እነማን ናቸው? Who Are They?
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 22, 2009
የሚከተለውን ታሪክ ዓይነት ተመሳሳይ ነገር የሰማ ወይም ስለነገሩ የሚያውቅ ወገን ይኖራል ብዬ በመገመት፡የሚከተለውን በጣም አስገራሚና ሃቀኛ ታሪክ ሳንሱር ሳላደርገው በደስታ ላንባብያን ላካፍል እወዳለሁ።
ልጅ እያለሁ፡ አንድ በጣም የተከበሩ አዛውንት ዘመዴ (ነፍሳቸውን ይማርላቸው) በብራና ጫር ጫር አድርገው የሳሉትን አንድ ስዕል ሊያሳዩኝ ወደ አንድ ኮረብታ ይዘውኝ ወጡ።
በጊዜው እድሜአቸው ምናልባት ወደ 70 ዓመት ይጠጋ ይሆናል። “ይህን ስዕል የሳልኩት ጣልያን ወደ ኢትዮጵያ ከመግባቷ በፊት ነው” አሉኝ። ይህም ምናልባት በ1930ቹ ዓመታት መሆኑ ነው። ስዕሉ ላይ ተሽከርካሪ መኪና የሚመስል ነገር ይታያል። “ምንድን ነው አባ?” በማለት ጠየቅኳቸው። “ልጄ ይህን ነገር፡ እዚያ የምታየው የጥርጊያ መንገድ ላይ ያለማቋረጥ ሲሽከረከር በማየት ነበር የሳልኩት” አሉኝ፡ መንገዱን ከኮረብታው ጫፍ ላይ ሆነው እያሳዩኝ። “እነዚህን ሰፋፊ ተሽከርካሪዎች የሚያሽከረክሯቸው እዛ ኩባ ሰፈር በሚባለው ቦታ የሚገኙትን አንዳንድ በቁምጥና በሽታ የሚሰቃዩትን ወገኖቻችንን የሚመሳስሉ “ሰዎች” ናቸው። እነዚህን ሰዎች ፊት ለፊት ስለሆነ ያየኋቸው፡ በጣም አጫጭር፡ ወፋፍራም ሆነው ነበር የታዩኝ። ተሽከርካሪው ውስጥ ሁለት ሁለት በመሆን ቁጭ ያሉት “ሰዎች” እንዴት ወደውጭ ማየት እንደሚችሉ በጣም ይገርመኝ ነበር፡ ምክኒያቱም በጣም ድንክየዎች ነበሩና።” አሉኝ
እኔም፡ “ለመሆኑ ስንት ተሽከርካሪዎች ነበሩ? አንዴ ብቻ ነው ወይ ያዩአቸው?” ብየ ስጠይቃቸው፡ “የለም! ልጄ፡፡በተደጋጋሚ ነበር ያየኋቸው። ግር ብለው በብዛት እንደ ሰንሰለት ተከታትለው ይጓዙ ነበር። እርስ በርሳቸው ጮክ እያሉ የሚነጋገሩ ይመስላሉ፡ ለኔ ግን፡ አስደንጋጭ ከሆነው የተሽከርካሪዎቹ ድምጽ ሌላ የሚሰማ ነገር አልነበረም። እነዚህ ሰዎች፡ እዚያ ውስጥ ሆነው በጣም ይቁነጠነጡ ነበር።” አሉኝ።
“ታዲያ እርስዎ ምን ተሰማዎት? ምንስ አደረጉ?” በማለት ጥያቄየን እየተርበተበትኩ ቀጠልኩ። “አይዞህ ልጄ፡ አንተ ጠንካራ ነህ፡ ለዚህ ነው ላንተ ላጫውትህ የወደድኩት፡ በወቅቱ እኔን ምን ተሰምቶኝ እንደነበር ለማውሳት በጣም አዳግቶኝ ነበር። ብቻ በዚያ መንገድ የሚያልፉበትን ወቅት እየጠብቅኩ ቆሜ ከማየት ሌላ ምንም ማድረግ አልቻልኩም፡ ለማንም አልተናገርኩም። ሁሉ ነገራቸው ግን አላስደሰተኝም ነበር፡ እነሱን የመሳሰሉ ሰዎች ልክ ኩባ ሠፈር እንዳሉት ለማየት ስበቃ ትዝ ይሉኛል፡ አሁንም ከፊቴ ድቅን ብለው ይታዩኛል። ንጉሥ ኃይለ ሥላሴ ከዙፋናቸው ሊወርዱ ጥቂት ዓመታት ሲቀራቸው ነበር እነዚህን ተሽከርካሪዎች በዚያው መንገድ ሲጓዙ ለመጨረሻ ጊዜ ያየኋቸው።” አሉኝ።
በጣም የሚደንቀው፡
-
ተሽከርካሪው፡ ልክ በ 2009 ዓ.ም በአሜሪካው የ General Motors ኩባንያ የሚመረተውን ዝነኛውን የ “Hummer” መኪና ዓይነት ይመስል ነበር ብል አላጋንንም
-
እኚህ ዘመዴ ያን ስዕል በሳሉበት ወቅት ተሽከርካሪ መኪና የሚባል ነገር በመንደራቸው አልነበረም፡ ጭራሽም አይተውት አያውቁም ነበር።
ምን ሊሆን ይችላል? እውነት “Reptile” የሚባሉት ደም መጣጭ ፍጥረታት በመኃከላችን ይገኙ ይሆን? ለምን በኢትዮጵያ? የጣሊያን ወረራና የንጉሡ ከዙፋን መውረድ ከዚህ ሁኔታ ጋር ምን የሚያገናኛቸው ነገሮች ይኖሩ ይሆን? ለምንስ በመስከረም ወር?
__________________________________________________________
-
- ይህ ጽሁፍ የረቀቀው በመስከረም ወር 2000 ዓ.ም ላይ ነው። ስዕሉ ላይ የሚታየው ዓይነት የመኪና ካራቫን በአዲሱ የሮላንድ ኤመሪሽ ፊልም „2012“ በተመሳሳይ ሁኔታ ማየት ይቻላል።
__________________________________________________________________
ኢትዮጵያ ተከብባለች – አዎን ከሁሉም አቅጣጫ! « AddisEthiopia Weblog said
[…] ነገሮች ለመከታተል ችሎታውን እያገኙ ነው። ከዚህ ቀደም ይህን ጽሑፍ አቅርቤ ነበር፤ ይህ ቦታ የኢትዮጵያ ምስጢራት ከተደበቁባቸው […]
navdomain said
Hi! This post could not be written any better! Reading through this post reminds me of my good old room mate!
He always kept talking about this. I will forward this article to him.
Fairly certain he will have a good read. Thank you for sharing!