Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2009
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

7 Heavens

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 14, 2009

ሰባቱ ሰማያት ፡ የመጀመሪያው ርእዮተ ዓለማትና ከዋክብት

እግዚአብሔር ከመጀመሪያይቱ ቀን አስቀድሞ በኃይሉ ቅነ ሰማያትን በጥበቡ በዘረጋ ጊዜ የሰማያትን ጠፈር ቀለም በማስተዋል በቀባና በደመደመው ጊዜ በሰማያት ክልል ውስጥ ምንም ፍጥረት አልነበረም።

እግዚአብሔር ከአሥራ ሁለቱ ሰማያት መካከል በመረጣቸውና ብሩሃን ብሩካን ሁኑ ከአላቸው ከሰባቱ ሰማያት ይልቅ በከበረው ግርማው በሚያስፈራው በሰባተኛው ሻዳያ ሰማይ ክበብና ክልል ውስጥ ላይ፡

  1. በአቃጣይነትና በነበልባል የተከበበውንና የእሳት ዓለም የሆነውን ኮሬብን
  2. የረጋና ከባድ የሆነ የአፈር ዓለምን ላሌብዱላሌብን
  3. የጠራ ፈሳሽና በረዶ ያለውን የውኃ ዓለም ናጌብን
  4. ረቂቅ ተንሳፋፊ ቀላል የሆነውን የነፋስ ዓለምን አዜብን

ካለመኖር ወደመኖር አምጥቶ ፈጠራቸው። እነዚህን አራቱን ታላላቅ ዓለሞች በሻዳያ ሰማይ ክልል ውስጥ አኖራቸው።

በእንዚህም ክበብና በውስጣቸው የሚንቀሳቀስና የሚሳብ ወይም የሚበርና የሚንሳፈፍ ሕይወት የአለው ፍጥረት እንዳይኖር አትሞ አፅንቷቸዋል።

የእግዚአብሔር መልእክተኞች መላእክት መናፍስት እንኳ አያልፉም በአካባቢያቸውም አይደርሱም።

እግዚአብሔር ብሩሃን ብሩካን ሁን ባላቸው በሰባቱ ሰማያት ክልል ውስጥ የከበረ ስሙን ለማሳወቅ የጥበቡን ኃይል ለመግለፅ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪና ባለቤት የምስጋና ጌታ መሆኑን ታምኖበት እንዲመሰገን ሲል በሰባቱ ሰማያት ምሳሌ፡

  1. ሦስት ፀሐዮችን
  2. አራት ጨረቃዎችን
  3. አንድ መቶ ዓለማትን
  4. አእላፋተማእለፍታት ከዋክብትን
  5. በሰው ልጆች አንድበት በመላእክትም አፍ ሊቆጠረ የማይቻል ልዩ ልዩ የሆነን ግዙፍና ረቂቅ ፍጥረት
  6. የማይንቀሳቀስን ማእድን
  7. የሚንቀሳቀስ አየራትን

በእግዚአብሔር ቃል ፈጠራቸው። በአፉ እስትንፋስም ሁሉም እንደየወገኑ ደማዊ ነፍስ የሌለው ግን ሕይወት የሚሆን እስትንፋስ እፍ አለባቸው። ተንቀሳቀሱም፡ ገደብ የአለው መኖሪያቸውንና ምግባቸውን የሚመርጡበት የሚይስቡበትም የጸጋ አእምሮ ሰጣቸው። በእግዚአብሔር ቃል የተፈጠሩበት ቀን ልደታቸው ሆነ።

እግዚአብሔር በቃሉ የፈጠራቸው የሦስቱ ፀሐዮች ስሞች የሚከተሉት ናቸው፡

  1. ኦርያ
  2. ያሪስያ
  3. ቶማስያ (እኛ በምንኖርበት ኢዮር ክልል ውስጥ)

እነዚህ ፀሐዮች እግዚአብሔር ለፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ብርሃንነት ከመሆናቸው ሌላ ሙቀታቸው ለአጥንት ኃይል ብርሃናቸው ለአእምሮ ግልጽነት በመሆን የተፈጥሮን ሕይወት ያድሳሉ። እያጠነከሩም እድገትን ይሰጣሉ።

ነገር ግን እኛ ከሦስቱ ፀሐዮች መካከል ቶማስያ የተባለውን ፀሐይ ብቻ እንጂ ኦርያንና ያሪስያን አናይም። ከኢዮር ሰማይ ክልል ውጭ ናቸው።

እንደነዚሁ የአራቱ ጨረቃዎሽ ስሞች የሚከተሉት ናቸው፡

  1. ኢራአያ
  2. ናስያ
  3. አብላያ
  4. አስንያ (እኛ በምንኖርበት ኢዮር ክልል ውስጥ የሚገኘውና በሰው ልጆች የሚታየውና የሚፈተነው)

አስንያ የሚባለው ጨረቃ ከቶማስያ ፀሐይ የሚያገኘውን የብርሃን ጨረር ለዚህች ምድር ያበራል።

ነገር ግን ቶማስያ ለዚህች ምድር በምታበራበት ጊዜ ብርሃኑ ይቀንሳል። የፀሐይን ክበብ በሚያውድበት ጊዜ የሰሌዳው ገጽ ይቀንሳል ምድርም እንዲሁ የምታገኘውን ብርሃን ትቀንሳለች።

እግዚአብሔር በቃሉ ለፈጠራቸው ለሰባቱ ሰማያት ብሩሃን ብሩካን ካላቸው በኍላ መቶ ዓለማትን እስከ ሰራዊቶቻቸው አደላቸው። ለዘለዓልምም በእነርሱ ክበብ ውስጥ እንዲኖሩ አደረግ። ለዓለማትና ለከዋክብትም የራሳቸው እጣ የሆነ ክበብን አዘጋጀላቸው።

መቶ ዓለማት በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥረው ወደ የእድል እጣቸው ወደሆነው ሰማይ እስከሚገቡ በውስጣቸው የሚንቀሳቀስ ፍጥረት አልነበረም። አንዱ ዓለም ከሌላው ዓለም በስፋትና በወርድ በዲካም እንዲበላለጡ አድርጎ ስለፈጠራቸው የተለያዩ ነበሩ።

እንዲሁ አእላፋተማእለፍታት የሆኑ ከዋክብት አንዱ ኮከብ ከሌላው ኮከብ በብርሃን በክብር በስፋትና በወርድ በቁመት በገጽና በቅርፅ ልዩ ልዩ አድርጎ ፈጠራቸው። ዓለማትም ይሁን ከዋክብት አንዱ ከሌላው ጋር እንዳይቀላቀልና እንዳይወሃድ ሲል በመካከላቸው ልዩ ልዩ የሆነ የተፈጥሮ ባህርይ እንዲኖራቸው አደረገ።

እግዚአብሔር ከአምስቱ ሰማያት ይልቅ በሰባቱ ሰማያት ዘንድ ክብሩንና ኃይሉን ቸርነቱንና ጌትነቱን ስሙንም እንዲያውቁትና እንዲያመሰግኑት ሲል ለፍጥረቱ ሁሉ ገደብ የአለው ነጻ አእምሮ ሰጣቸው ራሱንም ገልጾላቸዋል።

እኛም እድል እጣችን ከሆነችው ከዚህች ምድር ዓለም ተፈጥረናልና ሰለአለንበትና ወደፊት ወደ እጣ ክፍላችን ሰማያዊ ዓለም እስከምንሄድ ድረስ ለእግዚአብሔር በሰባቱ ሰማያት ክልልና በመቶ ዓለሞች ክበብ ሰለአለው ክብርና ኃይል ቸርነቱም ምህረቱንም በኪሩብ መልአክ እንድንጽፍ የተነገረንን እንጽፋለን። ከእኛ ጋር ሕብረትና አንድነት ይኖራቸው ዘንድ ከቃላቸው ብዛት የተነሳም መለያየት እንዳይኖር ለልጆቻችን እናስተምራለን።

በእዮር ሰማይ ክልል ውስጥ የአሉት አሥራ ሁለት ዓለሞች

ቀጣይ ነው…

ይህን ጽሑፍ እዚህ አቀርብ ዘንድ ፈቃዳቸውን የሰጡኝን፡ መሪራስ አማን በላይን ከልብ አመሰግናለሁ።



Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: