በርግጥ ኢትዮጵያ ሀገራችን ብዙ የተባለላት የፅኑ ሃይማኖት አገር ስትሆን ሕዝቧም በእምነቱ በአምልኮ እግዚአብሔር እጅግ የበረታ ነው።
ማስተዋል ለቻለ የገነት ምድርነቷ ለዛ መዓዛ ሽታ ጣዕም እስከ አሁን ይሰማል። እንስሳት እርባታ ተፈጥሯዊ ባሕል ነውና ባለ ሀገሩ ሕዝብ ለቤተሰቡ የሚሆን የወተት ላም አለው። አገራችን የማዕድናትና የውኃ ሰገነት እንደመሆኗ፡ የዓመት ቀለብ ከሦስት እስከ አራት ወራት በሚሆን ዝናብ ሊመረት ይችላል።
የኢትዮጵያንም ሕዝብ ቀረብ ብሎ በደንብ ለታዘበ የተደላደለ፡
ትዕግስተኛ፡ እንግዳ ተቀባይ ፍፁም፡ የዋሕ ነፃነቱንና ሀገሩን የሚወድ ኃያል ህዝብ ነው። ብሩህ አዕምሮውም አለ፡ ፍፁም መንፈሳዊ ነው። ታዲያ ኢትዮጵያ ይህን ሁል ፀጋ ለመጎናጸፍ በቅታ ሳለ፡ ለምን ይሆን እድሜ ልኳን ሰላም በማጣት፡ በረሃብና ችግር ላይ ልትወድቅ የበቃችው? ለምንስ ይሆን ኢትዮጵያውያን ሀብት ንብረታቸውን ለራሳቸው ሲጠቀሙበት ታይቶ የማይታወቀው? ከነፍስ ማሳደሪያ ይህል ያለፈ ሊጠቀሙበት ፈጽሞ በጭራሽ አልተፈቀደም። በሀብትና በድሎት ብዛት ሕገ እግዚአብሔርን ትተውና ረስተው የቃየንን እንዲሁም የሰዶምና ገሞራን መንገድ እንደተከተሉት ባዕዳን በራሳቸው መብት ስለሌላቸው ነውን? ግብጽ የጊዮን ወንዝን በሚመለከት የኢትዮጵያን ሕዝብ ለዘመናት በትዕቢትና በንቀት እየተመለከተች ፈላጭ ቆራጭ ለመሆን የበቃችው ይህን ማንነታችንን በደንብ አጠንቅቃ ስለምታውቅ ይሆን?
በሌላ በኩል ግን ኢትዮጵያውያን ሞኞች መሆናችንን፡ የያዝነውን ፤ ጥሩም ሆነ መጥፎ ነገር ፤ ቶሎ እንደማንለቅ ዓለም አውቆልናል፡ መጽሐፍ ቅዱስም ይህን ይነግረናል። የዋህነት ጥሩ ነገር ነው፡ ግን ልባችንን በጋሻችን መከላከል ካልቻልን በቀላሉ የጠላት እራት ለመሆን እንበቃለን። የሚገርመው ደግሞ ልባማንታችን ብልጣማነታችንን በአገራችን ሰው ላይ ብቻ እያሳየን መምጣታችን ነው። ያገርን ሰው ማክበሩን ትተናል፡ ላገር ሰው ቅድሚያውን መስጠቱን ረስተናል፡ እርስ በርስ ለመተማመን እየቸገረን መጥቷል። ለባዕዱ እና ባዕዳዊ ለሆኑ ነገሮች ግን እራሳችንን ግልጥ አድርገን ለመቅረብ ደቂቃም አይወስድብንም ። ይህም አሳዛኝ ክስተት ማናልባት ካለማወቅ፡ ከስንፍናና ከመንፈሣዊ ድክመት የሚመነጭ ሊሆን ይችላል። ወንድሞቻችንን እህቶቻችንን ሳናምን፡ ሳናከበርና ሳንወድ እንዴት ባዕዱን ልናምን ልናከብርና ልንወድ እንችላለን? ጠላትን ከራስ አብልጦ እንዲወድ የሚያዝ መንፈሥ ከእግዚአብሔር ሳይሆን ከሰይጣን ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው።
እኛ ኢትዮጵያውያን ሞኞች እንድንባል ካደረጉን ሁኔታዎች አንዱና ዋንኛው ከስህተቶቻችን ወይም ካለፈው ታሪካችን ለመማር ዝግጁ ባለመሆናችን ይመስለኛል። ያለፈው ታሪክ የመጪው ታሪክ መስተዋት ነው እንዲሉ…”እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። [ማቴ.10:16]ይለናል
ኢትዮጵያውያን በሦስቱም ኪዳኖች በሕጉልቦና በሕጉኦሪት እንዲሁም በሕጉወንጌል በምድር ላይ በብቸኝነት የተጓዙ ብቸኛ የሃይማኖት ቅርስ ስለተደረጉ ተገዥነታቸው ለክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ ሆነና ለሥጋውያንም ባርነት ሆነ ለተቃዋሚ መንፈሳውያን የሕሊና ባርነት ቀንበር ሳይንበረከኩ በነጻነትና በድሃነት ከዘመናት መጨረሻ ጫፍ ላይ ደርሰዋል።
የተትረፈረፈ የገነት ልማላሜና የግዮን ወንዝ ከነገባሮቹ የውኃ ሀብት ባለጠግነት ከኢትዮጵያውያን አልፎ ሱዳንን ያህል አገርና ዝናብ ብዙ ጊዜ የሌለባትን የግብጽን በዳም አፈር ደልድሎና አጠጥቶ አለምልሞ ሕዝቦችን አጥግቦ ይኖራል።
በኢትዮጵያ ስለሚገኝ ሀብት ንብረት በዐረቦች ቀደም ብሎ የታወቀ ቢሆንም በቀሪው ዓለም ግን አውሮፓውያን ወደ ሀገሪቱ መግባት እስከጀመሩበት እስከ 15ኛው መቶ ዓመት መጀመሪያ ድረስ የታወቀ አይደለም። ኢትዮጵያውያን ስለመንፈሳዊ ሕይወት እንጂ ስለ ሀብት ንብረት የማድነቅና የመጻፍ የላቸውም። ስለመንፈሳዊ ስጦታቸውም ቢሆን እንደ ግብጻውያንና ዐረቦች የማዳነቅ የይስሙልኝ የይወቁልኝ ባሕል ስላልተሰጣቸው በኢትዮጵያ ከሚሆነው ሁሉ አንጻር ሲታይ ምንም ያህል አልጻፉም አላወሩም ማለት ይቻላል።
ዐረቦች ከጥንት ጀምሮ እስከ አፄ ኃይለሥላሴ ድረስ የሚሰደዱባትን እንደአገራቸው የሚኖርባትን እንግዳ ተቀባይ ኢትዮጵያን ስለሚያውቋት፡ በቱርክ የእስልምና የበላይነት ግራኝ አሕመድ በዘመኑ በኢትዮጵያ ባልታወቀ ጠብመንጃ መድፍ አስታጥቀው በማስነሳት ለጦርነትና ለዝርፊያው ከቱርክ እስከ የመን ከፋርስ እስከ ሞሮኮ (መቅረብ) ተሳትፈውበታል። በዓለም ላይ ገናና ለነበረችው ኦቶማን ቱርክ ከኢትዮጵያ ይጫንላት የነበረው ዘረፋ በተለይ ወርቁ በእጅግ እንደጠቀማት ይነገራል። የኢትዮጵያ ሀብት፡ ማሩና ወተቱ፡ ወርቁና ዕንቁው፡ ስንዴውና ወርቁ፡ ወንዙና አፈሩ ለኢትዮጵያውያን ምንም ጠቅሞ አያውቅም።
በአሁኑ ትውልድ ደግሞ፡ የአገራችን ታሪካዊ ጠላቶች የሆኑት ግብጾች፡ አረቦችና ቱርኮች በምጣኔ ኃብት ሰብብ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ የተፈጥሮ ኃብቶቿን ለመቆጣጠር፡ ብሎም ሕዝቦቿን በመንፈሣዊ ባርነት ለመግዛት ታይቶ በማይታወቅ መልክ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።
በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ የአርመንና የግሪክ ክርስቲያኖችን በመጨፍጨፍ ዝናን ያተረፈችው ቱርክ፡ ባሁኑ ጊዜ ወደ ጥንቱ የእስልምና አኗኗር በመመለስ ባካባቢዋ ብሎም በአውሮፓ፡ በአፍሪቃ የሚገኙትን ክርስቲያኖች እንደገና በመዋጋት ላይ ትገኛለች። ቱርክ በኩርዲስታን በቅርቡ ሊመሠረት ከሚችለው ከአሹር መንግሥት ጋር በመሆን በእየሩሳሌም ላይ ጥቃት አድርሳ ክርስቶስን ለመዋጋት እንድተዘጋጅ ነብያት በትንቢት የተነገሩላት አገር ናት።
እንደሚታወቀው በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጨረሻ በኦሮሞ ሕዝቦች ዘንድ ጂማ፡ ጌራ፡ ጉማ፡ ሊሙ፡ ራያና ጎማ የተሰኙ የእስልምና ማዕከላት ተመሠረቱ። እነዚህ ሁሉ አካባቢዎች ጥንተ ክርስቲያኖች ናቸው። በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያም ከየመንና ከሂጃዝ በሚመጡ የእስላም አስተማሪዎች ተጽዕኖ ሥር ወደቁ። በጎረቤት አገር በሱዳን እስልምናን ለማስፋፋት ሲዳንን የሚገዙትን አንግሎ ሳክሶኖች የማስወጣት ዓላማ የነበረው አንድ የመሐዲስቶች እንቅስቃሴ ነበር። በአንድ በኩል ዐፄ ዮሐንስ በመሐዲስቶች ተከብበው ለነበሩት ግብጾች የመውጫ በር በመስጠታቸው እና በሌላ በኩል ደግሞ ዓፄ ዮሐንስ “በግድ ክርስቲያኖች ሁኑ አሉን” የሚሉ ወደ ሱዳን የኮበለሉ ሙስሊሞች አቤቱታ በማቅረባቸው የመሐዲስቶች ጥላቻ በንጉሡ ላይ ተጠናከረ። በመሆኑም በ1880 ዓ.ም. ጥር 10 ቀን መሐዲስቶች በቱርክ እየተደገፉ እስከ ጎንደር ድረስ ገብተው አያሌ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናትን አቃጠሉ፡ ሕዝቡን አረዱ፡ ቅርሶችን አወደሙ፤ ከዚህም አልፈው ለዐፄ ዮሐንስ ኅልፈት ምክንያት ሆኑ።
ቱርኮች ያለ ጎራዴ እየዘመቱ ነው
የቱርክ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች፡ በተለይ ፋሺንን የተከተሉና የገረጡ ጂንሶችን የሚያመረቱት ፋብሪካዎች ጥንቃቄ የተሞላባቸው የአሠራር ባህል ስለሚጎድላቸው እስከ ትናትናው ዕለት ድረስ 50 የፋብሪካ ሠራተኞች ህይወታቸውን አጥተዋል። የቱርክ የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ እስክ 20.000 የሚጠጉ ሠራተኞችን ባገሪቱ ቀጥሮ ያሠራል፡ ታዲያ የፋብሪካ ሠራተኞቹ ጂንሶችን ለማገርጣት የሚጠቀሙበት እጅግ አደገኛና ጨረራማ አሸዋ በሚያፈነጥቀው አቧራ ጠንቅ ምክንያት በሚቀጥሉት ወራት እስከ 5000 የሚሆኑ ሠራተኞች ሕይወታቸውን እንደሚያጡ ይነገራል።
ከነዚህ የቱርክ የጨረቃጨርቅ ፋብሪካዎች መካከል አንዳንዶቹ በኢትዮጵያም የፋብሪካዎቻቸውን አዳራሾች እየሠሩ ነው። በኢትዮጵያ አገራችን በአሁኑ ወቅት ወደ 40 የሚጠጉ የቱርክ ኩባንያዎች፤ የባሕልና የሃይማኖት ተቋሞች በሰፊው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ። ከትምህርት ቤት እስከ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ድረስ ቱርኮች ነጻ የሆነውን አውቶኖሚ አግኝተው በኢትዮጵያውያን ኑሮ ዘንድ ቸል ሊባል የማይቻል ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ። በቀላሉ ህሊናቸው ሊታጠብ የሚችሉት የዋህ ኢትዮጵያውያን በቱርክ ትምህርት ቤቶች የኢትዮጵያን ሳይሆን የቱርክን ብሔራዊ መዝሙር እንዲዘምሩ በመደረግ ላይ ይገኛሉ። የቱርክ ፋብሪካዎችና የንግድ ተቋማት የሚቀጥሯቸው ሰራተኞች የእስልምና ተከታይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሊሆኑ እንደሚገባቸው በግልጽ ይናገራሉ፡ ክርስቲያኖችም ለምስር ወጥ ሲሉ ሃይማኖታቸውን ከቀየሩ የሥራ ቦታ እንደሚሰጣቸው ቃል እየተገባላቸው ነው። ሴቶች ሠራተኞችም እስላማዊ አለባበስን እንዲያጠብቁ ትዕዛዝ ተላልፎ በሥራ ላይ ውሏል።
ይህን መሰሉ ጉድ በታሪካችን ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅና እጅግ በጣም አሳፋሪ የሆነ ጉድ ነው። ክርስቲያን እህቶቻችን ባሕር ማዶ ተሻግረው ወደ እስላም አገር በመጉረፍ የባርነት ቀንበር ውስጥ ይገባሉ፡ የኢትዮጵያ ዜግነት ያላቸው ሙስሊሞች ግን በክርስቲያኗ ኢትዮጵያ ደመወዝ እየተከፈላቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር አብረው በሰላም ይኖራሉ።
ይህ ሁሉ ጉድ እግዚአብሔር በሰጠን በውዲቷ አገራችን ፡ በታሪካዊ ጠላቶቻችን አማካይነት በኛ ትውልድ በመከሰቱ ደሙ የማይፈላበት ኢትዮጵያዊ ይኖራልን?ለልጆቻችንና፡ ለመጪው ትውልድስ ምን ብለን እናወራ ይሆን? እውነት እኛ ኢትዮጵያውያን ይህን ያህል ሞኞች ነን? ወይስ ሌላ ምስጢር ይኖር ይሆን?
“እናንተ ድሆች ብጹአን ናችሁ፡ የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ነውና።” “እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁአን ናችሁ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁአን ናችሁ፡ ትስቃላችሁና። ሰዎች ሁሉ ስለ ሰው ልጅ ሲጠሏችሁ ሲለዩአችሁ ሲነቅፎአችሁም ስማቸውንም እንደ ክፉ ሲያወጡ ብፁአን ናችሁ። እነሆ፡ በሰማይ ዋጋችሁ ታላቅ ነውና። በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና። ነገር ግን እናንተ ባለጠጎች ወዮላችሁ፡ መጽናናታችሁን ተቀብላችኋልና። እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ፡ ትራባላችሁና። እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ፡ ታዝናላችሁና ታለቅሳላችሁ።” [ሉቃ. 6:20-25] “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁአን ናቸው፡ መንግሥት ሰማያት የነሱ ናትና። የሚያዝኑ ብፁአን ናቸው፡ መጽናናትን ያገኛሉና። የዋሆች ብፁአን ናቸው፡ ምድርን ይወርሳሉና። ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁአን ናቸው፡ ይጠግባሉና።” [ማቴ. 5:3-69]