Water Is Life
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 30, 2008
ድሃ ውሃ ከየት አገኘ?
ከነዚያ ደናግላን ሁሉ አንዲት ገረድ ብቻ ይዛ በተዘጋጀላት አልጋ ስትተኛ ሰሎሞን ለአሽከሩ ውሃውን ቀድቶ ከኩሽኩሽት እንደገባ እንዲያደርግ አዞት አስቀመጠ፡፡
በመካከል ንግሥቲቱ ውሃ በመጠማቷ ገረድዋን ከተኛችበት ቀስቅሳ ከንጉሡ አጠገብ ካለው ኩስኩስት (ውሃ ማስቀመጫ) ውሃ እንድታመጣላት ታዛታለች፡፡ ንጉሥ ሰሎሞን እንቅልፍ ሲይዘው ዓይኑ የሚያይ ይመስል አይጨፈንም፡፡ ከእንቅልፉ ሲነቃም ያንቀላፋ ይመስላልና ዓይኑን ይከድን ነበር ይባላል፡፡ በመሆኑም ንግሥቲቱ የመጣለትን ውሃ ስትጠጣ ሰሎሞን እጅዋን ለቀም ያደርግና “ምነው መሓላውን አፈረስሽ” ቢላት “ብልህ ስትሆን ሳለ ምነው እንዲህ ያለውን ተራ ነገር መናገር፣ ውሃ ሊጠጡ መሃላ ይፈርሳልን? ስትለው ከውሃ የሚበልጥ ምን ገንዘብ አለ፣ ምድር በውሃ ላይ ፀንታለች፡፡ ሰማይም በውሃ ላይ ቆሟል፡፡ ሰው፣ እንስሳ፣ አራዊት፣ ሣር እንጨቱ፣ በውሃ ይኖራል፣ ይለመልማል ያብባል፣ ይፈራል ቢላት በዚህ ንግግሩ ተረታና ድንግልናዋን አስገስሳ ዕብነ ሐኪምን (ቀዳማዊ ምኒልክን) እንደፀነሰችና እንደወለደች ይነገራል፡፡
ውሃን በተመለከተ ስለ ንግሥተ ሳባና ንጉሥ ሰለሞን በትውፊት ሲነገር ቆይቷል፡፡ በልብ ወለድም፣ በታሪክም ተጽፏል፡፡ የውሃ ጥም ጥናቱ፣ አስከፊነቱ ሲታሰብ ንግሥተ ሳባን ልብ ይሏል፡፡ 500 የሴት ደናግል አስከትላ ጥበብን ለመማር ከሠራዊቷ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ከደረሰች በኋላ በአንድ ሌሊት በቤተ መንግሥቱ አዳራሽ ሲጨዋወቱ አምሽተው፣ አብረን እንሁን ቢላት ካንተ ማደር እፈራለሁ ድንግል ነኝ፣ በድንግልና ካልኖርሁ መንግሥቴ ይሻራል አለችው፡፡ አምርሮ ቢይዛት ተላልፌ አልደፍርሽም ብለህ ማልልኝ አለችው፡፡ እርሱም መልሶ አንቺም ተላልፌ ገንዘብን አልነካም ስትይ ማይልኝ ብሏት ተማማሉ፡፡
Leave a Reply