Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • September 2009
  M T W T F S S
   123456
  78910111213
  14151617181920
  21222324252627
  282930  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Thank God It’s Not 666!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 6, 2009

HaileKennySeleshi

ኢትዮጵያ አገራችን እንደ ቀነኒሳ የመሳሰሉትን ድንቅ ሯጭ ስፖርተኞች በማፍለቋ ምን ያህል የታደልን ነን!

ባለፈው ወር በተገባደደው የዓለም አትሌቲክስ አሸናፊነት ላይ በስፖርት ዓይነቱ ታሪክ አንድ አትሌት የ 5 እና 10 ኪሎሜትሮች ርቀትን ለመጀመሪያ ጊዜ ለማሸነፍ በቅቷል። ባለፈው ዓርብ እለት ደግሞ፡ ጎልደን ሊግየሚል መጠሪ የያዘውን ዓመታዊ ውድድር በ6 የዓለም ከተሞች እየተዘዋወረ ለ6ኛ ጊዜ ድሉን ተቀዳጅቷል።

ቀነኒሳ እነዚህን አስቸጋሪ የርቀት ውድድሮች በሚያስደንቅ መልክ ለማሸነፍ ሲበቃ ያልተደሰተ፡ ያላደነቀ የስፖርት አፍቃሪ አልነበረም። ከጀርመን፡ እስከ ጃፓን፡ ከሰዋዚላንድ እስከ ስዊትዘርላንድ፡ ከኮሎምቢያ እስከ ካምፖዲያ፡ ቀነኒሳን እያሞገሰ ያልጻፈ ጋዜጣ የለም።

ምንም እንኳን የምዕራቡ የዜና ማሰራጫዎች ተቀዳሚ ትኩረት ለምእራባዊው ድንቅ ሯጭ ለ ጃማያካዊው ኡሴን ቦልት ቢሰጡም፡ በይበልጥ ሊደነቅ የሚገባው የአትሌቲክስ ስፖርት ጀግና ግን ቀነኒሳ እንደሆነ ባለሙያዎች ሁሉ ይናገራሉ።

ታላቁ ቀነኒሳ በቀለ፡ የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ጸጋ፡ ምን ያህል ብርቱ፡ ጽኑና ተወዳዳሪ የማይገኝለት ልዩ ጸጋ እንደሆነ ሊያረጋግጥልን ችሏል። አንዳንድ ሰዎች የቀኒንሳን ሆነ የኡሴን ቦልትን ተፈጥሮአዊ ጸጋ ከ ዶፒንግ ጋር በማያያዝ፡ ችሎታቸውን ለማጣጣል ይሞክራሉ። እነዚህ ወገኖች ግን በቅናት የተወጠሩ ደካሞች፡ ልፍስፍሶች መሆናቸውን ነው እንጂ የሚያሳዩት የሯጮቻችንን ሞራል ሊነኩ እንደማይችሉ ይታወቃል።

በተለይ በህክምና ሳይንስ ጥበባቸው የሚመኩት ተመራማሪዎች ተፈጥሮን ለማሸነፍ በሚያካሂዱት ትግል ላይ እንቅፋት ሲገጥማቸው፡ ብዙ ያልሆነ ተልካሻ ነገር ለመቀባጥር ይቸኩላሉ።

ድኃ ከሆኑት ኢትዮጵያን፡ ኬኒያን፡ ደቡብ አፍሪቃን ወይም ጃማይካን ከመሳሰሉት አገሮች የሚመጡት ድንግል የተፈጥሮ ጸጋዎቾ፡ በሰው ሰራሽ ጥበብ የተካኑትን የስፖርት ሮቦቶች ሲቀጡ ለማየት አሻፈረኝ የሚሉ ሰዎች በተለይ ባሁኑ ጊዜ በጣም እየበዙ መጥተዋል። እነ ቀነኒሳ፡ እነ ጥሩነሽ፡ ኃብታም በሆኑ አገሮች የሚገኙትን የስፖርት ተቋሞችና የስፖርቱ አፍቃሪዎች ዓይን መከንከን ከጀመሩ ውለው አድረዋል።

ብልጥ የሆኑት የአውሮፓ ሯጮች እስከ ኢትዮጵያና ኬኒያ ተራራዎች ድረስ በመጓዝና ልክ እንደ አፍሪቃውያኑ ሆነው ልምምዳቸውን በማካሄድ ጥሩ ውጤት ለማምጣት ሲሞክሩ ቆይተዋል። ይህ መንገድ ሳይሳካላቸው ሲቀር ደግሞ ባቋራጭ ወደ ላብራቶሪ ተመራማሪዎቹ ቤት በመሄድና በተራቀቁ የኬሚካል ጭማቂዎች እራሳቸውን በሞሙላት ሯጮቻችንን ለመቅጣት ሲወራጩ ታይተዋል።

ይህ በእንዲህ ሆኖ፡ በርግጥ፡ የአፍሪቃውያንን ተፈጥሮአዊ ጸጋ እንደ መላው የሰው ልጆች ጸጋ፡ እንደራሳቸው ድል አድርገው በመውሰድ ከእኛ ጋር አብረው የሚደስቱ አውሮፓውያን፡ እስያውያንና አሜሪካውያን ብዙ ናቸው።

ሆኖም ግን፡ በእስፖርት ዓለም ለረጅም ጊዜ የበላይነቱን ይዛ የቆየችውና፡ የስፖርት ንግሥት በመባል የምትታወቀው አትሌቲክስባለፉት 20 ዓመታት ጥቁር የቆዳ ቀለም ባላቸው ስፖርተኞች ግዛት ሥር ለመውደቅ በቅታለች። ታዲያ፤ ይህ ሁኔታ ሌሎች ሕዝቦችን፡ በተለይ አትሌቲክስ አፍቃሪ የሆኑትን አውሮፓውያንን ቀስ በቀስ የበታቸኝነት ስሜት ውስጥ እንዲገቡ ስላደረጋቸው፡ የአትሌቲክስ ስፖርት በተመልካቾች ዘንድ የነበረው ተወዳጅነት በጣም እየቀነሰ መጥቷል። ይህን አሉታዊ ዝንባሌ የታዘቡት የስፖርት ባለሙያዎችና የዜና ማስራጫዎች የአትሌቲክስን ንግሥታዊ ዙፋን በይበልጥ ዝቅ ለማድረግ የሚከተሉትን ስልቶች ለመጠቀም እየሞከሩ ነው፦

 • የአትሌቲክስ ስፖርት ዋና ዋና በሆኑት የዜና ማሰራጫዎች ቅድሚያ የሆነ ቦታ እንዳይሰጠው ማድረግ። ለምሳሌ እንደ ጎልደን ሊግየመሳሰሉትን የአትሌቲክስ ውድድሮች ለተመልካች በቴሌቪዥን የማቅረብ መብቱን የሚወስዱት የኬብል ቴሌቪዥን ባለቤቶች ስለሆኑ፡ ለሰፊው ተመልካች ውድድሮቹን በቀላሉ አቅርቦ ለማሳየት አይቻልም።

 • ለ ዶፒንግ ትኩረት በመስጠት፡ ውጤታማ የሆኑትን ስፖርተኞች አድናቆት እንዳያተርፉ መፈታተን፡ ብሎም መላው የአትሌቲክስ ዓለም ለጥርጣሬ እንዲበቃ ማድረግ። ለምሳሌ፡ ይህ አሁን ተካሂዶ የነበረው አሸናፊነት ከመጀመሩ ጥቂት ቀናት አስቀድሞ፡ አፍሪቃውያን በቂ የሆነ የላብራቶሪ መሣሪያ ስለሌላቸው ተገቢውን የዶፒንግ ምርምራ ሳያደርጉ ነው ወደ በርሊን የመጡት” “የእነ ቀነኒሳና፡ ኃይሌ ገብረ ሥላሴ ማናጃር የሆኑት ሆላንዳዊው፡ በዶፒንግ ሤራ ተጠርጥረዋልበማለት ጸረአፍሪቃ የሆነውን ቅስቀሳቸውን ሲያካሂዱ ነበር። በተጨማሪ፡ የደቡብ አፍሪቃዋን የ 800 ሜትር ርቀት ሯጭ ካስተር ሴሜያንጾታ የወንድ ጾታ ሊሆን እንደሚችል ቅሌታማ በሆነ መንገድ በይፋ በመነዘዝ አሳፋሪ የሆነ ድርጊት እየተፈጸመ ነበር።

 • የስቴዲየም መግቢያ ዋጋን በማናር ተመልካች ከስቴዲየሞች እንዲርቅ ማድረግ። ለምሳሌ፡ ምንም እንኳን አንጋፋው የበርሊን ስቲዲየም አልፎ አልፎ ብዙ ተመልካቾችን ይዞ ቢታየም (በተለይ የጀርመን ስፖርተኞች የማሸነፍ እድል ካላቸው)ሶስት አባላት ያሉት አንድ ቤተሰብ ለመግቢያ ትኬት ብቻ እስከ 200ዩሮ ድረስ መድማት አለበት። ሆኖም አብዛኛው የአትሌቲክስ አሸናፊነት፡ በተለይ በደቡብ አውሮፓ፡ በእስያና በአሜሪካ፡ ባዶ ስታዲየም ውስጥ ነው የሚካሄደው። ባዶ የሆነ ስቴዲየም ደግሞ ለቴሌቪዥን ተመልካች እንደ እንቅልፍ ኪኒን ነው፡ ድብርትንና ማዛጋትን ብቻ ስለሚያመጣ ቴሌቪዥን ይጠፋል። ተመልካች ያጣ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ደግሞ፡ የማስታወቂያ ገንዘብ ለማግኘት ስለማይችል የስፖርቱ ተወዳጅነት እየመነመነ ይመጣል። ለዚህ ጥሩ ማስረጃ፡ በቅርቡ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፡ በየዓመቱ ሲካሄድ የነበረውን አገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር፡ በሁለት ዓመት አንድ ጊዜ ለማድረግ መወሰኑ ነው።

  እነዚህን የመሳሰሉት ድርጊቶች በ21 ክፍለ ዘመን ዓይን ባወጣ መልክ ሲፈጸሙ መታየታቸው፡ የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ነው። ኢትዮጵያውያን አፍሪቃዊው ሆነ፡ አውሮፓዊው፡ እስያዊው ሆነ አሜሪካዊው፡ በፈለገው የስፖርት ዓይነት፡ ልዩ የሆኑ ስፖርታዊ ውጤቶችን ሲያመጡ ልክ እንደራሱ ስፖርተኛ አድርጎ አብሮ ይደሰታል። እንደ ቀነኒሳ ያሉ ኢትዮጵያውያን ግን የአሸናፊዎችን ደረጃ ለመያዝ ሲበቁ፡ የተቀረው ዓለም፡ ሳይወድ በግድ አድናቆትን ያተርፋል እንጂ፡ በአትሌቶቻችን ድል ከ እኛ ጋር አብሮ አይደሰትም። እንኳን አውሮፓዊውና አሜሪካዊው፡ ሌላው አፍሪቃዊም ቢሆን በኢትዮጵያውያኖች ድል እስካሁን የሚደሰት የስፖርት አፍቃሪአላጋጠመኝም።

  ይህ በቅናት ላይ የተመረኮዘው ኢእስፖርታዊ ባሕርይ መወገድ ይኖርበታል። የሚመለከታቸው ወገኖችም ይህን አድሏዊ መንፈሥ ቢዋጉ በይበልጥ እራሳቸውን ነው ሊጠቅሙ የሚችሉት።

   

   

  እኛ መሮጡን እንቀጥላለን!

_________________________


One Response to “Thank God It’s Not 666!”

 1. biniam said

  this is unbeliveable

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: