Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2009
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for December 14th, 2009

7 Heavens

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 14, 2009

ሰባቱ ሰማያት ፡ የመጀመሪያው ርእዮተ ዓለማትና ከዋክብት

እግዚአብሔር ከመጀመሪያይቱ ቀን አስቀድሞ በኃይሉ ቅነ ሰማያትን በጥበቡ በዘረጋ ጊዜ የሰማያትን ጠፈር ቀለም በማስተዋል በቀባና በደመደመው ጊዜ በሰማያት ክልል ውስጥ ምንም ፍጥረት አልነበረም።

እግዚአብሔር ከአሥራ ሁለቱ ሰማያት መካከል በመረጣቸውና ብሩሃን ብሩካን ሁኑ ከአላቸው ከሰባቱ ሰማያት ይልቅ በከበረው ግርማው በሚያስፈራው በሰባተኛው ሻዳያ ሰማይ ክበብና ክልል ውስጥ ላይ፡

  1. በአቃጣይነትና በነበልባል የተከበበውንና የእሳት ዓለም የሆነውን ኮሬብን
  2. የረጋና ከባድ የሆነ የአፈር ዓለምን ላሌብዱላሌብን
  3. የጠራ ፈሳሽና በረዶ ያለውን የውኃ ዓለም ናጌብን
  4. ረቂቅ ተንሳፋፊ ቀላል የሆነውን የነፋስ ዓለምን አዜብን

ካለመኖር ወደመኖር አምጥቶ ፈጠራቸው። እነዚህን አራቱን ታላላቅ ዓለሞች በሻዳያ ሰማይ ክልል ውስጥ አኖራቸው።

በእንዚህም ክበብና በውስጣቸው የሚንቀሳቀስና የሚሳብ ወይም የሚበርና የሚንሳፈፍ ሕይወት የአለው ፍጥረት እንዳይኖር አትሞ አፅንቷቸዋል።

የእግዚአብሔር መልእክተኞች መላእክት መናፍስት እንኳ አያልፉም በአካባቢያቸውም አይደርሱም።

እግዚአብሔር ብሩሃን ብሩካን ሁን ባላቸው በሰባቱ ሰማያት ክልል ውስጥ የከበረ ስሙን ለማሳወቅ የጥበቡን ኃይል ለመግለፅ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪና ባለቤት የምስጋና ጌታ መሆኑን ታምኖበት እንዲመሰገን ሲል በሰባቱ ሰማያት ምሳሌ፡

  1. ሦስት ፀሐዮችን
  2. አራት ጨረቃዎችን
  3. አንድ መቶ ዓለማትን
  4. አእላፋተማእለፍታት ከዋክብትን
  5. በሰው ልጆች አንድበት በመላእክትም አፍ ሊቆጠረ የማይቻል ልዩ ልዩ የሆነን ግዙፍና ረቂቅ ፍጥረት
  6. የማይንቀሳቀስን ማእድን
  7. የሚንቀሳቀስ አየራትን

በእግዚአብሔር ቃል ፈጠራቸው። በአፉ እስትንፋስም ሁሉም እንደየወገኑ ደማዊ ነፍስ የሌለው ግን ሕይወት የሚሆን እስትንፋስ እፍ አለባቸው። ተንቀሳቀሱም፡ ገደብ የአለው መኖሪያቸውንና ምግባቸውን የሚመርጡበት የሚይስቡበትም የጸጋ አእምሮ ሰጣቸው። በእግዚአብሔር ቃል የተፈጠሩበት ቀን ልደታቸው ሆነ።

እግዚአብሔር በቃሉ የፈጠራቸው የሦስቱ ፀሐዮች ስሞች የሚከተሉት ናቸው፡

  1. ኦርያ
  2. ያሪስያ
  3. ቶማስያ (እኛ በምንኖርበት ኢዮር ክልል ውስጥ)

እነዚህ ፀሐዮች እግዚአብሔር ለፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ብርሃንነት ከመሆናቸው ሌላ ሙቀታቸው ለአጥንት ኃይል ብርሃናቸው ለአእምሮ ግልጽነት በመሆን የተፈጥሮን ሕይወት ያድሳሉ። እያጠነከሩም እድገትን ይሰጣሉ።

ነገር ግን እኛ ከሦስቱ ፀሐዮች መካከል ቶማስያ የተባለውን ፀሐይ ብቻ እንጂ ኦርያንና ያሪስያን አናይም። ከኢዮር ሰማይ ክልል ውጭ ናቸው።

እንደነዚሁ የአራቱ ጨረቃዎሽ ስሞች የሚከተሉት ናቸው፡

  1. ኢራአያ
  2. ናስያ
  3. አብላያ
  4. አስንያ (እኛ በምንኖርበት ኢዮር ክልል ውስጥ የሚገኘውና በሰው ልጆች የሚታየውና የሚፈተነው)

አስንያ የሚባለው ጨረቃ ከቶማስያ ፀሐይ የሚያገኘውን የብርሃን ጨረር ለዚህች ምድር ያበራል።

ነገር ግን ቶማስያ ለዚህች ምድር በምታበራበት ጊዜ ብርሃኑ ይቀንሳል። የፀሐይን ክበብ በሚያውድበት ጊዜ የሰሌዳው ገጽ ይቀንሳል ምድርም እንዲሁ የምታገኘውን ብርሃን ትቀንሳለች።

እግዚአብሔር በቃሉ ለፈጠራቸው ለሰባቱ ሰማያት ብሩሃን ብሩካን ካላቸው በኍላ መቶ ዓለማትን እስከ ሰራዊቶቻቸው አደላቸው። ለዘለዓልምም በእነርሱ ክበብ ውስጥ እንዲኖሩ አደረግ። ለዓለማትና ለከዋክብትም የራሳቸው እጣ የሆነ ክበብን አዘጋጀላቸው።

መቶ ዓለማት በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥረው ወደ የእድል እጣቸው ወደሆነው ሰማይ እስከሚገቡ በውስጣቸው የሚንቀሳቀስ ፍጥረት አልነበረም። አንዱ ዓለም ከሌላው ዓለም በስፋትና በወርድ በዲካም እንዲበላለጡ አድርጎ ስለፈጠራቸው የተለያዩ ነበሩ።

እንዲሁ አእላፋተማእለፍታት የሆኑ ከዋክብት አንዱ ኮከብ ከሌላው ኮከብ በብርሃን በክብር በስፋትና በወርድ በቁመት በገጽና በቅርፅ ልዩ ልዩ አድርጎ ፈጠራቸው። ዓለማትም ይሁን ከዋክብት አንዱ ከሌላው ጋር እንዳይቀላቀልና እንዳይወሃድ ሲል በመካከላቸው ልዩ ልዩ የሆነ የተፈጥሮ ባህርይ እንዲኖራቸው አደረገ።

እግዚአብሔር ከአምስቱ ሰማያት ይልቅ በሰባቱ ሰማያት ዘንድ ክብሩንና ኃይሉን ቸርነቱንና ጌትነቱን ስሙንም እንዲያውቁትና እንዲያመሰግኑት ሲል ለፍጥረቱ ሁሉ ገደብ የአለው ነጻ አእምሮ ሰጣቸው ራሱንም ገልጾላቸዋል።

እኛም እድል እጣችን ከሆነችው ከዚህች ምድር ዓለም ተፈጥረናልና ሰለአለንበትና ወደፊት ወደ እጣ ክፍላችን ሰማያዊ ዓለም እስከምንሄድ ድረስ ለእግዚአብሔር በሰባቱ ሰማያት ክልልና በመቶ ዓለሞች ክበብ ሰለአለው ክብርና ኃይል ቸርነቱም ምህረቱንም በኪሩብ መልአክ እንድንጽፍ የተነገረንን እንጽፋለን። ከእኛ ጋር ሕብረትና አንድነት ይኖራቸው ዘንድ ከቃላቸው ብዛት የተነሳም መለያየት እንዳይኖር ለልጆቻችን እናስተምራለን።

በእዮር ሰማይ ክልል ውስጥ የአሉት አሥራ ሁለት ዓለሞች

ቀጣይ ነው…

ይህን ጽሑፍ እዚህ አቀርብ ዘንድ ፈቃዳቸውን የሰጡኝን፡ መሪራስ አማን በላይን ከልብ አመሰግናለሁ።



Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

Ethiopia Conspiracy

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 14, 2009

ኢትዮጵያ ተከባለች

አውሬው ተለቅቋል፡ አውሬው ከግራ ከቅኝ፡ ከላይ ከታች፡ ከውጭ ከውስጥ እያለ ይፈታተነናል። አውሬው በተከታዮቹ አማካይነት ምድረ ሞርያን እና ምድረ ኢትዮጵያን ለመዉረር ዳር ዳር ይላል። የኢትዮጵያ አምላክ ግን እንደተለመደው በኢትዮጵያ ተራሮች ላይ በሠፈረው መንፈሳዊ ሠራዊቱ አማካይነት በዝምታ ይከታተላቸዋል።

ከየመን እስከ ሶማሊያ ከባህረ ገሊላ እስከ ቪክቶሪያ ሃይቅ ድረስ የአውሬው ሠራዊት እየቀበረ ያለውን ወጥመድ የኢትዮጵያ አምላክ ፎቶ በማንሳት ላይ ይገኛል።

የአውሬው አገልጋዮች፡ ሸህ ቢን ላድንን ወደ ሶማሊያ ሃጂ አልሳርካዊንን ደግሞ ወደ ጋዛ ለማሸጋገር ዝግጁ ይመስላሉ፡ እስካሁን ካልተሸጋገሩ።

ሊያውቁትና ሊቀበሉት ያልፈለጉት የእስራኤል አምላክ ቅዱስ መንፈስ በምድረ ኢትዮጵያ እንደሚገኝ ደርሰውበታል። ኢትዮጵያን ሊደፍሩ ይፈልጋሉ፡ ግን እስካሁን አልተቻላቸውም፡ ስለዚህ፡ በአውሬው ዓይን ከኢትዮጵያ ጋር በብዙ ነገሮች ተመሳሳይነትን በምታሳየው፡ ነገር ግን የቅዱሱ መንፈስ ተቃራኒ መንፈስ በተንሰራፋባትና የኢትዮጵያ ጆግራፊያዊ የመስተዋት ግልባጭ በሆነችው በአፍጋኒስታን አስፈላጊ ያልሆነ ትኩረት በማድረግ ከፍተኛ መስዋእትን በመክፈል ላይ ይገኛሉ።

በአሜሪካ ግዛቶች ብዙ ጥፋት የሚያስከትሉት አውሎ ንፋሶች መነሻ የኢትዮጵያ ተራሮች መሆናቸውን መመልከት የቻለው የጠፈር መርማሪው አሜሪካዊ ድርጅት፡ “NASA” ለኢትዮጵያ መንግስት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደሚከፍል ይታወቃል። የሚገርመውና ብዙዎቻችንን ምናልባት ሊይስደነግጥ የሚችለው ነገር፡ በመስከረም ፩፩ ፪ ሺ ፩ ዓ.. ሽብርተኞች በኒውዮርክ ከተማ ላይ ጥቃት ባደረጉበት በአዲሱ አመታችን መግቢያ እለት፡ “ISS” በመባል የሚታወቀው ዓለም አቀፋዊው የህዋ መመርመሪያ ጣቢያ፡ የኦርቢታዊ ቦታ አቅጣጫው፡ (Orbital Position) ልክ አፍሪቃ ቀንድ ላይ ማረፍ እንደነበረበት፡ ነገር ግን ፕላኑ በጊዜው በስራ ላይ እንዳልዋለ ጭምጭምታዎች መሰማታቸው ነው። ምስጢሩ ምን ይሆን?

ከክትባት እንቆጠብ

..አ በ August 1, 1989.. “The Sun” ተብሎ የሚታወቀው ታዋቂ የእንግሊዝ አገር የመንገድ ወሬ አሳዳጅ ጋዜጣ፡ “Big Brother’s Coming!” በሚል ርዕስ፡ በላብራቶሪ ውስጥ የተፈጠረ የአሳማ ጉንፋን ኤፒደሚ ገብቷል ይባልና የክትባት ዘመቻ ይካሄዳል ፣ ክትባቱ የሚያስፈልግበትም ምክኒያት በዚህ ሰበብ ህዝቡን ሁሉ በጸረክርስቶሱ የአውሬው መርዝ ለመንደፍ በማሰብ ነው የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር።

ጋዜጣው ገና ከ 20 ዓመታት በፊት እንዲህ የሚል ነገር በገጾቹ ላይ አስፍሮ ነበር፡

Coded microchips implanted in every person in the country would tie all of us into a master computer that could track anyone down at any moment, and plans for such a system are already under way whether you like it or not!”

ይቀጥልና

The tiny transmitters can be injected painlessly from a tiny gun in humans without them even knowing it through a nationwide vaccination program.”

በመጨረሻም፡

All the government would have to do is make up something like the swine flu vaccine.”

በማለት ጽፎ ነበር።

እነዚህ የዲያብሎስ አገልጋዮች፡ እንዲህ የመሳሰሉትን ሴራዎች ገና ጥንት ነው ሲጠነስሱ የቆዩት። እግዚአብሔር ይይላቸው፡ እግዚአብሔር ከተንኮላቸው ሁሉ ይጠብቀን።

ባካችሁ እኛ አንተነኳኮል፡ አንድከም፡ በመጨቃጨቅ በመሰዳደብ አውሬውን አንመግብ። እንቀራረብ፡ እንሰባሰብ፡ እንተሳሰብ፡ እንተባበር፡ እንፈቃቀር፡። በኋላ አቅሙም ጊዜውም ስለማይኖረን እንዳይዘገይብን።

http://www.mediafire.com/?mnhltmmyzqn

______________________________________


Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , | 2 Comments »

 
%d bloggers like this: