Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2011
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
    31  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for January 24th, 2011

UNESCO 50% የዓለማችንን ነዋሪ ግብረሰዶማዊ የማድረግ እቅድ አለው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 24, 2011

በሮማዋ የጵጵስና መስተዳደር የቤተሰብ ሚንስትር የሆኑት ካርዲናል አንቶኔሊ እንደነገሩኝ ከሆነ፡ የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት፡ ማህበረሰብና ባህል ድርጅት (UNESCO) በመጪዎቹ 20 ዓመታት 50% የሚጠጋውን የዓለማችንን ነዋሪ ግብረሰዶማዊ የማድረግ አጀንዳ ይዟልይላሉ፡ በስፔኗ ኮርዶባ የካቶሊክ ክርስቲያኖች መሪ የሆኑት ጻጻስ ዴሚትሪዮ ፈርናንዴዝ።

እንደሳቸው ከሆነ፡ ዩኔስኮ፡ የተለያዩ ፕሮግራሞችን በመከተል፡ ማህበረሰቦች ተለምዷዊ የሆነውን መሠረታዊ የጾታ አመለካከት በመቀየር በተለይ በትምህርት ቤቶች አካባቢ ግብረሰዶማዊነት መጥፎ የሆነ ድርጊት እንዳልሆነ ለማስተማር አቅዷል።

ይህን መሰሉ ሁኔታ አዲስ ባይሆን፡ አሁን ሰለጠነበሚባለው ዓለም እየተፈጠረ ያለው ክስተት ምናልባት በዓለማችን ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ክስተት ነው። ጠቢብ ነው የተባለው ወገን መጥፎ ድርጊቶችን በመፈጸምና በኃጢአት በመሰልጠን ከፈጣሪው ለመራቅ ቆርጦ ተነስቷል። የሰዎችን ህሊና በመቆጣጠር፡ ብሎም የሕሊና ህወከትን ፈጥሮ የቀረውን የሰው ልጅ ወደ ዲያብሎስ ካምፕ ለመሳብ የሚታገለው የሕሊና ፖሊስ፥ ጦርነት ሰላም፡ ባርነት ነፃነት፡ ግድየለሽነት ብርታት እንደሆነ፡ ባጠቃላይ፡ ኃጢአት ጽድቅ፡ ጽድቅ ኃጢአት እንደሆነ ሊያሳምነን እየሞከረ ነው።

ልብ ብሎ ላስተዋለ፡ የሰው ልጅ በተፈጥሮ ከፈጣሪው የተሰጠውን ነጻ ፈቃድ ያላግባብ በመጠቀም ተፈጥሮን የሚጻረሩ ድርጊቶች መፈጸም ከጀመረ ቆይቷል። ሰለጠኑ በሚባሉት የአውሮፓ፡ እስያና አሜሪካ፡ ግብረሰዶማውያን ሕጋዊ እውቅና እየተሰጣቸው ነው፡ ወንዶች ከወንዶች፡ ሴቶች ከሴቶች ጋር እንዲጋቡ እየተፈቀደላቸው ነው። ከጥቂት ሳምንታት በፊት እውቁ የእንግሊዝ ሙዚቀኛ ኤልተን ጆን ከወንድ ባለቤቱጋር እንደቤተሰብ ልጆች እንዲያሳድግ ስለተፈቅደለት ብዙ ታዋቂ የሙዚቃ፡ የፊልምና የፖለቲካ ሰዎች የተሳተፉበት ድግስ ደግሷል።

ክርስቲያኖች፡ በተለይ የተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትምሕርት የሚከተሉት ኢትዮጵያውያን ግብረሰዶማዊነትን አጥብቀው ስለሚያወግዙ፡ በዓለማችን በመታየት ላይ ያለውን የእኩልነት ወረርሽኝ በሽታ የሚያስፋፉት መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሊዋጓቸው በቆራጥነት ተነሳስተዋል። ማንነታችንን አጠንቅቀው የሚያቁትም እነዚህ ሃይሎች ሊበድሉን፡ ሊለዩን፡ ሊያጥላሉንና ሊገድሉን እንደተዘጋጁ ሁላችንም የምናየው ነው።

ባለፈው ሳምንት ላይ እንግሊዝ አገር ውስጥ ለሁለት ግብረሰዶማውያን ወንዶች የሆቴል ክፍል አልሰጡም የተባሉ ክርስቲያናዊ ባለቤቶች በግብረሰዶማውያኑ ተከሰው፡ ፍርድ ቤትም ፀረአድሎየሆነውን ሕግ ጥሳችኋል በማለት የገንዘብ ቅጣት ፍርድ ተሰጥቷቸዋል

ሆሊውድም ብዛት ባላቸው ፊልሞቹ የግብረሰዶማውያንን አጀንዳ የሚያራምዱ ፊልሞች በማውጣት ላይ ነው። ለምሳሌ ለመጥቀስ፡ ሮበርት ዲኔሮ፡ ደስቲን ሆፍማን፡ ጀሲካ አልባ እና ቤን ስቲለር የሚታዩበት “‘Little Fockers’…የተሳተፉበት ሦስተኛው የ ቤተሰቦችን ተዋወቁተከታታይ ፊልም ላይ መጥቀስ የማይስፈልገው አጸያፊ ግብረሰዶማዊ ተግባር በአንድ የጥቁር አክተር አማካይነት በሆስፒታል ውስጥ ሲካሄድ ይታያል። ማናቸውም በሰውነት ውስጥ ጠልቀው የሚገቡ ድርጊቶች ግብረሰዶማዊ የሆነ ባሕርይ የያዙ ናቸው። በጣም የሚገርመው ደግሞ ይህን ፊልም ለማየት የእድሜ ገደብ አለመኖሩ ነው፡ ሕፃናት ሁሉ ማያት ይችላሉ ማለት ነው። ስንቶቻችን እንሆን በዚህ ኤፒዞድ ከተመልካቹ ጋር አብረን ስንስቅ የነበርን?

አውሬው: የሰውን ልጆች ከእግዚአብሔር እጅ ፈልቅቆ ለማውጣት ከሚጠቀምባቸው መሣሪያዎች አንዱ ይህ ግብረሰዶማዊነት ነው። ይህን ድርጊት ለማስፋፋት በቅድሚያ ተለምዷዊ የሆነውን ጠንካራ የማሕበረሰባዊ ኑሮ ማናጋት ነው። ለዚህም የአንድ ህብረተሰብ ምሰሶ የሆነውን የቤተሰብን መዋቅር ማናጋት፡ የግለሰቦችን፡ ብሎም የህዝቦችን ማንነት የሚገልጹትን እንደ እምነት፡ ባሕልና ቋንቋ የመሳሰሉትን ድንቅ ሥራዎች ለማጥፋት ሃይማኖታዊ ተቋማትን፡ ድርጅቶችንና መንግሥታትን ሁሉ መፈታተን ነው።

ከፈጣሪአችን ጋር ጽኑ በሆነ እምነት ከተሳሰሩት ጥቂት አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት። የኢትዮጵያ ተዋህዶ ክርስትና በኢትዮጵያ ሕዝብ ዕምነት፡ መንፈሥ፡ ባሕል፡ ቋንቋና ስነጽሑፍ ላይ እጅግ በጣም ጥልቅ የሆነ ሚና ስለምትጫወት ለዘመናት ዲያብሎስ በገሃድ ሆነ በድብቅ ሲፈታተናት ኖሯል። ምንም እንኳን እስከ መጨረሻው መጽናት ያቃታቸው ደካማ ወገኖች ማንነታቸውን በመካድ በዲያብሎስ እጅ ሥር ለመግባት ቢበቁም፡ የኢትዮጵያ ክርስትና ኃይል ጠላቶቿን ሁሉ እየገረሰሰች እስካሁን ድረስ ለመቆየት በቅታለች፡ ለወደፊቱም የዲያብሎስን ሴራ እያጋለጠች ለደከመው የዓለማችን ክፍል ሁሉ አርአያ ለመሆን እንደምትበቃ የማያጠራጥር ነው፡ እግዚአብሔር ክርሷ ጋር ነውና።

ባዕዳን ፀረኢትዮጵያ ኃይሎች፡ ከኢትዮጵያ ተወላጆች ከሃዲዎች ጋር በመመሣጠርና በመተባበር፡ ምድረ ኢትዮጵያን ከመዋጋት ወድኋላ አይሉም። በረሃብ፡ በበሽታና በጦርነት ሕዝቡን ለማድከም ብሎም ቁጥሩን ለመቀነስ ስላልተቻላቸው፡ ለግበረሰዶማዊነት አመቺ የሆኑትን የአኗኗር ዘይቤዎች ቀስበቀስ ወደ አገራችን በማስገባት ላይ ይገኛሉ። እንደ ዩኔስኮ፡ (UNESCO) ዩኒሴፍ፡ (UNICEF) ፋኦ (FAO) እንዲሁም ቀይመስቀልን የመሳሰሉት የተባበሩት መንግሥት አካሎች፡ መንግሥታዊ ካልሆኑ ዓለምዓቀፋዊ ከሆኑ ድርጅቶች፡ ብሎም እንደ ፔንቲኮስታል እና እንደ ዋሀቢ እስላም ከመሳሰሉ የርዕዮት ዓለም ፋብሪካዎች ጋር በመተባበር ሰይጣናዊ ውጊያቸውን በማጧጧፍ ላይ ይገኛሉ።

ይህን ዲያብሎሳዊ ዘመቻቸውን እንደዱሮው ከውጭ ሆነውና ባዕዳውያንን ብቻ በመጠቀም ሳይሆን የሚያካሂዱት፡ በውስጣችን ሰርገው በመግባት እና ከእኛ የወጡትን ወይም እኛን የመሰሉትን ከሃዲዎች በመመልመል ነው። አዲስ አበባችን የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ማዕከል መሆኗ መልካም የሚሆነው፡ እነዚህ ከተማይቱ የምታስተናግዳቸው ድርጅቶች የሌላ ሳይሆን የእግዚአብሔር ልጆች አገልጋዮች ሆነው ሲገኙ ብቻ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝቦች፡ ኢትዮጵያና ኤርትራ በሚሉ ሁለት አገሮች ለመከፋፈል የበቁት፡ እንዲሁም በሚሊየን የሚቆጠሩ የሩዋንዳ እና የደቡብ ሱዳን ኢትዮጵያውያኖችአሰቃቂ በሆነ መልክ ለመጨፍጨፍ የበቁት፡ እንደ ቦትሮስ ቦትሮስ ጋሊ እና እንደ ኮፊ አናንን የመሳሰለቱ ከሃዲ አፍሪቃውያንየተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊዎች ሆነው ከተሾሙ በኋላ ነው።

የአፍሪቃውያን ትምሕርት ቤቶች ከሪኩለሞች እና አንዳንድ የማህበረሰባዊ መዋቅሮች ሁሉ ስር ሰደድ ለውጥ የተካሄደባቸው ፡ ለምሳሌ፡ ሴኔጋላዊው አማዱ ማኅታር እምቦ የዩኔስኮ ጀነራል ዳይረክተር በነበሩበት ወቅት ነበር። በዓለም የአትሌቲክስ ስፖርት የሩጫ ውድድሮች ከዓመት ወደ ዓመት በአደጉት አገሮች ተወዳጅነቱ እየቀነሰ የመጣው የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሪሸን ማኀበር (IAAF) ፕሪዚደንት የሴኔጋሉ ተወላጅ ላሚን ዲያክ ከሆኑ በኋላ ነው። በዚህ ዓመት በኮሪያ የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር በብዙ አውሮፓውያን አገሮች በቀጥታ እንደማይተላለፍ ለዚህም የቴሌቪዥን ስርጭት መብቱን የወሰደው ድርግት ተጠየቂ እንደሆነ ተገልጿል። በመጪው ዓመት በለንደን ከተማ የሚካሄደውን ኦሊምፒክስ የሚያስተናግደው አዲስ ስቴዲየም የመሮጫ ቦታ የማይኖረው የእግርኳስ ስቴዲየም ብቻ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው።

የግሪንፒስ (Greenpeace International)እንቅስቃሴ መሪ ሆነው የሚያገለግሉትም ህንድ ደቡብ አፍሪቃዊው ኩሚ ናይዶ ሲሆኑ፡ ኢትዮጵያዊው አቶ ከበደ ደግሞ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ፕሬዚደንት ናቸው።

እነዚህ አፍሪቃውያን የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መሪዎች ምን ዓይነት ጥቅም ወይም ጉዳት ለወገኖቻቸው ሊያመጡ እንደሚችሉ ስራዎቻቸውን በሚቀጥሉት ዓመታት አብረን በመገምገም ለመታዘብ ያብቃን።


 

 


Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: