Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

በኢትዮጵያ የሃይማኖት መቻቻል አለን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 12, 2011

 

ቪዲዮው ላይ የሳውዲው ዋሀቢ ሰባኪ ክርስቲያኖችንና አይሁዶችን የሚረግም ሱራት ከቁራን እየጠቀሰ በስሜት ተውጦ ሲያለቅስ ይሰማል። ሰሞኑን አብያተ ክራቲያናትን ባገራችን ያቃጠሉት አክራሪዎች ይህን አይነቱን ሰባኪ ይሆን የሚከተሉት?


በኢትዮጵያ የሃይማኖት መቻቻል አለን?ከሚለው የአባ ሳሙኤል መጽሐፍ የተወሰደ። ከታላቅ ምስጋና ጋር።

 

ወሀቢያ ምንድን ነው?

ወሀቢያ በ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መሐመድ ኢብን አብደል ዋሂብ /1703-1792 ../ በተባለ ሰው የተመሠረተ የእስልምና ርእዮተ ዓለም ነው። ኢብን አብደል ዋሂብ ከ18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የብዙ እስላሞችን ቀልብ የሳበውን አዲሱን አክራሪ እስልምና መሠረት የጣለ ነው። ተከታዮቹ ራሳቸውን ዋሂዲኖች ብለው ይጠራሉ። ትርጉሙም በተውሂድ የሚያምኑማለት ነው።

መሐመድ ኢብን አብደል ዋሂብ የተወለደው በማዕከላዊው ዐረቢያ ከሪያድ በስተ ስሜን ዑያናህ በተባለ ሥፍራ ከሃንባሊ የእስልምና ት/ቤት ጋር ግኑኝነት ከነበራቸው ቤተሰቦች ነው። አብዛኞቹ ቤተዘመዶች ከዚህ ት/ቤት የወጡ መምህራን ናቸው። በልጅነቱ በወግ አጥባቂው የሱኒ እስልምና ትምህርት ተኮትኩቶ አደገ፡ ከዚያም ለበለጠ ዕውቀት ወደ መካ እና መዲና ተጓዘ። በሃራማየን ት/ቤት በዘመኑ ዋና የአክራሪ እስልምና አቀንቃኞች ከነበሩት ከመሐመድ ሐያት አል ሲንዲ ከፍተኛ ዕውቀት አግኝቷል። በዚያም በተለይም ሃዲትን በተመለከተ በቂ የሆነ ዕውቀት ለመጨበጥ ችሏል። አብደል ዋሂብ በሃዲት በተገለጠው የጥንቱ እስልምና አሁን በሚያየው እስልምና መካከል ያለው ልዩነት ያሳስበው ነበር።

በልዩ ልዩ ቦታዎች ተዘዋውሮ ዕውቀቱን ካጎለመሰ በኋላ ወደ ሀገሩ ወደ ናጅድ ከተማ ተመለሰ። በዚያም ሕዝቡ የያዘውን የተለመደ ዓይነት እስልምና በመተው ቃል በቃል ቁራዓንን በሱኒ የእስልምና መርህ መሠረት እንዲከተል ማስተማር ጀመረ። ምንም እንኳን መጀመርያ ላይ ብዙዎች ቢቃወሙትም የዳሪያው ገዥ ሙሀመድ ኢብን ሳዑድ ጥሪውን በመቀበል የሃሳቡ ደጋፊ ሆነ። በአክራሪው የእስልምና መምህርና በጦረኛው መሪ መካከል የተጀመረው ወዳጅነት ወታደራዊ የሆነ እስላማዊ መንግሥት ለመመሥረት በቃ። ይህ እስላማዊ ወታደራዊ መንግሥት በአጭር ጊዜ ውስጥ ግዛቱን ወደ ሌላው የዐረቢያ ልሳነ ምድር ማስፋፋት ቻለ።

ይህ ኃይል በ1802 .. በደቡብ ኢራቅ የነበሩትን የሺአቶች ቦታዎች አስለቀቀ፡ በ1803 .. ደግሞ መካን ተቆጣጠረ። በዚያም የመጀመርያው ጠንካራ የሳዑዲ መንግሥት ተመሠረተ። በወቅቱ የእስልምናውን ዓለም አንድ አድርገን እንገዛለን ብለው የተነሱት ኦቶማን ቱርኮች ሁኔታው ስላሰጋቸው በግብጽ የነበረውን ጦር ወደ ሳዑዲ ላኩት። በዚህ ምዕራባዊውን አሠራር ይዞ የነበረው የኦቶማን ቱርክና አዲስ በመነሳሳት ላይ በነበረው ዐረባዊው አክራሪነት መካከል በተደረገው ጦርነት የሳዑዲ ወሀቢያዎች ለጊዜው ተሸነፉ። በ1818 .. የመጀመሪያው የሳዑዲ መንግሥት ተጠናቀቀ።

ወሀቢዝም ማናቸውንም ዓይነት የሱፊ እስልምና አካሄዶችን አይቀበልም። የተቀደሱ ሰዎች የሚባል ነገርን አያውቅም፡ በዚህ ዓይነት አምልኮ የተስፋፉ ስዎችም ከእስልምና ያፈነገጡ በመሆናቸው ሞት ይገባቸዋል ይላል። ከቁርዓንና ከሱና በስተቀር ሌላ የእስልምና መጽሐፍ አይቀበልም። እስልምና ብቸኛ የድኅነት መንገድ ነው ይህንን ደግሞ ሰዎች በውድም ሆነ በግድ መቀበል አለባቸው፡ ስለዚህም የተቀደሰ ጦርነትን ማካሄድ አስፈላጊ ነው ይላል። /ሱረቱ 8:65/

ይህ የወሀቢዝም አስተሳሰብ በሶማልያ ከሚገኘው የአልሸባብ ቡድን እስከ አል ቃኢዳ ድረስ ያሉ የዘመናችን አሸባሪዎች የሚመሩበት አስተሳሰብ ነው። የሀገራችን እና የቤተ ክርስቲያናችን የዘመኑ ፈተናም ይህ ነው። ወሃቢዝም በየሀገሩ በተለያየ ስም ይጠራ እንጂ አሠራሩ ተመሳሳይ ነው፡ እስልምናን አክራሪ በሆነ መንገድ ኃይል ቀላቅሎ መጠቀም ነው። የወሀቢዝም መነሻም መስፋፊያውም ሳዑዲ ዐረቢያ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረገው የአክራሪ እስልምና እንቅስቃሴ ዋናው ድጋፍ የሚገኘው ከሳዑዲ ነው።

ወሀቢዝም በአሁን ጊዜ በሀገራችን የሚያደርገው እንቅስቃሴ ምን ይመስላል?

ወሀቢዝም በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን እየሠራ ያለውን ነገር በሁለት ከፍለን እናየዋለን

.ወሀቢዝም ከኢትዮጵያ ውጭ ያለው እንቅስቃሴ

.ወሀቢዝም በሀገር ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ


ወሀቢዝም በውጭ ሀገር ያለው እንቅስቃሴ

በውጭ ሀገር የምንለው ከኢትዮጵያ ውጭ የሚያደርገውን ኢትዮጵያ ተኮር እንቅስቃሴ ነው። ወሀቢዝም ከኢትዮጵያ ውጭ እየሠራ ያለው የመጀመርያው ተግባር ወጣቶችን ወደ ልዩ ልዩ ሀገሮች በተለይም ወደ ሳዑዲ ዐረቢያ፣ ፓኪስታን እና ማሌዥያ በመውሰድ ማሠልጠን ነው። ስለ ሕግ ብትጠይቁ ፈሪሳዊ ነበርሁ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ብትጠይቁ ያለ ነቀፋ ነበርሁ /ፊሊጽ.35/

እነዚህ ከመላዋ ኢትዮጵያ ተመልምለው የሚሄዱ ወጣቶች ተምረው ሲመለሱ የመድረሻ ት/ቤቶች መምህራን አጭር ሱሪ ለባሾች፣ ጢም አሳማሪዎች፣ ሴቶቹ ከራስ ጸጉራቸው እስከ እግር ጥፍራቸው ሂጃብ የሚሸፋፈኑ፣ ሙስሊሙ ከከርስቲያኑ ጋር አብሮ እንዳይኖር የሚለያዩ፣ ኢትዮጵያ እስላማዊ መንግሥት ሊኖራት ይገባል እያሉ የሚሰብኩ ናቸው።

ሌላው ተግባር ደግሞ የኢትዮጵያ ጠላቶችን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ መርዳት ነው። ለምሳሌ ከሩቁ ዘመን የግራኝን ዘመን ከቅርቡ ዘመን ደግሞ የሙሶሊኒን እና የሶማልያ ወረራን ለመደገፍ ሳዑዲዎች ያደረጉት ጥረት የሚጠቀስ ነው።

በዘመናችን ከምናየው ደግሞ የቢን ላደንን /አልቃይዳ/ እና የሶማሊዎቹ አልሸባብ ኅብረትን ጥረት እናያለን። ይህም ድርጅት ታላቋን ሶማሊያ የመመሥረትና ወሀቢዝምን በኢትዮጵያ የማስፋፋት ሕልም ያለው ድርጅት ነው። ይህም ድርጅት እስከ አሁን ድረስ የዓለም ሙስሊሞች ማኅበር በሆነው የርዳታ ሰጭ ድርጅት በአልሐራማን ይደገፋል።

እንደ አልሸባብ የመሳሰሉት የእስላም ድርጅቶች መልካቸውን እየቀያየሩ የአክራሪ እስልምናን መንፈስ በምስራቅና በደቡብ ኢትዮጵያ ማናፈስ ከጀመሩ ቆይተዋል። እነዚህ ድርጅቶች በሚያናፍሱት የፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳ ኢትዮጵያ ውስጥ የነበሩት ደጋፊዎቻቸው የልብ ልብ እየተሰማቸው በትዕቢት እየተወጠሩ መጥተዋል። በአሁን ጊዜ የምናያቸው በልዩ ልዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በክርስቲያኖች ላይ ያደረሱት ጥፋቶች ከዚህ ንቅናቄ ጋር ትሥሥር አላቸው።

ለምሳሌ በ1998 .. በጂማ አካባቢ በክርስቲያኖች ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ የመሩት ከውጭ የመጡ አክራሪዎች እንደነበሩ እና ከነዚህ ድርጅቶችም ጋር ግኑኝነት ያላቸው መሆኑን መረጃዎች አረጋግጠው ነበር። ሰሞኑንም በጂማ እና አካባቢዋ በክርስቲያኖች ላይ የተካሂደው ጥቃት በነዚህ ድርጅቶች ቅስቀሳ የተመረዙት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን መሆናቸው የሚያጠራጥር አይደለም

በደቡብ ኢትዮጵያ የሚገኙትን ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በወሀቢ መርዝ ለመንደፍ ድጋፋቸውን የሚሰጡት ግብጽ፣ ሊቢያ፣ ሶርያ፣ ኳታር፣ የሊባኖሱ ሂዝቦላህ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ ዐረቢያና ጂቡቲ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት በ2007 .. ያቀረበው ሪፖርት ይናገራል።


. ወሀቢዝም በሀገር ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት ወሀቢዝም ኢትዮጵያ ውስጥ ካለፉት ዘመናት በባሰ ሁኔታ ሥራ በመሥራት ላይ ነው ማለት ይቻላል። የወሀቢያ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያውያን እስላሞች ከሌላው ሕዝብ /ማኅበረሰብ/ ጋር አብሮ ተቻችሎ የመኖር ነባር ባሕልን እያበላሸ መሆኑን የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤትም ይገልጣል። በተለይም ከሳዑዲ መንግሥት የሚረጨው ገንዘብ ወሀቢያን እያጠናከረው መሆኑን ያስረዳል።

የወሀቢያ እንቅስቃሴ ዋና ዋና ዓላማዎች

1. የሕዝቡን ተቻችሎና ተግባብቶ የመኖር ባሕል ማበላሸት

ከክርስቲያኖች ጋር በንግድ፣ በሥራ፣ ወዘተ አብሮ መሥራት እንደማይቻል ወሀቢያዎች ያስተምራሉ።

2. ኃይል የተሞላበት እንቅስቃሴ

እስላሞች የበለጠ እንዲሰልሙ ክርስቲያኖችም እስልምናን እንዲቀበሉ ኃይል የተሞላበት እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ነው። ክርስቲያኖችን ይገድላሉ፣ ቤቶቻቸውንና አብያተ ክርስቲያናትን ያቃጥላሉ፣ ሀብታቸውን ይዘርፋሉ፡ ክርስቲያኖችን ከትውልድ ቦታዎቻቸው እንዲፈናቀሉ ያደርጋሉ ወዘተ

ለምሳሌ፡

  • ሴቶች ብቻቸውን ውኃ መቅዳት አይችሉም፣ በሙስሊሞች ይደፈራሉ።
  • መስቀላቸው ተነሥቶ ጨረቃ ተቀምጦባቸው ወደ መስጊድነት የተቀየሩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶና የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት አሉ።
  • ዲያቆናት በግድ ሰልመው ቁርዓን እንዲቀበሉ ይደረጋል።
  • ካህን ሻሽ ጠምጥሞ ሲሄድ ከታየ ይደበደባል፣ ይዘረፋል፣ ይሰደባል።
  • ከሰለምክ ተቀምጥ፣ ካልሰለምክ ውጣ እየተባለ ብዙ ክርስቲያኖች በገጀራ እየተደበደቡ እንዲሰልሙ መደረጉን መገንዘብ ተችሏል።

3.መስጊዶችን ማስፋፋት

ወሀቢያ ሌላው ተግባሩ ከሳዑዲ በሚመነጭ ገንዘብ መስጊዶችን ማስፋፋት ነው። በጠቅላላ የተሠሩትን መስጊዶች ብዛት በአዲስ አበባ ብቻ

180 መስጊዶች ይገኛሉ። ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ግን 130 ብቻ ናቸው። የሙስሊሙንና ክርስቲያኑን ቁጥር በአዲስ አበባ ከመስጊዱና ቤተ ክርስቲያኑ ቁጥር ጋር ስናነጻጽረው የሚከተለውን መልክ ይሰጠናል።

 

ሃይማኖት መቶኛ የቤ/ክርስቲይን /መስጊድ ቁጥር
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ 87 130
እስልምና 13 180

 

ከላይ ከተጠቀሱት 180 መስጊዶች መካከል ከ130 የሚሆኑት ባለፉት 15 ዓመታት የተሠሩ ናቸው።

በሌሎች የሀገሪቱ ክልሎች ሳይቀር ተመሳሳይ ሥራ እየሠሩ ነው። ከአዲስ አበባ ወደ አዋሳና በሌሎችም ዋና ዋና መንገዶች ዳር ላይ ስትጓዙ ሰው በሌለባቸው አካባቢዎች እንኳን ሳይቀር መስጊዶች በየአምስት እና አሥር ኪሎ ሜትሮች ርቀት ተገንብተዋል።

4. የጥምቀተ ባሕርና የመስቀል አደባባዮችን መንጠቅ

ሕዝቡን አበሳጭቶ አላስፈላጊ ሁከት ለማስነሳትና ተጨቁነናል፡ አሁን በጂማ እና አካባቢዋ እንደታየው ቁራእንን ለሽንት ቤት ተጠቅመዋል ወይም ቀድደዋል ብለው ስም ለማጥፋት ወሀቢያዎች ከሚጠቀሙበት አንዱ ዘዴ የጥምቀተ ባሕርና የመስቀል ማክበርያ ቦታዎችን ለመስጊድ ግንባታ መንጠቅ ነው። በአዲስ አበባ የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረትን ቦታ ለመውሰድ የተደረገው ትግል የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው።

5. መረጃ ማዛባት

ሌላው የትንኮሳ መንገድ ደግሞ ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ሳይሆን የሙስሊም ሀገር ዳር አልኢስላምመሆን አለባት የሚለውን የመካከለኛው ምሥራቅ አክራሪ ወሀቢዎች አጉል ሕልም ለማሳካት በኢትዮጵያ ከክርስቲያኑ ይልቅ ሙስሊሙ በቁጥር ይበዛል የሚል ፕሮፓጋንዳ መንዛት ነው።

6. በክርስቲያኖች ተጨቁነናል የሚል ድምጽ በተደጋጋሚ ለዓለም ማሰማት

በሀገር ውስጥ ላሉት የእምነቱ ተከትዮችም ሆነ በልዩ ልዩ የእስልምና ሀገሮች እና በሰብአዊ ድርጅቶች ዘንድ በኢትዮጵያ ውስጥ ሙስሊሞች እንደ ተጨቆኑ አድርጎ በመናገር የወሀቢያን እንቅስቃሴ የነጻ አውጭ እንቅስቃሴ ቅርጽ ለመስጠት ጥረት በመደረግ ላይ ነው። በዚህ መልክ ሙስሊም ሀገሮችና ድርጅቶች የሚሰጡትን ርዳታ የተጨቆኑ ወገኖችን ከመርዳት ጋር ያያይዙታል። ለመሆኑ መቸ ነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሙስሊሞችን የጨቆነው? ራሱ ሕዝቡ ከግዥዎች ከፋፍሎ የመግዛት ዘይቤ ሲፈራረቅበት የኖረ ሕዝብ ነው፡ በርግጥ ነገሥታቱ ክርስቲያኖች ናቸው። ይህ ደግሞ ሀገሪቱ በታሪክ ሳይሆን በተግባር ሕገ ኦሪትንና ሐዲስ ኪዳንን ከሌላው ዓለማት በፊት የተቀበለች ሀገርና ሕዝብ ስለሆነ ነው። ስለዚህ ጨቋኝና ተጨቋኝ የለም። ለምሳሌ አፄ ኃይለ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ብቻ አልሰሩም መስጊድም ጭምር እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ አልነበረም ያሳተሙት ቁርዓንም ጭምር እንጂ።

ለምሳሌ የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች የተቀደሰች ከተማ በሆነችው አክሱም መስጊድ ካልሰራን ሙስሊሞች ተጨቁነናል እያሉ ፕሮፓጋንዳ በመንዛት ላይ ናቸው። የሚገርመው ሁኔታ ግን ሳዑዲ ውስጥ፡ እንኳን መካና መዲና በመላ ሀገሪቱ አንድም ቤተ ክርስቲያን የለም። ቤተ ክርስቲያን ይቅርና ክርስቲያን ሲሞት እንኳን መቀበር አይፈቀድለትም ወደ ባሕር ይጣላል ወይም ሰው ካለው ወደ ትውልድ አገሩ ይላካል። አንድ መንገደኛ የሳውዲ ዓውሮፕላን ማረፊያዎችን እንደረገጡ፡ መጽሐፍ ቅዱስ ይዛችኋልን? የሚል ጥያቄ ነው በጉምሩክ ሰራተኞች የሚጠየቁት። ከያዙ እንዲያወጡ ይጠየቁና እዚያው ፊታቸው መጽሐፍ ቅዱሱ በማሺን ተቀዶ ወደ ቆሻሻ ቅርጫት ይገባል።

7. በየአጋጣሚው ክርስቲያኖችን መክሰስ

በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ክርስቲያኖችን መክሰስና ሆ! ብሎ ነገር ማንሳት የወሀቢዎች አንዱ የመጠቀሚያ ስልት ነው። ለምሳሌ በአንድ ወቅት በአዋሳ ዩኒቨርሲቲ የዐረብኛ ቁርዐን ተቀደደ ተብሎ ግርግር ተነሳ። አንድ ምስኪን ተማሪም ተይዞ ታሰረ። ህግ ከሁሉም በላይ ነውና ሲጣራ ጽሁፉ እንኳን ቁርዓንን ሊሆን ዐረብኛም አይደለም፡ በወቅቱ የተፈጸመው በፓኪስታን የተደረገውን ድርጊት ተከትሎ ለማንጽባረቅ የተፈጠረ ነበር። ነገር ግን ድሀው ተማሪ የዚህ ሰለባ ሆነና ፍርድ ቤት እንኳ ነን ቢያወጣው ትምሕርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ ባለ ዩኒቨርሲቲዎች ገብቶ እንኳ እንዳይማር ከለከለው /ከህግ በላይ በመሆን/ ያሳዝናል።

በጣም የሚያሳዝነው ግን፡ በዚሁ የትምርት ተቋም በክርስትና ተከታዮች ተማሪዎች ላይ በጾም ጊዜ ለእስላሞች የተዘጋጀውን የፍስክ ምግብ አብራችሁ ካልበላችሁ ለእናንተ የሚሆን የጾም ምግብ የለኝም በማለት በፈጠረው ተጽእኖ ሳቢያ ተማሪዎቹ ለረሃብ አደጋ ተጋልጠው መገኘታቸው ነበር።

ኧረ ለመሆኑ መርካቶ ያሉ ሙስሊም ነጋዴዎች በክርስትና መጻሕፍቶች፣ መጽሔቶችና ጋዜጦች ስኳርና ቡና ጠቅልለውበት አያውቁምን?

የሰው ልጅ ከሌሎች ፍጥረታት በተለይም ከእንስሳት የሚለየው ከመናገሩና አዲሱን ነገር ከማፍለቁ በተጨማሪ አንዱ የአንዱን ክብርና ነፃነት ጠብቆ የመኖሩ ልምድ ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ሌሎች ዓለማት እንደ ሀገር ሳይሆን እንደ ቡድን የመደራጀትን መዋቅር ሳይጀምሩ በሥልጣኔና በመልካም አስተዳደር በነበረበት የውጭ ግንኙነት በስፋት የምትታወቅ ሀገር ናት።

የመጻሕፍት ሁሉ መጀመሪያና ታላቁ መጽሐፍ ቅዱስ ከ40 ጊዜ በላይ ስለ ኢትዮጵያ ጽፏል። አስተዳደሯም እጅግ የተመሰገነና በእንግዳ አቀባበልና የሰውን መብት ከማክበር አንጻር የተገለጠ ነበር በማለት አረጋግጦ ጽፎዋል።

ነብዩ ዕንባቆም የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁዕን 3:11 በማለት ኢትዮጵያውያን እንደ አብርሃም እንግዳን ለመቀበል እጅግ የሚጓጉና በእግዚአብሔርም የሚያምንም ይሁን የማያምን የሰውን ልጅ በሙሉ በፍጹም ፍቅር የሚቀበሉ መሆናቸውን ገልጿል። ነቢዩ ኤርምያስም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊነቱን ነብር ዥንጉርጉርነቱን አይለቅምበማለት እንደገለጸው።

ኢትዮጵያውያን የሰውን ሰብአዊ መብት በመጠበቅ አንፃር በመልካም አስተዳደር ሂደት በ70 .. በጥጦስ አማካኝነት የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ሲፈርስና ኢየሩሳሌም ስትወረር በርካታ አይሁዳውያን ፈላሻዎች ኢትዮጵያ ውስጥ መጥተው ኖረው ምንም እንኳ ኢትዮጵያ የክርስትናን ሃይማኖት ገና በ34 .. በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ አማካኝነት ብትቀበለም የሐ.. 8:29 አይሁድ ክርስቶስን የሰቀሉ ናቸው በማለት ማረፊያ አልተከለከሉም። ይልቁንም በክብር መኖር ጀመሩ እንጂ። ታዲያ በየትኛውም የኢትዮጵያም ታሪክ ይሁን በዓለም ታሪክ ኢትዮጵያውያን እነዚህን አይሁድ ማሰቃየታቸው አልተጻፈም። ነገር ግን በ8ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሳችው ዮዲት ጉዲት ክርስቲያኖችን ማስገደሏ አብያተ ክርስቲያናትን ማቃጠሏ ካህናትን ማሳደዷ ተጻፈ እንጂ።

እንደ አለመታደል ሆኖ ወርቅ ላበደረ ጠጠር እንዲሉ የዘመናችንም የእስልምና እምነት ተከታዮች ነን ባዮች በዮዲት ታሪክ የሚደግሙት በዚህች እንግዶችን በምትቀበል ሀገርና ሀገሪቱን ለዘመናት እያስተዳደረች በኖረችው ቤተ ክርስቲያን ላይ መሆኑ ያስገርማል።

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መቻቻልና መተሳሰብ በምትልበት ጊዜ ሁሉም ሰው የራሱን ሃሳብና ፈቃድ የሌላውን መብትና ህሊና በማይጎዳ መከናወን እንዳለበት ታስተምራለች። ይህ በመሆኑ ነው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በሀገራችን መኖር ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር በእድር፣ በዕቁብ፣ በመረዳጃ ኅብረት እየተሰባሰቡ ለሀገር ሰላም ለአካባቢ ጤና ሲሰሩ እንዲሁም በሐዘንና በደስታ ወቅት እየተጠያየቁና እየተረዳዱ እየኑሩ ለዘመናት የቆዩት።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕሙማኑን እንኳ ያለግዴታ በውዴታ በፈቃደኝነት የተመሠረተ በጥያቄ ልትድን ትወዳለህን?“ በማለት አስቀድሞ ይጠይቃቸው ነበር። ይህ ማለት የሰው ልጅ የራሱ ነፃ ፈቃድ እንዳለውን የፈቀደውን ሃሳብ የማራመድ መብት እንዳለው ያስረዳል። /ዮሐ. 5:1/

በሌላው ዓለም እንደሚሆነው ግን በኢትዮጵያ አይሆንም ምክኒያቱም ሁሉም ሀገር የራሱ የሆነ የአኗኗር ዘይቤ /context/ አለው። ሀገራችን ኢትዮጵያ ራሷን የቻለች ነፃ ሀገር ናትና። ኢትዮጵያ ለሰው ልጆች ሰብአዊ ክብር የምትቆረቆርና ስለሰው ልጆች እኩልነት የምታስተምር ጥንታዊ የነፃነት ሀገር በሕግና በሥርዓትም የምትመራ ሀገር እንጂ አንዳንድ የውጭ ኃይሎች የእስልምናውን ሃይማኖት ሰበብ በማድረግ ባዕድ የሆኑ የጭካኔ ተግባርን በሀገሪቱ ለማስፋፋት በጥረት ላይ ናቸው። በየእለቱም ከሚያከናውኗቸው ተግባራት መካከል በሠሯቸው የሚገልፁ ነጥቦችን ከዚህ በታች መመልከት ይቻላል። እንደ ሀገር፣ እንደ ሕዝብና መንግሥት የራሷ የሆነ ሕግ አላትና የእስልምና አክራሪ እምነት ተከታዮች መቻቻል ሲሉ፦

  • ፈጣሪያችን አምላካችንን እየተሳደቡ አልተወለደም አልተሰቀለም አልተነሳም እያሉ በሌላ ሃይማኖት ጣልቃ በመግባት ሕገ መንግሥቱን በመጣስ ሰብአዊ መብት በመግፈፍ፣
  • የኢትዮጵያን ሕግና አስተዳደር በሼርያ ይመራ በተባበሩት የዐረብ ማኅበራት ትታቀፍ እያሉ ነው የብዙኃኑን የኢትዮጵያውያን መብትና ሕገ መንግሥት በመጋፋት፣
  • የአክራሪዎች መቻቻል ትርጉም አብያተ ክርስቲያናትን ማፈራረስ ክርስቲያኖችን በጸሎት ላይ እያሉ መግደል ማቁሰል ነውን?
  • የእነርሱ የመቻቻል ትርጉም በሚጽፏቸው ጋዜጦችና መጽሔቶች እንዲሁም የስብከት ካሴቶቻቸው ላይ ክርስቶስ ፈጣሪ ነውን? የሚሉ የክህደት ትምህርታቸውን ማሰማታቸው በማይመለከታቸው ሃይማኖት ገብቶ ማጣጣልና መዳፈር ይገባልን?

ከአንድ በላይ የሆኑ ነገሮች በሙሉ አብረው ለመኖር አንዱ የአንዱን ሥርዓት ሕግ ጠብቆና አክብሮ መኖር አለበት። ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን?“ በማለት እንዳስተማረው የሰው ልጅ ከስነ ፍጥረት የሚማር ከሆነ ብርሃን ብርሃንነቱን ጨለማም ጨለማነቱን ይዞ ይጓዛል። ስንዴም ሲዘራ ስንዴ እንጂ ኑግ ሆኖ አይበቅልም። ውሃም ከድንጋይ ጋር ቢውል ድንጋይም ውሃን ቢያስጮኽው ጠባያቸው ለየቅል ነው። ነገር ግን ልዩነት ውበት የሚሆነው የተለያዩና ተቃራኒ የሆኑ ነገሮ መጠራጠር ሳይሆን መስማማት መለያየት ሳይሆን መከባበር ሲችሉ ነው።

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሀገሪቱ የሥልጣኔ መገለጫ ናት፡ ቤተ ክርስቲያኗ የኢትዮጵያን ኢትዮጵያዊነት በሌላው ዓለም ጎልቶ እንዲወጣ በማድርግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቷም አይካድም።

በሌላውም ቋንቋ ሌላው የእኔ የሚለው የትቂት ዘመናት ታሪክ ሊኖረን ይችላል። ነገር ግን ምንም ይሁን ምን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት ለሀገሪቱ ያበረከተችውን ይህን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሌላው አካል መቀበልና ማክበር ብቻ ሳይሆን ወደፊትም ይህ አገልግሎቷ እንዲቀጥል መቻቻል የሚሻው አካል እንቅፋት እንዳይሆን ያስፈልጋል። ይህም ታሪካዊ መቻቻልንም ያካትታል።

ተቻችሎ ለመኖር መተማመን ያስፈልጋል ሲባል ልቡን ሳውዲ አረቢያ፡ ኢራንና ፓኪስታን ካደረጉ የውጭ ኃይሎች ሰዎች ጋር ሳይሆን ኢትዮጵያውያን እንደ ኢትዮጵያ ሲያስቡ ብቻ ነው።

በማኅበራዊ ሕይወት የተጎራበቱን እንግዳ ሆነው የመጡ ሙስሊሞች እስከዛሬ ድረስ በኢትዮጵያ ውስጥ የኖርነው እኛ ስለቻልናቸው እንጂ ክርስቲያኖች ችለውን አይደለም” /ሪፖርተር ጋዜጣ ሚያዝያ 21. ቀን 1999 .. የታተመ/ በማለት እስከመናገር ያደረስናቸው እውነት በታሪክ በስንተኛው ክፍለ ዘመን ነው የቻሉን?

እንደ ታሪካችንማ ከሆነ ሁኔታዎችንና ወቅቶችን በመጠበቅ ብዙ ግፍ ደርሶብናል ቻዮች እኛ እንጂ እናንተ አይደላችሁም። ሌላው ለመቻቻል አክራሪ ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊነቱን ማመን ይስፈልጋል፡ በልባቸው ይረግማሉ በአፋቸው ይመርቃሉበማለት ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እንደገለጸው በልባቸው የአረብ አገራት ምኞትና አስተዳደራዊ አካሄድ በአፋቸው ግን መንግሥት በሰጠን የእኩልነት መብት ተደስተናል ይሉናል።

ከጥቂት ጊዚያት ወዲህ በሙስሊሙ ኅብረተሰብ ስም ቡድኖች ተከባብሮ መኖርን ለማደፍረስ ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ። እንዲህ ዓይነቱን ሥራ ክርስቲያኑ ላድርገው ካለ ምናልባትም በተሻለ መልኩ ሊያደርግ እንደሚችል መታወቅ ይገባዋል። የሀገራችን ሰው ሲተርት ከሳሽ የተከሳሽን ልብ ቢያውቀው ኖሮ እግሩን ይሰበስብ ነበርእንዳለው ሆነ ነገሩ።

የክርስቲያኑ ኅብረተሰብ ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በሚያምንበት ቁርዓን ላይ ምንም ነገር ሳይተነፍስና ሳይስነዝር ጸረክርስቲያን ጸረተዋሕዶ የሆኑ ጽሑፎች ለዚህ በሰላም ለሚኖር ሕዝብ ተርጉሞ ማቅረብ አላዋቂነት ነው። ክርስቲያኖችን የሚያንቋሽሹና፡ ለግድያ የሚቀሰቅሱና በኢራኑ አያቶላ ኮሜኒ የተጻፉ የጥላቻ መጣጥፎች ሳይቀሩ ወደ አማርኛ እየተተረጎሙ በአሁኑ ሰዓት በገበያ ላይ በመዋል ይገኛሉ።

ባንዳንድ አክራሪ ሙስሊሞች የሚሰጡ ከተራ አሉባልታና ስድብ የማይተናነስ መረጃ የሌለውና አሳማኝ ያልሆነ ዲስኩር እየለቃቀሙ ሕዝቡን ለማወናበድ እየተረጎሙ ማቅረብ ተገቢ ድርጊት አይደለም።

እንግዲያው የሚይስፈልግ ከሆነ ቁርዓኑን ከመነሻው ጀምሮ እስከመጨረሻው ሰፊ ትንታኔ በያዘ ምክንያታዊ በሆነ ተጨባጭ መረጃዎችና መልሶች ማውጣት የሚቻል ሲሆን ስለ ሰላምና ስለ ተቻችሎ መኖር ሲባል ይህ እስካሁን አልተደረገም።

አትግደል የገደለም እርሱ ይፈረድበታል የተባለውን ሰምታችኋል እኔ ግን እላችሁ አለሁ በወንድሙ ላይ በከንቱ የሚቆጣ ሁሉ እርሱ ይፈረድበታል። ወንድሙንም ጨርቅ ለባሽ የሚለው በአደባባይ ይፈረድበታል። በገሃነም እሳት ይፈረድበታል /ማቴ. 5:21-22/


 

 

 

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: