Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • February 2009
  M T W T F S S
   1
  2345678
  9101112131415
  16171819202122
  232425262728  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Archive for February 1st, 2009

The Third Temple — Cause For The 3rd World War?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 1, 2009

 

 

 

 

ምድረ ሞሪያ

 

በሀገረ እስራኤል በከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ ሥር ከሚገኙት ቅዱሳት መካናት አንዱ፦ የሞሪያ ምድር ነው። ጥንት የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ታንጾበት የነበረ ሲሆን ዛሬ ግን ሁለት የእስላም መስጊዶች ቆመውበታል። ቦታው በአይሁድም ሆነ በእስላሞች ዘንድ ልዩ ትኩረት የተሰጠው ነው። በአይሁድ ዘንድ ይህ ቦታ የመሠረት ድንጋይ የተጣለበት፡ አብርሃም ልጁ ይስሐቅን ለመስዋዕትነት ያቀረበበት፡ ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ያነጸበት፡ ባጠቃላይ የእምነታቸው የመሠረት ድንጋይ የተጣለበት መሆኑ ሲታመን፡ በእስላሞች ዘንድ ደግሞ ነብያቸው መሐመድ በሌሊት ተጉዞ ወደ ሰማይ ተነጥቆ የተመለሰበት ቦታ ነው ተብሎ ስለሚታመን ከመካና ከመዲና ቀጥሎ ሦስተኛው ቅዱስ ቦታቸው መሆኑን አበክረው ይናገራሉ።

 

ምድረ ሞሪያ ለሦስተኛው የዓለም ጦርነት መንሥዔ ይሆናል ተብሎ በብዙዎች ዘንድ ግምት የተሰጠው ቁልፍ ቦታ ነው። የጥንት ባለይዞታዎች እንደሆኑ በሚያምኑና የይገባኛል ጥያቄ በሚያቀርቡት አጥባቂ አይሁዶችና በአሁን ጊዜ ቦታውን በይዞታነት ይዘው ባሉት በእስላሞች ዘንድ ፍጥጫ ያለ ሲሆን፡ የአይሁድ አጥባቂዎች በቦታው ላይ ሦስተኛው ቤተ መቅደሳቸው መሠራቱ የግድ ነው የሚል አቋም ስላላቸው በቦታው ላይ የታነጹትን መስጊዶች ለማጥፋት አልመው ሳይሳካላቸው በእስራኤል የጸጥታ አስከባሪዎች ቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

 

140,000 / አንድ መቶ ዐርባ ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት እንዳለው የሚነገርለት ይህ አወዛጋቢ ቦታ በእስላሞች ይዞታ ሥር ያለ ሲሆን በስተቀኝ በደቡብ በኩል ኤል አቅሳ” (El Aqsa Mosque) የሚባለው መስጊድ፡ እንዲሁም በጥንቱ የሰሎሞን ቤተ መቅደስ መሠረት ላይ እንደታነጸ የሚነገርለት የዑመር ከሊፋ መስጊድወይም የድንጋይ ጉልላት (Dom of the Rock) በላዩ ላይ ታንጸው ከኢየሩሳሌም በአንጻር ባለው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ቆሞ የደሮዋን ኢየሩሳሌም ለሚቃኝ ሁሉ ከሁሉም ነገር ጎልተው ይታያሉ።

 

የክርስትና፡ የእስልምናና የአይሁድ እምነት ተከታዮች ሁሉ የዚህን ቦታ ቅድስና አምነው የተቀበሉት ሲሆን በአጥባቂ አይሁዶች ዘንድ ሦስተኛው ቤተ መቅደስ ከዚህ ቦታ ውጭ በሌላ በየትም ቦታ አይሠራም የሚል አቋም በመኖሩ ቦታው፦ የውጥረትና የሥጋት ቦታ ሆኗል።

 

የቦታው ጥንተ ታሪክ

 

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚመሰገንበት ቤተ መቅደስ እንዲሠሩለት እስራኤልን ባዘዛቸው መሠረት ወደ ተስፋ ሀገራቸው ለመግባት በጉዞ ላይ ሳሉ በሲና በረሐ ለእግዚአብሔር ታቦት ማደሪያ የሚሆን ድንኳን ካሰፈራቸው ራቅ አድርገው ተከሉ። ይኸውም የመገናኛ ድንኳን የተባለው የመጀመሪያው ቤተ መቅደስ ነው። እግዚአብሔርን የፈለገ ሁሉ ከሰፈር ውጭ ወዳለው ወደ መገናኛው ድንኳን በመውጣት ከእግዚአብሔር ጋር ይገናኝ ነበር። በድንኳኑም ደጃፍ ይቆም ነበር። እግዚአብሔርም ሙሴን ይናገረው ነበር። ሕዝቡም ሁሉ ተነሥቶ እያንዳንዱ በድንኳኑ ደጃፍ ይሰግድ ነበር።

 

ከሙሴ ሞት በኋላ እስራኤልን የመምራቱ ኃላፊነት የወደቀው በነዌ ልጅ በኢያሱ ትከሻ ላይ ስለነበር ኢያሱ እስራኤልን እየመራ ወደ ተስፋይቱ ምድር በገቡ ጊዜ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ማደሪያ የሆነው ድንኳን በሴሎ ተተከለ። በካህኑ በዔሊ ዘመን እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን ጋር ባደረጉት ፍልሚያ አራት ሺህ የሚያህሉ የእስራኤል ሠራዊት ስለተገደለ ዛሬ እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ፊት ስለምን መታን በመካከላችን እንዲሄድ ከጠላቶቻችንም እጅ እንዲያድነን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከሴሎ እናምጣበማለት ታቦተ ጽዮንን ይዘው ቢዘምቱም እግዚአብሔር አዝኖባቸዋልና ድል ሆኑ የእግዚአብሔርም ታቦት በፍልስጥኤማውያን ተማረከች።

 

ለሰባት ወራት በፍልስጥኤማውያን መንደር በምርኮ የቆየችው ታቦተ ጽዮን በፍልስጥኤማውያን ላይ መቅሰፍት በማምጣትዋ የፍልስጤማውያን ሽማግሌዎች መክረው እንደ ካሳ ይሆን ዘንድ ከአምስት የወርቅ እባጮችና ከአምስት የወርቅ አይጦች ጋር አድርገው በሁለት ላሞች በሚጎተት ሠረገላ ታቦተ ጽዮንን ጭነው ወደ እስራኤል መንደር ሰደዱአት። ታቦተ ጽዮንን የያዘው ሠረገላ በቤት ሳሚሳዊው በኢያሱ እርሻ በነበረ አንድ ትልቅ ድንጋይ ላይ ቆመ። የቤት ሳሚስ ሰዎችም ሳይገባቸው ወደ እግዚአብሔር ታቦት በድፍረት ቀርበው ወደ ውስጥ በማየታቸው እግዚአብሔር በመቅሰፍት መታቸው። በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መቅሰፍት ይከለክልላቸው ዘንድ በቂርያት ይዓሪም ወደ ተቀመጡት ሰዎች መልእክተኛ ልከው ፍልስጥኤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት መመለሳቸውንና መጥተውም እንዲወስዱ ነገሩአቸው። የቂርያት ይዓሪም ሰዎች መጥተው የእግዚአብሔርን ታቦት አወጡ። በኮረብታውም ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አገቡት፤፡ ለሃያ ዓመት ያህል የአሚናዳብ ቤት የእግዚአብሔር ታቦት ማደሪያ ቤተ መቅደስ ሆኖ ቆየ።

 

ቅድመ ልደተ ክርስቶስ አንድ ሺህ ዘመን ቀደም ብሎ የእሴይ ልጅ ዳዊት በእስራኤል ላይ በነገሠ ጊዜ የእግዚአብሔርን ታቦት ከአሚናዳብ ቤት አስመጥቶ በጌት ሰው በአቢደራ ቤት ለሦስት ወር ያህል ተቀመጠ። እግዚአብሔርም አቢደራንና ቤቱን ሁሉ ባረከ። ዳዊትም እግዚአብሔር የአቢደራን ቤት ቢበረከት እንደሞላው በሰማ ጊዜ የእግዚአበሔር ታቦት ወደ ገዛ ከተማው ወደ ደብረ ጽዮን በክብር አስመጣው። ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሔር ታቦት ማደሪያ የሚሆን ቋሚ ቤተ መቅደስ ሊኖር እንደሚገባ እግዚአብሔር አሳስቦት ለእግዚአብሔር ታቦት ማደሪያ የሚሆን ቤተ መቅደስ ለመሥራት ወሰነ።

 

ኢየሩሳሌምን ያቀናት መልከጼዴቅ እንደሆነ ይነገራል። ይህቺ ከተማ ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔር የተመረጠች ከተማ ናት። ንጉሥ ዳዊት ኢየሩሳሌምን ከኢያቡሳውያን እጅ አስለቅቆ ከያዘ በኋላ ለእግዚአብሔር መስዋዕትን የሚሰዋበትና ለታቦተ ጽዮን ማደሪያ የሚሆን ቤተ መቅደስን ይሠራበት ዘንድ በኢየሩሳሌም ውስጥ የሚገኘውን የሞሪያን ተራራ ከኢያቡሳዊው ኦርናን በስድስት መቶ ስቅል /ሸክል/ ወርቅ ገዛው። በሕይወተ ሥጋ እያለም ለቤተ መቅደሱ መሥሪያ የሚሆኑ የግንባታ ዕቃዎችን፡ እንዲሁም ባለሙያዎችን ጥሬ ገንዘብ ሁሉ አሰባስቦ ነበር። ዳሩ ግን ቤተ መቅደሱን ይሠራ ዘንድ በእግዚአብሔር የተመረጠው ልጁ ሰሎሞን በመሆኑ ልጁ ሰሎሞንን ጠርቶ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ማለፊያ የሆነ ቤት እንዲሠራ አዘዘው። እሥራኤልንም በሁሉ ነገር እንዲራዱት አደራ አላቸው።

 

950 ዓመት ቅደመ ልደተ ክርስቶስ ንጉሥ ሰሎሞን እግዚአብሔር ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ፡ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም፡ በእግዚአብሔር እጅ ተጽፎ ለዳዊት በመጣለት ምሳሌ መሠረት የእግዚአብሔርን ቤት ሠራ ቤተ መቅደሱም እጅግ ታላቅና ድንቅ የሆነ ነበር። እግዚአብሔርም ሰሎሞን የሠራውን ቤተ መቅደስ እንዲህ ሲል ባረከ ለዘላለም ስሜ በዚያ ያድር ዘንድ ይህን የሠራኸውን ቤት ቀድሻለሁ ዓይኖቼና ልቤም በዘመኑ ሁሉ በዚያ ይሆናል

 

ከንጉሥ ሰሎሞን ሞት በኋላ መንግሥተ እስራኤል በሁለት ተከፈለ። የይሁዳና የብንያም ነገዶች በሰሎሞን ልጅ በሮብዓም አገዛዝ ሥር ሆነው ኢየሩሳሌምንና መቅደሱን እንደያዙ ሲቀሩ። የቀሩት አሥሩ ነገደ እስራኤል ግን ኢዮርብዓምን በላያቸው አንግሠው የመንግሥታቸውን ከተማ በሰማርያ አደረጉ። በዚህ ጊዜ ኢዮርብዓም መንግሥቱ እንዳይፈርስበት እስራኤልም በአምልኮ ምክንያት ወደ እየሩሳሌም ወደ ሰሎሞን መንግሥት እንዳይመለሱበት ብሎ ሁለት የወርቅ ጥጆች ሠርቶ አንዱን በ ዳንሁለተኛውን በ ቤትኤልበሁለቱ አገሮች ጠረፍ ላይ አቁሞ እስራኤልን ለነዚያ ምስሎች እንዲሰግዱ በማድረግ ከአምልኮተ እግዚአብሔር ለያቸው። ይህ አስከሆነበት ቀን ድረስ ግን እስራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ቤተ መቅደሱ ይመጡ በዚያም አምልኮታቸውን ይፈጽሙ ነበር።

 

586 ዓመት ቅደመ ልደተ ክርስቶስ በሴደቅያስ ዘመነ መንግሥት የባቢሎን /የአሁኗ ኢራቅ/ ንጉሥ የነበረው ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን ወረረ። በወረራወ የኢየሩሳሌም ከተማ ቅጽር በውስጥዋ ያሉ ቤቶች ፈረሱ፡ እንዲሁም ማለፊያ ሆኖ የተሠራው ቤተ መቅደስ በእሳት ተቃጠለ። በውስጡ ያሉት ነዋየ ቅድሳቱም በወራሪው ኃይል ተዘረፉ። አይሁድም ወደ ባቢሎን ተጋዙ።

 

ከሰባ ዓመት የግዞት ዘመን በኋላ የፋርስ / የአሁንዋ ኢራን/ ንጉሥ የነበረው ቂሮስ ባቢሎንን በወረረ ጊዜ በባቢሎን በግዞት ለነበሩት አይሁድ ነፃነትን ሰጣቸው። አይሁድም ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። በግምት ከአንድ መቶ ዓመት በኋላ በነህምያና በዕዝራ አነሳሽነት በዘሩባቤል አማካይነት አይሁድ በናቡከደነጻር ሠራዊት ፈርሶ የነበረውን ቤተ መቅደሳቸውን ለሁለተኛ ጊዜ አነጹት ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤተ መቅደስ ክብር ይበልጣልበማለት የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር መናገሩን ነቢዩ ሐጌ ተናግሯል፡ ሁለተኛው ቤተ መቅደስ ከመጀመሪያው በአምስት ነገሮች እንደሚለይ በዕብራውያን መጽሐፍ በታልሙድ ተገልጿል። እነዚህ በመጀመሪያው ቤተ መቅደስ የነበሩ በኋለኛው ግን የሌሉ አምስቱ ነገሮች ታቦቱዩ፡ የሥርየት መክደኛው፡ ኪሩቤል፡ እሳቱ እንዲሁም ኡሪምና ቲሚም ናቸው።

 

ከትልቁ እስክንድር መነሳት በኋላ / 333 ዘመን ቅ../ ኢየሩሳሌምን የግሪኮች ሥልጣኔና ባሕል የወረራት ቢሆንም አይሁድ በመቅደሳቸው መስዋዕት ከማቅረብ አምልኮታቸውን በአግባቡ ከመፈጸም ያገዳቸው ሁኔታ እንዳልነበር ይነገራል። በአንጥያኮስ ዘመነ መንግሥት ግን (Emperor Antiochus Ephiphanes lV )ታላቅ ፈተና ገጥሟቸዋል። ራሱን በአምላክነት ላስቀመጠው አንጥያኮስ አይሁድ የአሣማ መስዋዕት በመቅደሳቸው እንዲሰዉ ተገደዋል። በዚህ የተነሣ የመቃብያን አመፅ ተቀሰቀሰ።

 

164 ዓመት ቅድመ ልደተ ክርስቶስ ግሪኮች ከኢየሩሳሌም ሲወጡ ሀሽሙኒያን (Hasmonean Dynasty Of Jewish)የተባለ የአይሁድ ነገዶች ሀገሪቱን ተረከቡ። እነዚህ ነገዶች በፓምፒ ሠራዊት አማካይነት ሀገሪቱ በ63 ...ክ በሮማውያን ቁጥጥር ሥር እስከዋለችበት ጊዜ ድረስ ሀገሪቱን አስተዳድረዋል።

 

33 ዓመት ቅ..ክ የሮማ ምክር ቤት /ሴኔት/ ለታላቁ ሄሮዶስ የንጉሥነት ማዕረግ እንዲሰጠው በወሰነው መሠረት ሄሮዶስ የይሁዳ ንጉሥ ሆነ። እርሱም አይሁድን ለማስደሰት ሲል በዘሩባቤል አማካይነት ተሠርቶ የነበረውን ሁለተኛውን ቤተ መቅደስ አስፋፍቶ አደሰው።

 

ከጌታ ልደት በኋ ከ66-70 .. ያለው ጊዜ ቭስፓስያንና ልጁ ቲቶ በአይሁድ ላይ ጠንካራ ክንዳቸውን ያሳረፈበት ወቅት ነበር። በአይሁድ ታሪክ ዘግናኝና አሰቃቂ ድርጊት የተፈጸመበት ጊዜ ሲሆን ሲፈርስ ሲሠራ የነበረው ቤተ መቅደስም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የፈረሰበትና ታሪክ ሆኖ የቀረበት ክስተት ነው። በእግዚአብሔር መሲሕና በደቀመዛሙርቱ ላይ አይሁድ ለፈጸሙት ወደር የማይገኝለት ግፍ የተቀበሉት ፍርድ መሆኑን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ የነበረው አውሳብዮስ ገልጿል።

 

አውሳብዮስ አይሁዳዊው ዮሴፍ (Josephus) በመጽሐፉ ላይ የገለጸውን መሠረት አድርጎ በጻፈው ላይ ከይሁዳ ምድር የተሰባሰቡ ከ3 ሚሊዮን ያላነሱ አይሁድ በኢየሩሳሌም ከትመው ነበር። ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ክርስቲያኖች ስለ ኢየሩሳሌም ጥፋት አስቀድሞ የተነገረው ንግርት መፈጸሙ የማይቀር መሆኑን አምነው ከተማዋን ለቀው በዮርዳኖስ ማዶ ፔላ በምትባል መንደር ሠፍረው ስለነበር ከአሰቃቂው እልቂት ተርፈዋል።

 

አይሁድ የእየሩሳሌምን በሮች በመዝጋት የቲቶ ጦር ወደ ኢየሩሳሌም እንዳይገባ አደረጉ። ሮማውያንም ከተማዋን ከበው ወደ ከተማዋ ምግብ እንዳይገባ አደረጉ። ቀኑ እየገፋ በመጣ ቁጥር የእህል አቅርቦት ባለመኖሩና የነበረውም እያለቀ በመምጣቱ ረሀብ በኢየሩሳሌም ከትመው ባሉ አይሁድ ላይ ጥላውን ማጥላት ጀመረ። ቀለባቸውን የጨረሱ፡ ካልጨረሱት መንጠቅ፡ ጥቂት የሚበላ ያለው ከሌሎች ተሰውሮ በሩን ዘግቶ መብላት ተጀመረ። በቡድን የተደራጁ ዘራፊዎች ምግብ ይኖራል ብለው የሚጠረጥሩትን ቤት በር እየሰበሩ በመግባት የሚበላ ካገኙ ባለቤቱቹን ከመሬት ላይ ጥለው ምንም ሳያስቀሩ ዘርፈው ይሄዳሉ። ካጡ አውቀው የደበቁ ስለሚመስላቸው ከመሬት ላይ በመጣል ባለቤቶቹን ይረጋግጧቸዋል። አረጋውያን፡ ሕፃናት በእነርሱ ዘንድ ቦታ የላቸውም። ከአረጋውያን እጅና ከሕፃናት አፍ ሳይቀር ይነጥቁ ነበር። ይህ አልበቃ ብሏቸው በረሀቡ ምክንያት በሞቱና ሊሞቱ ከሚያጣጥሩት ላይ የለበሱትን ልብስ ገፈው ይወስዳሉ። አንዳንዶቹም የጎራዲያቸውን ስለታምነት በሟቾቹና በማጣጣር ላይ ባሉት ሰዎች ሰውነት ላይ በመሰንዘር ይፈትኑ ነበር።

 

በአንድ ሰው ቤት ውስጥ የሚበላ ነገር መኖሩና አለመኖሩ ይገመት የነበረው በሰውነቱ አቋም ነበር። የከሳና የገረጣ መራመድ ያቃተው ከሆነ ምንም የሌላውና ዕለተ ሞቱን የሚጠብቅ መሆኑ ታውቆ ማንም ትኩረት አይሰጠውም። ሰውነቱ ያልከሳና ጠንከር ያለ አቋም ካለው ግን የሚበላ ነገር በቤቱ ውስጥ እንደደበቀ ስለሚገመት የዚያን ሰው ቤት ሰብረው በመግባት ጓዳ ጎድጓዳውን ሁሉ ሳይቀር ይበረብራሉ።

 

ጥቂት የሚበላ ያላቸው ቤታቸውን ዘግተው ድምፃቸውን አጥፍተው ሳያበስሉ ጥሬውን ይመገቡ ነበር። ያበሰሉ እንደሆነ የምግቡ ጠረንና ጢሱ ለጎረቤቶቻቸውም ሆነ ለነኛ ዘራፊዎች እንዳያሳብቅባቸው በመስጋት። ቀን አልፎ ቀን ሲተካ የእህል ዘር ከከተማዋ እየጠፋ በመምጣቱ ረሀቡ እየከፋ መጣ። የረሀቡ መባበስ እናት ከልጅዋ አፍ፡ ልጅ ከአባቱ አፍ እንዲነጣጠቁ አደረገ።

 

ከዮርዳኖስ ማዶ ትኖር የነበረች ማርያም የተባለች ሴት ያደረገችውን ዘግናኝና አሰቃቂ ድርጊት አይሁዳዊው ዮሴፍ የገለጸውን አውሳብዮስ ጠቅሶ እንደጻፈው ይህቺ ሴት በቤተሰብዋም ሆነ በንብረትዋ የታወቀችና የተከበረች ነበር። እንደሌሎቹ አይሁድ እርስዋም ሀብት ንብረትዋን እንዲሁም ቀለብዋን ይዛ በኢየሩሳሌም ያሉ አይሁድን ተቀላቅላ ነበር። ሀብትና ንብረትዋን በተከበበችው ኢየሩሳሌም ላይ የሠለጠኑት ዘራፊዎች ዘርፈው ባዶ እጅዋን አስቀርዋት። በዙሪያ ያሉት ደግሞ ለእርስዋም ሆነ አብረዋት ላሉት ይበቃል ብላ የያዘችውን ቀለብ ተናጥቀዋት ይህቺ ሴት የሚላስ የሚቀመስ አጣች። ረሀብ አንጀትዋን ሲያሳውሰው በደረትዋ ላይ ጡትዋን ጎርሶ የተለጠፈውን ልጅዋን በእጅዋ ምንጭቅ አርጋ በመያዝ ዓይን ዓይኑን እያየች የረሀብ፡ የጦርነት፡ የጨካኞች ሰለባ የሆንከው ያልታደልከው ልጅ ልታደግህ አልቻልኩም። ህልውናችን በገዢዎቻችን በሮማውያን እጅ ያለ ነው፡ ረሀብ ነግሦብናል ነጣቀ ዘራፊዎች ደግሞ ከሁለቱ ብሰዋል። ስለዚህ ና እኔ እናትህ ብመግብህ ይሻላል ብላ የገዛ ልጅዋን አርዳ አወራርዳ ጠብሳ ግማሹን በልታ ቀሪውን ሸፍና አስቀመጠች። የጥብሱ መዓዛ የጠራቸው ነጣቂዎች ዘው ብለው በመግባት ያዘጋጀችውን ምግብ ካላሳየቻቸው በሰይፍ እንደሚቆራርጥዋት ቢዝቱባት የሸፈነችውን ቀሪውን ገልጣ በማሳየት የገዛ ልጅዋን አርዳ ጠብሳ እንደበላች በመግለጥ እነርሱም እንዲበሉ ጋበዘቻቸው። ይህን በሰሙ ጊዜ ባሉበት በድን ሀነው ቀሩ። እርሷም ከእናት የበለጠ ለልጅዋ የሚያዝን ማንም ሊኖር አይችልም። እኔ በልጄ ላይ ጨክኜ እርሱን ተመግቤያለሁና እናንተም ጥቂት አስቀርታችሁልኝ ሌላውን ብሉ በማለት ይበልጥ እንዲረበሹና በሁኔታው ተደናግጠው እየተንቀጠቀጡ ከቤትዋ እንዲወጡ አድርጓቸዋል።

 

ኢየሩሳሌም በየቤቱና በየመንገዱ እንደ ቅጠል በሚረግፉ ሰዎች አስከሬን ሽታ ታወደች። በመጀመሪያ ላይ የሟቾቹ ቁጥር አነስተኛና የሰውም ኃይል ያልደከመበት ጉልበቱ ያልዛለበት ጊዜ ስለነበረ በአግባቡ በተገቢው ቦታ መቅበር ጀምረው ነበር። ኋላ ላይ ግን የሟቹ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ሲያሻቅብና ሰውም በረሀቡ ፅናት የተነሳ ኃይሉ ሲደክም ጉልበቱ ሲዝል እንደ ሥርዓቱ መቅበር ስላልተቻለ በግንቡ አሻግረው በትልቅ ጉድጓድ ውስጥ ይጥሉ ጀመረ።

 

ሮማውያን የኢየሩሳሌምን በሮች ቅጥርዋን ሰብረው ባይገቡ ከዚህ የከፋ ይደርስ እንደነበረ ዮሴፍ ወልደከርዮን ጠቅሷል። የቲቶ ሠራዊት በፊት የሚያጋጥሙትን በሰይፍ እየሰየፈ ኢየሩሳሌምን እጅ ባደረገ ጊዜ ታላቁን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አቃጠለው፡ የጌታ ትንቢትም ተፈጸመ።

 

 • መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዘመነ ስብከቱ ይህ እንደሚሆን አስቀድሞ ተናግሮ ነበር።

 

ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ አለቀሰላት እንዲህ እያለ፦ ለሰላምሽ የሚሆነውን በዚህ ቀን አንቺስ ስንኳ ብታውቂ፡ አሁን ግን ከዓይንሽ ተሰውሯል። ወራት ይመጣብሻልና ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኩሉም ያስጨንቁሻል አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን ወደ ታች ይጥላሉ። በአንቺ ውስጥም ድንጋይ በድንጋይ ላይ አይተውም የመጎብኘትሽን ዘመን አላወቅሽምና

 

ኢየሩሳሌም ግን በጭፍራ ተከባ ስታዩ በዚያን ጊዜ ጥፋትዋ እንደቀረበ እወቁ የዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራራዎች ይሸሹ በመካከልዋም ያሉ ከእርስዋ ፈቀቅ ይበሉ፡ በገጠር ያሉም ወደ እርስዋ አይግቡ የተጻፈው ሁሉ እንዲፈጸም ይህ የበቀል ጊዜ ነውና። በዚያን ወራት ለእርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው ታላቅ ችግር በምድር ላይ በዚህም ሕዝብ ላይ ቁጣ ይሆናልና በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ ወደ አሕዛብ ሁሉም ይማረካሉ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም ለአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች[ሉቃ.2120-24]

 

ኢየሩሳሌም በቲቶ ሠራዊት ቅጥርዋ ከፈረሰ ቤተ መቅደሱም ከተቃጠለ ከስድሳ ዓመት በኋላ በአይሁድ የተመራ ሌላ ታላቅ ዓመፅ በመቀስቀሱ (Barkochba) የሮማ ጄነራል ሀደርያን ኢየሩሳሌምን ሜዳ አደረጋት። የአሕዛብ ከተማም አድርጎ መሠረታት። አይሁድም ወደ እርስዋ ገብተው እንዳይቆሙ ተከለከሉ። የሀገሪቱንም ስመ ፓሌስቲና ብሎ ሰየመ። አይሁድም በሚደርስባቸው መንገላታት በተጣለባቸው ከፍተኛ ቀረጥና በነፃነት እጦት ሀገሪቱን ለቀው ወደ ሌላ ሀገር መሰደድ ዕጣቸው ሆነ።

 

የመቅደሱ በመሰጊድ መተካት

 

እንደ ስምዋ (የሩሻሌም = በዕብራይስጥ፡ የሰላም ሀገር ማለት ነው) ሳይሆን በተቃራኒው፡ ከተቆረቆረችበት ጊዜ አንስቶ ጦርነትና ኹከት ያልተለያት ኢየሩሳሌም፡ አንዱ ሲያፈርሳት ሌላው ሲገነባት የኖረች ከተማ ከመሆንዋ በተጨማሪ የተለያዩ እምነቶች መናኸሪያም ነች።

 

በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በቆስጠንጢኖስ ዘመነ መንግሥት ክርስትና በመላው የሮም ኢምፓየር ብሔራዊ ሃይማኖት እንዲሆን በታወጀበት ጊዜ ኢየሩሳሌም በባዛንታይን መንግሥት ቁጥጥር ሥር ስለነበረች የክርስቲያኖች ከተማ ሆነች። በዚህ የተነሣ ጌታ በተወለደባት በቤተልሔም እንዲሁም በተሰቀለበት በጎልጎታ ታላላቅ አብያተ ክርስቲያናት በቆንስጠንጢኖስና በእናቱ በእሌኒ አማካይነት ተገነቡ።

 

637 .. ገደማ እስላሞች በዑመር መሪነት ኢየሩሳሌምን ወረሩ ለቀጣይ አራት መቶ ዓመታት ያህል ኢየሩሳሌም የእስላሞች ከተማ ሆነች። በዚህ ጊዜ የሰሎሞን ቤተ መቅደስ ታንጾበት የነበረው የሞሪያ ተራራ በእስላሞች ዘንድ ነቢያቸው ከዚህ ቦታ በመነሣት በመላእክት አማካይነት ታዋቂ የሌሊት ጉዧቸውን አድርገዋል ተብሎ ስለሚታመንና ቦታውም በኢየሩሳሌም ከታማ የሚገኝ በመሆኑ ኢየሩሳሌምን ቅዱስዋ ከተማ ኤል ቅዱስ” (ይህ ቃል ከ ግእዙ ቋንቋ የተወሰደ ነው) ብለው ሰየምዋት። በቅዱስዋ ከተማ በሚገኘው በሞሪያ ተራራ ላይም በ691 .. “የዑመር ከሊፋወይም የድንጋዩ ጉልላት (Dome of the Rock)የተባለውን መስጊድ፡ በ703 .. ደግሞ ኤል አቅሳየተባለውን መስጊድ አነጹ።

 

እነዚህ ሁለት መስጊዶች በሞሪያ ተራራ ላይ ያላግባብ ከታነጹ ከአንድ ሺህ ዓመት በላይ ሆኗቸዋል። ምንም እንኳን መንግሥት እስራኤል ከተመሠረተ ከ1948 .. በኋላ እስራኤል አሮጌዋን ኢየሩሳሌምን ከአረቦች እጅ በጦርነት አስለቅቃ የያዘች ቢሆንም ታሪካዊውና የሞሪያ ምድር ዛሬም በእስላሞች ይዞታ ሥር እንዳለ ነው።

 

የምዕራቡ ግድግዳ

 

ለአይሁዳ እምነት የማዕዘን ድንጋይ ከሆነው ቤተ መቅደስ ዛሬ ከአይሁዳውያን የቀረው ቅርስ ቢኖር ትልቁ ሄሮድስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ20 ዓመት በሁለተኛው ቤተ መቅደስ ዙሪያ አሳጥሮት ከነበረው ግድግዳ ሳይፈርስ የቀረው የምዕራቡ ክፍል ነው።

 

በእብራይስጥ ቋንቋ ከቴል ህማ አራቪ የሚባለው የሁለተኛው ቤተ መቅደስ አጥር ቅሪት የአይሁዳውያን ቅዱስ ቦታ ነው። የምዕራቡ ግድግዳአይሁድ ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቅርሳቸውን የሚያስታውሱበት የማንነታቸው መግለጫ ነው። ከየትኛውም ዓለም ወደ ኢየሩሳሌም የሚመጣ ይሁዲ ይህን ቦታ ሳይረግጥ፡ ግምቡን ሳይሳለም፡ የልቦናውን ፍላጎት በወረቀት ላይ አስፍሮ በግድግዳው ስንጥቅ ውስጥ ሳይከት ወደ መጣበት አይመለስም። በሮማውያን ዘመን እስራኤላውያን ወደዚህ ቦታ መግባት አይፈቀድላቸውም ነበር። በባዘንታይን ዘመን በዓመት አንድ ጊዜ እየመጡ ቤተ መቅደሱ የፈረሰበትን ዕለት በማሰብ ያከብሩ ነበር። የማልቀሻ ግንብ ብለውም ይጠሩታል። አይሁድ ከሮማውያን መንግሥት ጀምሮ ጥቃትና ውርደት በዝቶባቸው የአሕዛብ ነገሥታት ቀንበር ከብዶባቸው፡ መቅደሳቸው ፈርሶ፡ ሕዝባቸው ተበትኖ የኖረበትን ዘመናት እያስታወሱ የሚያለቅሱበት የሚጸልዩበት በመሆኑ ነው። ዳሩ ግን አይሁድ በዚህ ተጽናንተው ሦስተኛውን ቤተ መቅደሳቸውን በቀደመው ቦታ በሞሪያ ተራራ ላይ ሳያንጹ ይቀሩ ይሆን? የሚለው ለብዙዎች መልስ የሚያሻው ጥያቄ ቢሆንም አክራሪ አይሁድ ግን ሦስተኛው ቤተ መቅደስ በጥንታዊውና በተመረጠለት በሞሪያ ምድር መሠራት እንዳለበት ያምናሉ። ይህ ደግሞ ከመሲሁ መምጣት ጋር የተያያዘ በመሆኑ በእነርሱ ዘንድ አይቀሬ ነው።

 

መሲሕ በስተምሥራቅ በኩል በጊቴሴማኒ አድርጎ ፈለገ ቄድሮንን አቋርጦ፡ ወርቃማውን በር(ወርቃማዊ በር ከኢየሩሳሌም ስምንቱ በሮች አንዱና ጥንት ቤተ መቅደሱ አሁን ደግሞ አል አቅሳ መስጊድ በምሥራቅ በኩል በሚገኝበት ያለ ነው። ይህ በርኢ በ1530 .. በቱርኮች በመዳፈኑ እስከዛሬ ድረስ እንደተዘጋ ነው። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአህያዋና በወርንጫዋ ላይ ተቀምጦ በሕዝቡ ታጅቦ ሆሳዕና ለዳዊት ልጅሆሳዕና በአርያምእያሉለት ወደ ኢየሩሳሌም ወደ መቅደሱ የገባው በዚህ በር እንደነበር ይነገራል።)ከፍቶ ወደ መቅደሱ በመግባት መስዋዕትን ያቀርባል ብለው ተስፋ ስለሚያደርጉ ሦሰተኛው ቤተ መቅደስ ከጥንታዊው ቤተ መቅደስ ቦታ ውጭ በሌላ በየትም ቦታ እንዲታነጽ እንደማይሹ የታወቀ ነው።

 

በአንዳንድ ይሁዲዎች ዘንድ ይህ በር እስከ መሢሑ መምጫ ቀን እንደተዘጋ ይኖራል የሚከፈተው እርሱ ነው የሚል እምነት ይንጸባረቃል። ከዚህ በር አንጻር ፈለገ ቄድሮንን ተሻግሮ የአይሁድ መካነ መቃብር ይገኛል። በዚህ የመቃብር ቦታ ለመቀበር በእስራኤልም ሆነ ከእስራኤል ውጭ ያሉ አይሁዶች ከፍተኛ ጉጉትና ምኞት ያላቸው ሲሆን የዚህ ምክንያት ደግሞ መሢሑ ሲመጣ ግንባር ቀደም የበረከቱ ተሳታፊ ለመሆን የታለመ ይመስላል።

 

ሦስተኛው ቤተ መቅደስ

 

በእስካሁኑ የአይሁድ ታሪክ ሁለት ቤተ መቅደሶች ታንጸው እንደነበርና በተለያየ የታሪክ አጋጣሚ መፍረሳቸውን ቀደም ሲል ተገልጧል። የቀደሙት ሁለቱ ቤተ መቅደሶች የታነጹት በታሪካዊው የሞሪያ ምድር ነበር። እንደ አይሁድ እምነትም ሆነ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮም ሦስተኛው ቤተ መቅደስ መሠራቱ የማይቀር ነው የሚሉ ወገኖች በርካታ ናቸው። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደሱ በሐሣዌ መሢሕ ዘመን ስለሚታነጽ ነው በማለት የሐዋርያውን አነጋገር ዋቢ አድርገው የሚያቀርቡ ሊቃውንት የመኖራቸውን ያህል ቤተ መቅደስ ያላት ኢየሩሳሌምን ነውበማለት የቤተ መቅደሱን መታነጽ ጉዳይ ችላ የሚሉም አሉ።

 

በአይሁድ ዘንድ ግን የሦስተኛው ቤተ መቅደስ መታነጽ ሃይማኖታዊ ጉዳይ ስለሆነ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም። አይቀሬ ነው። የሦስተኛው ቤተ መቅደስ መታነጽ ከዛሬ 2500 ዓመት በፊት ከአይሁድ ሕዝብ የተቋረጠው የመለኮት መገለጥ ዳግም የሚመለስበት ነው ተብሎ ይታመናል። የእግዚአብሔር መገለጥ በነቢያትና ከእነርሱ በፊት በነበሩ ቅዱሳን ዘመን በሕዝቡ መካከል ይደረግ ነበር። አሥራ ሦስቱ የዕብራውያን ነቢያት ንጉሥ ዳዊትን ጨምሮ መለኮታዊው ግልጸት በመሢሑ ዘመን ሦስተኛው ቤተ መቅደስ በሚታነጽበት ጊዜ ዳግመኛ በሕዝቡ መካከል እንደሚሆን መናገራቸውን በአይሁድ ዘንድ በስፋት የሚነገር ስለሆነ የሦስተኛው ቤተ መቅደስ መታነጽ የእምነታቸው የማዕዘን ድንጋይ ነው።

 

የእስራኤል የቀደመ ክብርና ሞገስ የሚመለሰው በመሢሑ ዘመን ሦስተኛው ቤተ መቅደስ በታነጸ ጊዜ መሆኑንና በዚህ ጊዜ ጉባኤያቸው ጸሎታቸው መስዋዕታቸው ሁሉ ቅድመ እግዚአብሔር የሚደርስበት መለኮታዊው ኃይል በመካከላቸው የሚገኝበት እንደሆነ ያምናሉ።

 

ዓለማችን ከጦርነት አባዜ ታላቅ የሰላም አየር የሚነፍሰው እንደ አይሁድ እምነት ሦስተኛው ቤተ መቅደስ ሲታነጽ ብቻ ነው። በዚያን ጊዜ ከምድር የተሰወረው የእግዚአብሔር መገለጥ (God’s Shechinah) ይሆናል።

 

ለሦስተኛው ቤተ መቅደስ መሠራት ጥርጊያ መንገድን ለማዘጋጀት በማሰብ Shechinah Third Temple, Inc” የተባለ በትርፍ ላይ ያልተመሠረተ ድርጅት ለዓለም ሁሉ ለማስገንዘብ የግንዝቤ የማስጨበጥ ተልዕኮን አንግቦ እንደተነሣ በመግለጽ ለዚህ በጎ ዓላማ መሳካት ፍላጉት ያላቸው ሁሉ እጃቸውን በመዘርጋት የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉለት በኢንተርኔት ባሰራጨው ጽሑፍ ገልጾአል።

 

ከላይ እንደተገለጸው በይሁዲ እምነት ተከታዮች ዘንድ የሦስተኛው ቤተ መቅደስ መሠራት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው። አይሁድ ከዘመናት በፊት ከእነርሱ የራቃቸው መለኮታዊ ምሕረት ዳግም ይመለስላቸው ዘንድ የዚህ በረከት መግለጫ የሚሆነው ቤተ መቅደስ መሠራት እንዳለባት ማመናቸው ዓለምን የሚያስጨንቅ ጉዳይ ለምን ሆነ? የሚለው ቁልፍ ጥያቄ ነው።

 

በአይሁድ ታሪክ ቤተ መቅደስ ማነጻቸው እንግዳና አዲስ ነገር አለመሆኑ የታወቀ ነው። የቀደሙት ሁለት ቤተ መቅደሶች የታነጹት በአንድ ቦታ ነው። ይህ ቦታ ደግሞ ከዚህ በፊት እንደተገለጸው የአይሁድም ሆነ የእስላሞች ቅዱስ ቦታ ነው። በአይሁድ ዘንድ ሦስተኛው ቤተ መቅደስ የቀደሙት ሁለቱ አብያተ መቅደሳት በታነጹበት ካልሆነ በሌላ በየትም ቦታ መታነጽ እንደሌለበት ይታመናል። እንደ እምነታቸው እንዳይሆን ደግሞ በታሪክ አጋጣሚ በቦታው ላይ እስላሞች ሁለት ታላላቅ መስጊዶችን ገንብተውበታል። ቦታውንም በይዞታነት ይዘውት ያሉት እስላሞች ናቸው። ይህ አጣብቂኝ ሁኔታ ነው የሦስተኛው ቤተ መቅደስ መታነጽ ጉዳይን የዓለም መነጋገሪያ ያደረገው።

 

አጥባቂ አይሁዶች በቦታው ላይ ያሉትን መስጊዶች በማፍረስና ሦስተኛው ቤተ መቅደስን በቦታው ቆሞ ለማየት ካላቸው ጉጉት የተነሣ በቦታው ላይ ተደጋጋሚ የጥፋት ሙከራ ለማድረግ አሲረው ሳይሳካላቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል። በሌላ በኩል የሦስተኛው ቤተ መቅደስን መሠራት ጉዳይ ያዘገየው እስራኤል በግዛትነት በያዘችው በኢየሩሳሌም ባለው በሞሪያም ተራራ የተሠሩት የመስጊዶቹ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ከመነሻው የመጀመሪያውን ቤተ መቅደስ ንጉሥ ዳዊት ሊሠራ ሲያስብ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት መንከራተትዋ አሳዝኖት ለቃል ኪዳንዋ ታቦት ማደሪያ (ማረፊያ)ይሆን ዘንድ በመሆኑ ቤተ መቅደስ ከመሥራት ለጊዜው ቸል እንዲሉ ያደረጋቸው የቃል ኪዳንዋ ታቦት ደብዛዋ መጥፋትና ያለችበትን ቦታ አለማወቅ ነው። ዳሩ ግን የቃል ኪዳንዋ ታቦት እጃቸው ከገባች ሦስተኛውን ቤተ መቅደስ ስጋት በነገሠበት በሞሪያ ተራራ ላይ ለመሥራት የሚያግዳቸው ኃይል የሚኖር አይመስለም።

 

ለሦስተኛው ቤተ መቅደስ መታነጽ የታቦተ ጽዮን መገኘት ወሳኝ ጉዳይ ከሆነ የቤተ መቅደሱ ግንባታ በአወንታዊም ሆነ በአሉታዊ መንገድ የሚነካቸው ወገኖች ሁሉ የቃል ኪዳንዋ ታቦት ጉዳይ ትኩረታቸው እንደሚሆን ማንም ተራ ሰው የሚገምተው ነገር ነው።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Posted in Curiosity | Tagged: , , | 3 Comments »

Effective Time Management

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 1, 2009

 

time

 

Time is something we all need more of, but how can you get more of it when there is only 24 hours in a day? Sadly there is no way to put more hours into each day, but what you can do is be more efficient with your time so you can follow your dreams.

 1. Sleep more – if you learn to take power naps, you will have more energy throughout the day. Although you may lose some time from napping, you will be able to work more efficiently, which will give you more time.

 2. Eat healthy meals – changing your diet maybe hard at first, but eating balanced meals will affect how you do your daily tasks. It will give you more energy so you can get your work done faster.

 3. Do less work – a lot of the things you do on a daily basis, don’t need to be done. Think about your daily routine and cut out anything that isn’t essential. You will be surprised on how much time you are wasting.

 4. Tell people what’s on your mind – being honest and to the point is a great way to accomplish things quicker. When you beat around the bush things don’t get accomplished as fast.

 5. Have some fun – all work and no play is a good way to make you feel depressed. Get some fun into your life, it will make you feel better, work harder, and hopefully make you want to accomplish your dreams.

 6. Adjust your working hours – many companies are very flexible on what times you can start and end work. If you work in a heavy traffic city such as Los Angeles you can easily spend an hour or 2 commuting to work during rush hour. But if you adjust your working hours you can cut back on driving time drastically.

 7. Cut down on your communication methods – cell phones, email, and instant messaging are just a few tools you probably use to communicate with others. The problem with some of these methods is that they can easily be abused. For example if you log onto AIM, you may waste an hour talking to others about junk. Try and use communication tools like AIM only when you need them.

 8. Don’t multi-task – when you mult-task you tend to switch between what you should be doing and what you shouldn’t. By single tasking you are more likely to do what you are supposed to be doing.

 9. Get rid of distractions – things you may not be thinking of can be distractions. Whether it is gadgets or even checking emails every 5 minutes, this can all distract you. By getting rid or distractions or controlling them, you will have more time on your hands.

 10. Watch television on the web – the problem with television is that you had to watch TV shows when they want you to watch them. Now with the technology advancements most entertainment channels like NBC, FOX, CW, and even a few cable networks let you watch your favorite TV shows online. It is free, you can watch the shows when you want to, and an hour show usually ends up being 45 minutes because there are a lot less commercials.

Any recommendations on how you can be more efficient so you have more time to follow your dreams?

Posted in Curiosity | Tagged: , | Leave a Comment »

Another Stealth War For Resources : The New Scramble for Africa

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 1, 2009

Biofuels war has broken out in Africa.

eurosauria3

Newspaper headlines have not proclaimed it but the gist of it is already out. Big money profiteers from Europe and United States are rushing to Africa in a new scramble for the continent, transforming large swathes of arable land into massive biofuels plantations.


Local but poor populations in many parts of Africa are increasingly being driven deeper into economic obscurity yet 60% of them still depend on agriculture for survival. Another 60% of that eke out a living by subsistence farming and animal husbandry.


The World Bank has been sitting on a secret report since April that says biofuels are responsible for the global food crisis; food prices have risen 75% because of the impact of the search for alternative fuels through the use of food products.


According to the anti biofuels investment campaigners, whole villages are being cleared or grabbed, but families have been given minimal compensation or opportunities for their loss of land, community and way of life.

African civil society is calling for a moratorium on new biofuels investments in Africa amid concern that that the biofuels revolution will bring more food insecurity, higher food prices and hunger to the continent. In Tanzania, thousands of farmers growing cereals like corn and rice are already being evicted from fertile land with good access to water, for biofuel sugar cane and jatropha plantations on newly privatized land.

Endangered wildlife are not spared too. It is claimed one European investor has been granted 13,000 hectares of land in Oromia state of Ethiopia; 87% of which is the Babile Elephant Sanctuary, a home to rare and endangered elephants.

Spiegel Online reported recently how African governments and local farmers were being showered with promises by these big money spenders out on a green gold mad rush on the continent and further questioned if the frenzy was a form of economic colonialism.


Sun Biofuels, a British firm, has been granted free of charge a 99 year lease by the Tanzanian authorities to put 9,000 hectares or 22,230 acres of farmland under biofuels crop in exchange of a paltry $20 million (€13 million) corporate social responsibility investment to build roads and schools, among other amenities.


This deal follows dozens others involving firms from Netherlands, the United States, Sweden, Japan, South Korea, Canada and Germany, the German website reported. It is emerging that the US and Europe may be in a trade war over biofuels subsidies.


To prove that the biofuels scramble has nothing to do with alternative fuels but profit and more profit, Spielgel reported that Prokon, a German company switched from its primary business of producing wind turbines to growing jatropha curcas, now the catch phrase of African biofuels, in a land area the size of Luxembourg. It is a shrub with toxic seeds which contain a high percentage of oil used for candles, soap and biodiesel production.


But skeptical European scientists, alarmed by the impact of biofuels on skyrocketing food prices, are pushing the European Union to back away from its commitment to eco-fuel. Part of this skepticism, however, means that while the Western world pursues biofuels, caution demands that other lands must be found to cultivate the crop, and Africa fits the bill.


With China also looming in the picture, Africa could just be the perfect battle ground of the Biofuels Armageddon. Sadly, her role, as in most other economic wars, will be that of the grass on which two elephants fight.

_________________________________________________________________


Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: