethiopia has been suggested.

Bishop Morcos, head of the information committee at the Holy Synod, said the strong ties between the two countries’ churches may help resolve the crisis, and said, “We won’t hold back in performing our roles if political leadership asks for that.”

Ethiopian Bishop Boules visited Egypt at the end of 2010 and prayed with Pope Shenouda, added the sources. They said Shenouda is willing to travel to Ethiopia — although he arrived from a treatment trip in the US weeks ago — for the sake of Egypt’s security.

Shenouda wants the Ethiopian church to convince the government there not to escalate the water problem with Egypt and Sudan. Shenouda had declared earlier that there have been communications with the Ethiopian church in this regard.

However, the Ethiopian church said the situation was difficult in light of the secular nature of the Ethiopian government.
Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , | 2 Comments »

Diverting The Nile in Myth and Legend

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 3, 2011


 

If the Ethiopian monarch really controlled the Nile, he would “have had all Egypt at his Devotion”, for the Turks would “deny him nothing”

 

The Greek historian Herodotus called Egypt the ‘Gift of the Nile’, and so it truly was until the construction of the Aswan Dam. The waters which swelled the Nile during the rainy season in Ethiopia sent a huge volume of water down to Khartoum via the Blue Nile, which there joined the White Nile, and so down to Egypt. The ancient Egyptians dated their years by this event, the season of the Inundation. All over the lands bordering the Nile in the long river valley, a rich dark silt was deposited when the waters went down, rendering Egypt so fertile that its ancient name was Kheme, the Black Land.

The ancients knew where the waters came from, even if later ages forgot. An Egyptian hieroglyphic inscription mentions that a downpour in Punt (nowadays identified as the Sudan/Ethiopia border region) caused the Nile to flood. A natural preoccupation of the Egyptians was attempting to predict the quantity of the inundation each year. Nilometers were constructed so that the rate of flow could be measured, and it could early be seen how ample the waters were likely to be. Incidentally, the record of these can now be employed to reconstruct possible climate trends in Ethiopia as well.

Nothing could impede the massive flow of the stately river. Or could it? Just this doubt sometimes nagged at the minds of the Egyptians, for whom the failure of the Nile caused disastrous famine. It was unfortunate that, sitting right where the largest flow of the waters had its source, was the kingdom of the negusa nagast, King of kings of Ethiopia. This Christian king, by a curious anomaly, received his bishops, always Egyptians, from the patriarch of Alexandria, who lived in Egypt under Muslim jurisdiction. Not infrequently, the kings of Ethiopia were embroiled in rows with Egypt over treatment of Christians and similar matters. Could they interfere with the flow of the Nile? Some thought yes, others rejected the idea.

An early mention of an incident involving the damming of the waters of the Nile is attributed to the patriarchate of Cyril II (1078-92). The story goes that a terrible famine in Egypt was caused by the king of Ethiopia damming the Nile. The Fatimid caliph, al-Mustansir (1039-1094) ordered Patriarch Cyril to send an agent to try to have the dam broken through representations to the king; and this was successful. The Egyptian bishop of Ethiopia, it seems, had also protested at the plan, but had been unable to convince the king. In another version, it was the Patriarch of Alexandria himself who was sent by al-Mustansir, bearing rich gifts. The king met him with reverence and enquired why he had come. After hearing the explanation, the king commanded certain works which restored the flow of the river.

The story, whose main theme recurs not infrequently, seems to be one exploited by the Coptic Christians to influence their treatment at the hands of the sometimes hostile authorities in Egypt. It was nice to know, or at least to say, that down in the mysterious mountains of Abyssinia there was a great king who, at the mere whisper of persecutions for his Christian brothers in Egypt, could react with a terrible weapon. The legendary tone of these tales, however, is probably confirmed by the silence in the official History of the Patriarchs of Alexandria about what would have been so emphatic a propaganda feature for the patriarchate.

Nevertheless, the Ethiopians themselves certainly believed or pretended to believe that they could control the flow of the waters of the Nile, or at least tried to exploit the Egyptians’ belief that they could. For example, in the reign of Emperor ‘Amda-Tseyon of Ethiopia, in the year 1326, when Sultan al-Nasir Muhammad b. Qala’un was ruler of Egypt, the chronicles mention that envoys from Ethiopia arrived in Cairo. They bore a letter from the emperor, which declared that the sultan should rebuild a number of churches which had been demolished (in 1324), and that the Christians should be well treated. Failing this, he threatened to destroy the mosques in his kingdom, and to tamper with the flow of the Nile. The sultan merely laughed at this and dismissed the embassy. The first threat was a tangible one, and the emperor was throughout his reign engaged in conflict with neighbouring Muslim states. But there has never been any hint – and certainly no demonstrable works – which would encourage the belief that an Ethiopian emperor actually made real efforts to block the Nile.

Still, the story was enjoyed in Ethiopia, entering into the folklore of the country. A book called the Matshafa Tefut relates it again with sovereign disregard for mere chronology, muddling a number of events into a new tale. The Egyptian ruler in the story is Caliph Marwan (745-751). The Patriarch of Alexandria is called Michael. He was arrested, and Sayfa Arad (1344-1372), king of Ethiopia, is said to have invaded Egypt and compelled the ruler to release him. When Sayfa Arad died, the patriarch was re-arrested. But another Ethiopian king, Dawit I (1382-1411), came down to Khartoum to commence the alteration of the waters of the Nile. Ahmad, Merwan’s son, duly released the patriarch, and offered an indemnity. But the religious King Dawit preferred a fragment of the True Cross to all the gold of Egypt, and this was sent instead.

The idea that the Nile could be tampered with in Ethiopia grew widespread. Arnold von Harff, between 1496 and 1499, observed that Ethiopian pilgrims were given all sorts of privileges when they passed to and from Jerusalem, when for others impediments were put in the way by the Muslim authorities. He added the old explanation; “no injury must be done them, lest the river Nile should be stopped”. Savants in Europe continued to argue the pros and cons of the question, particularly when, from 1520, Jesuit priests began to bring back some real information about Ethiopia.

Centuries later, we find an Ethiopian sovereign delivering the same threat. A letter from Emperor Tekla Haymanot I in 1706 to the authorities in Cairo confirms this. A dispute arose because of impediments in the free transit of ambassadors to and from Ethiopia. The king threatened that “The Nile might be made the instrument of our vengeance, God having placed in our hands its fountain, its passage, and its increase, and put it in our power to make it do good or harm.”

What is the reality of the old stories? Very likely, in the days of Cyril II of Alexandria and others, there were real failures of the rains in Ethiopia, with concurrent famine in Egypt. When the low Nile had been noted, it may be that messengers were on occasion sent to Ethiopia, particularly if, by coincidence, some misunderstandings had actually occurred between the two countries. The Ethiopian kings doubtless did nothing to discourage the idea that they were responsible, gaining credit for the next season’s liberal Nile. Whatever the case, nowadays elaborate international treaties govern the flow of the Nile for all the countries which share its waters.

 

 

 


Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , | 2 Comments »

‘Cyber War’ or World Wide War’

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 3, 2011


In “Cyber War,” author Richard Clarke explores the newest front of modern war: the Internet and how America could already be on the losing side.

Cyber War is a powerful book about technology, government, and military strategy; about criminals, spies, soldiers, and hackers. This is the first book about the war of the future — cyber war — and a convincing argument that we may already be in peril of losing it.

Cyber War goes behind the “geek talk” of hackers and computer scientists to explain clearly and convincingly what cyber war is, how cyber weapons work, and how vulnerable we are as a nation and as individuals to the vast and looming web of cyber criminals. From the first cyber crisis meeting in the White House a decade ago to the boardrooms of Silicon Valley and the electrical tunnels under Manhattan, Clarke and coauthor Robert K. Knake trace the rise of the cyber age and profile the unlikely characters and places at the epicenter of the battlefield. They recount the foreign cyber spies who hacked into the office of the Secretary of Defense, the control systems for U.S. electric power grids, and the plans to protect America’s latest fighter aircraft.

 

Read an excerpt of the book

 

 


Posted in Infos, Media & Journalism | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

‘The Net Delusion’

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 3, 2011

The net isn’t always what we think, thinks the author, Evgeny Morozov, in his book, “The Net Delusion”. Mr. Morozov argues, the west’s reckless promotion of technological tools as pro-democratic agents has provoked authoritarian regimes to crack down on online activity in some style: not just closing down or blocking websites, but using social networks to infiltrate protest groups and track down protesters, seeding their own propaganda online, and generally out-resourcing and out-smarting their beleaguered citizenry.

The following review of the book – in Egyptian context – is taken from the New York Observer

It’s not often that a nonfiction book appears whose thesis is immediately tested by events. But such is the fate of Evgeny Morozov’s “Net Delusion”

Morozov’s argument that the internet does more harm than good in political contexts is running up against violent reality in Egypt.

Morozov takes the ideas of what he calls “cyber-utopians” and shows how reality perverts them in one political situation after another. In Iran, the regime used the internet to crush the internet-driven protests in June 2009. In Russia, neofascists use the internet to organize pogroms. And on and on. Morozov has written hundreds of pages to make the point that technology is amoral and cuts many different ways. Just as radio can bolster democracy or — as in Rwanda — incite genocide, so the internet can help foment a revolution but can also help crush it. This seems obvious, yet it has often been entirely lost as grand claims are made for the internet’s positive, liberating qualities.

And suddenly here are Tunisia and, even more dramatically, Egypt, simultaneously proving and refuting Morozov’s argument. In both cases, social networking allowed truths that had been whispered to be widely broadcast and commented upon. In Tunisia and Egypt — and now across the Arab world — Facebook and Twitter have made people feel less alone in their rage at the governments that stifle their lives. There is nothing more politically emboldening than to feel, all at once, that what you have experienced as personal bitterness is actually an objective condition, a universal affliction in your society that therefore can be universally opposed.

Yet at the same time, the Egyptian government shut off the internet, which is an effective way of using the internet. And according to one Egyptian blogger, misinformation is being spread through Facebook — as it was in Iran — just as real information was shared by anti-government protesters. This is the “dark side of internet freedom” that Morozov is warning against. It is the freedom to wantonly crush the forces of freedom.

All this should not surprise anyone. It seems that, just as with every other type of technology of communication, the internet is not a solution to human conflict but an amplifier for all aspects of a conflict. As you read about pro-government agitators charging into crowds of protesters on horseback and camel, you realize that nothing has changed in our new internet age. The human situation is the same as it always was, except that it is the same in a newer and more intense way. Decades from now, we will no doubt be celebrating a spanking new technology that promises to liberate us from the internet. And the argument joined by Morozov will occur once again.


 


Posted in Infos, Media & Journalism | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: